Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

Re: መቀሌ የመሸገው የአሸባሪው የህውአት ቡድን ኢትዮጵያን አፈርሳለው ብሎ ጦር ከመዘዘ የመጀመሪያ የመልስ ምት የሚያገኘው ከኤርትራ መከላከያ ሀይል ነው !!!

Post by MatiT » 06 Jan 2020, 20:54

ከ1998 ጀምሮ በድንበር ሰበብ በትግራዮች ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ጦር 3 ወረራዎችን ኤርትራ ላይ ፈጽሞ ነበር። እነዚህም 1ይ፣ 2ይን 3ይን ወራር(1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ወረራ) በሚባሉ የሚታወቁ ግዙፍ ዘመቻዎች ናቸው።
ስለ 4ኛው ወረራ ግን ምን ያህል ያውቃሉ ???
ህውሃት 100 ሚልዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን እና 80 ብሄር ብሄረሰቦችን አደናግሮ እና አስተባብሮ ኤርትራን ለማጥፋት ሲነሳ ከ7 ዓመት በፊት የበተነውን የደርግ ወታደር አሰባስቦ ጭምር መሆኑን ስትመለከት ጉዳዩ የድንበር ግጭት ወይም የመንግስቶች አለመግባባት ነው ብለህ ማሰብ ሞኝነት ነው።
ነገርግን ይህን ግዙፍ ዘመቻ 3 ሚልዮን ህዝብ ብቻ የነበራት አገር መቋቋም መቻሏ ትንግርት ነበር፥ እውነት አትሰበርም እና። ይህ ያስደመማቸው እና ተስፋ ያስቆረጣቸው የትግራዮቹ መንግስት ይህን መንግስት እና ህዝብ በጦርነት እንደማያሸንፉት ሲገነዘቡ ያመሩት ታላቋን ሶብየት ህብረትን አዳክሞ ወደ በታተናት አይነት ስልታዊ ቀዝቃዛው ጦርነት ነው። ይህም ይች ትንሿ እና አዲሲቱ ሀገረ ኤርትራ 100% በሚባል ደረጃ የሰው፣ የኢኮኖሚ እና ግዜዋን በሙሉ ተጠቅማ ያላትን ሀይል እና አቅም አገር በመከላከል ላይ እንዳዋለችው ግልጽ ነበር። ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ የድንበሩን ጉዳይ በማንጠልጠል በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፎች አገሯን ማቃወስ፣ ማዳከም ብሎም ማፈራረስ ነበር የታቀደው ፕላን።
ይሄ እንዴት ተጀመረ?
በ2000 ላይ ሁለቱ ሀገራት የአልጀርስን ስምምነት ተቀብለው ጦርነቱን ባቆሙ ማግስት የጀመሩት እኩይ ተግባር ይህን ይመስላል። ከ110 ሽህ በላይ ኤርትራውያንን ለጸጥታ አስጊ፣ የሻብያ ኮማንዶ እና ሰላይ ብለው አበሳብሰው እና ዘርፈው ሲያባሩ በተመሳሳይ ከ3 ሽህ በላይ ለሻብያ የተጋደላቹ፣ ሳዋ እና ማእቶት(የተማሪዎች የክረምት ስራ ፕሮግራም) ተሳትፋቹሃል በሚል ከ15 እስከ 65 ዓመት እድሜ የሚገመቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የነበሩ ንፁሃን ኤርትራዊያንን መጀመርያ ከአዲስ አበባ ብዙም ከማትርቀው ፍቼ ከተማ ቀጥሎ ደግሞ ዴዴሳ ከሚባለው ወለጋ ውስጥ ከሚገኝ የደርግ ካንፕ የነበረ የእባብ እና የአውሬ መፈንጫ ጫካ ውስጥ ለ3 ዓመታት ያህል በግፍ ታስረው እንደነበረ ይታወቃል። የመጀመርያውን የስደተኛ ካንፕ ለመክፈት ያሰቡትም በነዚህ ከሰላማዊ ኑሯቸው እና ከትምህርት ገበታቸው ተለቅመው በግፍ ባሰሯቸው ዜጎቻችን ነው። ለነዚህ እስረኞች የቀረበላቸው ሁለት አማራጭ ነው፤ የመጀመሪያው ወደ ኤርትራ ትባረራላችሁ የሚል ማስፈራሪያ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የስደተኞች ካንፕ ውስጥ ግቡ እና አሜሪካ፣ አውሮፓ ወይም አውስትራሊያ ትሄዳላችሁ የሚል ማማለያ ሃሳብ ነው። እርግጥ ነው የበዙት አገራቸውን መሄድ መርጠው ጥር 2001 ላይ ወደ ኤርትራ ሲገቡ በተቀሩት እስረኞች የመጀመርያውን የስደተኛች ካንፕ በመክፈት ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስረከቧቸው። በአለም አቀፉ የስደተኞች ተጠሪ(UNCHR) ህግ መሰረት አንድ የስደተኞች ካንፕ የሚከፈተው የተፈናቀሉ ወይም የተሰደዱ ሰዎች ከ5 ሽህ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል። በመሆኑም ከዴዴሳ ተዛውረው በቀይ መስቀል እጅ የነበሩትን እስረኞች እና አንዳንድ ትግራይ ውስጥ ይንቀሳቀሱ ከነበሩ የኤርትራ ተቃዋሚ ኣባላት በመጨመር የራሳቸውን ሰው ከትግራይ ከተሞች ሰብስበው በመመዝገብ የመጀመርያውን ዋእላ ንህቢ የሚባለውን የስደተኞች ካንፕ በመክፈት እርኩስ አላማቸውን አህዱ አሉ። ማንም ሰው ሊረዳው የሚገባ በተለይ ኤርትራዊ የሆነ ሰው በደንብ ማወቅ ያለበት ይህ ሰፊና የተጠና ኤርትራን እና ኤርትራዊነትን የማጥፋት ሴራ ከጥንስሱ(ከመጀመርያው) እንዴት እንደተጀመረ መረዳት መቻል ፍጻሜው ወይም ዛሬ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለማወቅ አይከብድም። የመጀመርያው ካንፕ ከትግራይ ከተሞች የራቀ እና ለኤርትራ የቀረበ በመሆኑ የሻቢያ ስጋት አለ በሚል ምክንያት የትግራይ ከተሞችን ለመጥቀም ሲባል ሸራሮ አካባቢ በምትገኝ ሽመልባ ወደ ሚባለው ካንፕ በ2004 እንዲዛወር ተደረገ። በዚህ ካንፕ በቪዛ የተደለሉ እና ኢትዮጵያን እንደ መሻገሪያነት ሊጠቀሙ የመጡ ኤርትራውያን ወጣቶች ቢኖሩም 3 ሽህ ገደማ የሚሆኑት ግን ወያኔ 3ኛው ወረራ ላይ ባረንቱ ከተማ በገቡ ወቅት በኤርትራ ኩናማ ተቃዋሚ ስም በሚንቀሳቀሱ እና በወያኔ ጦር አማካኝነት ከኤርትራ ምድር እየተነዱ ይዘዋቸው የመጡ ኤርትራውያን ኩናማዎች ሲሆኑ የቀሩት እና የበዙት ግን በኤርትራዊያን ስም የተመዘገቡ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ይህን አሻጥር የተመለከተው እና የወያኔን ልብ አሳምሮ የሚያውቀው የኤርትራ መንግስት የህውሃትን ተንኮል ለማምከን በ2002 'ወፍሪ ዋራሳይ ይካእሎ' በሚል ፕሮግራም ወታደሩ እጥቁን ሳይፈታ አገሩን የሚያለማበት ስልት ቀይሶ የወያኔን 'ቀዝቃዛው ጦርነት' ፍሬ ኣልባ አደረገው። ይህን የተገነዘበው ህውሃት ግዜ ጠብቆ በ2008 የዲሞክራቶችን መመረጥ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ወደ ስልጣኗ በተመለሰቸው የምንግዜም የኤርትራ ጠላት በነበረቸው የአፍሪካ የፓለቲካ ጎዳዮች ጻህፊ ሱዛን ራይስ አማካኝነት በተቀነባበረ መልኩ ኤርትራ ላይ ከፍተኛ ወንጀል መስራት ተጀመረ። ይሄም በዚሁ አመት ኤርትራ ላይ ብዙ አይነት የኢኮኖሚ እና የጦር ማእቀብ መጣል። በኤርትራ መሪዎች ላይ የሰባእዊ እና የመብት ክሶችን በማዥጎድጎድ ኤርትራ እና ህዝቦቿን እያስጨነቁ ጎን በጎን ደግሞ ሽመልባ ካንፕ ያሉትን ስደተኞች በሙሉ ወደ አሜሪካ እና ወዳጆቿ አገራት በህብረት(Group Case) እንዲሄዱ ማድረግ ነበር። አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው መገንዘብ ያለበት በስዓቱ ሱዳን ገዳረፍ ውስጥ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ከአገራቸው የተፈናቀሉ ከ100ሽህ በላይ ኤርትራውያን ከ20 ዓመት በላይ ተቀምጠው ትግራይ ውስጥ በዛው አመት ማለትም 2008 ወደ ኢትዮጵያ የተሻገሩትን ጨምሮ ወጣት ስደተኞችን ቅድሚ እየተሰጠ ወደ አሜሪካና ሌሎች አገራት መላክ የኤርትራን ህዝብ የመበታተን ታላቁ ሴራ ነበር ። ይህን ተከትሎም ካንፑ ግንቦት 2008 ላይ ሞልቶ ተዘጋ። በዚህም መሰረት ኤርትራ ውስጥ ከወራት በፊት የነበሩ ሰዎች አሜሪካ በብዛት እንዲገቡ እና እንዲታዩ የተደረገበት በእቅድ እንደነበረ ልብ በሉ። ዜናውም በግፍ በትላልቆቹ የአለም ዜና አውታሮች ሳይቀር እንዲነገር ተደርጓል። ስለሆነም ይሄ ነው የሚባል ደሞዝ የለለው እና ለአመታት አገር ጠባቂ ሁኖ ለነበረው የኤርትራ ወጣት ከአገሩ እንዲኮበልል ግዴታም ምክንያትም ሆነ። በአጸፋው ከ2002-2008 ድረስ በብቸኛ ስታገለግል የነበረችው ይች የሽመልባ ካንፕ በቪዛ ምክንያት ሞልታ በዛው አመት ማለት በ6 ወር ግዜ ውስጥ ብቻ ሌሎች 2 ካንፓች ማለትም ማይ አይኒ እና ዓዲ ሓሪሽ ተከፍተው እና ሞለተው ሌሎች ተጨማሪ ካንፓች እንዲከፈቱ ተደረገ። 'ለመልካም ነገር ያልተፈጠረ ጭንቅላት ለተንኮል ተወዳዳሪ የለውም' እንደሚባለው ህወሓቶች በአገራችን ሰቆቃ በልጽገዋል። በዚህች ስዓት ጭምር በ60 ሽህ ኤርትራውያን ስደተኛች ስም የቦታ ክራይ ይከፈላችዋል። በሂወት ባሉትም ይሁን በየለሉት፣ ሊቢያ እና አውሮፓ በገቡት እና በተበታተኑት ምስኪን ዜጎቻች ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እየተላከላቸው በገንዘባቸው አዲስ አበባ በሚኖሩ ዜጎቻችን ስም ከአለም አቀፉ ማህበረሰቡ እና ድርጅቶች በሚሰበስቡት ብዙ ዓይነት እርዳታ የትግራይ ህዝብ ይቀለባል። ለነዚህ ሰዎች የኤርትራ ችግር ትልቁ ገቢ ምንጫቸው ስለነበረ እና ስለሆነ አሁን የተፈጠረው በዶ/ር አብይ የሁለቱ አገራት የሰላም ሁኔታ ቢያገሸግሻቸው እና ቢያበሳጫቸው ምን ያስደንቃል ???
ህውሃት ላለፈው ለዚህ ሁሉ እርኩስ ስራው በሙሉ አቅሟ ትደገፍ የነበረችው ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ጎዳይን በሽብርትኝነት ሰበብ ከአሜሪካ ጎንጎረስ ምልከታ ውጭ ተደርጎ ስልጣኑ በእጇ በነበረው Ambassador Susan Rice በምትባለው ጥቁር እባብ ነበር። ከ1998-2000 ሲፈልጎ የሻብያ ኮማንዶ እና ሰላይ ሲያሻቸው ደግሞ የአይናቹህ ቀለም ደስ ካላለን እንኳን ማባረር መብታችን ነው ያሉን ሰዎች፤ 2002 የመላእክት ክንፍ አውጥተው ለኤርትራዊ አዛኝ እና ተቆርቋሪ መስለው ህዝባችንን ለመበታተን በየከተሞቻቸው ካንፕ እየከፈቱ ምንም የማያውቁ አገር ተረካቢ ህጻናትን ጭምር አገራቸው ላይ ተረጋግተው ተምረው እና አድገው አገር የሚገነቡ ዜጎቻችን ላይ የፈጸሙት በደል ትውልድ አይረሳውም። ለኔ ይህ መርዘኛ የትግራይ ነጻ አውጪ(ህወሓት) ቡድን ተግባር ኤርትራውያንን ከኢትዮጵያ ካባረሩበት አስጸያፊ መንገድ ይልቅ ኤርትራዊያን ከአገራቸው እንዲሰደዱ እና እንዲበታተኑ ያደረጉበት ሰይጣናዊ አሻጥር መንገድ እጅግ በጣም የከፋ እና የባሰ ነው። አሁን ሱዛን ራይስ ከዋይት ሃውስ ህወሃትም ከ4ኪሎ ቤተ መንግስት ተባረዋል። ነገርግን ከአ/አ ወደ መቀሌ የተዛወሩት እና ጥቅማቸው የተነካባቸው ህወሓት እና ተላላኪዎቻቸው መርዛቸውን ከመርጨት እና ሰላሙን ከማድፍረስ መቸውም አይታቀቡም።
ልብ ያለው ልብ ይበል !!!
(ሰሚራ አምቼ)



MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

Re: መቀሌ የመሸገው የአሸባሪው የህውአት ቡድን ኢትዮጵያን አፈርሳለው ብሎ ጦር ከመዘዘ የመጀመሪያ የመልስ ምት የሚያገኘው ከኤርትራ መከላከያ ሀይል ነው !!!

Post by MatiT » 07 Jan 2020, 22:35

የኤርትራ ህዝብም ሆነ መንግስት የኢትዮጵያን የፌደራል መንግስትን እንጂ እውቅና የሚሰጠው መቀሌ የመሸገውን የወንጀለኞች ጥርቅም በፍጱም እውቅና አይሰጥም::
Eritrea//ኤርትራ🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷🇪🇷,,,https://www.facebook.com/yonasMalet/vid ... 593763250/


MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

Re: መቀሌ የመሸገው የአሸባሪው የህውአት ቡድን ኢትዮጵያን አፈርሳለው ብሎ ጦር ከመዘዘ የመጀመሪያ የመልስ ምት የሚያገኘው ከኤርትራ መከላከያ ሀይል ነው !!!

Post by MatiT » 24 Jan 2020, 20:01

From the whole world the only group or party that doesn’t accept Eritrea and Ethiopia internationally recognized borders is =TPlf

Digital Weyane
Member+
Posts: 8533
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: መቀሌ የመሸገው የአሸባሪው የህውአት ቡድን ኢትዮጵያን አፈርሳለው ብሎ ጦር ከመዘዘ የመጀመሪያ የመልስ ምት የሚያገኘው ከኤርትራ መከላከያ ሀይል ነው !!!

Post by Digital Weyane » 24 Jan 2020, 22:43

ጦርነቱ ኡዚህ ድህረ ገፅ ከተካሄደ ኡኛ ዲጂታል ወያኔ ኡናሸንፋለን። ጀግና ወያኔው ዎንድሜ አዋሽ ወዲ ዓድዋ ስሞቹን ኡንደ ሸሚዝ ኡየቀያየረ ይታገላችኋል።


Post Reply