Page 1 of 1

አንድ የኮሌጅ ምሩቅ ምህንድስና ስራ ቢያጣ ለማኝ ቢሆን ይሻላል ወይስ ሊስትሮ ቢሆን?

Posted: 18 Oct 2019, 00:15
by Horus
በሳይኮሎጂ ውስጥ ይህ ሰውዬ ፍጹም ጤነኛ ፍጹም ዘመናዊ ሰው ነው ። ይህ ነው ዳይናሚክ ታዳጊ ስብእና ወይም ፐርሰናሊቲ የሚባለው። አንድ ሰው ካንድ የህይወት ቦታ ወይም እስታተስ በዚህ መልክ እየለዋወጠ የህይወትን እንቅፋቶች ማለፍ ሲችል ነው የሳይኮሎጂካል ብቃት አለው የሚባለው ። ይህ ትልቅ ችሎታ ነው። ይህ ነው አዲሱ ካልቸር። የስራ ክቡርነት ማለት በአንድ ቃል ይህ ነው። ሁሉ ስራዎች እኩል አይደሉም ፣ ግን ስራ ሁሉ ክቡር ነው ። አሳፋሪና ትንሽነት መለመን ነው !!! ለማኝ መሆን ነው የመጨረሻው የሰው ቦታ ወይም እስታተስ ነው!!


Re: አንድ የኮሌጅ ምሩቅ ምህንድስና ስራ ቢያጣ ለማኝ ቢሆን ይሻላል ወይስ ሊስትሮ ቢሆን?

Posted: 18 Oct 2019, 00:52
by Horus
እናም ለምን የዚህ ልጅ ታሪክ እንደ ሳበኝ ልግለጽ ። የዛሬ 50፣ 60፣ 70 አመት በፊዉዳሉ ኢትዮጵያ ማንኛውም ዘመንዊ የፈጠራ የእጅ ስራ ፣ጥበብ እንደ ቆሻሻ በሚሰደብበት ኢትዮጵያ ከሊስትሮነት ተነስተው ግዙፍ ኢንዱስትሪ ላቆሙት ፍጹም ታዳጊ፣ ምንም ገደብ ለማይገታቸው፣ ኢትዮጵያን የስራ ክቡርነት ላስተማሩት ብርቅዬ ጉራጌ የባህል ፈጣሪዎች ምስጋና ለማድረስ ነው !!! አዲስ ኢትዮጵያ፣ አዲስ ካልቸር ማለት ይህ ነው እንጂ ማንም ያረጀ ቀኑ ያለፈ እምነት ይዞ አገርና ሰላም ማወክ አይደለም !! ኬር ዬሁን !!!

Re: አንድ የኮሌጅ ምሩቅ ምህንድስና ስራ ቢያጣ ለማኝ ቢሆን ይሻላል ወይስ ሊስትሮ ቢሆን?

Posted: 18 Oct 2019, 08:31
by eden
I was in Addis not long ago and a guy approached me and started talking. His university in the south was shut down due to security situation and he was willing to work any kind of work but unable to find any. He was clean and he sounded learned man. I have many families to help I told him as I felt guilty I couldn't give him more. It stuck with me.