Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

ለጠ/ሚር አብይ መፅሀፍ ምርቃት "ሚሊኒየም አዳራሹን ለቃችሁ ውጡ" የተባሉት የንግድ ትርኢት አዘጋጆች ተቸግረናል እያሉ ነው! [የአደባባይ ቅሌት]

Post by Revelations » 17 Oct 2019, 13:16

Please wait, video is loading...



Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ለጠ/ሚር አብይ መፅሀፍ ምርቃት "ሚሊኒየም አዳራሹን ለቃችሁ ውጡ" የተባሉት የንግድ ትርኢት አዘጋጆች ተቸግረናል እያሉ ነው! [የአደባባይ ቅሌት]

Post by Revelations » 17 Oct 2019, 14:21

ለጠ/ሚር አብይ መፅሀፍ ምርቃት "ሚሊኒየም አዳራሹን ለቃችሁ ውጡ" የተባሉት የንግድ ትርኢት አዘጋጆች ተቸግረናል እያሉ ነው!

አዘጋጆቹ ዛሬ እንዳሳወቁኝ ከ10 ሃገራት የተውጣጡ ከአንድ መቶ በላይ የንግድ ትርኢት ተሳታፊዎች እንዲሁም ከ4,000 በላይ ከሚሆኑ የንግድ ትርኢቱ ታዳሚዎች ከዛሬ ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ለ9ኛው የኢትዮ ፖልተሪ ኤክስፖ ለመሳተፍ ተዘጋጅተው ነበር።

ነገር ግን ትናንት ዱብዳ የሆነ ነገር አጋጥሞናል ይላሉ። እንደአዘጋጆቹ ከሆነ ቅዳሜ ለሚመረቀው የጠ/ሚር አብይ "መደመር" መፅሀፍ አዳራሹ ስለሚፈለግ "እቃችሁን አንሱ" ተብለዋል። ደብዳቤም ከከንቲባው ቢሮ እንደደረሳቸው ገልፀው አሁን ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ እንደገባቸው ተናግረዋል።

ስለዚህ ዛሬ ጠዋት ተከፍቶ የነበረው ኤግዚቢሽን ዛሬውኑ ተቋርጧል። "እቃችንን ይዘን እየወጣን ነው። ምን ማረግ እንዳለብን ግራ ገብቶናል" ብላ አንድ የንግድ ትርኢቱ አዘጋጅ በስልክ አሳውቃኛለች።

በጉዳዩ ላይ የከንቲባው ቢሮ መልስ ከሰጠበት እመለስበታለሁ!


Post Reply