Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ህወሃት ለመዝረፍ እንዲመቸው ለኢትዮጵያ የማሰቡን በጎ እድል ተሳስቶ በደግ አንስቶት ለማያውቀው የአማራ ህዝብ አሸከመው፡፡

Post by Za-Ilmaknun » 16 Oct 2019, 13:20

የኢትዮጵያ ብሄርተኝት ሰልፍ የተመናመነው ህወሃት ስልጣን ይዞ የዘውግ ፖለቲካን ህገ-መንግስታዊ እና መዋቅራዊ ካደረገ ወዲህ ነው፡፡ኢትዮጵያን በቅኝ ገዥነት ፈርጆ የፖለቲካ ጥርሱን የነቀለው ህወሃት ኢትዮጵያ እንድትኖር የሚፈልግው እርሱ መንበረ ስልጣኗ ላይ ሆኖ መዝረፍ እስከቻለ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ለመዝረፍ እንዲመቸው ደግሞ ህዝቦቿን በዘር ከፋፍሎ ማባላት ነበረበት፡፡ ያሰበውን በደምብ ለማሳካት ደግሞ ለኢትዮጵያ የማሰቡን በጎ እድል ተሳስቶ በደግ አንስቶት ለማያውቀው የአማራ ህዝብ አሸከመው፡፡ ስዚህ ኢትዮጵያን ማለት አማራ መሆን ማለት እስኪመስል ድረስ የታላቋ ሃገር የመኖር አለመኖር እጣ ህወሃት ሊያጠፋው ከቆረጠው የአማራ ህዝብ ጋር ተፈተለ፡፡ ህወሃት የአማራን አከርካሪ ሰበርኩ ሲል ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን ሽባ አደረግኩ ማለቱ ነበር፡፡

ኢትዮጵያን ማለቱ ያስጠቃው አማራም መዳን የሚችለው በሚያሳድነው አማራነቱ መደራጀት እንጅ የሞቱ መንስኤ በሆነው ኢትዮጵያዊነት አለመሆኑን ውሎ አድሮ በመረዳቱ ሳይወድ በግድ ወደ አማራነቱ መደብ ገባ፡፡ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትም በሞት ጥላ ስር ሆነ፡፡ይሄኔ የዘውግ ብሄርተኝነት በህገ-መንግስት ተደግፎ እናቱቤት እንዳለ ህፃን ሲዝናና ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ሰልፈኛ እንደ እንጀራ እናት ሆነች፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ቅሪት ያለው በኢትዮጵያ ከተሞች ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሃገሪቱ ከተሞች ከገጠር በመጡ የዘውግ ብሄርተኝነት ምልምሎች ቁም ስቅላቸውም ያያሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከተሞች ያለ ስጋት የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ያለበትን “የእልም ስልም” ኑሮ ያሳያል፡፡

እንዲህ ያለውን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ለመጥፋት የተቃረበ መዳከም እንደ ድል የሚያየው ኢትዮጵያ በግድ እንደተጫነችበት የሚተርከው የኦሮሞ ብሄርተኝነት ነው፡፡ከአክሱምጀምራ ስትሰፋ ሞያሌ የደረሰችውን ኢትዮጵያ “ነይልኝ” ብሎ ጋብዞ የተቀላቀለ ያለ ይመስል “ኢትዮጵያ መጥታ ተጭናብኛለች” በሚል የጫኝ ተጫኝ ተረክ የተገነባው የኦሮሞ ብሄርተኝነት እንደ ህወሃት ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን ለአማራ ለመሸለም ይቃጣዋል፡፡ ስዚህ ኢትዮጵያ ስትፈርስ ሰማይ ምድር የሚደፋበት አማራው ብቻ እንደሆነ ያስባል፡፡ አማራውን ግራ ማጋባት ካስቻለ ደግሞ ኢትዮጵያ ብትፈራርስም ለኦሮሞ ብሄርተኞች ችግር አይደለም፡፡

የኦሮሞ ብሄረተኞች ኢትዮጵያ ስትፈርስ ኦሮሚያን እንዳትነካ ተጠንቅቃ ይመስላቸዋልና ኢትዮጵያ ብትፈርስም ኦሮሚያ በፍፁም ሰላም ውስጥ የምትኖር አድርገው ያስባሉ፡፡ኢትዮጵያ ስትፈርስ ትልቁ ስባሪ ኦሮሚያ ስለሆነ፣ትልቁን ድርሻውን ይዞ ለመሄድ ያሰፈሰፈው የኦሮሞ ብሄርተኛ በርካታ ነው፡፡ እዚህ ላይ የተረሳው ነገር ሃገር ሲፈርስ የሃገር ስብርባሪ ለመካፈልም ጊዜ እንደሌለ ብቻ ሳይሆን በመፋረስ ሁኔታ ውስጥ ሁሉም ለራሱ ብዙ ለመውሰድ የሚሮጥ፣ መግደል የሚገባውን የሚገድል፣ማጥፋት የሚገባውን የሚያጠፋ ጉልበታም እንደሚሆን ነው፡፡