ጸንሰ ሃሳቡን የምወደው የቃሉ እምብርት ስራ ወይም ኤርጎን (ወርክ) ስለሆነ ነው። እኔ ብዙ ግዜ እንዳልኩት አንዱ ትልቁ የዘመናችን ኢዮጵያዊ እሴት መሆን ያለበት በስራ ክቡርነት ማመን ነው። መደመር የአብሮ መስራት ፍልስፍና እና ካልቸር ሆኖ መተርጎሙ አሜን የሚያሰኝ ነው።
አንድ አገር ወደ ስልጣኔ ሚሄደው በስራ ክቡረት ፍልስፍና ሲመራ ብቻ ነው።
አሁን ትልቁ የምሁራን ተግባር ይህ የመደመር ሃሳብ ወይም ሲ ነ ር ጂ፤
ፍልስፍናዊ ይዘቱን መተንተንና ማየት፣
ንድፈ ሃሳቡ ምን እንደ ሆነ በታትኖ ማየትና ማጥራት፣
ክህሎታዊ ወይም እስትራተጂው (ሜትዶሎጂው) ምን እንደ ሆነ ጸሃይ ላይ ማውጣትና
መደመር በተግባር ሲገለጽ ምን አይነት ውጤትና ፋይዳ እንደ ሚወልድ ማሳየት አለባቸው ።
ቁም ነገሩ የጽንሱ ዝርዝር ይዘት ላይ ነው። ማለትም
በፖለቲካ፣
ኢኮኖሚ፣
ሶሺያል፣
ካልቸር፣
ዲፕሎማሲ፣
ሚሊታሪ ፣
ወዘተ መስኮች መዘርዘር ማለት ነው
ግ ን የፍልስፍናው እምብርት ስራ መሆኑ እጅግ ትክክል እና ፋና ወጊ ነው !
ሰዎች የመደመር ፍልስፍናም እንበለው ፕሮግራምን ለመመዘን እንዴት ይችላሉ? ምን አይነት መለኪያ መጠቀም ይችላሉ?
አንዱና ብቸኛው መለኪያ የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው ። የሚጠይቁት ቀጥተኛ ጥያቄ ፤ ይህ ፕሮግራም የኢትዮጵያን አጀንዳ ከግብ ያደርሳልን የሚለው ነው ። አጀንዳው የሚከተሉትን 4 ግቦች አሉት ።
አንድ፣ የኢትዮጵያን አንድነት፣ መረጋጋት እና ጥንካሬ እውን ማደርግ ፤
ሁለት፣ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ህብረተሰብ እውን ማደረግ፤
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን የበለጸጉ፣ የተማሩ እና ጤናማ ሕዝብ ማድረግ ፤
አራት፣ በኢትዮጵያ የሚፈጥር፣ ከባቢ ሚጠብቅ እና መንፈሳዊ ካልችር መገንባት ናቸው ።
መደመር እነዚህን አላማዎች ካነገበ ፍጹም ተደጋፊና ስኬታማ ሃሳብ ይሆናል ፣ መለኪያውን የህው ነው ።