Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 33735
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የአደባባይ ሰይፍን ፈቅዶ የአደባባይ ስልፍን መከልከል ምን ይሉታል? [PHOTO]

Post by Revelations » 13 Oct 2019, 08:03

ባለአደራ ም/ቤቱም ሆነ ጋዜጠኛ እስክንድር ጨዋታውን በዝረራ አሸንፈዋል።

አማራ ሚድያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ማሸነፍ የሚገኘው ሁሌ የፈለከው ስለተደረገልህ አይደለም።በአፈና ውስጥም ማሸነፍ አለ።

የባለ አደራው ም/ቤት ለጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም የጠራው ሕዝባዊ ሰልፍ ዋና ዓላማው ያለምንም ወንጀል በማንነታቸው የታፈኑ ዜጎች እንዲለቀቁ ለመጠዬቅ፣ አምባገነንነትን ለመቃወም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን አፓርታይዳዊ አገዛዝ ለማውገዝ፣ የሕዝብ ፍላጎትና ድምፅ እንዲሰማ ለማሳሰብ፣ በአጠቃላይ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ሰላም እንዲኖር መንግስትን ለመጠየቅ ነበር።

ነገር ግን ሕዝቡ ወጥቶ በሰልፍ ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ ሳይጮህ፣ ፊቱ እስኪወረዛ ፀሐይ ሳይጠብሰው፣ የእግር ጉዞ ጉልበቱን ሳያዝለውና ውሃ ጥም ከንፈሩን ሳያቆረፍደው መንግስት አምባገነንነቱን ለዓለም አስመስክሯል።

ከሳምንት በፊት ከየገጠሩ በጭነት መኪና ሕዝብን በገፍ እየጫነ በማምጣት መሀል አዲስ አበባ ላይ የሀይማኖቱ ተከታዮች በማይኖሩበት ከተማ የእሬቻን ኃይማኖታዊ በዓል የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ አውርዶ የፈለገውን ዓርማ ሰቅሎ በነፃነት ያከበረው ተረኛው መንግስት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሰልፍ እንዳያደርጉ አግዷል።

ሰልፉን ከመከልከል በዘለለም በሰላማዊ መንገድ ሀሳባቸውን ለመግለፅ የተዘጋጁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በገፍ በማሰር አምባገነንነቱንና አፖርታይድነቱን ለዓለም አስመስክሯል።

ይህ ብቻም አይደለም በአዲስ አበባ ከተማ ለተከበረው የእሬቻ ኃይማኖታዊ በዓል ከመላው ኦሮሚያ በገፍ ሕዝብን በጭነት መኪና አምጥቶ ለፖለቲካ ትርፍ የተጠቀመው ተረኛው መንግስት ፤እንደራሱ መስሎት የባለአደራው ም/ቤት በጠራው ሰልፍ እንዳይሳተፉ በሚል አዲስ አበባ ከተማን በ4ቱም አቅጣጫ በፖሊስ በመዝጋት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ነጋዴዎች፣ የህክምና ቀጠሮ የነበረባቸው ታማሚዎች፣ መንፈሳዊ ጉብኝት አድርገው የሚመለሱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችንና ሌሎች ለግል ሥራ ወደ መዲናይቱ ለመምጣት በጉዞ ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎችን ለተጨማሪ ወጭና ለአላስፈላጊ እንግልት ዳርጓል።

ከዚህ በላይ አምባገነንነት ከየት ይመጣል ?!

ሀገሪቱ በነዚህና ከዚህም በባሰ የከፋ የሰላም እጦት ብትከርምም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ የሰላም የኖቬል ሽልማት መሰጠታቸውን አስመልክቶ በመላው ኦሮሚያ የድጋፍ ሰልፍ ተፈቀደ፤ በተመሳሳይ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ የታቀደው የተቃውሞ ሰልፍ ግን ታገደ።

ይኸው አምባገነኖችም ከእነሱ ፍላጎት ውጭ የሆነውን ሰልፍ በማፈን እነሱን ለሚደግፉት ሰልፍን ፈቀዱ።

ዓምባገነንነታቸውንም ትላልቅ የመገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ ለዓለም ሕዝብ ነገሩባቸው።

በዚህም የአዲስ አበባ ሕዝብና የባለ አደራው ምክር ቤት ያለምንም ልፋት ዓላማቸውን አሳክተው በዝረራ አሸነፉ። ለዚህ ነው በመታፈን ውስጥም አሸናፊነት አለ የምንለው።

በነገራችን ላይ የእሬቻ በዓል በተከበረበት ወቅት ከፖለቲካ ፖርቲ ዓርማ በተጨማሪ ሜንጫም በአደባባይ የያዙ ወጣቶች ያለማንም ከልካይ የሜንጫ ትዕይንት ሲያሳዩ ነበር።

ለባለተራዎች የአደባባይ ሰይፍ ሲፈቀድ ለከተማዋ ነዋሪዎች ግን ሰላማዊ ሰልፍ ተከልክሏል።

የአደባባይ ሰይፍን ፈቅዶ የአደባባይ ሰልፍን የሚከለክል ተረኛ ብቻ ሳይሆን አፓርታይድም ለመሆኑ ትልቅ ማስረጃ ነው።



Post Reply