Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
yaballo
Member
Posts: 2862
Joined: 16 Feb 2013, 02:30

BOOK & OPINION: [1] ፍጠኛ ስርዓት በደቡብ ክልል ብሔረሰቦች ታሪክ ሲተነተን። [2] ነውር ጌጣችን ነው ካላቹ እንግዴ ምን ይደረጋል። የነፍጠኛው ገዢ መደብ ግብር ይኽው።

Post by yaballo » 09 Oct 2019, 22:06

BOOK & OPINION: [1] ፍጠኛ ስርዓት በደቡብ ክልል ብሔረሰቦች ታሪክ ሲተነተን - የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የፀረ-ጭቆና ትግል ታሪክ። [2] ነውር ጌጣችን ነው ካላቹ እንግዴ ምን ይደረጋል። የነፍጠኛው ገዢ መደብ ግብር ይኽው።[1] - ነውር ጌጣችን ነው ካላቹ እንግዴ ምን ይደረጋል። የነፍጠኛው ገዢ መደብ ግብር ይኽው።

photo: on "The Abyssinian aka Ethiopian Neftegna-Gabbar system in Southern Ethiopia" ... extracts from books.

<<ነውር ጌጣችን ነው ካላቹ እንግዴ ምን ይደረጋል። የነፍጠኛው ገዢ መደብ ግብር ይኽው

ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ሆኖ እንጂ ነፍጠኛው ገዢ መደብ እንጂ አንድ ብሄር እንዳልሆነ ደጋግመን ተናግረናል። ክብር መስሎዋቹ ከዛ ግፈኛ ስርአት ጋር እራሳችሁን ማጣበቅ የምትፈልጉ ሰዎችን እንግዲ የነፍጠኛውን ነውሮች በመዘርዘር ለማስረዳት እንገደዳለን።

በዝባዥ የነበረው የነፍጠኛ ስርአት እጅግ አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩ ብሄሮች (ጉራጌ፣ ሲዳማ፣ ሀድያ፣ ከምባታ) ወዘተ ውስጥ የሚኖሩ ገባሮች ጣሊያን ሲመጣ ቀንበሩን ያቀልልናል በሚል ደስተኞች ነበሩ።

ጣሊያንስ ቢሆን ከደም መምጠጥ እና ከባዶ ትእቢት ሌላ ለህዝቡ የሚሰጡት ስልጣኔ ከሌላቸው ነፍጠኞች በምን ሊከፋ?? ኤቭሊን የተባለው ጸሀፊ እንደከተበው ነፍጠኞች ህዝቡን በንቀት እየገረመሙ ፣ ተጎልተው የህዝቡ ሰብል ከማራቆት ውጪ ያስተዋወቁት ስልጣኔም ይሁን በጎ ነገር እምብዛም አልነበረም (ለነገሩ በነፍጥ ሀይል ከወረሩት ማህበረሰብ የተሻለ አንዳች ስልጣኔ ቢኖራቸው አልነበር ስልጣኔን ማስተዋወቅ የሚችሉት??) በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ላይ በቀረበ ሪፖርት ላይም ነፍጠኛው ገባሮችን (በኦሮሚያ እና ደቡብ) እንዴት ያሰቃይ እንደነበር ተቀምጧል። ምግብ ከማቅረብ፣ አጥር ከማጠር፣ ቤት ከመስራት ጀምሮ ገባሮች ለነፍጠኛው በርካታ ግልጋሎቶችን ይሰጡ ነበር።

አንድ የጉራጌ አባት ስለ ነፍጠኛው ባሉት ነገር እጨርሳለሁ: "ነፍጠኛው እኛ ጉራጌዎችን እንደ አቻ ሳይሆን እንደ ባሪያ ነበር የሚያየን። በግፋቸው ምክን ያት እግዚአብሄር ወደ ማይጨው ወሰዳቸው ጣሊያንም እዛ ፈጃቸው። እግዚአብሄር ጩኽታችንን ሰምቶ ማይጨው ላይ ተአምር ተፈጠረ። ከዛ በኋላ ለነፍጠኛው ምንም ከፍለን አናውቅም። አሁን እኛም እነሱም እኩል ነን።"


እኚህን የጉራጌ አባት ይሄን ያህል በምሬት ያናገራቸው የሀገር ጥላቻ ሳይሆን የነፍጠኛው መረን የለቀቀ ብዝበዛ እና ግፍ ነው።

ነውር ጌጣችን ነው ላላቹ የነፍጠኛውን አጸያፊ ነውሮች አውጥተን ጸሀይ ላይ ማስጣቱን እንቀጥላለን። በመንጋ ጩኽት ብዛት እውነትን መደበቅ አይቻልም።
`
#ነፍጠኛው_ገዢ_መደብ_እንጂ_እንደማንም_ሲጨቆን_የኖረው_የአማራ_ህዝብ_አይደለም!>>


SOURCE: https://www.facebook.com/rediet.tamire? ... yo&fref=nf
...........


[2] - ፍጠኛ ስርዓት በደቡብ ክልል ብሔር ሔረሰቦች ታሪክ ስተነተን፣

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የፀረ-ጭቆና ትግል ታሪክ። ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) 2007. ካሳተመው መጽሐፍ በአጭሩ የተወሰደ፣ (ምዕራፍ ሦስት)።

3.0. የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፀረ-ጭቆና ትግል ገፅታ፣

ከላይ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተጠቀሰው የክልላችን ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ስርዓት ህልውናውን ሊያጣ የቻለው እ.ኤ.አ. ከ1880ዎቹ እስከ 1890ዎቹ ወይም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ አካባቢ (ከዛሬ መቶ ሃያ ዓመታት በፊት) በተስፋፋው የነፍጠኛ ስርዓት ምክንያት ነበር። የዚህ የጭቆና ስርዓት መስፋፋት የክልላችንን ህዝቦች ለገደብ የለሽ ብሄራዊና መደባዊ ጭቆናና ብዝበዛ ዳርጓቸዋል። ህዝቦችም ብሄራዊ መብታቸውን ላለመነጠቅና ከጭቆናው ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት መራራ ትግል አካሂደዋል።

3.1. በደቡብ የፊውዳል ነፍጠኛ ስርዓት አመጣጥና የጭቆናው ገጽታ፣

የፊውዳል ነፍጠኛ ሥርዓት በደቡብ የተስፋፋው በአስራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን አፄ ሚኒሊክ ግዛቱን ወደ ዛሬው ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የማስፋፋት ሲል ባካሄደው ወረራ አማካኝነት ነበር፡፡ ይህ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግስት ግዛት ለማስፋፋት የጦርነት ዘመቻ በአፄ ቴዎድሮስና በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግስትም ተጀምሮ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም የግዛት ማስፋፋት ዘመቻውን ከሰሜን ወደ ደቡብ በማዝለቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና የነበረው አፄ ሚኒሊክ እንደነበር ይታወቃል፡፡
የአፄ ሚኒሊክ የደቡብ ዘመቻ ከግዛት ማስፋፋት በተጨማሪ ሌሎች ኢኮኖማያዊና ፖለቲካዊ መነሻዎችም ያሉት መሆኑን ታሪክ ያስረዳል፡፡ ፖለቲካዊ መነሻው አፄ ሚኒሊክ በወቅቱ ከሰሜን ተቀናቃኞቹ ጋር በስልጣን ፍክክር ላይ ስለነበረ በዚህ ፉክክር የበላይነት እንዲኖረው የሚያግዘውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ሀብት ለማግኘት የነበረው አማራጭ ሰፊ የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆኑትን ከላይ የተጠቀሱ አካባቢዎችን በወረራ መያዝ ነበር፡፡ በወቅቱ በሀገሪቱ በተከሰተው ድርቅና ረሀብ ምክንያት በሠራዊቱና በህዝቡ ዘንድ የተከሰተውን ችግር መፍታት ይችል ዘንድ ሠራዊቱንም ሆነ ሲቭሉን ህዝብ ማስፈር የሚያስችል አዲስ፤ ሰፊና ለም አካባቢ መፈለግ ደግሞ የወራሪው ኃይል ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንደነበረ ይጠቀሳል፡፡
የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አካባቢዎች የነበራቸውን የተፈጥሮ ሀብት እና ለረጅም አመታት የገነቡትን የተረጋጋ አስተዳደር ሁኔታ በማየት አፄ ሚኒሊክ ለዘመናት የጦርነት ግንባር ሳይሆን የቆዩ አካባቢዎችን በራሱ ቁጥጥር ስር ቢያደርግ አንድም ከሰሜኑ የሀገራችን አካባቢዎች በየጊዜው እየተነሳ የሚያስቸግረውን የስልጣን ተቀናቃኝነት ግጭቶችን ለማስወገድ ሰፊ ተከታዮችን በማፍራት መቋቋም እንደሚቻል በመረዳት እና በሌላ በኩል የአስተዳደር ግዛቱን በማስፋት ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለውን የኢኮኖሚ አቅም ለመፍጠር ለም እና ምርታማ መሬት በማግኘት ሰፊ ግብር ለመሰብሰብ ነበር፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ እንደተመለከተው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት የደረጀ ሥርዓት ነበራቸው፡፡ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ (ነፍጥ) የታጠቁ የአፄ ሚኒሊክ ወታደሮች ወደ ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች አካባቢ ነባሩን የአስተዳደር ስርዓት በሃይል በመደምሰስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነትን ለመያዝ ባካሄዱት ዘመቻ ህዝቦቹ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸውን ላለማጣትና ህሊውናቸውን ላለማስደፈር እስከመጨረሻው ተፋልመዋል፡፡
አፄ ሚኒሊክ ግዛት የማስፋፋት ወረራ ለማካሄድ ወደ ደቡብ እንቅስቃሴ ሲጀምር ባጭር ጊዜ ያለ ብዙ መስዋትነት አካባቢውን መቆጣጠር እንደሚቻል ግምት ቢኖረውም የደቡበ ክልል ሁሉም ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀደም ሲል ለረጅም ዓመታት ህዝባቸውንና መሬታቸውን ከወራሪዎች የሚጠብቁበት የየራሳቸው የሆነ ሥርዓት ስለነበራቸው የአፄ ሚኒሊክን የማዕከላዊ መንግስት ምስረታ ጥሪንና የግብር ክፈሉ አዋጅ በቀላሉ ሊቀበሉት አልቻሉም፡፡

ከላይ የተመለከተውን ፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ዓላማ ለማሳካት ሲል አፄ ሚኒሊክ በተደራጀ ሁኔታ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሰፊ የጦርነት ዘመቻውን ከፈተ፡፡ በመሠረቱ የሚኒሊክ ወረራ በመላው ሀገሪቱ በሁለት መልክ የተፈፀመ ሲሆን አንደኛው አካባቢዎችን ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት መቆጣጠር እና ሌላው ደግሞ ያለውጊያ ጥሪውን ተቀብሎ በመፈፀም የሚገለፁ ነበሩ፡፡ ከዚህ አኳያ ሁሉም የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ነፃነታቸውን ላለማጣት እና ግዛታቸውን ላለማስደፈር ባካሄዱትና ዓመታትን ባስቆጠረው ጦርነት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የክልሉ ህዝብ ህይወቱን እንዳጣ የታሪክ ድርሳናት ያመለክታሉ፡፡ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ የሚኒሊክ ጦር በተደጋጋሚ እ.ኤ.አ. ከ1867 እስከ 1875 እና በ1889 ከጉራጌ እና ከቀቤና ህዝቦች ጋር ከፍተኛ የሆነ ውጊያ አካሂዷል፡፡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

የካፊቾ ህዝብ በተመሳሳይ መልኩ ከ1880 እስከ 1897 የፊውዳሉ ነፍጠኛ ስርዓት ወረራ ለመከላከል ከ18 ዓመታት በላይ የፈጀ ጦርነት አካሂዷል፡፡ ከፍተኛ ጦርነት በመካሄዱ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠር የከፋ ህዝብ መስዋዕት ሆኗል፡፡ የቤንች፣ የሸካ፣ የመኢኒት፣ እና ሌሎች በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ወረራውን ለመመከት ከ1890 እስከ 1897 ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውጊያ አካሂደዋል፡፡ ከ1894 እስከ 1897 ድረስ ባለው ጊዜ የወላይታም ህዝብ የነፍጠኛውን ስርዓት አስከፊነት ተገንዝቦ ከአፄ ሚኒሊክ ጦር ጋር ከፍተኛ የሆነ ውጊያ በማድረግ በብዙ ሺዎች የሚገመት ህዝብ መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡

የዳውሮ ፣ የጋሞ፣ የጎፋ ፣ የየም ፣ የኦይዳ፣ የባስኬቶ እና የኮንታ ህዝቦችም ከ1889 እስከ 1897 ዓ.ም ባለው ጊዜ ሰፊ ውጊያ አካሂደዋል፡፡ ከ1890 እስከ 1897 ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ የሲዳማ፣ የጌዴኦ ፣ የከምባታ ፣ የሃላባ፣ የጣምባሮ፣ የዶንጋ፣ የቡርጂ፣ የኮንሶ፣ የደራሼ እና የኮሬ ህዝቦች ውጊያ አካሂደዋል፡፡ ከ1875 እስከ 1891 ባሉት ዓመታት ውስጥ የሃዲያ፣ የማረቆና የስልጤ ህዝቦችም ከአፄ ሚኒሊክ ጦር ውጊያ ላይ ሆነው የእርሻን ስራ ሴቶች ወጥተው በሬ ጠምደው ያርሱ እንደነበር የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡
በአሁኑ የደቡብ ኦሞ ዞን ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦችም ከ1897 እስከ 1898 ባሉት ዓመታት የየራሳቸውን አካባቢ ከወረራ ለመከላከል ጦርነት አካሂደው የብዙ ወገኖች ህይወታቸው አልፏል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ሂደት በተለያዩ የደቡብ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች ይህን የፊውዳሎች የግዛት ማስፋፋት እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ ከ1867 እስከ 1898 ድረስ ባለው ጊዜ ቢፋለሙትም በተለይ በአንዳንድ አካበቢዎች በመጀመሪያው ዙር ሽንፈት ገጥሞት ከወጣ በኋላ ከጣሊያን ወረራ በኋላ በአድዋ ድል ወቅት የተገኘውን ዘመናዊ መሳሪያ በመጠቀም ኃይሉን አጠናክሮ በመግባቱ በ1890ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች አካባቢን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ቀደም ሲል ዓላማ አድርጎ ሲንሳቀስ የነበረውን መሠረታዊ የፖለቲካ እና የመሬት (የኢኮኖሚያዊ ) የበላይነት የሚያረጋግጥበት ሁኔታ ተፈጠረለት፡፡
የአፄ ሚኒሊክ ነፍጠኛ ሰራዊት ወደ ደቡብ ያደረገውን የመስፋፋት ዘመቻ ሁሉም የክልሉ ህዝቦች በመቃወም ታግለዋል፣ ተዋግተዋል፡፡ የትኛውም ህዝብ ጨቋኙን ስርዓት አሜን ብሎ ያልተቀበለ መሆኑን ከየአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይመሰክራሉ፡፡ ይሁን እንጂ የመከላከሉ ትግል ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ከታጠቀ ኃይል ጋር እና ያልተቀናጀና የተበታተነ በመሆኑ መሸነፍ ግድ ሆኖበት ነበር፡፡

3.1.2 የፊውዳል ነፍጠኛ ሥርዓት የጭቆና ገፅታ፣

የፊውዳል ነፍጠኛ ስርዓት ከላይ በተጠቀሰው መልኩ በኃይል በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መሬት ላይ ከተተከለ በኋላ ህዝቦቹ ለገደብ የለሽ ኢኮኖሚያዊና ብሄራዊ ጭቆና ተዳርገዋል፡፡ ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳደሩበት ሥርዓታቸው ተወግዶ በባዕድ አገዛዝ ስር ወድቀዋል፡፡ በተፈጠሩበት፣ በኖሩበትና ባለሙት መሬት የባለቤትነት መብት ተነፍገው ለገባርነትና ለጪሰኝነት ተዳርገዋል፡፡ የህሊውናቸው መሰረት የሆነውን ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና እምነታቸውን እንዲተውና እንዲክዱ ተገድደዋል፡፡ በአጠቃላይ ማንነታቸውን፣ ሥልጣናቸውን፣ በራስ የመተማመን ብቃታቸውንና ደህንነታቸውን አጥተው ለበታችነት ተዳርገዋል፡፡

የፊውዳል ነፍጠኛ የፖለቲካ ስልጣን ኢኮኖሚያዊ መሰረቱ መሬት በመሆኑ ከመሬት ይዞታ አንፃር በተለያዩ ጊዜያት ሥርዓቱ የተከተላቸውን ፖሊሲዎች ማየቱ ስርዓቱ በህዝቦች ላይ ያስከተለውን ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ ተፅእኖ የመግለፅ እቅም ይኖረዋል፡፡

የታሪክ ምሁራን በነፍጠኛው ስርዓት ወቅት በደቡብ የነበረውን የመሬት ይዞታ ፖሊሲ በሶስት ይከፍላሉ፡፡ አፄ ሚኒሊክ የደቡብን መሬት በወረራ ከያዘበት ጊዜ አንስቶ እስከ ፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ድረስ ባለው ጊዜ የነበረው የመሬት ይዞታ በአብዛኛው ‹‹ የገባር-ነፍጠኛ‹‹ ሥርዓት ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የመሬት ይዞታ ፖሊሲ መሰረት የደቡብ መሬትና ህዝብ ለማዕከላዊ መንግስቱ፣ ለጦር አበጋዞች፣ ለጉልተኞችና ለባለስልጣኖች ደመወዝ ይሆናቸው ዘንድ ተቆጥሮ የተሰጠበትና ለነፍጠኛው የገንዘብ፣ የዓይነትና የጉልበት ግብር እንዲከፍል የተገደደበት ሥርዓት ነበር፡፡ ሁለተኛው ወቅት ደግሞ በፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት የነበረው የመሬት ይዞታ ፖሊሲ ሲሆን ይህ ወቅት የፋሽስቱ ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የደቡብን ህዝብ ከአገሪቱ መንግስት ለይቶ ለራሱ እንዲወግን ለማድረግ በማሰብ ህዝቡ የመንግስት ግብር ብቻ በመክፈል የመሬቱና የምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረገበት ወቅት ነበር፡፡ ሦስተኛው የመሬት ስሪት ደግሞ አፄ ኃይሌ ሥላሴ ከነፃነት በኋላ በህገ-መንግስትና ተያያዥ ህጎች በማስደገፍ ያመጡት የመሬት ስሪት ‹‹የጉልተኛ-ጪሰኛ‹‹ የመሬት ስሪት ነበር፡፡ ይህ የመሬት ፖሊሲ የጥንቱ የገባር ህግና ሥርዓት ቅርፁንና መልኩን ብቻ ለውጦ ህዝቡ ከመሬቱ ተነቅሎ ለጉልተኛው ጪሰኛ የሆነበትና መሬት በጉልተኛው የግል ባለቤትነት የተያዘበት ሥርዓት ነበር፡፡

በገባር-መልከኛም ሆነ በጉልት-ጢሰኛ የመሬት ስሪት መሰረት በደቡብ ተጨባጭ ሁኔታ የጦር መሳሪያ ወይም ነፍጥ ታጥቆ የዘመተው ኃይል ወታደራዊ የበላይነቱን ቋሚነት ባለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት ተካው ፡፡ ይኸው ነፍጠኛ በየአካባቢዎቹ የለም መሬት ባለቤትም ሆነ፡፡ ይህን ለም መሬት ራሱ አርሶ ሊጠቀምበት ስለማይችል የአካባቢው ህዝብ ለነፍጠኛው በገባርነት/በጭሰኝነት ተደለደለ፡፡ መሬትም በሶስት የይዞታ ፈርጆች ተመድቦ ለመንግስት ሹማምንቶች እና ለጦር አበጋዞች ተከፋፈለ፡፡

በዚህም መሠረት “የገባር መሬት” “የባላባት መሬት” እና “የመንግስት መሬት“ በሚል ተለየ፡፡ በዘመኑ በደቡብ የገባር መሬት ሲባል የአካባቢው ነባር ብሔረሰቦችና አርሶ አደሮች ለሰፋሪ ወታደሮች፣ ሹማምንቶችና ቄሶች እንዲሁም ለማዕከላዊው መንግስት ለሚሰጡ ልዩ ልዩ መንግስታዊ የምግብ፣ የጉልበት፣ የሥራ፣ የአስራት የምርትና የግብር አገልግሎቶች ዋጋ በግል ይዞታ የሚሰጣቸው የአገልግሎት ግዴታውን ባያሟሉ በመንግስት የሚወረስ መሬት ነበር፡፡ የባላባት መሬት ደግሞ የአካባቢው የቀድሞ የጎሳ ተጠሪዎች የገዥ መደብ መሪዎችና አባሎች አሁን በህዝቦቻቸው ላይ የማዕከላዊው መንግሥትና ሰፋሪ የመንግስት ሹማምንቶች ጉዳይ አስፈፃሚ ወኪሎች በመሆን ለሚሰጡት የሥራ አገልግሎት ከመንግስት በግል ይዞታ የሚሰጥ፤ ባላባቱ የሚፈልግበትን አገልግሎት ለተጠቃሚው ክፍል በወቅቱ ባይሰጥ ግን በመንግስት የሚወረስ መሬት ነው፡፡ የመንግስት መሬት ሲባል ደግሞ ቋሚ ይዞታው የማዕከላዊው መንግስት ሆኖ የቤተመንግስት መሬት እየተባለ ለተወሰነ አገልግሎት ዘመን ከነፃ የገባር አገልግሎት ጋር የመሬቱን ፍሬ አበል እንዲጠቀሙበት ለወታደር፣ ለሹም፣ ለመሳፍንት፣ ለቤተክርስቲያን ለንጉስ የሚታደል በተጠቃሚው ግለሰብና ድርጅት ግን እንደ የግል ሀብትና ንብረት የማይሸጥ የማይለወጥ በውርስም ለሌላ የማይሰጥ የህብረተሰቡ ብሔራዊ ሀብትና ንብረት ነበር፡፡ ከዚህ ከተከፋፈለው መሬት ውስጥ ገባሩ /ጭሰኛው/ አርሶ ከሚያገኘው ምርት እስከ 75 በመቶ ድረስ ለነፍጠኛው ያስረክባል፡፡ የሚያገኘው ምርት ምን ያህል ቁና ወይም ኩንታል እንደሚሆን የሚገምተው ነፍጠኛው ነበር፡፡ አርሶአደሩ በተጨባጭ ያመረተው ምርት ከዓመቱ በታች ከሆነ ወይም ምርቱ በተፈጥሮ አደጋ ቢወድም ተበድሮ ተለክቶ የተገመተውን ያህል ግብ ለነፍጠኛው ማቅረብ የአርሶአደሩ ግዴታ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጭሰኛው እና መላው ቤተሰቡ ለነፍጠኛው የተለያዩ የጉልበት አገልግሎቶችን የመስጠት ግዴታም ተጥሎባቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት በሚያገኘው የኢኮኖሚ ጥቅም በመታገዝ የፊውዳል ነፍጠኛ ሥርዓት የፖለቲካ ስልጣኑን ማጠናከር ችሏል፡፡

አርሶ አደሩ ለነፍጠኛው በዓይነትና በገንዘብ ግብር እንዲከፍል ማድረግና በጉልበቱም እንዲያገለግላቸው ማስገደድ የሥርዓቱ የብዝበዛ ስልት ነበር፡፡>>


SOURCE: https://www.facebook.com/melkamu.temesg ... 6089984641