Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member
Posts: 4402
Joined: 24 Aug 2012, 12:02

TPLF CC starts its Regular meeting

Post by MINILIK SALSAWI » 09 Oct 2019, 07:48

የህወሓት ማዕካላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ።

ማዕከላዊ ኮሚቴው በስብሳበው የ2011 ዓ.ም ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራትን የሚገመግም ሲሆን፥ በተለይ መልካም አስተዳደርን በማስፈን እና ልማትን በማረጋገጥ በኩል ያሉትን አፈፃፀሞች በዝርዝር ይመለከታል።

ከዚህ ባለፈም በ2012 ዓ.ም አቅድ ዙሪያ በዝርዝር በመወያየት እቅዱን እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው።

እንዲሁም የድርጅቱን መመሪያዎች እና አሰራሮችን በመገምገም ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በ2011 ዓ.ም የነበሩ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጥንካሬዎችን እና ጉድለቶችን በዝርዝር በማየት ያሉትን ተግዳሮቶች ለመከላከል የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተጠቁሟል።

እነዚህ ተግዳሮች የሚፈጥሩትን ጫና ከክልሉ ህዝብ ነበራዊ ሁኔታ ጋር በማያያዝ በመልካም አስተዳደር፣ ልማት እና የህዝብ ህልውና ያሉትን ሁኔታዎች ገምግሞ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)