Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 21355
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

[DW UPDATE] ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Revelations » 07 Oct 2019, 00:05

Please wait, video is loading...
Last edited by Revelations on 09 Oct 2019, 14:26, edited 1 time in total.

Revelations
Senior Member+
Posts: 21355
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Revelations » 07 Oct 2019, 00:10

ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ

ዋዜማ ራዲዮ- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት መርሀ ግብር ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተገነቡ 20/80 የጋራ መኖርያ ቤት ኮንደሚኒየሞች ውስጥ 22915 ቤቶች ነገ በአዲስ አበባ ዳርቻ ለልማት በሚል ተነስተዋል ለተባሉ አርሶ አደር አባወራዎችና 18 አመት ለሞላቸው ልጆቻቸው ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቋል።

ዋዜማ ራዲዮ ቤቶቹን ለመረከብ ከጫፍ ደርሰዋል ከተባሉ ግለሰቦች ያገኘቸው መረጃ እንደሚያሳየውም ተነሽ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ነገ ማክሰኞ መስከረም 27 ቀን 2012 አ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የትኛው ሳይት ምን አይነት ቤት እንደደረሳቸው ይገለጽላቸዋል ተብሏል።ቀደም ብሎም የእጣ ቁጥር እንደተሰጣቸውም ታውቋል።

ነገ ለሚከናወነው ስነስርአትም ሲባል ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተመረጡት የጋራ መኖርያ ቤቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚወስዳቸው ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል። ጉዳዩንም የቤቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ሚስጥር እንዲይዙት የተነገራቸው መሆኑን ፣ መረጃው ከወጣም ለሂደቱ እንቅፋት ይሆናል በሚል ተነግሯቸው እንደነበር ገልጸውልናል።

ለአባወራ አርሶ አደር ባለ ሶስት መኝታ ቤት ኮንደሚኒየም የሚሰጥ ሲሆን 18 አመት ለሞላቸው ለእያንዳንዱ ልጆቻቸው ደግሞ በእጣ ባለ አንድም ባለ ሁለት ክፍል ኮንደሚኒየም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ቀሪ 106 ቤቶችም ለተጠባባቂ ሰዎች መያዙንም ሰምተናል።

ለአርሶአደር የልማት ተነሺዎች ከሚተላለፉት የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥም በካራ ቆሬ በረከት ሳይት ከተገነቡት ውስጥ 3,500 ቤቶች እንዲሁም ኮዬ ፈጬ የተገነቡት ይገኙበታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ልናናግራቸው የሞከርን ሀላፊዎች ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተወሰኑት ደግሞ ጉዳዩን እንደማያውቁትም ነው የገለጹልን።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ባለፈው አመት የካቲት ወር መጨረሻ የ40 /60 እና የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣት ስነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር መንግስት በአዲስ አበባ በልማት ምክንያት ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው የጋራ መኖርያ ቤት እንደሚሰጣቸው መግለጻቸው ይታወሳል።

የእጣ እድለኞች የሆኑ ቆጣቢዎች በኦሮሞ መብት ተከራካሪ ግለሰቦች አስተባባሪነት በተነሳ የወሰንና የአርሶ አደሮች የካሳ ያንሳቸዋል አመጽ የቆጠቡበትና እድለኛ የሆኑበት ቤት የወሰን ጥያቄ ኮሚቴ ተቋቁሞ ይታያል በመባሉ እስካሁን አልተላለፈላቸውም። ነገር ግን የልማት ተነሽ የተባሉ አርሶ አደሮችንና ልጆቻቸውን የመመዝገብ ስራ በሰፊው ሲሰራ መቆየቱን ከዚህ ቀደም ዋዜማ ራዲዮ መዘገቧም የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት የቤት ተጠቃሚ የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር 22, 915 መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
እነዚህ የልማት ተነሽ እንደሆኑ የተነገረላቸው የቤት ተረካቢዎች ለሚሰጣቸው የጋራ መኖርያ ቤትም ምንም አይነት ክፍያ አይከፍሉም።ሂደቱም ከፍተኛ የህጋዊነትና የፍትሀዊነት ጥያቄን አስነስቷል።

በመጀመርያ አሁን የጋራ መኖርያ ቤት እንዲያገኙ የሚደረጉት የልማት ተነሽ የተባሉት አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ቁጥራቸው ተጋኗል የሚል ነው። የልማት ተነሽ ያልነበሩ ግለሰቦችም በሰፊው ገብተውበታል ; ማንነት ላይ የተመሰረተ ምልመላም ተደርጎበታል የሚል ስሞታ በሰፊው እየቀረበ ነው።

አሁን የጋራ መኖርያ ባለቤት ይሆናሉ ከተባሉት ውስጥ የዛሬ አምስት አመት አካባቢ ከካራ ቆሬ ለልማት ተብለው የተነሱት አርሶ አደሮች ይገኙበታል። በወቅቱ ከዚህ ስፍራ የተነሱ አርሶ አደር ያልሆኑ ቤተሰቦችም ነበሩ። ይሁን እንጂ የቱንም ያክል ይዞታ የነበራቸው ቢሆንም የተሰጣቸው ግን 75 ካሬ ሜትር ልዋጭ መሬት ብቻ ነው። ልዋጭ መሬቱም ለአባ ወራ ብቻ እንጂ ልጆችን አላካተተም። ቤት መስሪያ ተብሎ የተሰጣቸው ብርም በዛ ቢባል ስምንት ሺህ ብር ነበር።

አርሶ አደር ለነበሩት ተነሺዎች ግን እስከ 500 ሺህ ብር በጥሬ ተሰጥቷቸዋል። ምትክ ቦታም ለአባወራ 500 ካሬ ሜትር ለልጆቻቸው ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 250 ካሬ ሜትር ተሰጥቷቸዋል። ከነዚህ ተነሽ አርሷ አደሮች ውስጥ አሁን ላይ በጥሩ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉት አሁንም ያለ ምንም ክፍያ የጋራ መኖርያ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በተመሳሳይ ጊዜ በዚሁ ካራ ቆሬ 73 አርሶ አደር ያልሆኑ አባወራዎች ህገ ወጥ ናችሁ በሚል ያለ ምንም ካሳ ቤታቸው ፈርሶ እስካሁን ችግር ውስጥ ያሉ አሉ። ከዚህ ቀደም ከመሀል አዲስ አበባ ለልማት ተብለው የተነሱ ነዋሪዎች ኮንደሚኒየም ሲሰጣቸው ክፍያ ይጠየቁ እንደነበር ይታወሳል።

እንዲሁም መንግስት ከቆጣቢ ዜጎች የሰበሰበውን ገንዘብ ጨምሮ የሰራውን የጋራ መኖርያ ቤት የ20/80 ባለእድለኛ ለሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳይተላለፍ የተደረገውን እገዳ ለማንሳት ጥረት ባልተደረገበት ሁኔታ 23 ሺህ የሚደርሱ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለማስተላለፍ መወሰኑ የፍትሀዊነት ጥያቄን አስነስቷል። [ዋዜማ ራዲዮ]
Ethoash
Senior Member+
Posts: 22027
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Ethoash » 08 Oct 2019, 13:03

ምነው እበት፤

ብቻህን ማወራት ጀመርክ እኮ ማንም ሳይመልስልህ ሲቀር ፤እኔ ብቻ ነኝ ያንተን ድብርት ሞቅ ሞቅ የማረግልህ ።።።።

ዛሬ ደግሞ ምን አባህ እያልክ ነው ። በትግሬዎች በስሩት ኮንዶሚኒየም እየተጣላቹሁ ነው ውይ።።። መልሴ አንድና አንደ ነው ምን አባህ ታመጣለህ ። ታከለ ጎማ ስትለው ስትንቀው የነበረ ስው አሁን ደግሞ ካንዶሚኒየም ስጠኝ ተለዋለህ። መዳኒት ህን ነው ያረገልህ ምንም አታመጣም ። መቶ እጂን ለኦሮሞዎች ቢስጠው።

እውነተኛ ከሆንክ እስከዛሬ ለአማሮች ይስጥ ስለነበር ከእንግዲህ በኋላ ለያንዳንዱ ጎሳ በኮታ ይደረስው ብትል አንድ ነገር ነበር። ሲንጋፑር ኮንደሚናቸውን በጉሳ ነው የሚያከፋፍሉት አንደን ኮንዶሚኒየም ቻይኒስ ብቻ መያዝ አይችልም ሕንዱም ሌላው ሌላው ዘር በሙሉ ትንሽ ትንሽ ደርሻቸውን ያገኙና አብሮ የመኖርን ዘይቤ አብረው ይለምዱታል ።።።

by the way i did not even read all your document i just read your title .. i have no time to waste on your idiotic ... if u want Amahr to get apartment who stop you why not build it yourself you have two million Amhara alone in USA why not form company and start building instead of building party after party useless people... another question for u .. what will happened once all the house that Golden built finished what would happened would u build ? or public housing will stop pls tell us...

it is not a good policy to have good term with mayor of the city so when he build new public housing he will be fair to u.. now u dare him u will favor his own tribe what the FK are u going to do nothing beside running your mouth..

Maxi
Member+
Posts: 5016
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Maxi » 08 Oct 2019, 13:49

የአዲስ አበባ ህዝብ ተደራጅተህ የኦነግን ወረራ መክት!

የአብይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳና ታከለ ኡማ የኦነግ አሸባሪና የዱርዬ መንግስት አዲስ አበባ ላይ የኦሮሞ ቁጥር እንዲበዛ፣ አዲስ አበባን የኦሮሞ ለማድረግ፣ ቀጣዩን ምርጫ ከቻለ ለማሸነፍ ካልቻለም አንዳች አይነት ተፅዕኖ ለማሳረፍ በሚል በግልፅና በህቡዕ ዘርፈ ብዙ አሻጥሮችን እየፈፀመ መሆኑ እሙን ነው። ከዚህ ውስጥ አንዱ፣ በአዲስ አበባ ህዝብ የወር ቁጠባ የተሰሩ 23 ሽህ ኮንዶሚኒየሞችን ለኦሮሞ ፅንፈኛ ቄሮዎች ማደል ነው። በዚህም የልማት ተነሽዎች ተብዬዎቹ ማሳበቢያዎች በካሳ መልክ 500 ካሬ ሜትር ቦታና ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደተሰጣቸው እየታወቀ በነሱ ሰበብ ፀረ ኢትዮጵያ አሸባሪ ኦነጎችን ከየትም እያመጣ ለማስፈር አዲስ አበቤው በኑሮ ውድነቱ አልበላም አልጠጣም ብሎ ቆጥቦ የሰራውን የምስኪን ህዝብ ቤት ለቄሮ በነፃ ለማደል ለዛሬ ቀጠሮ መያዙ በማህበራዊ ሚዲያው ሲጋለጥበት በመደንገጡ ዕጣው የሚወጣበትን ጊዜ በማራዘም ለተወሰነ ጊዜ ህዝቡን አዘናግተቶ በድብቅ ኦነጋዊ ዘረኛና የእብሪት አሻጥሩን ለመፈፀም እንዲያመቸው ከታች ያለውን አይነት ማስታወቂያዎችን በአንዳንድ ወረዳዎች ለጥፏል። የአዲስ አበባ ህዝብ በቶሎ ተደራጅተህ የኦዴፓ ኦነጎችን ወረራ መመከት ግድ ይላል!!!
Ethoash
Senior Member+
Posts: 22027
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Ethoash » 08 Oct 2019, 14:45

Maxi wrote:
08 Oct 2019, 13:49
የአዲስ አበባ ህዝብ ተደራጅተህ የኦነግን ወረራ መክት!

!

አዲስ አባባ አስር ኪሎ ሜትር እስኴር ናት ። የት ቦታ ነው መኖሪያ ቤቱ የሚስራው ። ኦሮሞ መሬት ላይ ነው ታድያ ፀባይ መግዛት አያዋጣም ውይ

selu
Member
Posts: 17
Joined: 06 Oct 2019, 09:49

Re: ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by selu » 08 Oct 2019, 15:32

Revelations wrote:
07 Oct 2019, 00:05
Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 21355
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Revelations » 09 Oct 2019, 12:58

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 21355
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [DW UPDATE] ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ [ዋዜማ ሬዲዮ]

Post by Revelations » 09 Oct 2019, 14:27

Please wait, video is loading...

Post Reply