Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያ አጀንዳ እና የጎሳ መንጋ ቀውስ !! አዲስ ካልቸር ለምን ?

Post by Horus » 05 Oct 2019, 23:37

ባህል ወይም ካልቸር ያንድ ማህበረሰብ ያኗኗር መንገድ፣ ዘይቤ፣ ዘዴ ወይም ክህሎት ማለት ነው። ያንድ ሕዝብ ማህበራዊ የወል ባህሪው በባህሉ ይገለጻል። ባሁን ሰአት ባህል የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖዋል ። ማለትም ጎሳዎች የጎሳ አገዛዝ ፖለቲካዊ ባህላቸው ከሃይማኖት፣ ከእምነት፣ ከቋንቋ እና ከሌሎች ብዙ ማሃበራዊ ባህርያት ጋር በዘፈቀደ በማያያዝ ይህ ነው የማይባል የስተሳሰብ፣ የሳይኮሎጂ ጭንቀትና ቀውስ ውስጥ ገብተዋል ።

ኢትዮጵያዊያን የጋራ እሴትና ባህል ይፈጥራሉ እንጂ ያንድ ጎሳ ባህል በቀሩት ላይ ለመጫን ከቶም አይችሉም፣ ማንም አይቀበላቸውም። ስለዚህ ምሁር ነው ባይ የጎሳ ልሂቃን በግድ በኢትዮጵያ የወል እሴትና ባህል ላይ ግልጽ ግንዛቤ መያዝ አለባቸው ፣ ጎሳቸውን በትክክል ሊመሩ ከፈለጉ ።

በእኔ ግምት ጠንካራ የኢትዮጵያ ካልቸር በዚህ 4 ጽኑ መሰረተ እሴቶች ላይ የቆመ ነው። እነሱም (1) የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣(2) የሰው ልጅ ልዕልና፣ (3) የስራ ክቡርነት እና (4) የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ናቸው። ይህ ካልቸር እያቆጠቆጠ ይመስላል ። የተለያዩ ምሁራን የሚያደርጉትን ውይይት፣ ልዩ ልዩ የሲቪል ማህበራት የሚሰሩትን፣ ኢትዮጵያዊው ሚዲያ፣ የዜጋ ፓርቲዎችና አቢይ አህመድ የሚሰጡዋቸው ትምህርቶችን ማስተዋል ነው።

ለምሳሌ እሴት ቁጥር አንድን እንውሰድ፤ ኢትዮጵጵያዊያን የኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣ እስልምና ሃይማኖትና ሌሎች ጥቂት ሃይማኖት ያልሆኑ እምነቶች በደቡብ አሉ ። እነዚህን ልዩ ልዩ አማኝ ሕዝቦች አንድ የሚያደርጋቸው ሁሉም በአንድ ፈጣሪ ማመናቸው ነው። ስለዚህ ነው በአንድ ፈጣሪ ገናናነት ማመን የሁሉም ሕዝብ መሰረታዊ እሴት ነው ያልኩት ። የሰው ልጅ ልዕልናም፣ የስራ ክቡርነትም፣ የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነትም እንዲሁ።

ኢትዮጵያዊያን የምር በነዚህ 4 መሰረቶች ማለትም በአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ በሰው ልጅ ልዕልና፣ በስራ ክቡርነት እና በኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ካመኑ ባጭር ግዜ ታላቁን የኢትዮጵያ ካልቸር መገንባት ይቻላል።

የዚህ ባለ አራት ምሰሶ ካልቸር ፋይዳ ምንድን ነው?

የዚህ ካልቸር ተግባል ወይም ተለኮ የኢትዮጵያን አጀንዳ ከስኬት ማድረስ ነው ። የኢትዮጵያን አጀንዳ ምንድን ነው?

አንድ፣ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን ማረጋገጥ፤
ሁለት ፣ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ፤
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ፤
አራት፣ በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት ናቸው ።

ይህ ነው የዚህ ዘመን ትወልድ ታሪካዊ ተልእኮና ያለበት ሃላፊነት። ኬር !!
Last edited by Horus on 06 Oct 2019, 21:41, edited 1 time in total.

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 45809
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: ለጎሳ ልሂቃን የቀረበ ሃሳብ ፤ የኢትዮጵያ አጀንዳ በጎሳ አጀንዳ መተካት አይቻልም

Post by Halafi Mengedi » 05 Oct 2019, 23:46

Your Menelik Ethiopia is buried in 1991, goodbye primitive savages.

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ለጎሳ ልሂቃን የቀረበ ሃሳብ ፤ የኢትዮጵያ አጀንዳ በጎሳ አጀንዳ መተካት አይቻልም

Post by Horus » 06 Oct 2019, 00:01

Halafi Mengedi wrote:
05 Oct 2019, 23:46
Your Menelik Ethiopia is buried in 1991, goodbye primitive savages.
ታዲያ ኢትዮጵያ ሞታ ከሆነ በጣም መደሰት ሊገባህ ለም ይህን ያህል ትበሳጫለህ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ለጎሳ ልሂቃን የቀረበ ሃሳብ ፤ የኢትዮጵያ አጀንዳ በጎሳ አጀንዳ መተካት አይቻልም

Post by Horus » 06 Oct 2019, 21:37

የግለሰብ ልዕልና እጅግ መሰረታዊ እሴትና መርህ የሚሆነው ለምድን ነው? ግለሰብ ማለት የህብረተሰብ መጀመሪያ፣ መጸነሻ ዘር ስለሆነ ነው። ያለ ዘር እህል የለም ። ያለ ስር ዛፍ የለም ። ያለ አንድ ቁጥር ሂሳም የለም ። ያለ ማእከል ክብ ነገር የለም። ስለዚህ ግለሰብ የማህበረሰብ መጀመሪያ ጽንስ፣ መነሻ ማእከል ነው።

ያለ ግለሰብ፣ ባልና ሚስት፣ ቤተሰብ፣ ጎሳ፣ ብሄር፣ ሕዝብ ወይም አገር የሚባል ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም። ግለሰብ የነዚህ ሁሉ ሰርና ግንድ ሲሆን የቀሩት መድብሎች ማህበር፣ ጎሳ ሕዝብ ከዚያ ሰር በቅለው ከግንዱ ግለሰብ የተፈለቀቁ ቅርንጫፎች ናቸው።

ሰለሆነም ያንድ ጋብቻ፣ ቤተሰብ፣ ቡድን፣ ጎሳ፣ ብሄር ወይም አገር የመጀመሪያ አላማ፣ ዋነኛ ትልዕኮ የግለሰቡን ደህንነት፣ እድገት፣ ደስታ፣ ብልጽኛ እና ማበብ እውን ማድረግ ነው። ይህን አላማ ያላደረገ ማህበረስብ ሆነ ድርጅት አላማው ምን እንደ ሆነ የማያውቅ፣ ያልነቃ፣ ደንቆሮ ስብስብ ወይም መንጋ ነው ።

ግለሰብ የማያብብበት ጋብቻ የእንስሶች ነው። ግለሰቡ የማያብብበት ቤተሰብ የድህነት፣ የስቃይ፣ የመከራ ስብስብ ነው። ግለሰብ የማያብብበት ጎሳ የጥቂት አለቆች ተገዥ የሆኑ እስንሰሳት መንጋ ነው። አገርም እንዱ ባንድ አምባገነን የሚነዳ የሚሊዮኖች መንጋ ነው።

የሰው ልጅ በሃሳቡ የሚወልዳቸው ጽንሶች ሁሉ፣ በእጁ የሚሰራቸው ቁሶች ሁሉ፣ በህብረት የሚያቆማቸው ድርጅትና ተቋማት ሁሉ ያላቸው ተልዕኮ ሆነ ግብ ግለሰቡ በሁሉም ሕይወቱ እንዲያብብ መርዳት ነው።

በዚህ መልክ የግለሰብ ማበብ አንደኛ አላማ ያላረጉ ቤተሰቦች፣ ቡድኖች፣ ጎሳዎች፣ አገሮች ከሰው በታች ሆነው እንደ እንሰሳ በድንቁርና፣ በድህነት፣ በበሽታ፣ በአመጽ፣ በጦርነት፣ በሁከት፣ በቀውስ ለዘለለም ከትወልድ ወደ ትውልድ ያልፋሉ ።

ኢትዮጵያ በሰው ቁጥር የአሜሪካ 1/3 ነች፣ ግን የበሰበሰ ስንዴ ካሜሪካ ለምና ግለሰቧን የምትመግብ አላማ አልባ የጎሳ እንሰሶች የሚነዷት አገር ናት ። ይህ ሁሉ ነጋ ጠባ እንደ ሰረንገቲ የእንሰሶች ፓርክ የምናየው የመንጋ ሰልፍ እና ሆሆታ ምን ያህል ድምጹ ቢጎላ ከስር ያለው የቆረቆዘ፣ ያልተማረ፣ የማያሳብ፣ የማይፈጥር፣ ያላበበ፣ ያልበልጽገ የጫጨ ግለሰብ ነው።

ግለሰቡ ልኡል ሳይሆን ሺ ክልል፣ ሺ ጎሳ ቢጮህ ቢያጓራ ከእንሰሳ ባህሪ የተለየ ሊሆን አይችልም።
Last edited by Horus on 06 Oct 2019, 23:28, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳ እና የጎሳ መንጋ ቀውስ !! አዲስ ካልቸር ለምን ?

Post by Horus » 06 Oct 2019, 23:42

ያበሎ
እኔ ደግሜ ደግሜ ልንገርህ፣ በአለም ላይ ብዙ አላማ ይዘው ስልጣኔ ለመስራት የሚተጉና ሞዴል የሚሆኑ ህዝቦች አሉ ። ከነሱ ትምህርት መወሰድ ትችላልህ ። ኢትዮጵያ ውስጥ ባንድ እምነት ቆመው፣ ግለሰቡን ለማሳደግ፣ ስራን እንደ ትልቅ ክቡር ነገር ይዘው፣ ሌላው ኢትዮጵያን እንደ ወንድማቸው የሚወዱ ሕዝብ ካሉ ቁጥር አንድ ጉራጌ ነው። ይህን አለ መሽኮርመም እነግርሃለሁ ። አሁን አንተ ደሞ ትንሽ አንገትህን ዝቅ አድርገህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንደ ጉራጌ ቢሆን አገሪቱ ምን ትመስል ነበር ብለህ ጥይቅ? መኩራራቱን ለግዜው ያዝ አርገውና! እናም እኔ አንድ ሳህንሳዊ ነገር ባልኩ ቁጥር ጉራጌ ጉራጌ የምትል ከሆነ መልሴ ይህ ነው።

በመንጋ ፍልስፍና የትም አትደርስም ። ኋላ ቀርነትን እንደ ባህል ባደባባይ ቢሰበክ ስልጣኔ አይሆንም !! ነጋቲ !!

TGAA
Member+
Posts: 5626
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳ እና የጎሳ መንጋ ቀውስ !! አዲስ ካልቸር ለምን ?

Post by TGAA » 07 Oct 2019, 00:00

As it has been recorded in history the most distractive people are those who have develope self loath. Yabllo is a self-loathing negga , who work to destroy his own community. Not out of love but complete disdain for his community existence, so he is cheerleading them in mission impossible suicide mission. this degenerate mind is summarized by his own perverted statement.
"As indicated before, Ethiopians, Africans, Haitians, blacks in general (even those in countries run by whites such as the USA, Brazil, UK) keep failing mainly because they are?? ... BLACKS/NEGRO! .. Failure is in blacks' DNA. " This supposed to be the person who is standing to protect the interest of the Great Oromo People?


Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ለጎሳ ልሂቃን የቀረበ ሃሳብ ፤ የኢትዮጵያ አጀንዳ በጎሳ አጀንዳ መተካት አይቻልም

Post by Ethoash » 07 Oct 2019, 13:08

Horus wrote:
06 Oct 2019, 00:01
Halafi Mengedi wrote:
05 Oct 2019, 23:46
Your Menelik Ethiopia is buried in 1991, goodbye primitive savages.
ታዲያ ኢትዮጵያ ሞታ ከሆነ በጣም መደሰት ሊገባህ ለም ይህን ያህል ትበሳጫለህ?
HOROROR,

What "Halafi Mengedi" telling is there is two kind of Ethiopia one is Amhara Ethiopia the other one is fed. ethnic state of Ethiopia .. so what "Halafi Mengedi" saying is your old Amhara first Ethiopia is dead.. but he look like worried u might be right that the old Amhara first will be rises from dead for this u will stand guard to make sure u will bury u with the old Ethiopia if need be but he will not allowed u to entertain the old Ethiopia .. Meles greatest mistake is for keeping the name Ethiopia

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ለጎሳ ልሂቃን የቀረበ ሃሳብ ፤ የኢትዮጵያ አጀንዳ በጎሳ አጀንዳ መተካት አይቻልም

Post by simbe11 » 07 Oct 2019, 13:13

You are right. Ethiopia is dead and your next stop is killing Tigray.
Let me tell you this!!
The only thing dead is your dream of killing Ethiopia.
Your nightmare, Ethiopian-ship will flourish while you dream is dead and buried at Dedebit.

Halafi Mengedi wrote:
05 Oct 2019, 23:46
Your Menelik Ethiopia is buried in 1991, goodbye primitive savages.

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ለጎሳ ልሂቃን የቀረበ ሃሳብ ፤ የኢትዮጵያ አጀንዳ በጎሳ አጀንዳ መተካት አይቻልም

Post by Ethoash » 07 Oct 2019, 13:22

simbe11 wrote:
07 Oct 2019, 13:13
You are right. Ethiopia is dead and your next stop is killing Tigray.
Let me tell you this!!
The only thing dead is your dream of killing Ethiopia.
Your nightmare, Ethiopian-ship will flourish while you dream is dead and buried at Dedebit.
ምነው ነገርኩህ እኮ ኢትዬዽያ ደህና ናት አለች ትተነፍሳለች። የሞተችው እኮ የነፍጠኞች ኢትዬዽያ ናት። ስም ሞሽኬ ስለሆነበህ ነው የተምታታብህ እንጂ ይህችኛዋ ኢትዬዽያ እናንተ የምታቆች ኢትይዽያ አይደለችም ። ይህቺኛው ፈደራል የብሔርና የብሔረተስብች ሐገር ናት ። በፍፁም ከአንተ ነፍጠኛ ኢትዬዽያ ተለያለች ።

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳ እና የጎሳ መንጋ ቀውስ !! አዲስ ካልቸር ለምን ?

Post by Horus » 08 Oct 2019, 01:05

ስራ ክቡር ሆኖ ከፍ ከፍ ተደርጎ መከበር ያለበት ለምንድን ነው?

እኔ ብዙ ቃላት በመሸመን ሰው ማሰልቸት አልወድም ። ለራሴ ብዙ ሺ ኮፒ ማስታወሻዎች በሁሉም ነገር ላይ አለኝ ። ያለ ማስታወሻ አላነብም። ይህን የምለው ስለ ስራ ስነ ምግባር ወይም ንድፈ ተግባር ሙሉ መጻፍ መድረስ ይቻላል።

ከላይ እንዳልኩት ስለ ኢትዮጵያ ካልቸር እሴት መሰረት ሲነሳ አንደኛ ስለ አንድ ፈጣሪ ተስማማን።

ከፈጣሪ ቀጥሎ ያለው ሰው፣ የሰው ልጅ ነው። ያ ደሞ ልኡል እንደ ሆነ ተስማማን።

በሰው አለም ውስጥ ማለትም በፊዚካል አለም ሳይሆን በሰባዊ (ሂዩማን) አለም ውስጥ ያሉት ሁለት ነገሮች ናቸው። አንዱ ሰው ነው። ሌላው የሰው ስራ ወይም ባህሪ ነው ። በቃ !! ይህን ሳያውቁ እድሜያቸውን ሙሉ የተማሩ ያሳዝኑኛል። በሰው ልጅ ማሀበር ውስጥ ሌላ ነገር የለም ፤ ከሰውና ከስራው፣ ከስብእናና ከሰባዊ ባህሪ (ሁማን ቢሄቪየር) ውጭ!

የቀረው ሁሉ የዚያ ቅርንጫፍ ነው ። ባህል፣ ካልቸር ፣ ስልጣኔ ወዘተ ወዘተ ሁሉ በሰው ልጅ እና በስራው የተፈጠሩ ናቸው።

ማለትም ስራ በዚህ ሁሉ የአለም እጹብ ድንቅ ውስጥ ቁጥር 3 ሃያል፣ ቅዱስ፣ የፍጥረት ምስጢር ነው። የስራን ሃያል ምስጢር የስራን ክቡርነት ያላወቁ ገና ከእንሰሳ አለም ወይም አይምሮ ካላበለይሰገው የቋሳዊ አለም ያልተለዩ ናቸው።

ስለዚህ ከሰው ልጅ ክቡርነት ቀጥሎ ያለው ዘላለማቂ ታላቅ ነገር፣ ታላቅ ክስተት፣ ታላቅ እውነት ስራ ነው።

ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ካልቸር 3ኛው ወጋግራ በስራ ክቡርነት ማመን ነው ያልኩት ። ሌሎች ጨምሩበት !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳ እና የጎሳ መንጋ ቀውስ !! አዲስ ካልቸር ለምን ?

Post by Horus » 08 Oct 2019, 02:30

4ተኛው የኢትዮጵያ ካልቸር መቆሚያ ምሰሶ የሕዝቧ ወንድማማችነት ነው ። እስቲ ይህ ምን ማለት እንደህነ የናንተን ሃሳብ እስማ? ለምንድን ነው ። በምን ምክንያት ነው ኢትዮዖያዊያን እንድማማች ምንባለው?

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳ እና የጎሳ መንጋ ቀውስ !! አዲስ ካልቸር ለምን ?

Post by Horus » 24 Oct 2019, 01:11

I have said this zillions of times. Tribal drama in any form and shape will never see the light of a day. Give it up Jawar, Ethiopia is too big and too complex for cow slaughtering zero !!!

Post Reply