Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Awash
Senior Member+
Posts: 28957
Joined: 07 Aug 2010, 00:35

Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

Post by Awash » 26 Sep 2019, 06:13

Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

 admin September 26, 2019

Eritrean bishops protested the government’s seizure of Catholic schools and asked that the Church be enabled to continue its educational and health services.

“If this is not hatred against the faith and against religion, what else can it be?” the bishops said in a letter to Eritrea’s minister of public education...
https://www.irishcatholic.com/eritrean- ... -closures/

tekeba
Member
Posts: 666
Joined: 17 Dec 2013, 03:03

Re: Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

Post by tekeba » 26 Sep 2019, 07:38

Dummy ugum jeberti, who cares. The pseudo bishops should go to jail. Do you get it, MORON

Meleket
Member
Posts: 659
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

Post by Meleket » 26 Sep 2019, 08:37

tekeba wrote:
26 Sep 2019, 07:38
..., who cares. The pseudo bishops should go to jail. ...
ወንድማችን አቶ tekeba ምነው፡ ምን ነካህ? ምንስ ሆነሃል! ነውርም እማደል? እንዲህ ይባላል እንዴ? ሰውንስ ደህና የለመድከው ነው የምትመስል፡ እግዝአብሄር ይታዘበኛል አትልም! አሁን አንተም እንዲህ እያሰብክ ኤርትራዊ ነኝ ልትለን ነውን? ወንድማችን በል እንግዲህ ባንተው ‘ቅባት’፡ ለኤርትራዋ የካቶሊክ ቤተክርስትያን፡ እነዚህ ለወንጌል ለኅሊናቸውና ለሐቅ ያደሩ ጳጳሳትን ሽረህ፡ እንዳተ ሃሳብ ላንተ እንዳሻህ የሚያጎበድዱና እንዳሻህ አድርገህ የምታሽከረክራቸውን ጳጳሳት ሹምልን እንጂ! ኣይዞህ ይቻላል ቻይናም እንዲያ አድርጋ ይሆናል! :mrgreen: . . ወንድም፦. ይልቅስ በጨዋና በሰለጠነ መንገድና መንፈስ ለዚህ ጥያቄያቸው ምላሽ ፈልግ፤ ሐቅና ዓለም ዓይናቸውን አፍጥጠው እየታዘቡህ መሆናቸውንም አትዘንጋ። እግዚሔሩም እንዲሁ!
Meleket wrote:
25 Sep 2019, 09:44
ስልጡን በሆነ መንገድ ኤርትራዉያን የካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳሶች ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያሰራጩት ግልጽ መልእክትን፣ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን በተለይም ወጣቱ ስልጡን ጠቅላዪ ሚኒስትራቸው ዶ/ር ኣብዪ ኣሕመድ ይማሩበት እንዲሁም የኤርትራዉያን ካቶሊክ ጳጳሳትን ስልጡን አካሄድ ይገነዘቡበት ዘንድ እናጋራቸዋለን። የኤርትራ ትምህርት ሚንስተር ለዚህ ስልጡንና አግባብነት ላለው ግልጽ ጥያቄና ስሞታ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ አንዳችም ምላሽ አለመስጠቱ ይታወቃል። የኤርትራ መንግሥት “ናትና ኣይንህብን ዘይናትና ኣይንደልን” ማለትም “የራሳችንን አንሰጥም የሰውንም አንሻም” በሚል መፈክሩ የታወቀ ቢሆንም ቅሉ፣ ያለ አንዳች ውይይት እየወረሳቸው ያሉትን እነዚህን ዓመታት ያስቆጠሩ የትምህርትና የጤና ተቋሞች ገንብታና አንጻ ለአገልግሎት ያበቃቻቸው የባለቤትነትም ህጋዊ መብትና ህጋዊ ማረጋገጫን የያዘችው የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን መሆኗ ይታወቃልፍትሐዊዉንና ስልጡኑን የኤርትራ ካቶሊካዉያን ጳጳሳት አካሄድ ለማጤን ይቻል ዘንድ የጳጳሳቱ መልእክት ሙሉ ይዘትን በአፍሪካ ቀንድ ቋንቋዎች በአንዱና በዋንኛዉ እንደሚከተለው ለኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን ስናጋራቸው በዚህ ግሩም ድረ-ገጽ ታሪኩን ለመጪዉ ትውልድ እየከተብን እንዲሁም “የሰው ገንዘብ አትመኝ” የሚለውንም ትእዛዝ ማክበር እንደሚገባ ለመንግስታትም ጭምር በማሳሰብ ነው። መልካም ንባብ!

ሃገረ ኤርትራ - ለ አቶ ሰመረ ርእሶም - ትምህርት ሚንስተር - ኣሥመራ።
ኣሥመራ 04.09.2019 (፳፱ ነሐሴ ፳፻፲፩ ዓ. ም. )

ጕዳዩ፦ በመንግሥት ስለተወሰዱት (የተወረሱ) የቤተክርስትያን ትምህርት ቤቶች

1. እኛ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጳጳሶች፣ ሃገራችንን ሆነ የሃገራችን ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንን በሚመለከት ጉዳይ፣ ከመንግሥት አካላት ጋር ተገናኝተን ለመነጋገርና ለመወያየት ሁሌም ፍላጎታችንና መሻታችን ነው። ይህ ፍላጎታችን ግን በመንግሥት በኩል ምንም ዓይነት ትኵረት አልተሰጠውም። ስለሆነም አሁንም፣ ተቃውሟችንን ለሚመለከተው የመንግሥት አካል አቅርበናል። ተቃውሟችንም ቤተክርስትያን ተልእኾዋን የምትፈጽምበት የህክምናና የትምህርት ተቋማት ክንፎቿን፣ ከቅርብ ግዜ ጀምሮ መንግሥት በማን አለብኝነት ለመውሰድ የሚያደርገውን እርምጃ በተመለከተ ነው።

2. በአሥመራ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የመድኃኔ ዓለም 2ይ ደረጃ የዘርአክህነት ትምህርት ቤት በመንግሥት ትእዛዝ መሰረት ከተዘጋ ሁለት አመቱ ተቃርቧል፣ ይህ ትምህርት ቤት ከ1860 እ.ኤ.አ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች እየተተከለ፣ ከ100 ዓመት በላይ ያስቆጠረ፣ ይህም ማለት በኤርትራ ውስጥ ዘመናዊ ትምህርትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጋራ ወይም በጥምረት በመመገብ፣ ቤተክርስትያንና ሃገርን የሚያገለግሉ ወጣቶችን የመለመለ ትምህርት ቤት ነው፣ ይህን የመሰለ ግልጽና ልዑል አበርክቶ ያለውን ተቋም መዝጋት፣ በዚች የትምህርት ጥማት ባለባት ሃገራችን ይህን ውሳኔ ማሳለፍ፣ ለታዛቢም ሆነ፣ ለጠያቂ ምንም ዓይነት ምላሽ የማይገኝለት እጅግ የሚገርም ይህ ነው ሊባል የማይችል ተግባር ነው።

3. በመቀጠልም ስምንት የሚሆኑ በካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሚተዳደሩ የጤና ተቋማትን፣ በምንም ዓይነት መለኪያ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን፣ “ተደራቢዎች” በሚል አጉል ፈሊጥ የህክምና ተግባራቸውን እንዲያቋርጡ ተደርጓል። ባለፉት ወራትም፣ 21 የሚሆኑ ትንንሽና ትልልቅ ክሊኒኮችና የጤና ተቋማት በሃይል ተወርሰዋል፣ ንብረታቸውም ተወስዷል። አሁን ደግሞ ትላንት በ03.09.2019 እ.ኤ.አ. የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማለትም ሦስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ከነዚህም አንዷ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝባት ትምህርት ቤቶች፦
1) የቅዱስ ዮሴፍ [ላ-ሳል] ከረን አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
2) የካፑቺኒ ወንድሞች ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንደፈራ
3) የቅዱስ ፍራንቸስኮስ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በምጽዋ
እንዲዘጉ ወይም በመንግሥት እንዲወሰዱ (እንዲወረሱ) ተደርጓል። ይህን በተመለከተም ተገቢውንና ቀጥተኛውን ተቃውሟችንን እናቀርባለን።

4. በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተገለጸው፣ ቤተክርስትያን የተለያየ ሓሳቦቿን ስታቀርብ የምትጀምረው፣ ማንነቷንና ተልዕኾዋን በመተንተን ነው። ይህም የምትሰብከውንና የምታስተምረውን ዓላማዋ ማንነቷንና ተልዕኮዋን ተከትሎ የሚመጣ ነው። ቤተክርስትያን እናትም መምህርም ነች። መስራቿ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስና ያስተምር እንደነበረው ሁሉ፡ ለቤተክርስትያንም እንድትፈውስና እንድታስተምር ሥልጣንን ሰጥቷታል። ዋንኛ ስራዋ አምላካዊዉንና ዘላለማዊዉን ሓቅ ማስተማርና መስበክ ቢሆንም እንኳ፡ የሰው ልጅን በነፍስና በሥጋ የመርዳት ሃላፊነትም አለባት። ይህን ሃላፊነቷንም በተግባር የምትፈጽመው፡ በቤተክርስትያን አጥር ግቢ ውስጥ ብቻ ታጥራ ሳይሆን፣ በትምህርት ቤቶቿና የሕክምና ተቋሞቿ እንዲሁም ባጠቃላይ ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት በምትሰራባቸው ማእከላቶቿ አማካኝነት ነው።

5. አጠቃላይ የሁለት ሺ ዓመት ታሪኳና ጉዞዋ በግልጽ እንደሚያሳየው፣ ይህ ተግባሯ ከባህሪዋና ከተልእኾዋ አኳያ የሚመነጭ መብትና ግዴታ እንዳላት ጠንቅቃ ትረዳለች። ክርስትያናዊ የእምነት ትምህርትን ስታስተምር፡ ሰብአዊ እውቀትንና እድገትን የምታስተምርበትና የምታካሂድበት ትምህርት ቤት፣ ከዚህ ጋር የሚያያዝ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረትን የማፍራትና የማካሄድ መብት አላት። ይህ መብትም በአምላክ የሚሰጥ ባህርያዊ መብት ስለሆነ፣ በማንኛውም አካል በጎ ፍቃድ ወይ ፍላጎት የሚቸር ወይ የሚሰጥ ወይም የሚከለከል አይደለም። ይህ የጸና እውነታም፣ በምንም መልኩ የማይደፈር መብት ስለመሆኑ አያጠያይቅም።

6. ከጥንት ከጥዋቱ በመላው ዓለም እያዘወተረችው ያለው፣ ማንኛውንም ሰብአዊና መንፈሳዊ ዕውቀትን የሚያሳድግና የሚያበለጽግ፣ ከሙዓለ-ሕፃናት እስከ የዩኒቨርስቲ ደረጃ ድረስ የሚያስተምሩ የተለያዩ ተቋማትን መመስረትና ማካሄድ መብቷና ግዴታዋ ነው። ለምን ቢባል መምህር ናትና ነው። እነኝህ በቤተክርስትያን የሚካሄዱ ተቋማት ዓላማቸው ምንድን ነው? ከተባለ፦

ሀ) የሰው ልጆችን ኅሊና በመኮትኮትና በመመልመል ፣ በኅብረተሰብና በሀገር ውስጥ በብቃትና በተገቢ ሁኔታ አስፈላጊውን ገንቢ ሚና የሚያበረክቱ ብቁ ዜጎች ይሆኑ ዘንድ፣ ስለ ፍትሕ ሰላም መብትና ነጻነት ሓቀኝነትና ወንድማማችነት . . . የሚማሩበት ነው፣

ለ) ወላጆች ለልጆቻቸው ብቁ የሆነ ትምህርትን የመምረጥ ያላቸውን ማንም ሊገፍፋቸውና ሊቀማቸው የማይችልን ባህርያዊና ተፈጥሯዊ መብት ይከበርላቸው ዘንድ፣ ትውልድን በማነጽና የበሰለ ዜጋን በማፍራት ረገድ የበኩሏን አስተዋጻኦ ለማድረግ፣

ሐ) ዜጎች በሥልጣኔና በዕውቀት እንዲያድጉ ለማገዝ፣ በበለጠውና የዘመናት ልምድ ማካበቱ በተመሰከረለት የቤተክርስትያን ሃብታም ልምድና ተሞክሮ እንዲጠቀሙ ለማድረግና ለማስቻል፣

መ) ቅኑና ብቁ የሆነ ለሰው ልጆች እድገት ከመትጋት ውጭ፣ እኒህ የቤተክርስትያን የትምህርት ተቋሞች፣ ሌላ ከዚህ ውጭ የሆነ ድብቅ አላማ ሆነ አካሄድ እንዳልነበራቸው እንደሌላቸውም፣ በትምህርት ተቋማቱ ውስጥ ተምረው፣ ብርቅና ድንቅ ይዞታዉን ያጣጣሙ፣ የተለያዩ የእምነትና የሃይማኖት እንዲሁም የህይወት ዘይቤዎችን የሚከተሉ፣ በሃገር ውስጥና በሃገር ውጭ በተለያዩ ሃገራት ተዘርግተው የሚገኙት ዜጎች ህያው ምስክሮች ናቸው።

የእምነት ማእከላትና የትምህርት እድገት በታሪኽ አዃያ


7. የትምህርት ታሪኽንና አመጣጡን እንዲሁም አስተዳደጉን በመላው ዓለም ስናጤንና ስናጠና፣ አንድ በፍጹም ልንክደው የማንችል ሓቅ ቁልጭ ብሎ ይታያል። ከጥንት ከጥዋቱ የትምህርትና የሥነጽሑፍ መኮትኮቻና ማሳደጊያ ቦታዎች የሃይማኖት ተቋሞች ሲሆኑ፣ በተለይም ቤተክርስትያንና መስጊዶች ለትምህርት እድገት የነበራቸው አስተዋጽኦና ገንቢ ሚና በቀላል የሚገመት ብቻ ሳይሆን እጅግ አስደናቂና አንጸባራቂ ምዕራፍን የያዘ ነው።

የሃገራችንን ታሪክ ወደኋላ ተመልሰን ስንመለከትም፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጥንታዊ ገዳሞችና ደብሮች፣ እንዲሁም ጥንታዊ መስጊዶች፡ ከጽሑፍና ከንባብ አኳያ፡ ጥንታዊ ታሪኽንና ትምህርትን በማቀብ ረገድ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፣ ባጭር አገላለጽ የዚህ ህዝብንና ሃገርን ባህላዊ ሕንጸትንና ለማንነቱና ለምንነቱም መሰረትን ያስቀመጠ ገንቢ ሚና ተጫውተዋል።

8. የኤርትራ ዘመናዊ ትምህርት ውልደትና እድገት በሚገለጽበትና በሚተነተንበት ወቅትም፣ ካቶሊካዊ ትምህርት ቤቶቻችን እንዲሁም ቤተክርስትያናችን ባጠቃላይ በዚህ ረገድ፣ እጅግ ደማቅና አንጸባራቂ ቦታ እንዳላት ማንም ሰው የሚያዉቀው ፍንትዉ ብሎ የሚታይ ሓቅ ነው። በአፍሪካ ምድር ለመጀመርያ ግዜ የኅትመት ጥበብን በማስተዋወቅ፣ በሃገራችን የትምህርትና የጽሕፈትን በር የከፈተችና የትምህርትን ጉዞ ያፋጠነች ቤተክርስትያን ነች።

በዓዲወግሪ [ሳን ጆርጆ]፣ በሠገነይቲ [ስኮላ ኣርተ መስቲየሪ ሳን ሚኬለ]፣ በዓድቐይሕ፣ በከረን[ሳልቫጎ ራጊ]፣ በኣሥመራ [ስኮላ ቪቶሪዮ]
በጣልያን ግዛት ዘመን ለሃገራችን ሰዎች መማርያ የተመሰረቱ ትምህርት ቤቶች ነበሩ፣ እነኝህም በቤተክርስትያን ወይም በቤተክርስትያን ሰዎች የሚተዳደሩና የሚካሄዱ የነበሩ ናቸው። ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላም በዝች በዘመናዊቷ ኤርትራ የተመሰረቱት በተለይም በርእሰ ከተማችን በአሥመራ የተመሰረቱትና የተቋቋሙት የትምህርት ማእከላት ለአብነት ለመጥቀስ፦ ኮምቦኒ ኮሌጅ፣ አሥመራ ዩኒቨርስቲ፣ ኮለጆ ላሳል፣ ኮለጆ ቅድስት ሓናና፣ በቀትር ህጻናትን በምሽት ደግሞ ጎልማሶችን የሚያስተምረው የቅዱስ በርናርዶስ ትምህርት ቤትና . . . ሌሎችም ነበሩ። በተለይም በ 1965ዓ.ም (እ.ኤ.ኣ) ለትምህርት ልዩ ፍቅር በነበራቸው በተወዳጁ ብፁዕ አቡነ ኣብርሃ ፍራንስዋ አነሳሽነት እስከ 70 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ቀየዎች በመላዉ ኤርትራ ተመስርተውና ለረዢም ዓመታት ብዙ ኤርትራዉያን ሕፃናትን በትምህርት ገበታ እንዲሳተፉ አስችለው እንደነበር ማስታወስ ተገቢ።

ከጣሊያን የአገዛዝ ዘመን ጀምሮ፣ ዘመናዊ አስተዳደርንና የአማማር ዘዴንና ዘይቤን፣ ፖለቲካዊ ጉዞንና ስነጽሑፋዊ ፈጠራን እንዲሁም የቋንቋን ዕድገት በተመለከተ ረገድ የተካሄደን የህዝባችን የመጀመርያ ተግባራቶች በብዛት በስኬት የተካሄዱት፣ በቤተክርስትያን ተቋሞች በተማሩ ልጆቻችን ብርታት ነው። ይህም ለዘመናዊቷ ኤርትራ መሰረት ሆኗል። በዝች ሃገራችን የፖለቲካ ሂደት ጅማሬም ሆነ በፖለቲካዊና በነጻነት የትግል ጉዞ ሂደትም፣ በቤተክርስትያን ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተማሩ ሰዎች ሚና የራሱን ትልቅ ምዕራፍ የያዘ ነው።

9. በታሪኽ ይህን የመሰለ ትልቅ ሚናና ምእራፍ ያበረከቱትን የእምነት ተቋሞችና ማእከሎች፣ በተግባር በትምህርቱ ዘርፍ ያስመዘገቡትን ድልና ስኬት መቀማትና መካድ፣ የትምህርቱ ዘርፍን “ኣይመለከታችሁም” ብሎ ማለት ታድያ ከምን ይቆጠራል? ይህን አካሄድ ከእምነትና ከሃይማኖት ጋር መጻረር ከማለት ውጭ ሌላ ምንም ዓይነት መግለጫ ሊገኝለት አይችልም። እምነትንና ፈሪሃ እግዚአብሄርን ከሚያስተምሩ ማእከላት ሕፃናትንና ወጣቶችን ነጥለንስ፣ ለዝች ሃገር ምን ዓይነት አዲስ ትውልድ እንድናፈራላት ነው የታሰበው ማለት ነው?

10. በተለይም የካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ፡ ይህን መሰሉን ውሳኔ ለመወሰን የሚያስገድድ አንዳችም ዓይነት የትምህርት ሥርዓትን የማዛባት፣ ወይም ሕግን የመጣስ፣ ማለትም የትምህርት ጥራትንና ብቃትን እንዲሁም አማማርን ማለትም የመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከተ፣ በትምህርት ቤቶቻችን የተገኘ እክል ወይም ከተገቢው መሥመር የማፈንገጥ አዝማሚያ፣ በመንግሥት በኩል እንደ ማስረጃነት አልተጠቀሰብንም። ሊጠቀስ የሚችል እክል ወይ ጉድለትም በጭራሽ የለንም። ትምህርት ቤቶቻችን ዛሬ ብቻ ሳይሆን ከምስረታቸው ጀምሮ፣ በዕለታዊ አሰራራቸውና እንዲሁም ተማሪዎቻቸው በሃገራዊ ፈተናዎች የሚያስመዘግቡት ድንቅ ውጤት፣ በብቃታቸው ሆነ በዓይነታቸው የተመሰገኑና የተመሰከረላቸው በመሆናቸው፣ ይህን ለመሰለው አሉታዊ የመንግስት ውሳኔ ሳይሆን፣ ሽልማትና ማበረታታት ሊቸራቸው የሚገባ መሆኑን፣ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ማለትም የትምህርት ሚኒስቴር በየግዜው የሚቀርቡለትን ሪፖርትና በአርካይቮቹ ይዟቸው የሚገኙት መዛግብቶቹ ምስክር ናቸው።

11. እንደ የቤተክርስትያናችን ግንዛቤ፡ ትምህርትን በተመለከተ፡ የመንግሥት ግዴታና ኃላፊነት፡ ዜጎች ሁሉ አስፈላጊዉንና ብቁ የሆነን የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን ማረጋገጥ፣ መብትና ግዴታቸውንም መግለጽ፣ ሕፃናት ተገቢዉን ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ፣ የትምህርት ተቋሞች በተገቢው ሁኔታ እያስተማሩ ናቸው ወይስ አይደሉም ብሎ መቆጣጠር፡ በሃገር ደረጃ የሚወጡ መመሪያዎችንና የትምህርት ሥርዓትን እየተከተሉ ናቸው ወይስ አይደሉም ብሎ መቆጣጠር ነው። የሚወጣው የትምህርት መመሪያም የመማርና ማስተማሩን ሂደት የሚያግዝ ይሆን ዘንድ፣ መበረታታት የሚገባዉን አካል ማበረታታት፣ ሊታረም የሚገባዉን አካልም በማረም፣ በግል ይሁን በቤተክርስትያን አማካኝነት የሚካሄድን የመማርና የማስተማር ሂደት ወደ ፊት ይበልጥ ይራመድ ዘንድ ማስቻል ነው።

የቤተክርስትያንና የወላጆች መብት


12. መንግሥት በዓለምአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለዉን የወላጆችንና የቤተክርስትያንን መብት ማወቅና ማክበር ግዴታው ነው። ወላጆች ለልጆቻቸው ያሻቸውን የትምህርት ዓይነትና የአማማር ዘዴን የመምረጥ፣ ቤተክርስትያንም በውስጧ ያሉ ልጆቿን ሆነ ትምህርት ቤቶቿን መርጠው የሚመጡ ማናቸውም ዜጎችን በነጻነት የማስተማር መብቷና ግዴታዋ በአግባቡ ሊታወቅና ሊከበር ይገባል

13. ከዚህ ባሻገር የወላጆችንና የቤተክርስትያንን መብት በሚጻረር መልኩ እርምጃዎችን መውሰድ ተቀባይነት የሌለውና እጅጉኑ ጎጂ አካሄድ ነው። ሕፃናትንና ወጣቶችን ከወላጆቻቸው፣ በሞራልና በሥነምግባር ከምታንጻቸው ቤተክርስትያንና የእምነት ቤታቸው በመነጠል፣ ይህን መሠረታዊና ባህርያዊ መብትንና ግዴታን ችላ በማለት የሚኬደው፣ “ወጣቶችን ለመያዝ” የሚደረግ አካሄድ፤ ሲቪል ኅብረተሰብ ሆነ የእምነት ማእከላት ሕግና ሥርዓትን ተከትለው፣ ለሰው ልጆች ይጠቅማል ብለው ያሰቡበትን አሰራራቸውን እንዳይተገብሩ የሚገታበት አካሄድ ሁሉ ነጻነት የለበትም፤ በዚህ ሁኔታ ዓለም አቐፋዊ የሰው ልጆች መብትም አልተከበረም ማለት ነው። ማንኛውም ስራ በመንግስት አካል ብቻ የሚያዝበት አሰራርና አካሄድ፣ የግልንና የሰብአዊ ነጻነትንና አካሄድን የሚገታ አካሄድ ነው፣ ነጻነትና መብት ባልተከበረበት ደግሞ፣ ሰላም ሆነ መረጋጋት እንዲሁም እድገት ሊመጣና ሊገኝ አይችልም።

እንግዲያዉኑስ በዚህ መርህ መሠረት፣ በየጊዜው ከተቋሞቻችን አንጻር የሚደረገው መብትን የመጋፋት የመርገጥና የመጣስን ውሳኔና ተግባር እኛ እንደግለሰቦች፣ እንደ ኤርትራዉያን ዜጎችና እንደ ካቶሊካዉያን መጠን በጭራሽ አንቀበለዉም፤ ዜጎችና አማንያን እንደመሆናችን መጠን ያለንን መብትና ግዴታም ችላ አንለዉም፣ ይህ እላይ የጠቀስነውን መብታችንን ስንገፈፍ ወይም የጠቀስናቸውን ግዴታዎቻችንን ሳንወጣ ስንቀር፣ በዋነኛነት የሚጎዳው በዚች ሃገራችን ውስጥ ያለው ዜጋ ወይ ኅብረተሰብ ነው፣ ቀጥሎም ሃገር እንደ ሃገርነቷም ትጎዳለች። በተቋቋሙበት ዓላማና በተግባር በተፈተኑበት አሰራራቸው መሰረት፣ ተቋሞቻችንን በሙሉ ለህዝብና ለሃገር ጥቅም መሆኑን ስለምንተማመንባቸው፤ እነዚህ ተቋሞች ሲወረሱና የቤተክርስትያን መብት ሲደፈር በዋነኛነት የሚጎዳው ሕዝብና ሃገር መሆኑን መረዳትና መታወቅ አለበት።

መደምደሚያ

14. በዚህች አገራችን ውስጥ አሁን ያለንበትን ሁኔታና ያለፈውን ታሪኽ በጥልቀት ከመረመርን በኋላ፣ በተለይም በትምህርት ረገድ የቤተክርስትያን ታሪኽ አንጸባራቂ መሆኑን እንጂ አንዲትም ጥቁር ነጥብ ወይም ጉድፍ እንደማይገኝበት አፋችንን ሞልተን መናገር እንችላለን። ስለሆነም በአሁኑ ወቅት፦

ሀ) ከትምህርትና የሕክምና ተቋሞቻችን አንጻር የሚተላለፈው ውሳኔና፣ ውሳኔውን ተከትሎ የሚካሄደው ተግባር፣ በዋነኛነት የቤተክርስትያንን መብትና የእምነት ነጻነት የሚጻረር ተግባር፣ በእምነቷ በማንነቷና በአገልግሎቷ ውስጥ ጣልቃ ገብነትና ህልውናዋን የሚፈታተን መሆኑን እየገለጽን፡ ይህ ተግባር ዳግም ተመርምሮ በአፋጣኝ እንዲቆም እንጠይቃለን፣

ሁ) የቤተክርስትያን ተቋማት የኤርትራ ልጆች ተቋም እንደመሆኑ መጠን፣ መደበኛውንና ድንቁን የትምህርትና የሕክምና አገልግሎቱን በነጻነትና በታታሪነትን ይቀጥል ዘንድ ዕድል እንዲሰጠው እንጠይቃለን፣

ሂ) ሊታረም ወይ ሊወገድ የሚገባው ማንኛውም እንከን ካለም፣ በጋራ ውይይትና የመግባባት መንፈስ እንዲፈታ ማድረግ መልካም ብቻ ሳይሆን ብቸኛው መንገድ መሆኑን እናስገነዝባለን።

15. እንግዲያዉኑስ ቤተክርስትያን ለዘመናት ባካበተችው ልምድ፣ ረዢም ትዉፊትና ዓቅም ኣኳያ፣ ለሰው ልጆች እድገት ወሳኝ ሚና ባለው በትምህርቱ ዘርፍ፣ የመንግስትን መመሪያ በመከተል፡ የተለያዩ ትምህርት ቤቶችን መክፈትና ማካሄድ፣ ከተልእኾዋ አንዱ ክፍል መሆኑን መግለጽ ትወዳለች። ይህን ተልእኮዋን የሚቃወም ማንኛውም ዓይነት ውሳኔ ወይ ሂደት ነጻነቷንና መብቷን እንደገፈፋት ትረዳለች፣ ይህን መብቷን ዳግም እስክትጎናጸፍና ነጻነቷን እስክትጨብጥ ድረስ ከመእምናኖቿ ጋር ሆና ወደ አምላክ ያለማቋረጥ ጸሎቷንና ምህለላዋን ታሳርጋለች፣ በህጋዊ መንገድም ለሚመለከተው አካል መብቷ ይከበር ዘንድ ስሞታዋን እያቀረበች “ጥያቄዋ ይመለስ መብቷም ይከበር ዘንድ አቤቱታዋን ሳታሰልስ ከማቅረብ አትቦዝንም።

አምላክ ሃገራችንን፣ የሰላምና የፍትህ ሃገር የርትዕና የፍቅር ሃገር ያድርግልን።
ካቶሊካውያን ጳጳሶች

1. ኣቡነ መንግሥተኣብ ተስፋማርያም ፣ ሊቀጳጳስ ዘመንበረ ኣሥመራ
2. ኣቡነ ቶማስ ዖስማን፣ ጳጳስ ዘመንበረ ባረንቱ
3. ኣቡነ ኪዳነ የዕብዮ፣ ጳጳስ ዘመንበረ ከረን
4. ኣቡነ ፍቅረማርያም ሓጎስ፣ ጳጳስ ዘመንበረ ሠገነይቲ
ኮፒ ለ፦
1. ዞባዎች አስተዳደ ሚንስትሪ
2. ሃይማኖታዊ ጕዳዮች ጽሕፈት ቤት
3. ህ.ግ.ደ.ፍ. ጽሕፈት ቤት
4. ደቡብ ዞባ አስተዳደር
5. ዓንሰባ ዞባ አስተዳደር
6. ሰሜናዊ ቀይ ባሕር ዞባ አስተዳደር

https://www.vaticannews.va/ti/church/ne ... zione.html

Awash
Senior Member+
Posts: 28957
Joined: 07 Aug 2010, 00:35

Re: Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

Post by Awash » 26 Sep 2019, 13:40

I think you should heed the advice of brother Meleket. I'm just a messenger. This is about a much bigger issue than me, a humble soul who's trying to bring to the attention of forumers the plight of the people.
tekeba wrote:
26 Sep 2019, 07:38
Dummy ugum jeberti, who cares. The pseudo bishops should go to jail. Do you get it, MORON

Zmeselo
Senior Member+
Posts: 21037
Joined: 30 Jul 2010, 20:43

Re: Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

Post by Zmeselo » 26 Sep 2019, 14:26


Awash wrote:
26 Sep 2019, 13:40
I think you should heed the advice of brother Meleket. I'm just a messenger. This is about a much bigger issue than me, a humble soul who's trying to bring to the attention of forumers the plight of the people.
tekeba wrote:
26 Sep 2019, 07:38
Dummy ugum jeberti, who cares. The pseudo bishops should go to jail. Do you get it, MORON

Awash
Senior Member+
Posts: 28957
Joined: 07 Aug 2010, 00:35

Re: Eritrean bishops call out ‘hatred of faith’ after school closures

Post by Awash » 27 Sep 2019, 01:01

And you call yourself an Eritrean or Christian? You're an Agame worshipping stooge aka zombie.
Zmeselo wrote:
26 Sep 2019, 14:26

Awash wrote:
26 Sep 2019, 13:40
I think you should heed the advice of brother Meleket. I'm just a messenger. This is about a much bigger issue than me, a humble soul who's trying to bring to the attention of forumers the plight of the people.
tekeba wrote:
26 Sep 2019, 07:38
Dummy ugum jeberti, who cares. The pseudo bishops should go to jail. Do you get it, MORON

Post Reply