Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
banebris2013
Member
Posts: 821
Joined: 09 Apr 2013, 20:53

Re: <<የማጀት ሥር ትምክህት>> .. የዲያቆን ዳንኤል ክብረትንና የዶ/ር አብይን ፀረ-ኦሮሞ ራዕይ ላበሰረው የወ/ሪት ህሊና ደሳለኝ ግጥም የተሰጠ የግጥም ምላሽ።

Post by banebris2013 » 14 Sep 2019, 18:16

yaballo wrote:
14 Sep 2019, 05:03
የማጀት ሥር ትምክህት፤ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትንና የዶ/ር አብይን ፀረ-ኦሮሞ ራዕይ ላበሰረው የወ/ሪት ህሊና ደሳለኝ ግጥም የተሰጠ የግጥም ምላሽ።







የማጀት ሥር ትምክህት፤

(By Abbaa Daraar).

>>>X<<<
ሙያተኛ አገርሽ
ከማጥገብ የጎደለው፤
የገበታዋን ለዛ
በረከት የራቀው፤
ግብዝ ዲያቆናት
እንምራሽ ቢሏት ነው።
++
ተሻምቶ ለመጉረስ
ማዕዱን መድፋቱ፤
ሰርክ ማይጠረቃ
ሆኖበት ቀፈቱ፤
ከበላው በይበልጥ
የደፋው መብዛቱ፤
አመል ሆኖበት ነው
የቀን ጅብነቱ።
++
ሙያዋ ቢያስደፍር
አጀብ ባይሰኙበት፤
ማዕድዋ ባይብላላ
ዓይነቱ ባያምርበት፤
ከሰው በዘረፉት
ከራስ ላብ ባልመጣ፤
ገበታ እንዴት ይመር
ውበት ከየት ይምጣ።
++
አበዛዙም ባይሆን
ቢሆን አበላሉ፤
አያምርም ገበታ
ዘርፈው ለሚበሉ።
++
ባይገባችሁ እኮ ነው፤
በፉክክር ቅሚያ
በራብ ስትናጡ፤
ከደፋችሁት በልቶ
ከሰው መሳይ ውሾች
ውሻችሁ መብለጡ፤
የቀን ጅብ ብትሆኑ ነው
የሰው ደም በመምጠጥ
አጥንቱን ስትግጡ።
++
ከምርት ያላነሰው
የሞላው ጓዳችሁ፤
አርሳችሁ እንዳልነበር
ያውቃል ልቦናችሁ፤
‘አርሰን ነው’ ስትሉ
ከደሆች ዘርፋችሁ፤
በልቶ ማይጠረቃ
ከርሳምነታችሁ፤
መርቶ መርቶ ወስዶ
ገደል ከተታችሁ።
++
ገበታ እድሜ ነው
ባለማሰብ መክነን
ሳይጣዱ ማረር፤
ራስን እየካቡ
ሌሎችን ማሳጠር፤
በማን ተጀመረ?
እስቲ እንነጋገር!
ከዘመን ገበታ
ከአጼነት መንበር፤
በሞዓ አንበሳነት
አጉል መንጠባረር፤
በማን ተጀመረ
ቅድሚያ ዘር መቁጠር?
++
ገበታ ሀቅ ነው
በትምክህት ጋግራችሁ፤
በሆዳም እስክስታ
በተንኮል ረግጣችሁ፤
በነፍጥ ስትገዙት
ህዝቡን አፍናችሁ፤
በዝቶ ገዝፎ ሞልቶ
ቢፈስ ግፋችሁ፤
የጭቁኖች ቁጣ
ያንድነት ወላፈን
ቢፈነግላችሁ፤
ንስሃ እንደመግባት
ስድብ አማራችሁ?
++
እስቲ ልጠይቅህ
በጥም ደዌ ደቆ
የረሃብ ጠኔ ደፍቶት
ድፍን የወሎ ህዝብ
ሲረግፍ እንደቅጠል፤
የራብ ጣር እናትን
ካራስ ልጅ ሲነጥል፤
ምድረ መኳንንቱ
ጠግቦ ሲቀማጠል፤
ስንዴ ጤፍ ገብስ ማር
ቅቤና እንቁላል፤
ከአጼዎች ማጀት
ያኔስ ጠፍቶ ኖሯል?
++
ዘመን ካልመከረው
ከትምክህት ተራራ፤
እንዴት እንሻገር?
ከጭራቆች መንጋ
ከቀን ጅቦች ጋራ!
++
በቄሮዎች ትግል
ስልጣን ሲጨብጡ
ያልደከሙበትን
ሥልጣን መደራደር፤
በፋኖዎች ባዶ ሥም
በቄሮዎች ደም ላይ
ወንበር መበዳደር፤
ያሳፍራል አይደል?
++
ነጻነት በነጻ
አግኝቶ መኮፈስ
መፎከር መሸለል፤
እያደጉ ማነስ
ለሥልጣን ሽሚያ
የራስ ወገን መግደል፤
ያሳፍራል አይደል?
++
መከባበር ከሚያባላ
እኵልነት ከሚያቃቅር፤
ባርነት ይሰንብት
ያንድ ወገን አንድነት
ጥንቅር ብሎ ይቅር።
++
እርስ በራስ ተጋድለው
ደም እየተቃቡ፤
ደረት እየደቁ
ያዞ እምባ ቢያነቡ፤
የእምዬን ወደ አብዬ
ከንቱ ማሳበቡ፤
ሲኖር አብሮ ገድሎ
ሲሞት ሙሾ ማውረድ፤
የእርስ በርስ ጥላቻ
የሴረኞች ወጥመድ፤
++
በናታችሁ አድባር
በፍቅሯ ይሁንባችሁ፤
የማሳችሁት ጉድጓድ
መልሶ እናንተን
ቢሰለቅጣችሁ፤
ታጥቦ የማይነጻ
ቢሆን እድፋችሁ፤
ቆሽሻችሁ መኖርን
ማን ከለከላችሁ!?
++
በመጠማት ሲቃ
እስትንፋስ እስኪያንቃት
ብትቃትት ነፍስህ፤
ወሎ በራብ ሲረግፍ
ባያውርህ ኖሮ
ማይሞላ ቀፈትህ፤
ሰብዓነት ቢኖርህ
ያኔ ነበር ሚያምር
ሰው የመሆን ውበትህ።
++
“አንተነትህን ትተህ
እኔነትን ልበስ”
ብለህ ማለት ይብቃህ፤
ለሀቅ በመታገል
አንድ የመሆን መንፈስ ይንዳህ፤
ከትምክህተኝነት ተፈወስ
ሰው የመሆን ጸበል ይንካህ።
++
አየህ!
ሰው ስትሆን
ከትምክህት እሚያግድ
እረኛ አያሻህም፤
ከህሊናህ ሚበልጥ
ፈራጅ አይኖርህም፤
ስታስብ ህዝብ ነህ
በብስለት ከፍታ፤
ከትምክህት ተላቀህ
ሰው የሆንከው ለታ።
++
አየህ!
ሰው ስትሆን
የትምክህት አረም ነቅለህ፤
ባንድነት መስክ ላይ
ፍቅር ትዘራለህ፤
ያኔ ከሌሎች ጋር
በአንድነት ድልድይ
ትሸጋገራለህ።
++
አየህ!
ሰው ስትሆን
ዝምታህ ሀያል ነው
ስትጸዳ ከትምክህት፤
ካጓጉል ፉከራ
ከባዶ ሰው ጩኸት፤
ሀገር ላምስ ከሚል
ከዲያቆን እስስት፤
ከአጼነት ራዕይ
ከራስ ባዶ ተረት።
++
አየህ!
ሰው ሳትሆን ስትቀር
ጥላቻን ተጠምቀህ፤
አንድነት ካልጣመህ
ክብር ካልሆነልህ፤
ዳግም ካገረሸ
ትምክህተኝነትህ፤
ረግጦ የመግዛት ሱስ
የዘመናት መርዝህ።
++
እስቲ ልጠይቅህ
ጠልተህ ላይሆንልህ
ችለህ ላትጋደል፤
ነደህ ላትፋጀው
ታግለሀው ላትጥል፤
ጡት እየቆረጥክ
እጅ እየጎመድክ
እንደ አያቶችህ
የሰው አካል ማጉደል፤
በትንታጉ ትውልድ
በቄሮዎች ዘመንም
ያሰኝሃል አይደል?
++
ማንነታችን ነው
ያንድነታችን ውል
የፍቅራችን ቀለም፤
አንድ የመሆን እውነት
በውዴታ እንጂ
በግዴታ የለም፤
ቁቤ ኬኛ መሌ
ፊደልና አፍህ
ቋንቋችን አይደለም።
++
ከትምክህት በመጽዳት
ትውልድ እናስተምር
ዘመን ይመርቀን፤
ክንዳችን ምን ጎሎት
ቅኔያችሁ ያስታርቀን!?
++
በቄሮዎች አጥንት
በደም ኪዳን ምለን
ቃል ተገባብተናል፤
ከትምክህት የጸዳ
ሀገር የሚያሻግር
ድልድይ ገንብተናል፤
ለብሔራዊ አንድነት
ለአብሮነት ህብር
መሰረት ጥለናል፤
ባንድ ሀሳብ ተጋምደን
በድል ድር አብረን
ጉዞ ጀምረናል።
++
በሞላ ጎዳና
ባልጠበበ ምድር፤
ፊንፊኔን ኮ ተሁ
ስትገጥም ክርክር፤
ማሞኘት ሲያምርህ
አንድ ነን ትላለህ፤
ባንዳ በከፈተው
በአጥራችን ቀዳዳ
ጓዳ ድረስ ገብተህ።
++
ጥላቻና ትምክህት
ልቦናህን ደፍኖ
ማሰቢያህ ቢከዳህ፤
እንዴት አንድ እንሁን?
ከትምክህት ነቀርሳ
ልቦናህ ሳይጸዳ።
++
ሞቶ እሚያነግስ
ህይወቱን ሰውቶ፤
የባርነትን ዕድፍ
በደሙ አጽድቶ፤
ነጻነት ቢሰጥህ
ቢያነግስህ ቀብቶ፤
ማንቋሸሽ አማረህ
በቅኔ ድርደራ
ትምክህተኝነትህ
ዳግም አገርሽቶ።
++
ነጻነት ምርጫ ነው
ጥፋት ያመነነው
የትምክህት ጎዳና
አምሮ ቢደላደል፤
ራስ ማጥፋት ምርጫ ነው
ባንድ ቋንቋ ትርክት
አጉል ከመጃጃል።
++
ነጻነት ማመን ነው
በትምክህት ታውሮ
ከሚዋትት የጅብ ሆዳም፤
እራስን ማዳን ነው
የነጻነት ገዳም።
++
ነጻነት ማሰብ ነው
ባንድነት መለምለም፤
ከህሊና ሲነቅሉ
ያጼነትን አረም፤
ባንድ ቋንቋ አዋጅ
ላንድነት ከመልፋት፤
ይበጀናል ለኛ
ዘር ሆነን መክሰሙ
መንደር ሆነን መጥፋት።
++
ንገሯት ላገሬ
በጀግኖቿ ትግል
ድምበር ባታስደፍር፤
ነጻ ነኝ እንዳትል
እየተገረፈች እየተወገረች
በነፍጠኞች ብትር።
++
ሥሩን ካልሸመንነው
በመዋሀድ ጥለት
በማስተዋል ሸማ፤
ታሪክ አናደምቅም
በቅኔ ድርደራ
በዲያቆናት ዜማ።
++
ምን ብታቀነቅን
በባንዳዎች መድረክ
ቅኔ ብትደግስም፤
በታወረ አዕምሮ
ባንድ ቋንቋ ትርክት
ሀገር አናድስም።
>>>X<<<




EXACTLY, thanks Yaballo for sharing.