Page 1 of 1

@Amharic: የአድዋ ጦርነት ላይ የነበረውን የሚንሊካዊያን አስፀያፊ ተግባር ያንብቡ። ዛሬ ላይ ግን የአማራ ኦርቶዶክስ፣ በማርያም ነው ወላሂ ማለት ይዳዳታል።

Posted: 11 Sep 2019, 14:39
by AbebeB
የአድዋ ጦርነት ላይ የተሰዉ የክርስትና እምነት ተከታይ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮችን አስክሬን ለቅሞ “እንደነገሩ” ለመቅበር ተሞክሮ ነበር። ይሄን ያደረጉት የሚኒሊክ ሰዎች የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ወታደሮችን አስክሬን ለይተው ሳይቀብሩ ቀርተዋል። ይሄ የተመዘገበ የታሪክ እውነታ ነው።

ከድሉ በኋላ አሁን ድረስ ሃገሪቱን አንቀው ለያዙት የፖለቲካ ተቃርኖዎች መሰረቱን የጣለውና በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል (ኦሮሚያን ጨምሮ) ላይ የተጣለውን ጨለማ የጪሰኛ ሰርዓትን እንኳ ብንተወው፣ የጋራ ከፍታ በሚባለው በራሱ ባድዋው የጦርነት ውሎ ላይም እንኳ እንዲህ ዓይነት ለወሬ እንኳን ማይመቹ (በዚያን ዘመን ልኬትም ቢሆን) አስቀያሚ ነገሮች ነበሩበት።

አንዳርጋቸው ጽጌ ካዲሱ መጽሃፍ ጋር በተያያዘ ለተነሱለት ጥያቆዎች በዚህና ሌሎች ጉዳዮች ላይ እንዴት እንዲህ ትላለህ በሚል ለተናደዱበት ደጋፊዎቹ አለሳልሶ ለማስረዳት ሲጨነቅ ሲጠበብ አይቼው ከምሬን ሳላዝንለት አልቀረውም።

ይልቅ በባለፈው ጊዜ ስላልነበረ የጋራ የከፍታ ታሪክ ላይ ስንጨቃጨቅ ለወደፊቱ የከፍታ ታሪክ በጋራ ልንሰራው ያለን እድል እንዳያመልጠን።

https://kichuu.com/dubbiin-kun-garamitt ... eeyyadhaa/