Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 10 Sep 2019, 01:54

ዳዊ፣
እኔ አይኔን ትላልቅ ነገሮች ላይ ብቻ ለማሳረፍ ስለወሰንኩ ሰዎች ግላዊ ህይወታቸውን እንዴ እንደ ሚመሩ ለነሱት ትቼያሉ ። የቀድሞው ሎሬት ጸጋዬ ምን ብሏል መሰልህ ፤ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ህይወት ኖሮ የራሱን ሞት ዪሞታል' ! ትልቅ አባባል ነው። ግን ቃል ሃይል አለው። ሰዎች ሳያቁትም ቢሆን ጥሩ ቃል ሲሰብኩ ጥሩ ነገር ነው ።

እንደ ምታቀው በፊዚክስ ውስጥ The Arrow of Time (የግዜ ቀስት) የሚባል ፕሪንሲፕል አለ። እሱም የነገሮች ሁሉ እድገት፤ የሁነታዎች ሁሉ አቅጣጫ (ትራጀክተሪ) የሚወስነው ሕግ ነው። ስለዚህ አንድ የሰው ባህሪ (ቢሄቪየር) የሚዘውን ትራጀክተሪ ልብ ማለት የግድ ነው ። ያኔ ነው ለእቃወም። ገለልተኛ ለመሆን፣ ለመደገፍ የሚቻለው በትክክል ማለት ነው።

እኔ ለብዙ አመት በትግዕስትና በዝምታ የሰበሰካቸው እጅግ ብዙ መመሪያ ፕሪንሲፕልስ አሉኝ ። ነገሮችን የምለካበት ።ያንን ነው የምጠቀመው ። የምወዳቸው ሰዎች እኔ የማስበውን ሃሳብ ሲናገሩ በዪፋ ወጥቼ ደግፌ ዚፎዞ እሆናለሁ ። እኔ የማላስበውን ግን ኢትዮጵያን የምይጎዳ ነገር ሲናገሩ ዝም እላለሁ ግን ለነሱ ያለኝ መወደድ አይቀነስም ። የሚቀነሰው የኔ ቲፎዘነት ብቻ ነው ።

ለኔ የኢሳት ታጋዮች የሰሩት ስራ ለዘላለም አይረሳም ። ዛሬ ደሞ የራሳቸውን መንገድ የመጉዋዝ መብት አላቸው። እነ እስክንድር፣ እነ ኤርሚያ ስላዲሳባ የሚያደርጉት ሙግት አንዱ አዲሳባ የሚፈልገው ነገር ነው። ኢዚማ የሚያገርገው ነገር እንዲሁ አዲሳባ ኢትዮጵያ የሚፈልጉት ነገር ነው። ይብዛም ይነስ ዴሞክራሲ ወደ እኛ የመጣ ቀን ይህን ነው ሚመስል ።

ያቢይ መንግስት ስለሚያረገው የውን ሆነ የገጽታ ስብከትና ትምህርቶች በሚመለከት ያቢይ አላማና የትግባሩን ውጤት ለይቶ ለማየት ሶሺያል ሂስትሪ የሚባል ነገር ማውቅ ያሻል ።

ገዚዎች ለነሱ ብለው በሚሰብኩት እውነት መሰል ነገር ሌላው የውነት አርጎ ነው የምወስደው ። ስለዚህ ስለ አንደነት፣ ዘረኝነት፣ እድገት፣ ሰላም፣ ብልጽና ኢትዮጵያዊነት መሰበኩ እነ አብዬ ለተቀባይነት ቢያረጉትም ህዝቡ ግ ን የ28 አመት ዎያኔ ስህተት ነበር ብሎ ቤቱ እየገባ ነው። አቢይ ከዚህ በኋላ የዎያኔ ተሟጋች ሊሆን ከማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው።

Actors produce unintended consequences !

Dawi
Member
Posts: 2875
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Dawi » 10 Sep 2019, 11:10

Horus,

I respect that; you have taken it seems a balanced approach.

Though, that "የብልፅግና ቀን" video reminded me the time when Meles was accused of saying something in regards to "development" over "freedom"? :P The only person who was advocating for "economics first" here, of all people, was Zemedeneh Negatu? The "American" who talked about S. Korea & Chinese capitalism. Interesting!

Be that as it may, he seems to be the only one who clearly supported Developmental State Capitalism. "Development" is the bottom line he said; in other words, the rest is the "fluffy stuff" that most were discussing. You ain't going no where with out that; Zemed is t least right on that.

Going back to talking about "What ፍትህ?" though, where is Ermias Amalga? Was it too much to bail him out?
He would have been the only one & the few in the country among the discussant who "walked the talk!" on the economy; very qualified to talk about real "ብልፅግና".

You know what? That is the kind of stuff Ermias of 360 is raising & is hard to ignore.
Horus wrote:
10 Sep 2019, 01:54
ዳዊ፣
እኔ አይኔን ትላልቅ ነገሮች ላይ ብቻ ለማሳረፍ ስለወሰንኩ ሰዎች ግላዊ ህይወታቸውን እንዴ እንደ ሚመሩ ለነሱት ትቼያሉ ። የቀድሞው ሎሬት ጸጋዬ ምን ብሏል መሰልህ ፤ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ህይወት ኖሮ የራሱን ሞት ዪሞታል' ! ትልቅ አባባል ነው። ግን ቃል ሃይል አለው። ሰዎች ሳያቁትም ቢሆን ጥሩ ቃል ሲሰብኩ ጥሩ ነገር ነው ።

እንደ ምታቀው በፊዚክስ ውስጥ The Arrow of Time (የግዜ ቀስት) የሚባል ፕሪንሲፕል አለ። እሱም የነገሮች ሁሉ እድገት፤ የሁነታዎች ሁሉ አቅጣጫ (ትራጀክተሪ) የሚወስነው ሕግ ነው። ስለዚህ አንድ የሰው ባህሪ (ቢሄቪየር) የሚዘውን ትራጀክተሪ ልብ ማለት የግድ ነው ። ያኔ ነው ለእቃወም። ገለልተኛ ለመሆን፣ ለመደገፍ የሚቻለው በትክክል ማለት ነው።

እኔ ለብዙ አመት በትግዕስትና በዝምታ የሰበሰካቸው እጅግ ብዙ መመሪያ ፕሪንሲፕልስ አሉኝ ። ነገሮችን የምለካበት ።ያንን ነው የምጠቀመው ። የምወዳቸው ሰዎች እኔ የማስበውን ሃሳብ ሲናገሩ በዪፋ ወጥቼ ደግፌ ዚፎዞ እሆናለሁ ። እኔ የማላስበውን ግን ኢትዮጵያን የምይጎዳ ነገር ሲናገሩ ዝም እላለሁ ግን ለነሱ ያለኝ መወደድ አይቀነስም ። የሚቀነሰው የኔ ቲፎዘነት ብቻ ነው ።

ለኔ የኢሳት ታጋዮች የሰሩት ስራ ለዘላለም አይረሳም ። ዛሬ ደሞ የራሳቸውን መንገድ የመጉዋዝ መብት አላቸው። እነ እስክንድር፣ እነ ኤርሚያ ስላዲሳባ የሚያደርጉት ሙግት አንዱ አዲሳባ የሚፈልገው ነገር ነው። ኢዚማ የሚያገርገው ነገር እንዲሁ አዲሳባ ኢትዮጵያ የሚፈልጉት ነገር ነው። ይብዛም ይነስ ዴሞክራሲ ወደ እኛ የመጣ ቀን ይህን ነው ሚመስል ።

ያቢይ መንግስት ስለሚያረገው የውን ሆነ የገጽታ ስብከትና ትምህርቶች በሚመለከት ያቢይ አላማና የትግባሩን ውጤት ለይቶ ለማየት ሶሺያል ሂስትሪ የሚባል ነገር ማውቅ ያሻል ።

ገዚዎች ለነሱ ብለው በሚሰብኩት እውነት መሰል ነገር ሌላው የውነት አርጎ ነው የምወስደው ። ስለዚህ ስለ አንደነት፣ ዘረኝነት፣ እድገት፣ ሰላም፣ ብልጽና ኢትዮጵያዊነት መሰበኩ እነ አብዬ ለተቀባይነት ቢያረጉትም ህዝቡ ግ ን የ28 አመት ዎያኔ ስህተት ነበር ብሎ ቤቱ እየገባ ነው። አቢይ ከዚህ በኋላ የዎያኔ ተሟጋች ሊሆን ከማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው።

Actors produce unintended consequences !

Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 10 Sep 2019, 12:31

እነዚህ ናቸው የኢትዮጵያ አዲስ ካልቸር የሚያቆሙት

Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 10 Sep 2019, 12:37

አዲሱ የኢትዮጵያ ካልቸርና የኢትዮጵያ ምሁራን
መስክረም 1 2012

የአንድ አገር ስልጣኔም ሆነ የአንድ ሕዝብ ካልቸር የሚፈጠረው፣ የሚጠበቀው፣ የሚያድገውና የሚለወጠው ባሉት ልሂቃና እና ምሁራን ነው። የዚያ አገር ስልጣኔም ሆነ እድገት የሚደክመውና የሚፈርሰው ባሏት ደካማ ልሂቃና ምሁራን ነው፤ ማለትም ምሁር አልባ አገር ስትሆን ማለት ነው።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ስላገራችን ካልቸርና ስልጣኔ ቀውስ ብዙ እየተባለ ነው። ብዙም አበረታች አዝማሚያዎች እየታዩ ነው ። ይህም ማለት ስለምሁርን፣ ስለካልቸር፣ ስለስልጣኔ እድገትና ሂደት በቅጡ ማሰብና መወያየት መጀመር ያለብን ግዜ ነው ።

ባሁኑ ዘመን በኢትዮጵያም ሆነ በሌላ አገር ያሉት የካልቸር ፈጣሪ የሆኑት ምሁራን በአራት ክፍል ይመደባሉ። እነሱም ሳይንቲስቶች፣ አርቲስቶች፣ ሂዩማኒስቶች እና ቴክኖሎጂስቶች ናቸው። እነዚህ ግዙፍ የምሁራን ክፍሎች እያንዳንዳቸው በውስጣቸው ንኡስ ክፍሎች አላቸው ። እንዲሁም እያንዳንዱ የምሁር መደብ የራሱ የሆነ ያስተሳሰብ ዘይቤ፣ የምክንያት አሰጣጥ ስልት፣ ንድፈ ሃሳብ እና ክህሎት አለው።

እዚህ እጅግ አጭር ማሳሰቢያ ላይ ስለያንዳንዱ የምሁራን ምድብ ዝርዝር ተልእኮና ተግባር ማንሳት አይቻልም። በአንድ ቃል የጉዳዩን ፋይዳ መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያዊያን የምር ባራት መሰረቶች ማለትም በአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ በሰው ልጅ ልዕልና፣ በስራ ክቡርነት እና በኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ካመንን ባጭር ግዜ ታላቁን የኢትዮጵያ ካልቸር እንገነባለን ። የዚህ ካልቸር ተግባር ወይም ተልእኮ የኢትዮጵያን አጀንዳ ከስኬት ማድረስ ነው ። ይህ የኢትዮጵያን አጀንዳ ምንድን ነው?

አንድ፣ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን ማረጋገጥ፤
ሁለት ፣ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ፤
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ፤
አራት፣ በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት ናቸው ።

በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ከላይ የጠቀስኳቸው አራት የምሁራን ክፍሎች የኢትዮጵያን አጀንዳ እንደ ሚከተለው ይከፋፈላሉ ።

የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን የሚያረጋግጡት ሳይንቲስቶቿ ናቸው። በዚህ አጀንዳ ስር ያሉት ተግባራት ሁሉም ሳይንሳዊ ስነ ሃሳብ፣ ሳይንሳዊ ዘዴ እና ሳይንሳዊ ትግበራ የግድ የሚሉ ናቸው።

ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ የሂዩማኒስት ምሁራን ተግባር ነው። ይህም ግዙፍ መስክ የራሱ የሆነ ፊሎሶፊ፣ ስነ ሃሳብ፣ ዘዴና ትግበራ አለው።

ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩና፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ የቴክኖሎጂስት ምሁራን ተግባር ነው። እዚህ ላይ ቴክኖሎጂን ሰፋ ባለው ጽንሱ መወሰድ አለበት ። የኢኮኖሚ ፈጠራም ሆነ የእውቀት ግንባታ ስራ በመሰረቱ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የብልሃት ፈጠራ ተግባር ነው።

በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት የአርቲስት ምሁራን ተግባር ነው።

ስለዚህ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ታልቅ ካልቸር የቆመበትን መሰረት ጥርት አድርጎ መግለጽ ። ቀጥሎ የዚህ ታላቅ ካልቸር ፋይዳ የሆነውን የኢትዮጵያ አጀንዳን ጥርት አድርጎ መዘርዘር ። ቀጥሎ አራቱ የስልጣኔ ተሟጋች የሆኑት ምሁራኖችን መለየት ። በመጨረሻም አራቱ የኢትዮጵያ አጀንዳ ክፍሎች ለአራቱ የምሁራን መደቦች በግልጽ ማከፋፈል ።

ይህን ዙሪያ ገብ ራዕይ በያላችሁበት አይምሮ ጫሪ የሃሳብ ጮራ አርጉት ። ርእሱ ሙሉ መጽሃፍ ይፈልጋል፤ ግን ሃተታ ቢበዛ ባህያ አይጫንም ብዬ ነው ። መልካም አዲስ አመት! ኬር !!

Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 10 Sep 2019, 13:11

The Ethiopian Artist has the duty to build an Ethiopian culture!


Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 10 Sep 2019, 23:04

ያንድ ስልጡን ካልቸር አንድ ትልቅ መገለቻው መፈላሰፍ ነው። ይህ አንዱ ያዲሱ ባልህ ምልክት ነው ። ይህን ሰው እኔ የማየው እንደ ሂዩማኒስትም እንደ አርቲስትም ነው። ድንቅ ነው።


Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 13 Sep 2019, 22:54

ከትላንቲና የቤተ መንግስት ግጥም ወዲህ 'መንጋ' ስለተባለው ጽንሰ ነገር ወይም ቅርጸ ነገር (ክንሴፕት) ብዙ እየተባለ ነው። መንጋ የሚለው ቃል በሜታፎርነት የመጣ ሲሆን ቃሉ ለከብቶች ስብስብ ወይም ለንሰሶች ስብስብ መጥሪያ ነው ። ነገር ግ ን የንሰሳ መንጋ ባህሪ እንዳለው ሁሉ የሰዎችም መንጋ (ቡድን) ባህሪ አለው። መንጋ የሚለው ድንቅ የሆነ ቅርጸ ነገር በሰው እና በእንሰሳ ባህሪ መካከል ያለውን ልዩነት የሚገልጽ ቃል ነው።

ሰው በአማርኛ ወይም ሰብ በግዕዝ ሴፒየን ከሚለው የላቲን ስር ያለ ነው ። የሚያስቡ ህሊና ያላቸው የማውቅ የመገመት፣ የመወሰን፣ የመለየት ህክሎት ወይም ተሰትዎ ታለንት ኢንተለጀንስ ባለ ጸጋ የሆኑ የሰው ፍጡራን ማለት ነው። የሰዎች ቡድን ምንም ይሁን ምንም የነዚህ አዋቂ ግለሰቦች ስብስብ ስለሆነ አንድ የሰዎች ማህበር ራሱ እንደ ሰው ማሰብና የሰው ልጅን ባህሪ መተግበር ግዲታው ነው።

ነገር ግን የሆኑ ሰው መሰል ቡድኖች ተሰተው ልክ እንደ እንሰሳ ቡድን ማለትም መንጋ ሲሰሩ የመንጋ ባህሪ ሲፈጽሙ ነው ይህ ጽንስ የተነሳው ። እጅግ ትክክል እና በአስተሳሰብ እና በባህል ደረጃ መደረግ ያለበት መለየት (ዲስቲንክሽን) ነው። መንጋ የሚለውን ሲያሜ የሚቃወሙት ሰዎች ያስገርማሉ ። ምንድን ነው የሚሉት? መንጋ መሆን ትክክል ነው ወይ የሚሉት? መንጋ ካልሆኑ ደሞ ለምን አስቆታቸው?

ይህ የኢትዮጵያ ካልቸር እና ፖለቲካ እድገት ምልክት ነው። በዜጋ ህብረተ ሰብ ውስጥ እያንዳንዱ ሰብ ማሰብ አለበት፣ መወሰን አለበት እንጂ እንደ ከብት ዝም ብሎ መነዳት የለበትም ።

Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 16 Sep 2019, 23:41

አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር አራት መቆሚያ የመሰረት አለቶች አሉት ። እንሱም በአንድ ፈጣሪ ማመን፣ በግለሰብ ልዕልና ማመን፣ ኢትዮጵያዊያን ወንድማማችነት ማመን፣ በስራ ክቡርነት ማመን ናቸው ።

ዛሬ ዶ/ር አቢይ በመሰረቱ አራቱንም መሰረቶች በንግግሩ ጠቅሷቸዋል።

ከፋ ክቡር ስልጡን ህዝብ ነው ።

ይህን መሰል ካልቸር የያዝነው ህዝቦች ነው ኢትዮጵያን ዘላለማዊ ምናረጋት !!!Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 05 Oct 2019, 22:45

.....................................................

Horus
Senior Member
Posts: 13820
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 05 Oct 2019, 22:48

ይህን እንደ ገና አንብቡት
ሃምሌ አጋማሽ ላይ 'የዘመናችን ብሄራዊ ቅውስ' በሚል ርእስ በለጠፍኩት አጭር ሃተታ የሚከተለው መደምደሚያ ብዬ ነበር ፡ ባገራችህ ህይወት ውስጥ 3 አዝማሚያዎች እንዳሉ ።

"አንደኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በብትንትንነቱና በቀውሱ ለረጅም ዘመን ሊቀጥል ይችላል። ይህም ማለት አገሪቱ ምንም አይነት መሰረታዊ መፍትሄ ሳታገኝ በሞትና በህይወት መካከል አሳዛኝ የሆነው ህልውናዋ እንደ ተንጠለጠለ ሊቀጥል ይችላል።

ሁለተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በተወሰኑ ሰፋፊ መሬቶች ፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ግዛቶች፣ ተከፋፍሎ በአዲስ ፌዴራላዊ ወይም ኮንፌዴራላዊ ስብስብ ሊቀጥሉ ይችላሉ። ኢትዮጵያ በብዙ አገሮች የምትከፋፈለው ይህ አዝማሚያ እውን ከሆነ ነው።

ሶስተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ መሰረታዊ ያስተሳሰብና የእስትራተጂ ለውጥ አድርጎ ስርወ እሴታችን የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልና፣ የስራ ክቡርነት እና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ሆኖ አገሪቱ ከውድቀት ልትድን ትችላለች ።

ከነዚህ ሶስት አዝማሚያዎች የትኛው እውን እንደሚሆን የሚወሰነው በኢትዮጵያ ምሁራን መካከል ባለው የሃይል ሚዛንና የማሰብ ችሎታ ነው። ለምሳሌ ያንድነትም ሆነ የብሄረሰብ ምሁራን ከደከሙና አዲስ መፍትሄ ማቅረብ ካልቻሉ ወይም አንዱ ከሌላው በልጦ ማሸነፍ ካልቻለ አንደኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የብሄረሰብ ምሁራን የበላይነት ይዘው የጎሳ ክፍፍል አሁን ባለው ቀጥሎ ካደገና ካሸነፈ ሁለተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ከጠነክሩ ሶስተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።"

ይህን ያልኩት የዛሬ 24 አመት ነበር ። ባሁን ወቅት በሃተታዬ ውስጥ ካነስኋቸው የቀውስ መስኮች ብዙዎቹ ጥሩ ወይይት እየተደረገባቸው ነው ።

በእኔ ግምት ጠንካራ የኢትዮጵያ ካልቸር ማለትም በአራቱ ጽኑ መሰረተ እሴቶች የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልና፣ የስራ ክቡርነት እና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ላይ የቆመ ካልቸር እያቆጠቆጠ ይመስላል ። የተለያዩ ምሁራን የሚያደርጉትን ውይይት፣ ልዩ ልዩ የሲቪል ማህበራት የሚሰሩትን፣ ኢትዮጵያዊው ሚዲያ፣ የዜጋ ፓርቲዎችና አቢይ አህመድ የሚሰጡዋቸው ትምህርቶችን ማስተዋል ነው።

ኢትዮጵያዊያን የምር ባራቱ መሰረቶች ማለትም በአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ በሰው ልጅ ልዕልና፣ በስራ ክቡርነት እና በኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ካመኑ ባጭር ግዜ ታላቁን የኢትዮጵያ ካልቸር እንገነባለን ።

የዚህ ባለ አራት ምሰሶ ካልቸር ፋይዳ ምንድን ነው?

የዚህ ካልቸር ተግባል ወይም ተለኮ የኢትዮጵያን አጀንዳ ከስኬት ማድረስ ነው ። የኢትዮጵያን አጀንዳ ምንድን ነው?

አንድ፣ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን ማረጋገጥ፤
ሁለት ፣ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ፤
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ፤
አራት፣ በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት ናቸው ።

ይህ ነው የዚህ ዘመን ትወልድ ታሪካዊ ተልእኮና ያለበት ሃላፊነት። ኬር !!


Post Reply