Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ፤ ሁሉንም የሚያስማሙ የኢትዮጵያ መሰረታዊ እሴቶች

Post by Horus » 07 Sep 2019, 22:10

ሃምሌ አጋማሽ ላይ 'የዘመናችን ብሄራዊ ቅውስ' በሚል ርእስ በለጠፍኩት አጭር ሃተታ የሚከተለው መደምደሚያ ብዬ ነበር ፡ ባገራችህ ህይወት ውስጥ 3 አዝማሚያዎች እንዳሉ ።

"አንደኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በብትንትንነቱና በቀውሱ ለረጅም ዘመን ሊቀጥል ይችላል። ይህም ማለት አገሪቱ ምንም አይነት መሰረታዊ መፍትሄ ሳታገኝ በሞትና በህይወት መካከል አሳዛኝ የሆነው ህልውናዋ እንደ ተንጠለጠለ ሊቀጥል ይችላል።

ሁለተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በተወሰኑ ሰፋፊ መሬቶች ፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ግዛቶች፣ ተከፋፍሎ በአዲስ ፌዴራላዊ ወይም ኮንፌዴራላዊ ስብስብ ሊቀጥሉ ይችላሉ። ኢትዮጵያ በብዙ አገሮች የምትከፋፈለው ይህ አዝማሚያ እውን ከሆነ ነው።

ሶስተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ መሰረታዊ ያስተሳሰብና የእስትራተጂ ለውጥ አድርጎ ስርወ እሴታችን የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልና፣ የስራ ክቡርነት እና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ሆኖ አገሪቱ ከውድቀት ልትድን ትችላለች ።

ከነዚህ ሶስት አዝማሚያዎች የትኛው እውን እንደሚሆን የሚወሰነው በኢትዮጵያ ምሁራን መካከል ባለው የሃይል ሚዛንና የማሰብ ችሎታ ነው። ለምሳሌ ያንድነትም ሆነ የብሄረሰብ ምሁራን ከደከሙና አዲስ መፍትሄ ማቅረብ ካልቻሉ ወይም አንዱ ከሌላው በልጦ ማሸነፍ ካልቻለ አንደኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የብሄረሰብ ምሁራን የበላይነት ይዘው የጎሳ ክፍፍል አሁን ባለው ቀጥሎ ካደገና ካሸነፈ ሁለተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ከጠነክሩ ሶስተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።"

ይህን ያልኩት የዛሬ 24 አመት ነበር ። ባሁን ወቅት በሃተታዬ ውስጥ ካነስኋቸው የቀውስ መስኮች ብዙዎቹ ጥሩ ወይይት እየተደረገባቸው ነው ።

በእኔ ግምት ጠንካራ የኢትዮጵያ ካልቸር ማለትም በአራቱ ጽኑ መሰረተ እሴቶች የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልና፣ የስራ ክቡርነት እና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ላይ የቆመ ካልቸር እያቆጠቆጠ ይመስላል ። የተለያዩ ምሁራን የሚያደርጉትን ውይይት፣ ልዩ ልዩ የሲቪል ማህበራት የሚሰሩትን፣ ኢትዮጵያዊው ሚዲያ፣ የዜጋ ፓርቲዎችና አቢይ አህመድ የሚሰጡዋቸው ትምህርቶችን ማስተዋል ነው።

ኢትዮጵያዊያን የምር ባራቱ መሰረቶች ማለትም በአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ በሰው ልጅ ልዕልና፣ በስራ ክቡርነት እና በኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ካመኑ ባጭር ግዜ ታላቁን የኢትዮጵያ ካልቸር እንገነባለን ።

የዚህ ባለ አራት ምሰሶ ካልቸር ፋይዳ ምንድን ነው?

የዚህ ካልቸር ተግባል ወይም ተለኮ የኢትዮጵያን አጀንዳ ከስኬት ማድረስ ነው ። የኢትዮጵያን አጀንዳ ምንድን ነው?

አንድ፣ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬን ማረጋገጥ፤
ሁለት ፣ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ ማህበረሰብ ማደግ፤
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያንን ሃብታም፣ የተማሩ፣ ጤነኛ ሕዝብ ማድረግ፤
አራት፣ በፈጠራ የተካነ፣ ከባቢውን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት ናቸው ።

ይህ ነው የዚህ ዘመን ትወልድ ታሪካዊ ተልእኮና ያለበት ሃላፊነት። ኬር !!

viewtopic.php?f=2&t=189695
Last edited by Horus on 05 Oct 2019, 22:53, edited 2 times in total.

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 07 Sep 2019, 23:13

ልብ በሉ፣ አዲሱ የኢትዮጵያ ካልቸር ያልኩት ለምክኛት ነው ። አንደኛ ካልቸር የሚለው ቃል እኛ ባህል ከምንለው የሰፋ ስለሆነ ነው። ካልቸር ማለት የሰው ልጅ በተፈጥሮ ያገኘውን ሳይሆን በራሱ ማህበራዊ እድገቱና ጥረቱ የፈጠራችውን ያመረታቸውን ነገሮች ሁሉ ከእውቀት እስከ ማንኪያ፣ ከእርሻ እስከ ቤት ግንባታ። ከምግብ እስከ ጠፈር መንኮራኩር ወዘተ ስለሚጠቅልል ነው ። የካልቸርን ሙሉ ይዘት የሚገልጽ ቃል እስከ ምንቀርጽ ካልቸርን የፈጠሩትን እያመሰገንን እንጠቀመዋልን ።

አዲስ ያልኩበት ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሁን ሰአት እምነት የሌለው ሰው የለም፤ በሞላ ጎደል፤ እምነቱ የዳበረ ሆነም አልሆነ ። እፍኝ የማይሞሉ ፈጣሪ ሃይል የለም የሚሉ የምር ኮሚኒስት ካለ እሱን አልቆጥርም። እናም እኛ በተለያየ ሃይማኖት ስር ያለን ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ዞሮ ዞሮ ፈጣሪ አንድ ነው ብለን ስለምናምን ያንን ነው ይሁላችንም የጋራ ለሆነው የኢትዮጵያ ካልቸር ስርወ እሴት ነው የምለው ።

ሌላው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ወንድማማች ናቸው የሚለውም ጄኔቲክ እውነታ ቢሆንም በሌጣው አዲስ እሴት፣ አዲስ ቫልዩ ስለሆነ ።

ሌላው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በስራ ክቡርነት አያምኑም። አንዱ የካልቸራችን ኋላ ቀርነት እና የኛም ድህነት በዚያ ሳቢያ ነው። ስለዚህ በስራ ክቡርነት ማመን ለብዙ ሰው አዲስ ነው።

ሌላ በጎሳ የተወሰነ ጠባብና በሞራል መርህ ያልዳበረ ትናንሽ ባህላትን ዘሎ የአዲሱ ካልቸር አባል መሆን ራሱ አዲስ ስለሆነ ነው አዲስ ካልቸር ያልኩኝ ! ኬር

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 08 Sep 2019, 00:13

የነ ጃዋር እዝቃኤላዊ ጸረ ኢትዮጵያ ቅዠት በደንብ መመታት አለበት

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 08 Sep 2019, 00:18

ክርስትና ትልቁ የኢትዮጵያ ባህል ነው ። ያንን የሚነኩ ደደቦች ናችው

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 08 Sep 2019, 00:38

በቃ አዲስ ካልቸር የሚፈጠረው እንደዚህ ነው

Ethoash
Senior Member+
Posts: 22324
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Ethoash » 08 Sep 2019, 00:53

Horus wrote:
08 Sep 2019, 00:18
ክርስትና ትልቁ የኢትዮጵያ ባህል ነው ። ያንን የሚነኩ ደደቦች ናችው

ሆረር እንደ እብድ ብቻህን መነጋገር ጀመርክ ውይ።

ወይ ወንድሜን ትንሽ እኔ እንኮን ቤት ህን ልግብኝ ለደሮ ግዜ ውለታ ብዬ ።
በመጀመርያ ሲኖዶሱ ትግሬዎች ነበሩ
ከዚያ አቶ ሐይለ ስላሴ አማሮችን ሾመ
ከዚያ መንጌ ከደላቸውና የሚፈልገውን ሾመ
ከዚያ ትግሬዎች ደግሞ የራሳቸውን ሰው ሾሙ
ወያኔ ደጉ አቡኑን ስላልገደላቸው አሜሪካ ሄደው ተቃወሞ አስሙ።

በትግሬዎች አብነ አንገዛም ብለው ሁለት ሲኖዶስ መስረቱ

እንግዲህ እግዛብሔር ያሳያቹ ለስልጣን በለው ሁለት ሲኖዶስ መሰረቱ
ዘረኝነታቸውም ግጥጥ በሎ ወጣ።።። ምክን ያት ሲስጡ ሲወርድ ሲዋረድ ብህሉ አቡኑ ሲሞቱ ነው ሌላ መሾም ያለበት ይላል። ግን ሁለት ሲኖዶስ አቆቁም ይላል ወይ። እኔ ጥሉ በፍፁም ባህል ስነስራት ይከበር ለማለት አይደለም በትግሬዎች አንገዛም ለማለት ነው።

ታድያ ይህ ከሆነ ለምን ብሎ ነው ኦሮሞ በአማሮች የሚገዛው፤ እሱስ ይቅር ደርሶ በአገሩ በመሬቱ በቤቱ ልዘዥህ መምጣቱ ነው እኮ ግራ ያስጋባን።

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 08 Sep 2019, 00:58

አዲስ ካልቸር የሚፈጠረው እንዲህ ነው !

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 08 Sep 2019, 01:06

የታላቁ ኢትዮጵያ ካልቸር ግንባታ እንዲህ ነው ። ይህ ወብ ዘመን ነው !!! ኤቦ የቆሬ ለደሀ፣ የዎሬ ለታዬ !!!

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 08 Sep 2019, 01:51

በቃ በኢትዮጵያ አዲስ ካልቸር፣ አዲስ ስልጣኔ እየተገነባ ነው። ለጀመመሪያ ግዜ ሳይኮሎጂ ወደ አገራችህን ገብቷል።

እድገት፣ ስራ፣ ሌላም ሌላም ይህ ነው ያገር መንቃት ። ያገር መነሳት !!!

Ethoash
Senior Member+
Posts: 22324
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Ethoash » 09 Sep 2019, 08:10

ምን ሆነናል፧
የሆኖነው ቡዳ ማንነታችሁን ለመተወ ባለመፈለጋቹሁ ነው።
አሁን በምን ሒሳብ ነው የአቶ ሐይሌ ስላሴ ባንድራ ከዚህ ቡትቶ የዛገና ያረጅ ሐስተሳሰባችሁ በሌላው ለመጫን መፈለጋች ሁ ነው።

እኔ በምንም ተሐምርም የተቀየረ ባንድራ እያዙ አንድነት የሚሉት ቀልድ አይስራም። ይህ እኮ ማለት የአሜሪካኖችን ኮንፈደርሽን ባንድራ እያወለበለቡ አንደነት እንደማለት ነው።

Selam/
Member
Posts: 2405
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Selam/ » 09 Sep 2019, 08:29

Irrelevant woyane rat - He’s silently telling you, you’re a piece of sh!t not worth responding to. Scratch a little bit more, still no cheese. KIFU!

Ethoash wrote:
09 Sep 2019, 08:10
ምን ሆነናል፧
የሆኖነው ቡዳ ማንነታችሁን ለመተወ ባለመፈለጋቹሁ ነው።
አሁን በምን ሒሳብ ነው የአቶ ሐይሌ ስላሴ ባንድራ ከዚህ ቡትቶ የዛገና ያረጅ ሐስተሳሰባችሁ በሌላው ለመጫን መፈለጋች ሁ ነው።

እኔ በምንም ተሐምርም የተቀየረ ባንድራ እያዙ አንድነት የሚሉት ቀልድ አይስራም። ይህ እኮ ማለት የአሜሪካኖችን ኮንፈደርሽን ባንድራ እያወለበለቡ አንደነት እንደማለት ነው።

Ethoash
Senior Member+
Posts: 22324
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Ethoash » 09 Sep 2019, 08:56

Selam/ wrote:
09 Sep 2019, 08:29
Irrelevant woyane rat - He’s silently telling you, you’re a piece of sh!t not worth responding to. Scratch a little bit more, still no cheese. KIFU!
HOW insulting me answer the question ... those guys waving illegal flag , it is personal property of Ato haile selassie flag, how would u like it if oromo waving OLF flag and claim it is Ethiopian flag ....yes, the old the loyalist flag once it was the Amhara flag ... but the Ethiopians citizen come and change the flag after extensive people discussion .... now tell me i am dying to know do u think oromo and Golden will accept the Amhara flag they dont. so this singer himself is the problem the source of the problem ....do u also notice only Ethiopian loyalist flag waved that means they dont accept the fed. flag . oromo over their dead body they will give up their state flag....

by the way each 50 state of America have their own flagif this old time singer if they really want unity they should have waved all state flag alone side of fed. flag .. flag doesnt harm anything it is just flag even if those buda cant accept this simple thing why they think they will solve the problem..

as i said million time over Amhara should be kick out of the union, if the rest of nation and nationality want a peace.. we must kick out the Amhara even we should give the Addis Ababa as going gift..

dear Selam, dont rush to answer read what i try to say.. if u dont understand it read it 40 times..

Selam/
Member
Posts: 2405
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Selam/ » 09 Sep 2019, 17:59

Nifitam woyane - I would punch you in the face if I see you. What’s the flag of the state you live in the US?
Ethoash wrote:
09 Sep 2019, 08:56
Selam/ wrote:
09 Sep 2019, 08:29
Irrelevant woyane rat - He’s silently telling you, you’re a piece of sh!t not worth responding to. Scratch a little bit more, still no cheese. KIFU!
HOW insulting me answer the question ... those guys waving illegal flag , it is personal property of Ato haile selassie flag, how would u like it if oromo waving OLF flag and claim it is Ethiopian flag ....yes, the old the loyalist flag once it was the Amhara flag ... but the Ethiopians citizen come and change the flag after extensive people discussion .... now tell me i am dying to know do u think oromo and Golden will accept the Amhara flag they dont. so this singer himself is the problem the source of the problem ....do u also notice only Ethiopian loyalist flag waved that means they dont accept the fed. flag . oromo over their dead body they will give up their state flag....

by the way each 50 state of America have their own flagif this old time singer if they really want unity they should have waved all state flag alone side of fed. flag .. flag doesnt harm anything it is just flag even if those buda cant accept this simple thing why they think they will solve the problem..

as i said million time over Amhara should be kick out of the union, if the rest of nation and nationality want a peace.. we must kick out the Amhara even we should give the Addis Ababa as going gift..

dear Selam, dont rush to answer read what i try to say.. if u dont understand it read it 40 times..

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 09 Sep 2019, 21:58

ይህን ሰው ልብ ብላችሁ አድምጡት ። እነዚህ ናቸው ያዲሱ ካልቸር መሪዎች

Horus
Senior Member
Posts: 13879
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Horus » 09 Sep 2019, 22:13

በኢትዮጵያ ውስጥ ፖዘቲቭ ወይም ገምቢ ሳይኮሎጂ ትልቅ ኢንዱስትሪ ሆኖ እንዲያድግ መጣር አለበን ። ይህ እጅግ ደስ የሚለኝ የካልቸር ልውጥ ነው ።

Dawi
Member
Posts: 2881
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: አዲሱ ኢትዮጵያዊ ካልቸር እና የኢትዮጵያ አጀንዳ

Post by Dawi » 09 Sep 2019, 23:50

Horus wrote:
08 Sep 2019, 01:51
በቃ በኢትዮጵያ አዲስ ካልቸር፣ አዲስ ስልጣኔ እየተገነባ ነው። ለጀመመሪያ ግዜ ሳይኮሎጂ ወደ አገራችህን ገብቷል።

እድገት፣ ስራ፣ ሌላም ሌላም ይህ ነው ያገር መንቃት ። ያገር መነሳት !!!
Horus - Talking about side issue.

I tried to think of all the good things Frealem Shibabaw was offering to the discussion and was going to leave her alone but, she repeated forcefully at the end emphasizing the "long life", retirement, example for kids and so on which are great points. My question however is, how is she doing with her weight issue? the same with that big "Kess? He needs to go fasting", seriously; that is Tewahedo culture; isn't it? Walk the talk!

Horus,

I am curious, what do think of Ermias of 360 not buying all this "buz words" of Dr. Abiy "የብልፅግና ቀን", የፍትህ ቀን" ምናምን. What ፍትህ? He says. Well, he has good reasoning behind his thoughts; I do sympathize with you giving support for "the new Ethiopian culture" as well. We are all between a rock and a hard place.

[/quote]

Post Reply