Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33738
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

[ሰበር መረጃ] ወደ ሱዳን የተሸጋገርው ሕገ ወጥ ወታደራዊ ትጥቅ በተ.መ.ድ. ሱዳን ላይ ተይዞ ወደ ኢትዮጲያ እየተመለሰ ነው

Post by Revelations » 31 Aug 2019, 15:36

ባለፈው ሳምንት ከአንቦ ከተማ ተነስቶ በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ሊሸጋገር ሲል በመተማ ህዝብ ንቁ እንቅስቃሴ በአማራ ልዩ ሃይል ቁጥጥር የዋለው የአምስት ጭነት መኪናዎች ወታደራዊ ትጥቅ በአዴፖ እና በፌዴራል አመራሮች ህገ ወጥ የሀይል ውሳኔ ወደ ሱዳን ተሸጋግሮ የሄደ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦር መሳሪያ ዝውውር ቁጥጥር አካላት ባደረጉት ክትትል ገዳሪፍ ከተባላችው የሱዳን ከተማ ላይ በሱዳን ወታደራዊ ሀይል በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ ከቆየ በኋላ በዛሬው እለት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ በተላለፈው የተመድ ውሳኔ መሰረት ወታደራዊ ትጥቁን የጫኑት መኪናዎች ሱዳን ኢትዮጵያ ጠረፍ ገላባት ከተማ መድረሱን እና ወደ መተማ ለመሸጋገር በዝግጅት ላይ እንደሚገን ከስፍራው የደረስን መረጃ ገለጠ።




Revelations
Senior Member+
Posts: 33738
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [ሰበር መረጃ] ወደ ሱዳን የተሸጋገርው ሕገ ወጥ ወታደራዊ ትጥቅ በተ.መ.ድ. ሱዳን ላይ ተይዞ ወደ ኢትዮጲያ እየተመለሰ ነው

Post by Revelations » 31 Aug 2019, 17:27

Please wait, video is loading...




gurre
Member
Posts: 186
Joined: 03 Aug 2013, 05:32

Re: [ሰበር መረጃ] ወደ ሱዳን የተሸጋገርው ሕገ ወጥ ወታደራዊ ትጥቅ በተ.መ.ድ. ሱዳን ላይ ተይዞ ወደ ኢትዮጲያ እየተመለሰ ነው

Post by gurre » 31 Aug 2019, 18:07

This is very big breaking news and the Amhara fanos scored a multifaceted victory and undeclared recognition by the United Nations Arms Control as a real partner in fighting arms smuggling and terrorism.That puts them in the crosshairs of state arms dealers,smugglers and terrorists.
The Amhara people were in danger for the last 30 years and they are more in danger now by the combined forces of woyane and by Abiye led opdo/olf. General Asaminew Tsige was right
to say that the Amharas are in real danger and he paid the ultimate price.The Ethiopian people minus all sorts of tribal extremists must stand with Amharas if they want to have any semblance of remaining Ethiopia.

Revelations
Senior Member+
Posts: 33738
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [ሰበር መረጃ] ወደ ሱዳን የተሸጋገርው ሕገ ወጥ ወታደራዊ ትጥቅ በተ.መ.ድ. ሱዳን ላይ ተይዞ ወደ ኢትዮጲያ እየተመለሰ ነው

Post by Revelations » 01 Sep 2019, 15:23

ከመተማ ፋኖወች የወጣ መግለጫ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።..
ነሃሴ 26.12.2011 መተማ

የጥቂት ጀኔራሎችን: ወንጀል በመተማ: ፋኖ: ላይ ማላከክ አይቻልም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።


በቀን 12.12.2011..ንብረትነቱ ሜቴክ የኔ ነው ያለው 5 ጭነት ሙሉ የክላሽ፣የመትረየስ፣የኤም ፎርቲ:የስታር ሽጉጥ፡በደረሰን መረጃ መሰረት ከ12 እስከ 17.12.2011 በመተማ ዮሃንስ ህዝብ ወጣት ፋኖወች በቁጥጥር ስር ውሎ ጀኔራል ሙሃሙድ ሃምዛ ከሜቴክ መተማ መጥቶ:የተጫነው ኬሚካል ነው ጥይት አይደለም ሲል ቢያስተባብልም:በግዳጅ ባደረግነው ፍተሻ 5 መኪና ጥይት ሁኖ አግኝተነዋል።

ነገር ግን መከላከያ ሃይል ተጠቅሞ ሽኸዲ 8 መኪኖ ኦራል ሙሉ ወታደር፣ኮኪት 5 መኪና ሙሉ ወተደር፣መተማ 10 መኪኖ ኦራል ሙሉ ወተደር ህዝብን ለመጨፍጨፍ ከተማው ሲወረር:ቅዳሜ በ17.12.2011:ፋኖ እና ወጣቱ የሃገር ሽማግሌወች ባደረግነው በሳል ውይይት ደም መፋሰስን በማስቀረት ወደሱዳን እንዲያልፍ ፈቅደን አሳልፈነዋል።

በውጭ ሃገር ያሉ የአማራ ሙሁራን መረጃውን ለተባበሩት መንግስታት የደንበግ ጦር መሳሪያ ተቆጣጣሪ መረጃውን በማቀበላቸው በ19.12.2011 ገድልሪፍ ላይ በተባበሩት መንግስትልት የጦር መሳሪያ ተቆጣጣሪ እና በሱዳን ደህንነቶች በቁጥጥር ስር ውሎ የሱዳን መንግስትም ከኢትዮጵያ መንግስ እንዳልገዛ በማሳወቁ 5 መኪና ሙሉ ጥይት እንዲመለስ ተደርጎ ትናንት በ25.12.201 ገላባት መተማ ደንበር ተመልሶ ገብቷል።

ነገር ግን ወደሱዳን የገባው ሙሉ 5 መናን ጭነት ምክኒያቱ ባልታወቀ መንገድ 3 መኪና ጭነት ተዘርፎ ተመልሶ አሁን በዚህ ስሃት ገላባት ይገኛል።

ነገር ግን ዝርፊያ እና ስርቆታቸውን በጭቁኑ የመተማ ህዝብ ላይ ለማላከክ የፈለጉ ወንጀለኛ ባለስልጣናት:መኪናወቹ ጭነውት የመጡ ሌላ የጦር መሳሪያ ነው በማለት ለህዝቡ እያስወሩ ወጣቱ ዳግም ለፍተሻ እንዲያስቆማቸው ቅስቀሳ እየደረጉ ነው።

የቅስቀሳው አላማ
።።።።።።።።።።።።።።።

1..እኛ ፋኖወች ትናንት ገላባት የገባውን 5 መኪና በራሳችን ገብተን ኬንዳውን ገልበን አይተነዋል:የተቀየረ የጦር መሳያይ የለም ቅዳሜ በ17 የተሻገረው ጥይት ነው የተመለሰው

2..5 መኪና ጥይት ውሳን ውስጥ ከግማሽ በላይ ተዘርፈዋል

በመሆኑም ግርግር አስነስተው የመተማ ህዝብ እና ፋኖ ዘረፈው ለማባብል ቦዘኔ ወጣቶችን አንዳንድ የአዴፓ እና የመከላከያ ደህንነቶች በአካል:በስልክ በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ።

ይህ የተዘረፈ ንብረት ግርግር አስነስቶ በመተማ ህዝብ እና ፋኖ ላይ ማላከክ በፍጽም የማይቻል ነገር መሆኑን እናሳውቃለን
እንዳሰቡት ግርግር ካስነሱ ራሳችን የመከላከል ሙሉ መብታችን እንጠቀማለን

ከዚህ ውጭ 5ቱ የተዘረፈው ጥይት ሙሉ መኪና የመተማ ፋኖ ዳግም የመፈተሽ ፍላጎትም አላማም የለንም።

ግርግር ከተፈጠረ ሆን ተብሎ ፋኖወችን እና ተቆርቋሪ አማራወችን ለመግደል:ለማሰር የጠጥመደ ወጥመድ መሆኑን ስለተረዳን:ህዝባችንም እንዲረዳልን እንፈልጋለን።

"አማራነት ጥበብ ነው..ለጠላት ወጥመድ እጅ አንሰጥም""


ሌባ ጀኔራሎች እና አሽከሮቻቸው እጃቸውን ከመተማ ህዝብ እና ፋኖ ላይ እንዲያነሱ እናስጠነቅቃለን...ይህ ካልሆነ በሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ጠጥያቂው የስርአቱ ካድሬወች እና ጀኔራሎቻቸው ናቸው።

ፋኖ አርበኛ መተማ

ነሃሴ 26.12.2011 መተማ ዮሃንስ

Post Reply