Please wait, video is loading...
-
- Senior Member+
- Posts: 33975
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
- Senior Member+
- Posts: 33975
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: ከየኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)/ Ethiopian Democratic Party (EDP) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የፓርቲው 7ኛ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ከኢዴፓ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የፓርቲው 7ኛ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ፓርቲያችን ኢዴፓ ከጥቅምት 2009 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ምክንያት ከፍተኛ የህልውና ፈተና ላይ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ፓርቲያችን ቀደም ሲል በምርጫ ቦርድ በኩል እየተፈፀመበት ስለነበረው የአፍራሽነት ድርጊት ቀደም ሲል ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ ከአንድ ዓመት ወዲህ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ችግሩ ያለአግባብ ሳይፈታ በመቀጠሉ ፓርቲያችን ኢዴፓ ከአገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ያለአግባብ ተገልሎ ቆይቷል፡፡ ስለ ለውጥ እና የፖለቲካ ምህዳር መስፋት በሰፊው እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት በሰላማዊ ስልቱና ምክንያታዊ አስተሳሰቡ የሚታወቀው ኢዴፓ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለዚህን ያህል ረዥም ጊዜ ተገልሎ እንዲቆይ መደረጉ ግራ አጋቢ እንቆቅልሽ ቢሆንም ሰኔ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ከምርጫ ቦርድ በተፃፈ ደብዳቤ መሰረት የፖለቲካ ትግሉን ለመቀጠል የሚያስችል መፍትሄ አግኝቷል፡፡ መፍትሄው እኛ ልንረዳው ባልቻልን ምክንያት ያለአግባብ ለረዥም ጊዜ የዘገየ ቢሆንም ይህ መፍትሄ እንዲገኝ ክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ላደረጉልን ትብብር በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ በአጠቃላይም በዚህ የህልውና ፈታና ውስጥ በነርንበት የሶስት ዓመት ግዜ ከጎናችን ሳትለዩ ሁለንተናዊ ድጋፍ ላደረጋችሁልን የኢዴፓ አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት ምንም ዓይነት እገዳ እንደሌለበት እና ስራውን መቀጠል እንደሚችል በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ከተገለፀለት በኋላ ልዩና አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
- በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከፓርቲው መልቀቂያ ሳይወስዱ የሌላ ፓርቲ አባል መሆናቸው በታወቀ የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምትክ የማሟያ ምርጫ አካሂዷል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ አዳነ ታደሰን የፓርቲው ፕሬዝደንት፣ ወ/ሪት ፅጌ ጥበቡን ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ መርጦ ይህንኑ ውሳኔውን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል፡፡
- ፓርቲው በአለፉት ሶስት ዓመታት ከገጠመው የህልውና ፈተና በፍጥነት አገግሞ በአገሪቱ ፖለቲካ ተገቢ ሚና መጫወት እንዲችል በጥቂት ወራት ውስጥ 7ኛው የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ወስኗል፡፡ ይህንን ጉባዔ በፍጥነትና በጥራት ማዘጋጀት እንዲቻልም አቶ ልደቱ አያሌውን፣ አቶ ሄኖክ ሄዴቶን፣ አቶ ተስፋዬ መንበሩን፣ አቶ ግዛቸው አንማውንና አቶ አንድአርጋቸው አንዷለምን በጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ አባልነት መርጧል፡፡
2- ከብሄራዊ ምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ከተወሰኑት ውሳኔዎች ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
2.1.- ከኢዴፓ አፈንግጠው የወጡ አራት ግለሰቦች በምርጫ ቦርድ ፍፁም ህገ-ወጥ የሆነ ትብብር የፓርቲውን ፅህፈት ቤቶች፣ በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ፣ መዛግብት እና ማህተም ያለ አግባብ በህገ-ወጥ መንገድ እንዲረከቡ መደረጉን ቀደም ሲል መግለፃችን ይታወሳል፡፡ እነዚህ አራት ግለሰቦች ኢዴፓ ከግንቦት 7 ጋር እንዲዋሃድ የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባዔ ተሰብስቦ እንደወሰነ አድርገው የሃሰት መረጃ በማቅረብ ከላይ የዘረዘርናቸውን የፓርቲውን ንብረቶች በፓርቲዎች ውህደት ሳይሆን በግለሰቦች ስብስብ ለተቋቋመው ኢዜማ አስረክበዋቸዋል፡፡ ኢዜማም ያለምንም ህጋዊ መሰረት እነዚህን የኢዴፓ ንብረቶች እየተጠቀመባቸው ይገኛል፡፡ በዚህ ምክንያት ፓርቲያችን የዕለት ተዕለት ስራውን በአግባቡ ለማከናወን ስለተቸገረ በኢዜማ ላይ ክስ መስርቶ ንብረቶቹን ለማስመለስ ወስኗል፡፡ ነገር ግን ኢዜማ በእርግጥም እንደስሙ ለህግና ለፍትህ የቆመ ፓርቲ ከሆነ፣ አራቱ ግለሰቦች የፈፀሙት ድርጊት የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ተገንዝቦ ንብረቶቹን ለኢዴፓ እንዲያስረክብ አስቀድሞ ጥያቄ እንዲቀርብለት ተወስኗል፡፡
2.2- ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት በመመርመር አጠቃላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ሞክሯል፡፡ ይኸውም- ከኢህአዴግ የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴና ከክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የለውጥ ስሜትና ተነሳሽነት በአገራችን ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም በሂደት ግን የለውጥ ዓመራሩ እየሰራቸው ባሉ ስህተቶች እና ሳይሰራቸው በቀሩ መሰረታዊ ጉዳዮች ምክንያት የለውጥ ሂደቱ በከፍተኛ ፍጥነት የመክሸፍ አደጋ ውስጥ እየገባ መምጣቱን ተገንዝቧል፡፡ በአገራችን በተፈጠረው ከፍተኛ የዓመራር ድክመት፣ በፅንፈኝነትና በተካረረ የብሄር ፖለቲካ ምክንያት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሆኑ ስራ አስፈፃሚው ተገንዝቧል፡፡ አገርንና ህዝብን ከዚህ አደጋ ለመታደግ እንዲቻል ኢዴፓ ለህዝብ እኩልነትና ለአገር አንድነት የሚያደርገውን ትግል ከመቼውም ግዜ በላይ አጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ወቅት ላይ መሆኑን ተገንዝቦ በ7ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔው በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክሮ የሚወጣበትን ስራ በትጋት ለማከናወን ወስኗል፡፡
2.3- ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መጭውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ባደረገው ግምገማ አገሪቱ ውስጥ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ባለመኖሩ፣ የአገሪቱ መንግስት በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ህግና ስርዓትን በብቃት ለማስከበር ባለመቻሉ፣ የለውጥ ሂደቱን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉና ከመጭው ምርጫ በፊት መከናወን የሚገባቸው ከብሄራዊ መግባባት ጋር የተያያዙ በርካታ ስራዎች በብቃት ስላልተሰሩ፣ ለገባንበት ፖለቲካዊ ቀውስ መሰረታዊ ምክንያት የሆኑ መዋቅራዊ ችግሮች ( ማለትም ህገ-መንግስቱና የአገሪቱ አስተዳደራዊ አከላለል) መዋቅራዊ መፍትሄ ገና ስላላገኙ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገሪቱ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ በሚስችል ዝግጁነት ላይ ስላልሆነ ምርጫው እነዚህን ተግባራት በአግባቡ ለማከናወን ለሚያስችል ግዜ መራዘም እንዳለበት አምኖበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምርጫው በህግ በተቀመጠው ጊዜ መካሄድ አለበት በማለት ግፊት እያደረጉ ያሉ ጥቂት የፖለቲካ ሃይሎች ይህንን ለማድረግ ያስገደዳቸው ምክንያት የህግ መከበር ተቆርቋሪነት ሳይሆን የአንድነት ሃይሉ በተዳከመበት በዚህ ወቅት አዲስ የትብብር ግንባር በመፍጠር ምርጫን አሸንፈው ለስልጣን የሚበቁበት የተሻለ እድል እንደሚኖር ስለገመቱ እንደሆነ ስራ አስፈፃሚው ተገንዝቧል፡፡
በዚህ የአገር ህልውና እጅግ አሳሳቢ አደጋ ውስጥ በገባበት ሁኔታ የአገርን ሳይሆን የቡድንን የስልጣን ጥቅም በማስቀደም አገርን ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ ሊያስገባ የሚችል ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት ማድረግ ሃላፊነት ከሚሰማው ሃይል የማይጠበቅ እና በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው አመለካከት ነው፡፡ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አገራዊ ምርጫ በዚህ ወቅት ማካሄድ ሊያስከትል የሚችለውን አገራዊ አደጋ ተገንዝቦ በጉዳዩ ላይ ከወዲሁ ሊወያይ እና መፍትሄ ሊያስቀምጥ ይገባል፡፡ በእኛ እምነት ከምርጫው በፊት ሊከናወኑና የለውጥ ሂደቱን በዘላቂነት ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በዝርዝር ታውቀው፣ ተግባራቱም ተገቢ የትግበራ ቅደም-ተከተል ተቀምጦላቸው፣ ሊያስፈፅማቸው የሚችል አገራዊ የለውጥ ኮሚሽን ተቋቁሞ የለውጥ ሂደቱ በአዲስ የለውጥ ፍኖተ-ካርታ እንዲመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የለውጥ ሂደቱ አሁን በተያዘው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ግን ለውጡ ከክሽፈት የሚድንበት ዕድል ይኖራል ብለን ለማመን እንቸገራለን፡፡ ሆኖም እነዚህ አገራዊ ሃላፊነት የማይሰማቸው የኮንፌዴሬሽን ሃይሎች በሆነ ምክንያት አሸናፊ ሆነው ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ ግን ኢዴፓ የሁልግዜም የተሳትፎ መርሁን መሰረት በማድረግ በምርጫው አቅሙና ሁኔታው በፈቀደው መጠን ተሳታፊ ይሆናል፡፡ በአለፉት ዓመታት በገጠመው የህልውና ፈተና ምክንያት ኢዴፓ ምንም ዓይነት ድርጅታዊ ስራ ሳይሰራ በመቆየቱና ለመጭው ምርጫ የቀረው ጊዜም በጣም አጭር በመሆኑ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በመላ አገሪቱ በቂ የምርጫ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደማይችል ይገነዘባል፡፡ ስለሆነም በመጭው ምርጫ ዋናው ትኩረቱን አዲስ አበባ ከተማ ላይ በማድረግ በ1997 ዓ.ም እንዳደረገው ሁሉ የአዲስ አበባ ምክር ቤትን በድጋሜ በምርጫ አሸንፎ ለመረከብ የሚያስችለውን ዝግጅት ለማድረግ ወስኗል፡፡ ይህንን ዓላማውንም በአዲስ አበባ ህዝብ ድጋፍና ትብብር በቀላሉ ዕውን ማድረግ እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡
3- የኢዴፓ 7ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴም የራሱን የመጀመሪያ ስብሰባ በማካሄድ የሚከተለውን አቋም ወስዷል፡፡ ይህ 7ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ፓርቲው በከፍተኛ ሁኔታ በተዳከመበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ልዪ ትኩረት ሊሰጠውና በቂ ዝግጅት ሊደረግበት የሚገባ ጉባዔ እንደሆነ አምኖበታል፡፡ ፓርቲው በዚህ ጉባዔ የፖለቲካ ፕሮግራሙንና የመተዳደሪያ ደንቡን እንደገና መፈተሽና ማሻሻል ስለሚገባው ከመጭው መስከረም ወር ጀምሮ የማሻሻያ ሃሳብ ግብዓት የሚገኝባቸው የውስጠ ፓርቲ የውይይት መድረኮች በተከታታይ አካሂዶ፣ ጠቃሚ ምክረ ሃሳብ የሚያገኝባቸውን ህዝባዊ የውይይት መድረኮች በተለያዪ የአገሪቱ ከተሞች አካሂዶ፣ በተጨማሪም ፓርቲው ህብረ-ብሔራዊ የሆነ ጠንካራ ዓመራር እንዲኖረው የሚያስችሉ በቂ ዝግጅቶችን ካደረገ በኋላ በጥቂት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔውን ለመጥራት ወስኗል፡፡
በመጨረሻም- በአሁኑ ወቅት በአገራችን የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ በቂ ውክልናና ተቆርቋሪ ያጣው ኢትዮጵያዊ ማንነትና ምክንያታዊ የፖለቲካ አመለካከት ከግዜያዊ የመደፈቅ አደጋ ወጥቶ ጥቅሙንና ፍላጎቱን በዘላቂነት ወደ ማስጠበቅ ደረጃ እንዲሸጋገር የምትፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሁለንተናዊ ድጋፋችሁ እንዳይለየን በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የፓርቲው 7ኛ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ
ነሐሴ 15 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ