Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: [VOA] "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

Post by kibramlak » 20 Aug 2019, 13:37

And Jawar could be the IIS representative in Ethiopia. One can't write off this possibility.


Revelations
Senior Member+
Posts: 33735
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [VOA] "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

Post by Revelations » 20 Aug 2019, 16:00

"እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ



ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገልጿል። ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልመላ የማካሄድ ዓላማ እንዳለው ያመለክታል ተብሏል።
ዋሺንግተን ዲሲ —

ይህ ማስታወቅያ ባለፈው ወር በሦስት ደቂቃ ቪድዮ መልክ የተለቀቀው በፅንፈኛው ቡድን ደጋፊ ድረ-ገፆች ላይ ሲሆን ኦፊሴላዊው እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ሚድያ ደግፎታል። ቪድዮው የአማርኛ ቃላትን ተጠቅሟል፣ ተጨማሪ ጽሑፎችን በአማርኛ እንደሚያወጣም ተናግሯል ተብሏል።

ማት በረየደን የተባሉ ኬንያ ባለው የሳሃን ጥናትና ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታን ተጠቅሞ ሙስሊም ማኅበረሰብን የመስበክ ዓላማ አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም ተንታኙ ጽንፈኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድል እንዳለው ይታየዋል የሚል አመለካከት እንዳላቸው ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙም ባይሳካለትም አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘትና እንቅስቃሴውን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ይላሉ ብራይደን።[

https://amharic.voanews.com/a/under-pre ... .html/size]


Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: [UPDATE- VOA AUDIO] "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

Post by Meleket » 22 Aug 2019, 08:39

መሃረሜን ያያችሁ፣ . . . !” ተተወሰኑ ዓመታት በፊት “አይ ኤስ እስልምናን ይወክላልን?” የሚል ጥሁፍ አንድ ‘ጎነጠ’ በተባለ ሰው cyberethiopia.com ላይ የተጣፈ ጥሁፍ ገርመም አድርገን ነበር፣ ዳግም ልናነበው ብንፈትሽ ልናገኘው አልቻልንም። እንዲያዉ ለውይይት ያህል፣ ለመሆኑ ግን አይ ኤስ እስልምናን ይወክላልን? ምን ትላላችሁ! ‘ጎነጠ’ ሃሳቡን ለማስረገጥና ለማሳመን በርካታ ነገሮችን ሊተነትን ሞክሮ እንደነበር እናስታውሳለን! ጥሁፉ ለመማማሪያነት፣ ለመወያያነትና ለመተራረሚያነት ድንቅ ነበር! :mrgreen:

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: [UPDATE- VOA AUDIO] "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

Post by Ethoash » 22 Aug 2019, 15:56

ጎሳ ከጎሳ ጋራ ማጣላት ጨርሰህ ወድ ሀይማኖት ዞርክ።

ጎሳ ና ጎሳ ቢጣላ ሁለት የተለያዩ ጎሶች ናቸው ። ግን ሰው በሀይማኖት ከተታላ አንድ ጎሶች ናቸው የሚገዳደሉት ። ይሄንን አስበህበታል ከግብፅ የምግብ ሲቆነጠርልህ።

ነደደ እሳትማ ለመጀመር አንድ ክብሪት ትበቃለች ። ይህንን ነደደ እሳት ጥፋ ስትለው የሚጠፋ ከመስለህ የጎረቤት ህን ቤት አቃጥሎ። ዋ ብያለሁ አልነገረኝም እንዳትል አላውቕሁም እንዳትል።

ስማ ይሄንን መልዕክት የለጠፍኩት ያንተን መርዝ ለሚያነቡት ። መርዙን ቢያመክን ብዬ ነው።

እስላሞችን ይህንን ያህል የምትጠላ ከሆን ልክ እንደህንድና ፓኪስታን መሬት ተከፋፍለን እንሽኛኝ ። አለበለዚያ ተከባብረን እንኑር።

በዚህች ድሃ ሐገር የሀይማኖት በሽታ ስትመኝላት አንተን ይዞ ይሄድ። ጦሱ ለአንተም ይተረፍ። ምን አይነት መርዛም ነህ። ትንሽ አስቀጥጥህም ሁሉም እስላም አይሲስ ስትል። ትንሽ እንኳን አይስቀጠጥህም። አሁን በምን እዳችን ነው ከአይሲስ ጋራ አፍ የምንካፈት ። ለምንስ ጠላት እናበዛለን። አረ ጎመን በጤና ፬ ሚልዬን ሕዝብ ተርቦብናል አረ በፈጠረህ አምላክ ። ችግር ችግር እየጎለጎልክ ማውጣት ምን ይሉታል ። እንዴት ነው የስው ደም የሚያስተኛህ። አረ ታክሲም ኡበርም ፓርኪንግም ስረተህ ንፁህ ገንዘብ አግኝ ። የግብፅ ገንዘብ በደም የጠጨማለቅ ነው። ባንተ ባይደርስ በልጆች ህ ይደርሳል ። አረ ተው።

ሺህ አመት ተካባብረው የኖሩትን አይማኖቶች አታጋጭ ። አለም የሚቀናብን በዚሁ ጥራታችን ነው። ሌላስ ምን አለንና ነው ሰው የሚቀናብን። አረ እስራሄሎች ይህንን ሚስጥራችንን ባወቁት። ድሬ ስርግ ሲደገስ ሁለት ድንኳን ይጣልና አንዱ የስላም ሌለኛው የክርስታን ተብሎ ሁለቱም አይማኖቶች በአንድነት ስርግን ያከብራሉ። ይህ ታድያ በሚልዬን አይገዛም።

መሲጉድ መሽታ ቤት እና ቤተክርስታን በአንድ ተርታ የሚገኝበት አገር ኢትዬዽያ ብቻ ናት አረ ተው ይህንን እንጠብቀው።

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: [UPDATE- VOA AUDIO] "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

Post by Meleket » 24 Aug 2019, 04:05

""እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ’ የሚል ዜናን እንደሰማን ይህቺ በዚሁ አካል ወይም ቡድን ዙርያ የምታጠነጥን ጽሑፍን አስታወስን፣ “ፈልጌ አስፈልጌ” ነበር ያለው መረዋ ድምጣዊው! በሉ እንግዲህ የጠፋችዉን ጥሁፍ ፈልገን አፈላልገን አግኝተናታል። ጠሐፊው ‘ጎነጠ’ በcyberethiopia.com በተጠቀሰው ዕለት ማለትም ከ2 ዓመታት በፊት የጣፈው ጥሑፍ ነው። የጥሁፍ ይዘት ጠሐፊውን ይመለከታል። እኛ እዚህ ለግንዛቤና ለውይይት ለመማማርና ለመተራረም አምጥተነዋል። በሚሊዮንና በቢሊዮን የሚቆጠሩት ቅኑና ሰላማዉያን ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ትክክለኛውን እይታቸውን እንዲያካፍሉንና ግንዛቤያችንን እንድናሰፋ ሊረዳን ይችላል በሚል ሃሳብ የጽሑፉን ሙሉ ይዘታ እዚህ በመረጃ ዱለነዋል! ሰላም ለሁላችን! መልካም ንባብ።

አይ ኤስ እስልምናን ይወክላልን?
by ጎነጠ » Mon May 01, 2017 2:38 pm
አይ ኤስ እስልምናን ይወክላልን?

የኢራቅና የሦርያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) ወይም እስላማዊ መንግሥት (IS)፣ በአረብኛ ደግሞ ዳዕሽ የተሰኘው የሽብርተኞች ቡድን እስልምናን እንደማይወክልና ድርጊቱም ደግሞ እስላማዊ እንዳልሆነ፣ እንዲያውም እስልምናን የሚፃረር እንደሆነ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ነገር ግን የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ የሚገኘው ይህ የነፍሰ ገዳዮች ስብስብ ተግባር እውን እስልምናን የሚፃረር ነውን? እስላማዊ ጽሑፎችስ እንዲህ ዓይነቱን ተግባር ይኮንናሉ ወይንስ ያበረታታሉ? አይ ኤስ እስላማዊ ከሆነ ለምንድነው ሙስሊሞችም ጭምር ሰለባዎቹ የሆኑት? ብዙ ሙስሊሞችስ ለምን ይሆን ድርጊቱን በመኮነን እስላማዊ አለመሆኑን የሚገልፁት? አይ ኤስ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካና የእስራኤል የስለላ ድርጅቶች ሴራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ኤድዋርድ ስኖውደን ይፋ ማድረጉን በተመለከተ የተናፈሰው ወሬ እውነት ነውን? የፖለቲካ መሪዎች ለምንድነው የእስልምናን ሰላማዊነት የሚሰብኩት? በዚህ ጽሑፍ ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሾችን እንሰጣለን፡፡

የአይ ኤስ አነሳስ

አይ ኤስ ወይም ዳዕሽ የተስፋፋው በሦርያ የተፈጠረው ግጭት እና በኢራቅ ያለው ደካማ የመንግሥት ይዞታ በፈጠረለት ምቹ ሁኔታ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ከዚያ ቀደም ብለው በነበሩት ዓመታት ይህ ድርጅት የአልቃኢዳ ክንፍ ሆኖ በአካባቢው ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ አቡ ሙሳብ አል ዛርቃዊ የተሰኘው መሪው በአሜሪካ የአየር ጥቃት በ2006 እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ የንፁሃን ወገኖችን አንገት እየቀላ ቪድዮዎችን ያሰራጭ ነበር፡፡ ይህ ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት ከኢራቅ ወረራ በኋላ የተቀዛቀዘ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ አይ ኤስ በሚል ሥም እንደገና ተመልሶ ከመጣ በኋላ መሰል ቪድዮዎችን በተሻለ ጥራትና በብዛት እየቀረፀ መልቀቁን ተያይዟል፡፡ ከሦርያና ከኢራቅ ባሻገርም በብዙ ሃገራት ንፁሃን ዜጎች ላይ የግፍ ክንዱን አሳርፏል፡፡ የቅርብ ጊዜ ሰለባዎቹ ደግሞ በሊብያ የሚገኙ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሆነዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በሃገሪቱ ላይ ከባድ የኀዘን ድባበድ ሰፍኗል፡፡ የአይ ኤስ መኖር ለዓለም ሕዝብ ይፋ የሆነው ከሦርያ ወደ ኢራቅ በመግባት በአስገራሚ ፍጥነት የኢራቅን ሰራዊት እየበታተነ ብዙ አካባቢዎችን መቆጣጠር በጀመረበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህም ውስጥ ለውስጥ ለረጅም ጊዜያት ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበርና የጥንካሬ ደረጃውን ካረጋገጠ በኋላ በራሱ ፈቃድ ሀልዎቱን ይፋ ማድረጉን ያመለክታል፡፡ በአካባቢው ሽብርተኛ ድርጅቶች እንደሚንቀሳቀሱ ቢታወቅም ነገር ግን ይህን ያህል ጥንካሬ፣ አደረጃጀትና ትጥቅ ያለው ሽብርተኛ ድርጅት መኖሩ ለምዕራባውያኑ የስለላ ተቋማት እንኳ ሳይቀር ድንገተኛና አስደንጋጭ እንደነበር መረዳት አያዳግትም፡፡ ይህም የቡድኑ አደገኛነት ምን ያህል እንደሆነ አመላካች ነው፡፡

አይ ኤስ እስላማዊ ነውን?

ይህ መልስ የሚሻ የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ በአጭር ቃል አይ ኤስ እስላማዊ ነው፡፡ አባላቱ በእስልምና ያደጉና ብዙዎቹ እስልምናን በሚገባ ያጠኑ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ አቡበከር አል-ባግዳዲ (ኢብራሂም አወድ ኢብራሂም አል በድሪ) የተሰኘው መሪያቸው በእስላማዊ ጥናቶች ከባግዳድ ዩኒቨርሲቲ ፒ.ኤች.ዲ. የተቀበለ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያኑን ጭፍጨፋ በሚያሳየው ቪድዮ ውስጥ ሲናገር የሚታየው የሰዑዲ አረብያ ዜግነት እንዳለው የሚነገረው አነስ አል-ነሽዋን (የሚስጥር ሥሙ አቡ ማሊክ አል-ተሚሚ) ደግሞ በሸሪኣ ህግ የማስተርስ ድግሪ ያለው ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እስልምናን የማያውቁ፣ በስሜት የሚነዱ የመንደር ዱርዬዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ እስልምናን ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለእምነታቸው ሲሉ የተሻለውን ኑሯቸውን በመተው ጦርነት ውስጥ የገቡ ሙስሊም ሊቃውንት ናቸው፡፡ ያልተማሩና በአንድ ሰው ስብከት በቀላሉ የሚወሰዱ መሃይማንም አይደሉም፡፡ ብዙዎቹ በምዕራብ ሃገራት ውስጥ ኑሯቸውን የመሰረቱ፣ ፊደል የቆጠሩና ጥሩ ገቢ የነበራቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የአይ ኤስ ዋና አራጅ የሆነው መሐመድ ኤምዋዚ (የቅርብ ጓደኛው ለሽብር ተግባር ሲንቀሳቀስ ተይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛል) የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያና የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ሰዎች እስልምናን የማያውቁ፣ ያልተማሩ ተራ ወሮበሎች አድርጎ መፈረጅ እውነታን የሚፃረር ነው፡፡

አይ ኤስ የሚጠቀሟቸው ቃላት (Vocabulary) እስላማዊ ናቸው፡፡ ደቢቅ የሚለው የመጽሔታቸው ሥያሜ በሦርያ ውስጥ ከሚገኝ የቦታ ሥም የተወሰደ ሲሆን በእስላማዊ ትንቢቶች መሰረት በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች መካከል የመጨረሻው ጦርነት ይደረግበታል ተብሎ የተነገረ ቦታ ነው፡፡ አል-ፉርቃን የሚለው የቪድዮ ፕሮዳክሽን ሥያሜ “መመርያ” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን የቁርኣን ሌላኛው መጠርያ ነው፡፡ ቃሉም በቁርኣን ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት ተደጋግሞ ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያውያን ስደተኞቹን ጨምሮ የእርድ ቪድዮዎችን እየቀረፀ የሚያሰራጨው ይኸው የአይ ኤስ የሚድያ ክንፍ ነው፡፡ የአይ ኤስ ሥያሜ፣ የአባላቱ መጠርያዎች፣ ቅፅል ሥሞቻቸው፣ የዘመቻ ሥያሜዎቻቸው፣ ወዘተ. ሁሉ እስላማዊ ናቸው፡፡ እስላማዊ ያልሆነ ንግግር አይጠቀሙም፡፡ በእርድ ቪድዮዎቻቸው ውስጥ የሚገኙት ንግግሮች ፍፁም እስላማዊ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ጭፍጨፋ በሚያሳየው የእርድ ቪድዮ ውስጥ አነስ አል-ነሽዋን (አቡ ማሊክ አል-ተሚሚ) የተሰኘው አሸባሪ የሚከተለውን የዛቻ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ መልዕክቶቹ ከቁርአን የተውጣጡ ሲሆኑ አነጋገሩም እስላማዊ ቋንቋን የተላበሰ ነው፡-

“በሁሉም ቦታዎች የሚገኙትን ክርስቲያኖች ኢንሻ አላህ እስላማዊው መንግሥት እንደሚስፋፋ እንነግራቸዋለን፡፡ በምሽጎቻችሁ ውስጥ በደህና ብትቀመጡም እንኳን [እስላማዊ መንግሥት] ያገኛችኋል፡፡ የሚሰልሙ ሰዎች ሰላምን ያገኛሉ፤ የዚሚን ደረጃ የሚቀበሉ ሰዎችም በሰላም ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን የኛን መመርያ የማይቀበሉ ሰዎች ከሰይፍ ስለት በስተቀር ከኛ የሚቀበሉት ሌላ ነገር የላቸውም፡፡ ወንዶች ይገደላሉ፤ ሴቶችና ህፃናት ደግሞ ባርያዎች ይሆናሉ እንዲሁም ገንዘቦቻቸው እንደ ጦር ዘረፋ ይወረሳል፡፡ ይህ የአላህና የነቢዩ ትዕዛዝ ነው፡፡ ከፍታ የአላህ ነው፤ እንዲሁም የምዕመናን ነው፡፡ ነገር ግን አስመሳዮች አይገነዘቡም፡፡”

(ዚሚ ከአቅም በላይ የሆነን ግብር (ጂዝያ) እየከፈሉ በእስልምና አገዛዝ ሥር በውርደት የሚኖሩ ክርስቲያኖችና አይሁዶች ናቸው፡፡ ሥርኣቱ ዚማ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ሰዎቹ ደግሞ ዚሚ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህንን ነጥብ ወደ ኋላ እንመለስበታለን፡፡)

የአይ ኤስ ጥቁሩ ባንዲራ የጥንት ሙስሊሞች በጂሃድ ወቅት የሚጠቀሙት ባንዲራ ነው፡፡ በላዩ ላይም በአረብኛ ተጽፎ የምናየው ሌላ ነገር ሳይሆን ሸሃዳ (የእስልምና የእምነት አቋም) ነው፡፡ “ላ ኢላ ሀኢለላ መሐመደን ረሱልአላህ” (ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም መሐመድም መልእክተኛው ናቸው) የሚል ነው፡፡ ይህ የአንድ ሙስሊም የመጀመርያና የመጨረሻ ቃሉ ነው፡፡

አይ ኤስ አለባበሳቸው፣ አመጋገባቸው፣ የጋብቻ ሁኔታቸው፣ ጢም አቆራረጣቸው፣ ሙስሊም ካልሆኑት ሰዎች ጋር ያላቸው መስተጋብር፣ የማህበረሰብ አደረጃጀታቸው፣ ባጠቃላይ የኑሮ ዘይቤያቸው ሁሉ ፍፁም እስላማዊ ነው፡፡ ከእስልምና ጋር የሚጣረስ፣ በመሐመድ ሱና (ምሳሌነት) ያልተረጋገጠ፣ በቁርአንና በሐዲሳት ያልፀደቀ ምንም ነገር የላቸውም፡፡

ለሚያደርጉት ለእያንዳንዱ ነገር ቁርኣንና ሐዲሳትን ጨምሮ እስላማዊ ምንጮችን ይጠቅሳሉ፡፡ የቁርኣንን አተረጓጎም በተመለከተ የሱኒ ነባር ሐታቶችን (Classical Sunni Commentators) ይጠቀማሉ፡፡ ምናልባት እስላማዊ ቃላትን መጠቀማቸውና እስላማዊ የኑሮ ዘይቤዎችን መከተላቸው በራሱ ትክክለኛ ሙስሊሞች ሊያደርጋቸው አይችልም የሚል ሐሳብ ሊነሳ ይችላል፡፡ ይህ አባባል የተወሰነ እውነታነት አለው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ድርጊቶች በእስላማዊ የመመርያ መጻሕፍት መደገፋቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ትክክለኛ ሙስሊሞች ናቸው ብሎ መናገር አዳጋች ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች የሚፈፅሟቸው ነገሮች ሁሉ ፍፁም እስላማዊ መሆናቸውን ቁርኣንና ሌሎች እስላማዊ ምንጮችን ያነበበ ሰው ሁሉ የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡ ከእስልምና የወጣ ምንም ነገር አላደረጉም፡፡ ነገር ግን ችግሩ ብዙ ሰዎች ስለ እስልምና ያላቸው መረጃ በመገናኛ ብዙኃን በሚነገሩ ፖለቲካዊ ትክክለኝነትን (Political Correctness) በተከተሉ ንግግሮችና ሙስሊም አቃቤ እምነታውያን በሚናገሯቸው የተቀመሙ ንግግሮች ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ብዙ ድምፆች ውዥንብሮችን በሚፈጥሩበት ዘመን ዋናዎቹን ምንጮችና የእምነቱን መስራች የመሐመድን ሕይወት ካላጠናን በስተቀር የእስልምናን ትክክለኛ ገፅታ ማወቅ ቀላል አይሆንም፡፡ የሚፈፀሙ የሽብር ጥቃቶችንም የእምነቱን ሽፋን በመጠቀም የተወሰኑ የግል ጥቅም አሳዳጆች ወይንም እምነቱን በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ሰዎች እንደሚፈፅሙት የውንብድና ተግባር ልንቆጥር እንችላለን፡፡ ይብዛም ይነስም እንዲህ ዓይነት ሰዎች በሁሉም እምነቶች ውስጥ እንደሚገኙ ይታመናልና፡፡

ዛሬ አንድ ክርስቲያን ተነስቶ በእምነቱ ሥም የሽብር ተግባር ቢፈፅም ድርጊቱ ክርስቲያናዊ አለመሆኑን መጽሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ ማስረዳት እንችላለን፡፡ ለድርጊቱ ማፅደቅያ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች ቢጠቅስ ከአውድ ውጪ እንደጠቀሰና በተሳሳተ መንገድ እንደተረጎመ በማስረዳት ልናርመው እንችላለን፡፡ የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ የሚል የማያወላዳ ትዕዛዝ ሰጥቶናልና፡- “ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።” ማቴዎስ 5፡43-48

አንድ ክርስቲያን ከዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ በማፈንገጥ የሽብር ድርጊቶችን ቢፈፅም በክርስቲያኖች ዘንድ በፅኑ ይወገዛል፡፡ ክርስቲያን ተብሎም ሊጠራ አይችልም፡፡ በእስልምና ግን እንዲህ አይደለም፡፡ እውነተኛና ትክክለኛ የመሐመድ እስልምና አይ ኤስን በመሳሰሉት የጥላቻ ቡድኖች እየተተገበረ የሚገኘው እንጂ በተከሸኑ ቃላት ተሽሞንሙኖ በሚድያዎች፣ በፖለቲከኞችና በሙስሊም አቃቤ እምነታውያን የሚሰበከው “ክርስትና የተነሳ” እስልምና አይደለም፡፡ ቁርኣንና የመሐመድን ግለ ታሪክ ቀረብ ብለን ብንመለከት መሐመድ በአይ ኤሶች “እንደተሠገወ” እና በዘመናችን “እንደተገለጠ” ማስተዋል እንችላለን፡፡ በአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ የእስልምና ታሪክ ፕሮፌሰር የነበሩትና እስልምናን በመተው ክርስትናን የተቀበሉት ማርክ ገብርኤል (በቀድሞ ሥማቸው ሙስጠፋ) የቁርኣንን አስተምህሮና የእስልምናን ታሪክ በተመለከተ የሚከተለውን ይላሉ፡-

“በቁርአን ውስጥ የተገለጠው አምላክ፣ አላህ አፍቃሪ አባት አይደለም፡፡ ሰዎችን በተሳሳተ መንገድ መምራት ይፈልጋል (ሱራ 6፡39፣ 126)፡፡ በእርሱ ወደ ተሳሳተ መንገድ የተመሩትን አይረዳቸውም (ሱራ 30፡29)፡፡ ገሃነምንም ለመሙላት ይጠቀምባቸዋል (ሱራ 32፡13)፡፡ እስልምና በሴቶች ላይ፣ ሙስሊም ባልሆኑት ላይ፣ በክርስቲያኖች ላይ እና በተለይም ደግሞ በአይሁዶች ላይ አድሎን በማድረግ የተሞላ ነው፡፡ ጥላቻ የኃይማኖቱ አካል ነው፡፡ የእኔ ልዩ የጥናት መስክ የሆነው የእስልምና ታሪክ የደም ወንዝ በመባል ብቻ ነው ሊገለፅ የሚችለው፡፡”[1]

ዛፍና ፍሬው

ሙስሊም ሽብርተኞች በዓለም ዙርያ የሚፈፅሟቸውን ፀረ ሰላም ድርጊቶች በመጥቀስ እስልምና የሰላም ሃይማኖት አለመሆኑን ስንናገር “የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች በሃይማኖታቸው ይለካሉ እንጂ ሃይማኖት በተከታዮቹ አይለካም” የሚል አባባል በተደጋጋሚ ይጠቀስልናል፡፡ ይህ አባባል ከፊል እውነትን እንጂ ሙሉ እውነትን ያዘለ አይደለም፡፡ በክርስትና ታሪክ ውስጥ እንደሆነውና ዛሬም አልፎ አልፎ እንደሚታየው አንዳንድ የእምነቱ ተከታዮች የነውጠኝነት ድርጊቶችን ቢፈፅሙ እነዚህን ሰዎች በእምነቱ መለካት ይኖርብናል እንጂ እምነቱን በነዚህ ሰዎች መለካት የለብንም፡፡ እስልምናም ቢሆን እንደ ክርስትና ዓይነት አልፎ አልፎ ብቻ የሚታዩ የነውጠኝነት ታሪኮች ቢኖሩት ኖሮ አባባሉ ይሰራል ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ አባባል ለእስልምና ለምን እንደማይሰራ ከማየታችን በፊት ክርስትናን በተመለከተ ሙስሊሞች ብዙ ጊዜ የሚጠቅሷቸውን ሁለት ጉዳዮች ግልፅ አድርገን እንለፍ፡፡

ሙስሊም ወገኖች ብዙ ጊዜ በመካከለኛው ዘመን በአውሮፓ ታሪኮች ውስጥ የተፈፀሙትን የመስቀል ጦርነቶች (ክሩሴድ) በመጥቀስ የክርስትናን ሰላማዊነት አጠያያቂ ለማድረግና ከእስልምና ጋር ለማነፃፀር ይሞክራሉ፡፡ ክሩሴዶች እንዴት ተጀመሩ የሚለውን ወደ ኋላ መለስ ብለን ብናጠና ግን ሃቁ ይገለጥልናል፡፡ ለክሩሴዶች መቀስቀስ ምክንያት የሆኑት የሙስሊም ወራሪ ኃይላት እንጂ ክርስቲያኖች አልነበሩም፡፡ ዛሬ እስልምና ተደላድሎ የተቀመጠባቸውን የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ ሃገራትን ስንመለከት የክርስቲያን ሃገራት የነበሩና በእስላም ወራሪ ኃይላት ተደምስሰው የክርስትና ታሪካቸው እንዲጠፋ የተደረገ መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ዛሬም ድረስ የሚታዩት የጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሾችና ከብዙ የግፍ ስራዎች በእግዚአብሔር ተዓምር ድነው ክርስትናቸውን ጠብቀው የሚገኙት ቅሬታዎች ምስክሮች ናቸው፡፡ ሙስሊሞች እነዚህን ሃገራት ያሰለሙት በሰይፋቸው እንጂ በመጽሐፋቸው አልነበረም፡፡ እስፔን ድረስ በመዝለቅ ጎሮሯቸው ላይ ሰይፉን ያስቀመጠውን ይህንን እስላማዊ የጂሃድ ወረራ ለመቋቋም እና ልክ እንደ ዛሬዎቹ የአይ ኤስ ወታደሮች ጨካኝ በነበሩት ጂሃዲስቶች እጅ ለወደቁት የመካከለኛው ምስራቅ ክርስቲያን ወንድሞቻቸው የድረሱልን ጥሪ ጩኸት ምላሽ ለመስጠት የነበራቸው አማራጭ ኃይልን መጠቀም እንደነበረ ስለተሰማቸው የአውሮፓ ክርስቲያኖች የጦርነት ዘመቻዎችን በማድረግ ምላሽ ሰጡ፡፡ ነገር ግን ክርስቲያኖች በዚያ የታሪክ አጋጣሚ የተፈጠረውንና በክርስትና ላይ ጥቁር ጠባሳን ጥሎ ያለፈውን ድርጊት ሲያስቡ ዛሬም ድረስ ይፀፀታሉ፡፡ የአውሮፓ ቤተ ክርስቲያንም በተደጋጋሚም ይቅርታ ጠይቃለች፡፡ ሙስሊሞች ግን አንድም ጊዜ ለይቅርታ ጥያቄው ዕውቅና ሰጥተው አያውቁም፡፡ የጦርነቱ ቀስቃሾችና አሸናፊዎች እነርሱ ሆነው ሳሉ ነገሩ ከተፈፀመ ከአያሌ ምዕተ ዓመታት በኋላም ቢሆን ያነሱታል፡፡ የክርስቲያኖች የይቅርታ ጥያቄ የመነጨው ሰይፍን መጠቀም ከክርስቶስ ትምህርት ጋር የሚጣረስ መሆኑን ከማመን እንጂ እነርሱ የፈፀሙት በደል ሙስሊሞች ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በክርስቲያኖች ላይ ከፈፀሙት በደል ጋር የሚነፃፀር ሆኖ አይደለም፡፡ ቢሆንም ግን ሰይፍ የክርስቶስ ትምህርት ባለመሆኑ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ አጋጣሚ እንደዚያ ዓይነት መንፈሳዊ ዝቅጠት ውስጥ መግባቷ በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ሌላው ሙስሊሞች ክርስትናን ወደ እስልምና ደረጃ ለማውረድ የሚጠቀሙት ምሳሌ ሂትለር በአይሁዶች ላይ የፈፀመውን ግፍ ነው፡፡ በርግጥ ሂትለር ለእኩይ ተግባሩ የቤተ ክርስቲያንን ድጋፍ ለማግኘት ጥረት አድርጓል፡፡ “ማይን ካምፍ” በሚለው መጽሐፉም ውስጥ የሚያደርገውን ሁሉ የሚያደርገው “ለጌታ” ብሎ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ሂትለር ጥንታዊውን የአርያኖች አረማዊ (Pagan) እምነት የሚከተል እንጂ ክርስቲያን ስላልነበረ ልክ እንደዘመኑ ዲፕሎማቶች በጽሑፉ ውስጥ አሳሳች ምልከታ የሚሰጡ ቃላትን በመጠቀም ራሱን ክርስቲያን ለማስመሰል ሞክሯል፡፡ የሚገርመው ነገር ግን ሂትለር ክርስትናን ለጀርመናውያን “ውድቀት” ተጠያቂ በማድረግ እስልምናንና መሐመድን እያሞካሸ የተናገረባቸው ጊዜያት መኖራቸው ነው፡፡ በአንድ ወቅት “የእስላም ህዝቦች ከፈረንሳይ ህዝብ ይልቅ ለኛ (ለናዚዎች) መቼም ቢሆን ቅርበት አላቸው” በማለት ተናግሮ ነበር፡፡[2] ጀርመኖች የክርስትናን የፍቅር መንገድ ከመከተል ይልቅ የእስልምናን የጦረኝነት መንገድ ቢከተሉ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ እንደነበርም በቁጭት ተናግሯል፡፡ ሙስሊሞች የታውርስን ጦርነት ቢያሸንፉና አውሮፓን ቢያሰልሙ ኖሮ የተሻለ እንደነበርም ተናግሯል፡፡ በሂትለር ግምት መሰረት አረቦች የአውሮፓን የአየር ፀባይ መቋቋም ስለማይችሉ ሰፊውን የእስልምና ግዛተ ዓለም የመቆጣጠር እድሉ የጀርመኖች ይሆን ነበር፡፡[3] የሂትለር “ማይን ካምፍ” በ1930 ዓ.ም. “የኔ ጂሃድ” በሚል ርዕስ ወደ አረብኛ የተተረጎመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአረቡ ዓለም ውስጥ በምርጥ ሽያጭነት 6ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሂትለር በሚስጥር እስልምናን ተቀብሎስ እንደሆን ማን ያውቃል? ሂትለር አይሁዶችን ለማጥፋት ሞክሯል፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ አንድ ቀን በአላህ እርዳታ አይሁዶችን ሁሉ እንደሚያጠፉ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ማለት የእስልምና ትንቢቶች እውነት ከሆኑ እስልምና እያንዳንዱን ሙስሊም እጩ ሂትለር አድርጓል ማለት ነው፡፡

“የአንድ ሃይመኖት ተከታዮች በሃይማኖታቸው ይለካሉ እንጂ ሃይማኖት በተከታዮቹ አይለካም” የሚለውን አባባል እየተመለከትን ነው፡፡ ይህ አባባል ክርስትና ካሳለፋቸው ውሱን የነውጠኝነት ታሪኮች አኳያ ሲታይ በሚገባ ይሰራል፡፡ ነገር ግን ከእስልምና አንፃር አይሰራም፡፡ እስኪ እንዲህ ብላችሁ አስቡ፡፡ በዓለም ዙርያ የሚገኙ 85 ከመቶ በላይ ክብርን የማስጠበቅ ግድያዎች (Honour Killings) በአንድ የሃይማኖት ቡድን አባላት የሚፈፀሙ ቢሆኑ፤ 90 ከመቶ በላይ ሰዎችን የማረድ ተግባራት እና ሰዎች ሲታረዱ የሚያሳዩ ቪድዮዎችን ሆን ብሎ ቀድቶ የማሰራጨትን መቶ ከመቶ ድርሻ የሚወስዱት የዚሁ እምነት አባላት ቢሆኑ፤ እንዲሁም የአጥፍቶ መጥፋት የቦምብ ጥቃቶች መቶ በመቶ የሚፈፀሙት በዚሁ በአንዱ ሃይማኖት ተከታዮች ሆኖ ቢገኝ የዚያን ሃይማኖት ትምህርት ሰላማዊነት ከመጠራጠር አልፈን ሰላማዊ አለመሆኑን አፋችንን ሞልተን ብንናገር ከእብለት ሊቆጠር ይገባል ትላላችሁ? ድምዳሜያችንስ ምክንያታዊ አይደለም ሊባል ይችላል? እነዚህ ሁሉ የእስልምና ገንዘቦች ናቸውና በፍፁም አይችልም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 7፡15-20 ላይ እንዲህ የሚል መርህ አስቀምጦልናል፡-

“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።”

እንግዲህ በዚህ የጌታችን መርህ መሰረት እስልምና ምንም ይበል ምን በዘመናት መካከል ካፈራቸው መራራና ገዳይ ፍሬዎቹ በመነሳት መሰረቱ ሐሰትና ፀረ-ሰላም መሆኑን መስራቹም ከእግዚአብሔር ያልተላከና ሐሰትን ያስተማረ መሆኑን መደምደም እንችላለን፡፡ የኩርንችት ዘር በብርትኳን ቅጠል ተጠቅልሎ ስለተቀበረ የብርቱኳንን ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ወደመሆን ማደግ እንደማይችል ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያት የሚያስተምሩት ትምህርትም ምንም ያህል ለጆሮ የሚጣፍጥና በጥሩ ቃላት የተቀመመ ቢሆን መልካም ፍሬን ማፍራት አይቻለውም፡፡ አይ ኤስና ሌሎች እስላማዊ የሽብር ቡድኖች ሁሉ የእስልምና ፍሬዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ የእስልምና ትምህርት ባህሪ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ሙስሊሞች፣ ይልቁኑ የዚህ “የሰላም ሃይማኖት” ኢ-ሰላማዊነት እና ፃዕረ ሞት ገፅታ በግልፅ እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት እነዚህ ቡድኖች እስላማዊ አለመሆናቸውንና እስልምናም የሰላም ሃይማኖት መሆኑን እየሰበኩ ይገኛሉ፡፡ እስልምና የሰላም ሃይማኖት መሆኑንም ለማሳየት ከቁርኣን ውስጥ የተወሰኑ ጥቅሶችን ከታሪካዊና ምንባባዊ አውዳቸው ውጪ በመጥቀስ ሊያሳምኑን ይሞክራሉ፡፡ አሳዛኙ ነገር ብዙ ሰዎች በነዚህ ከንቱ ስብከቶች ተታልለው የእስልምናን ፀረ ሰላም መሆን መጠራጠራቸው ነው፡፡ ሙስሊሞች የእስልምናን ሰላማዊነት ለማስረዳት በተደጋጋሚ የሚጠቅሷቸው ሁለት ጥቅሶች አሉ፡፡ የመጀመርያው ሱራ 2፡256 ላይ የሚገኘው ነው

“በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡”

ይህ ጥቅስ ቁርአንን የማያነበውንና የእስልምናን ታሪክና አስተምህሮ በወጉ የማያውቀውን ህዝብ ለማደናገር በእጅጉ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የቁርኣን ሐታቾች እንደሚናገሩት ይህ ጥቅስ ጊዜው አልፎበታል፡፡ እስልምና “ናሲክ” የሚባል አስተምህሮ አለው፡፡ “ናሲክ” መሻር የሚል ትርጉም ያለው የአረብኛ ቃል ሲሆን በዚህ አስተምህሮ መሰረት ሁለት እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ የቁርኣን ጥቅሶች ቢኖሩ የኋለኛው የፊተኛውን ይሽረዋል፡፡ ይህንን በተመለከተ ኢብን ከሢር የተሰኘ ትልቅ ተቀባይነት ያለው የሱኒ ሐታች የጥቅሱን ትክክለኛ ትርጉም፤ ማለትም ሰዎች እምነታቸውን እንዲቀይሩ ማስገደድ አስፈላጊ አለመሆኑን እንደሚናገር ካብራራ በኋላ እንዲህ ይላል፡- “… ነገር ግን ይህ ጥቅስ በውጊያ ጥቅሶች ተሽሯል ስለዚህ ሁሉም የዓለም ህዝቦች ወደ እስልምና እንዲመጡ ጥሪ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ማናቸውም ሰዎች ያንን ለማድረግ ፍቃደኛ የማይሆኑ ከሆነ ወይም ጂዝያን ለመክፈል እምቢ የሚሉ ከሆነ እስኪገደሉ ድረስ ውጊያ ሊደረግባቸው ይገባል…”[4]

አይ ኤስ ክርስቲያን ኢትዮጵያውኑ የተገደሉበትን ምክንያት ሲገልፅ ጂዝያን ለመክፈል ፍቃደኞች ባለመሆናቸው ይህ ፍርድ እንደተላለፈባቸው ተናግሯል፡፡ ሌሎች ብዙ ሙስሊም ሐታቾች ይህ ጥቅስ በኋለኞቹ መገለጦች መሻሩን ይገልፃሉ፡፡ ስለዚህ ጥቅሱ “ካፊሮችን” ከማደናገር የዘለለ ጥቅም የለውም፡፡

ሙስሊሞች እስልምና የሰላም ሃይማኖት መሆኑን ለማሳየት የሚጠቅሱት ሌላው ጥቅስ ሱራ 5፡32 ላይ የሚገኘው “ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው” የሚለው ነው፡፡ ነገር ግን ሙስሊሞች ይህንን ጥቅስ ከአውድ ውጪ ነው የሚጠቅሱት፡፡ ሙሉ አውዱ እንዲህ ይላል፡- “በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡ መልክተኞቻችንም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጡዋቸው፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው፡፡”

የቁርኣን ጸሐፊ ይህንን ሐሳብ የቀዳው ከአይሁድ መጻሕፍት ላይ ነው፡፡ ጥቅሱ የሚናገረው ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው ለእስራኤላውያን መሆኑን ነው፡፡ ለሙስሊሞች ደግሞ ምን ዓይነት ትዕዛዝ እንደተሰጠ ቀጣዩ አንቀፅ ይናገራል፡- “የእነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚዋጉ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ በነሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው፡፡ በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡” ሱራ 5፡35

ቀደም ሲል የተጠቀሰው በጎ ትዕዛዝ የተሰጠው ለእስራኤላውያን ሲሆን በማስከተል የተቀመጠው የጭካኔ ትዕዛዝ ደግሞ ለሙስሊሞች የተሰጠ መሆኑን እናያለን፡፡ አላህንና መልክተኛውን መዋጋት ማለት በእስላማዊ አተረጓጎም መሰረት ማንኛውንም ቁርኣንንና እስላማዊ ህግጋትን መፃረር እንዲሁም የመሐመድን ነቢይነት አለመቀበል ማለት ነው፡፡ “በምድር ላይ ማጥፋት” ደግሞ ለሙስሊም ማህበረሰብ እንቅፋት የሚሆን ማንኛውንም ነገር ማድረግን ያመለክታል፡፡ ይህም ደግሞ ወንጌልን መስበክን ያጠቃልላል፡፡ ስለዚህ “ሂዱና ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” የሚለውን የጌታን ትዕዛዝ በሸሪኣ ህግ በሚተዳደር የሙስሊም ማህበረሰብ መካከል የምትተገብሩ ከሆነ በሸሪኣ ህግ መሰረት ቅጣቱ በጥቅሱ ውስጥ የተዘረዘረው ነው፡፡

“ጅብ እስኪይዝ ያነክሳል” እንደሚለው የሃገራችን ብሒል እስልምናም እነዚህን የመሳሰሉ ጥቅሶችን በመጠቃቀስ ምቹ ጊዜ እስኪመጣለት ድረስ ይሸነግላል፡፡ የበላይ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ግን ትክክለኛ ገፅታውን ያሳያል፡፡ በመታረድና ለእርሱ በመገዛት መካከል ምርጫ ይሰጣችኋል፡፡ በመስለም ወይንም የተዋረዳችሁ ሆናችሁ ጂዝያን በመክፈል ትገዛላችሁ አለበለዝያ ሰይፍ ይጠብቃችኋል፡፡ ሦስተኛ አማራጭ የለም፡፡ ትገዛላችሁ አልያም ልክ እንደ ሰላሳዎቹ ሰማዕታት አንገታችሁን በካራ ትገዘገዛላችሁ፡፡ ወደ ትክክለኛው እስልምና (አይ ኤስ) እንኳን በደህና መጣችሁ! በእስልምናና በአይ ኤስ መካከል ልዩነት አለ ብሎ ማመን ራስን ማታለል ነው፡፡

Post Reply