Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Abaymado » 18 Aug 2019, 23:03


ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበሩ አምስት የመከላከያ ሰራዊት መኪኖች በሕዝቡ እንዲፈተሹ ሲጠየቁ እምቢ በማለታቸው ችግር ተፈጥሮ ነበር:: የአማራ ልዩ ኃይልም ስላስገደዳቸው ሲፈተሹ መሳሪያዎችን እንደጫኑ ተረጋግጧል:
ወታደሮቹ እንደሚሉት ወደ ዳርፉር እያመሩ እንደሆነ ቢናገሩም ምንም ማስረጃ ግን እንዳልያዙ ነው:: በተጨማሪም ታርጋቸው ራሱ በግልፅ አይታይም ነበር ተብሏል::

ሱዳን ምን እየተሰራ ነው ያለው?

Axumawi
Member+
Posts: 6322
Joined: 28 Apr 2018, 00:31

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Axumawi » 18 Aug 2019, 23:10

There are still many unhappy groups with the peace deal signed by some of the protestors and the military.

Two Darfur rebels
One East rebels (bordering Eritrea)
SPLM North
Communist party
Umma party

All the onece that were opposition to Al Bashir. go figure

Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Abaymado » 19 Aug 2019, 09:49

ይሄ መሳርያ ወደ ትግራይ እየሄደ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል::
ወደየት ናችሁ ሲባሉ ወደ ዳርፉር ቢሉም: ማለፊያ ወረቀት አምጡ ሲባሉ:ምንም የላቸውም::
ሁሉም ሹፌሮች ትግራዮች ናቸው ተብሏል::
እንደተባለው ሱዳን በመደናገጥም ወደ ድንበር ጦሯን አስተግታለች::
4595 ሳጥን ጥይት ተይዟል:
በፍሬ 5.5 ሚልዮን ይሆናል::
ወደ በላይ አለቆቻቸው ሲደወልም:እኛ መጥተን መፍትሄ እስክንሰጥ ይቆይ ብለዋል ተብሏል::
እንደሚባለው ወደ ትግራይ ነው የሚሄደው ወይም ለኮንትሮባንድ ነው ::
ምንጭ:


Axumawi
Member+
Posts: 6322
Joined: 28 Apr 2018, 00:31

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Axumawi » 19 Aug 2019, 10:31

Abaymado wrote:
19 Aug 2019, 09:49
ይሄ መሳርያ ወደ ትግራይ እየሄደ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል::
ወደየት ናችሁ ሲባሉ ወደ ዳርፉር ቢሉም: ማለፊያ ወረቀት አምጡ ሲባሉ:ምንም የላቸውም::
ሁሉም ሹፌሮች ትግራዮች ናቸው ተብሏል::
እንደተባለው ሱዳን በመደናገጥም ወደ ድንበር ጦሯን አስተግታለች::
4595 ሳጥን ጥይት ተይዟል:
በፍሬ 5.5 ሚልዮን ይሆናል::
ወደ በላይ አለቆቻቸው ሲደወልም:እኛ መጥተን መፍትሄ እስክንሰጥ ይቆይ ብለዋል ተብሏል::
እንደሚባለው ወደ ትግራይ ነው የሚሄደው ወይም ለኮንትሮባንድ ነው ::
ምንጭ:


It has become automata for your type to make alubalta about Tigray on any subject.
You never realize that after a while, your manufactured news and fake pictures become routine and expected.

Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Abaymado » 19 Aug 2019, 10:47



የትግራይ አቅትቪስቶች መከላከያ ጎንደሮች ላይ እርምጃ እንዲወስድ እየጮሁ ነው:: እናም ይህ ነገር እውነት ነው ማለት ነው?

የአማራ ክልል ምን ይጠብቃል ይሄ ሁሉ ሲሆን? ድንበር ጠባቂ የለም እንዴ? የአማራ ልዩ ኃይል ስራው ምንድነው?>
ህዝቡ የመጠበቅ ግዴታ አለበት ?

እንዴት ነው ከነዚህ ከርፋፋ አመራሮች የምንላቀቀው?

Last edited by Abaymado on 19 Aug 2019, 11:10, edited 1 time in total.

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Meleket » 19 Aug 2019, 11:03

ባለፈው ዘመን ማለትም በወያኔ ዘመን እንዲህ ዓይነት ጉዳይ ሲያጋጥም፣ “በኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ ላይ ሆን ተብሎ ሽብር ለመፍጠርና ሰላም ለማደፍረስ በኤርትራ መንግሥት የተላኩ የሽብር ኃይሎች ሰርገው ያቀነባበሩትን የተንኮል ተልዕኮ የጸረ ሽብር ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ስር አውሎታል።” ይባል ነበር ያኔ! አሁን ግን . . . :mrgreen:

ጎንደር ጎንደር የቴድሮስ አገር፣ . . . እናንተው ትሞሉት ብለን ነው!!!
:mrgreen:

Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Abaymado » 19 Aug 2019, 13:41

ቢቢሲ እንደዘገበው ከከፍተኛ የመከላከያ ባለስልጣናት ስለ ጉዳዩ ምንም የተባሉት እንደሌለና : እዛው ያሉት መከላከያዎች ስለ ጉዳዩ ምንም እንደማይቁ ገልፀዋል::
https://bbc.In/2z6p6Fh
መንገድ ይከፈትልን እያሉ የሚያለቅሱት ይህ ቀርቶባቸው ነው?

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Meleket » 20 Aug 2019, 04:36

ጎበዝ ከወራት በፊት በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈጸመውን ድርጊት በዚህኛው መነጽር ሲታይ ፍንጭ አይሰጥም ትላላችሁን? ያገሬ ሰዎች ሲተርቱ “ጉዳይ ወይ ነገር ኪጠፍእ፣ ዳይና ቅተል” ይላሉ። ይህም ማለት “የአንድ ጉዳይ ዱካዉና ምንጩ መሠረቱም ከናካቴው እንዲጠፋ፣ ዳኛውን (ሁሉን ነገር የመረመረውን፣ ምሥጢር የሚያውቀውን አካል) አስወግድ” ማለት ነው። ታድያ የባህርዳሩና የአዲስአበባው ፍጻሜ እንዲህ ከመሰለው ድርጊት ጋር ሳይያያዝ ይቀራል ትላላችሁን? መጠርጠር ሳይሻል አይቀርም? ጠርጥር . . . ሌቦች በተሰገሰጉበትና የቀድሞ ጥቅማቸውን ለማስመለሰና ዳግም ስልጣን ላይ ቁጢጥ ወይ ፊጢጥ ለማለት የሚፍጨረጨሩና ባንድ ለሊት ራሳቸውንና ዘርማንዘራቸውን በሃብት ለማደለብ የሚቅበጠበጡ አካላት እስካሉ ድረስ፣ ህግን አስከባሪዎችንና በትክክለኛው መንገድ እንሂድ ባዮችን በተለያየ ምክንያት ማስወገድ አንዱ ፈሊጣቸው ነው። ለማንኛውም የሴራዉ ቋጠሮ እዚህ አካባቢ አልታያችሁምን? “ጠርጥሩ፣ ያልጠረጠሩ፣ ተመነጠሩ!” ነው ነገሩ። በቪኦኤ ቃለ መጠይቅ ያደረገው የሰራዊት ወይ የቦሊስ ባለሥልጣን ከዚህ በፊት 'በርካታ' ተመሳሳይ መኪኖችን በሕጋዊ መንገድ መጥተው ሸኝተናቸዋል ነው ያለው? ይህ የሆነው መቼ ነው? ከክልል 3 አመራሮች ህልፈት በፊት ነው በኋላ? ከነ ርእሰ መስተዳድሩ ዶ/ር አምባቸውና ጀነራል አሳምነው ህልፈት በፊት ወይስ በኋላ? ከኢታማዦር ሹሙ ህልፈት በፊት ነው በኋላ? ከሳቸው ጋር ያለፈው ጡረተኛው ጄነራል የሎጂስቲክ ሰው ነበር ነው የተባለው? ሱዳንም ነበር ነው የተባለው? ታድያ በርግጥ ይህ ንብረት ወደ ሱዳን ከሆነ ስንት ተሸጠ? ለማን ተከፈለ? በየትኛው ደረሰኝ? ሂሳቡ ሲወራረድ የት ገባ? የዚህ ሴራና ተመሳሳይ ሴራን ለመሸፋፈንና ለማድበስበስ የተደረገ ሙከራ መዘዝ ይሆንን ያን ሁሉ ደም ያፋሰሰው? ወይስ ይህ ንብረት እንደሚባለው ወደ ወያኔዎቹ እንዲደርስ የተጫነ ነው? እነሱስ ማንን ለማስታጠቅ ሊጠቀሙበት ፈልገው ነው? ከዚህ በፊት በህጋዊ መንገድ መጡ የተባሉት ተመሳሳይ የመከላከያ መኪኖች የተሸኙት ወዴት ነው? መዳረሻቸው የት ነበር? የሹፌሮቹ ማንነት ምን ይገልጻል? ምንስ እንድንጠረጥር ያደርጋል? ይህ ያለፈው ክስተት ከክልል ሶስትና ከመከላከያ አመራር ህልፈት በኋላ ከሆነ ደግሞ እንዲሁ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ይጭራሉ። ለማንኛውም እዚህ መረጃ ላይ የተዋወቅነው አንዱ ዲተክቲቭ ወንድማችን በዚህ ስሌት ነበር ነገሮችን ሲመረምር ያስተዋልነው ለማለት ነው። ጠርጥር! :mrgreen:

Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ወደ ሱዳን ሲያመራ የነበረ አምስት የመከላከያ መኪና በጎንደሮች ታገተ!

Post by Abaymado » 23 Aug 2019, 12:37

ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣው ስለ ጥይት ስለጫነው የመከላከያ መኪናዎች ይህን ፅፏል:

“ መኪናዎቹን ሲያሽከረክሩ የነበሩት: አርአያ ወልደማርያም; ተስፋዬ ይፍጠር: ጎዳፋይ : ባይነፋኝ ግደይ እና ፈለቀ አበበ ነበር:; እነዚህ መኪኖች ሰኞ እለት ከአምቦ ተነስተው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን:ከአዲስ አበባ ደጀን:ባህርዳር :አዘዞ: ከዛም መተማ ደርሷል:: ድንበሩን ሊለቁ ሲትንሽ ሲቀራቸው ነው በአካባቢው ሰዎች እንዲቆሙ የተደረጉት::
አሽከርካሪዎቹ በሰጡት ቃል : ተልዕኮውን የተቀበሉት ከኮለነል ስለሺ ነገራ ሲሆን ካርቱም ደሞ የሚቀበላቸው ጀነራል መሐመድ የተባለ ሰው እንደሆነ ተናግረዋል::
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ወታደራዊ ተንታኝ ‘ ይጓጓዙ የነበሩት ጥይቶች አይነትና ጥራት: በሱዳን መንግስት ይሄን ያህል ተፈላጊ ካለመሆናቸው አኳያ ምናልባት የመጨረሻ መዳረሻቸው የሊቢያ አማፅያን ሊሆን ይችላል:: ‘

ተሜ ፈልፋዩ!

Post Reply