Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by simbe11 » 18 Aug 2019, 01:46

Why are you surprised?
They raised him up. He is here to quash the revolution through lies and deceit.
Never trusted him.
The only thing I like of him is his talk about Ethiopia. Just the words.

Revelations
Senior Member+
Posts: 33729
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by Revelations » 18 Aug 2019, 04:32

ሹክ፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ እንዴት ነበረ?

አለምአየሁ ምህረቴ

አራት ኪሎ

ነሓሴ 2011




ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ቀውስ አፋፍ ላይ እንደደረሰች የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ለውጥ ደጋፊዎች የሆኑት ፈረንጆችም ካመኑበት ሰነባብተዋል። ከ 3 ሚልዮን በላይ ህዝብ በብሄር ጥቃት ምክንያት በአገር ውስጥ ተፈናቃይ (IDP) ያለባት እና ከ 8 ሚልዮን በላይ የአስቸካይ ምግብ እርዳታ የሚፈልግ ህዝብ አደጋ ውስጥ ያለባት አገር የሚያስተዳድረው በዶክተር አብይ የሚመራው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በነሃሴ በመጀመርያው ሳምንት ውስጥ ስብስበዋን ማጠናቀቁ በአቶ ፍቃዱ ተሰማ የድርጅቱ ፅህፈት ቤት ሃላፊ በኩል መግለጫ ሰጥቷል። ይሁን እንጂ መደበኛው የተለመደው መግለጫ እስካሁን ድረስ አልተሰጠም።

መግለጫው ‘የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስት በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል።’ ይላል፡፡ የአቶ ፍቃዱ ፋና ማህበራዊ ገፅ ላይ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በሚል ከሰፈረው የወሰድኩት ነው።

ከፍተኛ የአመራር ውድቀት ያለባት አገር የሚመራ ድርጅት የህዝቦችን ከፍተኛ የሰላምና የመረጋጋት ጥማት ለምን ተፈጠረ? ማን ነው ተጠያቂው? ብሎ መመርመር ሲገባው አጀንዳው ስልጣኑ ላይ የመጣውን አደጋ ላይ አደረገ። አሁንም የፈጠረው ነውጡን ትቶ የሌለው ለውጡን እያለ የሙጥኝ ብሎ ስልጣኑን ይዞ ገደል ሊከተን ምን ያህል እንደቆረጠ የአቶ ፍቃዱ መግለጫ በሚገባ ያሳያል።

ምነው? ምነው? ዶክተርየ! ፓርላማ ፊት ቀርበው ከአሁን በኃላ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሳንሸፋፍን በግልፅ እንዳለ ይቀርባል ብለው እንዳስጨበጨቡን ረስተዉት ነው፡፡ በቀጥታ ይተላለፋል የታበለውስ እሺ ይቅር መደበኛውና የተለመደው መግለጫ ለምን ይቀረናል? እንዴት ይባስ ብለው ተሸፋፍኖ በስብሰባው በነበረ አንድ አባል በተሰጠው አቅጣጫ ልክ ይገለፃል?

ከስብሰባው በፊት የነበሩትን ሁኔታዎች እስቲ በአጭሩ እንይ። የክልል ሃላፊዎች በጠራራ ፀሓይ በአዴፓ ማ/ኮሚቴ አባል በሆነ ሰው በቢሯቸው ተረሸኑ። የዚህ ድርጊት ፈፃሚዎችን በመከታተል የነበሩ የአገራችን ኤታማዦር ሹም ከድሮ የስራ ባልደረባቸው ከነበሩት ጄነራል አብረው በጠባቂያቸው በቤታቸው ውስጥ ተገደሉ። በዚህ ጉዳይ በተነሳ ምክንያት በህወሓትና በአዴፓ እንዲሁም በፌደራል መንግስት መካከል ልዩነት ተፈጠረ፡፡ በደቡብ ህዝቦች የራስ በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በማቅረባቸው በአፈታት ችግርና ጊዜ መገተት ምክንያት ህውከት ተፈጠረ፡፡ ለፓርላማ ተጠሪነት የሌለውና ህጋዊነት የሌለው ኮማንድ ፖስት ታወጀ፡፡ ክልሉ የራስ በራስ የማስተዳደር ስልጣኑ በወታደሮች ስር እንዲቆይ የለውጡ መሪ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴርና የኢህአዴግ ሊቀመበር ዶክተር አብይ ከስልጣናቸው ውጭ ወስነው በደቡብ ህዝቦች ወረራ ፈፀሙ። ይህ ባዘዙበት ቅፅበት ዓላማው ምንም ግልፅና ይፋ ያልተደረገ ድንገተኛ ጉብኝት በኤርትራ አደረጉ። የእሳቸው መውጣት ተከትሎ በደቡብ ህዝቦች ከልክ ባለፈና ያልተመጣጠነ እርምጃ የፌደራል መንግስት ወስዶ በሞቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ። ቆሰሉ። ተፈናቀሉ።

ከዚህ በኃላ ዘግይቶ ቢሆንም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሲቀመጡ የጠበቅነው፣ በአገራችን ኢትዮጵያ ለምን ተከታታይ ቀውስ ገጠመ? ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው? ተጠያቂው ማን ነው? መፍትሔውስ? ከአፋርና ትግራይ ክልሎች በስተቀር በሁሉም ክልሎች በኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አገዛዝ ስር እስከ መቼ ይቆያሉ? ብሎ ለውጥ ያደርጋል ብለን ነበር። ስብሰባው ግን ጭራሽ ሽፍንፍን በማድረግ አሁንም እንደጨለመን፣ ተስፋ እንደቆረጥን፣ መዳረሻው ወደ ማይታወቀው የጥፋት ጎዳና በደመነፍስ እየቀጠልን ነው። ጎዳናው አገራችንን ወደ ሚያፍረስ ወደ የመን፣ ሊብያ፣ ሶርያና ሶማሊያ ዓይነት ነው። ለዛውም ዕድለኞች ከሆን ነው።

ዶክተር አብይ ከቅድመ ጥልቅ ተሃድሶ በባሰ ደረጃ ከወሰዱን ፓርላማ ላይ የተጨበጨላቸውን ንግግራቸው በሾርት ሞመሪ ችግር ህዝቡ አያስታውሰውም ብለው ከደበባበቁ ያለን አማራጭ ሹክ ብለን ህዝባችንን ማሳወቅ ነው።

አንደኛ ሹክ። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ አጀንዳዎች ሁለት ነበሩ። ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ግምገማና ቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች። ሁለተኛው አጀንዳ ስለ ፓርቲ ውህደት ነበር።

ሁለተኛ ሹክ። አቶ ለማ ከረዥም የአሜሪካ አገር ጉዞ በኃላ በስብሰባው ተገኝተዋል። ዶክተር ደብረፅዮን ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በስብሰባው አልተገኙም። ሌሎች ሁሉም ነበሩ አቶ ሚሊዮን ጭምር።

ሦስተኛ ሹክ። ስብሰባው እንደተጀመረ የአዴፓ አመራሮች በህወሓት ላይ ፕሮስጀር በተደጋጋሚ እያፈረሳቹሁ … ብለው ምሬት በተሞላበት መንፈስና ሁኔታ ጥቃት ጀመሩ። ሌሎችም ተከትለው በህወሓት ላይ የተጀመረውን ጥቃት ተቀላቀሉ። የኢህአዴግ ዲሲፒሊናዊ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አሰራር ጣሳቹህ ብለው አምርረው ወቀሱ። መርህ በማፍረስ ህወሓት የውስጥ ገበናችንን ወደ ውጭ ማጋለጡ ትክክል አይደለም አሉ። ነገሩን ስብሰባ እንዲጠራ ጠይቆ በዝግ ስብሰባ እንዲታይ ማስደረግ እየተቻለ መግለጫ ማውጣት አልነበረበትም አሉ። የፀረ-ህወሓት ቃል ኪዳን ግንባር አሁንም እንደጠበቀ ይመስላል። ህወሓት ዛሬ ጉድ ሆኑ አለቀላቸው ብሎ አድፍጦ ምንም ቃል ሳይተነፍስ የሚያዳምጥም ቀላል ያልሆነ አባል አለ። አጎንብሶ መልሶ የማያየውና የማያነበውን ማስታወሻ ላይ የሚቸከችክ እንደዛው። ህወሓት ተራው ደርሶ ቀጠለ። አምርረው ግን ቀስ ብለው በትዕግስት ጉዳዩ በመካከላችን ያለው ችግር ልዩነት ፕሮስጀራል ቢሆን ነሮ ምንኛ በታደልን ብለው ጀመሩ። ግን ባለመታደል ሆኖ ልዩነታችን ከፕሮሲጀር በላይ ነው። እኛና እናንተ የተለያየንው በመስመር ነው። የአብዮታዊ ዲሞክራሲን መስመር አሽቀንጥራችሁ የኒዮ-ሌበራሊዝም አቀንቃኝ ነን ከምትሉ ጋር ምንም አንድ የሚያደርገን ነገር የለም አሉ። ፕሮሲጀር ይከበር የምትሉት መጀመርያ ፕሮሲጀሩ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የፓርቲ እስርቤት አሰራር ነው ብሎ አሽቀንጥሮ የጣለው ማን ሆኖ ነው? ብለው ሞጎቱ። ህገ መንግስቱን በአደባባይ የሚቃወምና በተግባር እያፈረሰ ካለ የኢህአዴግ ፓርቲ አባላት ጋር ችግርና ልዩነት እንጂ እንዴት ተብሎ ፕሮሲጀራዊ አንድነት ይኖረናል። የትኛው ነው እንዴ የሚቀድመው? በይዘት ተለያይተን በፕሮሲጀርና በዲሲፒሊን እንዴት እንጠያየቃለን? ፈደራሊዝም አልሰራም አሃዳዊ እንመለስ ብላቹሁ ይህን መፈክር ከሚያሰሙ የፋሽስት ደርግ ርዝርዦች ግንቦት ሰባትና ሌሎች አሰላለፋቹህን ካሳመራቹህ ጋር እንዴት አንድ እንሆናለን? ይህ ሁኔታቹህ ደግሞ አገራችን አሁን ለደረሰችበት ፈታኝ የመበተን አደጋ አፋፍ ላይ እንድትሆን ዳረጋት በማለት እንደሁሌም ህዋሕቶች ያላቸውን ፅኑ አቃምና ልዩነታቸውን ሲያቀርቡ አዲሱ ቤት ፀጥ ረጭ ብሎ ተሰብሳቢዎቹ በድንጋጤ ክው ብሎው ያዳምጡ ነበር አሉ።

አራተኛ ሹክ። ማፈግፈግ አይሉት ሽወዳ የህወሓትን መልስ ያልጠበቁት የኢህአዴግ የለውጥ መሪ ነን ባዮች ፈጥነው ልዩነት የለንም አሉ። አብዮታዊ ዲሞክራሲ መመርያችን ነው። ህገ መንግስቱን በተለይ ፌደራሊዙም አማራጭ የሌለው ስርዓት ነው። ምርጫም ማን አባቱ ያስረዝመዋል በወቅቱ ይካሄዳል ተባለ። ለአንድ ዓመት ተኩል ያልተናገርዋቸውና ሲፀየፏቸው የከረሙትን አብዮታዊ ዲሞክራሲና ፌደራሊዝም የኛ ነው አሉ። ቀጠሉ ምንም ልዩነት የለንም። ምርጫውም በህገመንግስቱ እንጂ እኛ የምንወስነው አይደለም አሉ። አሁን ጥቃቱ ከህዝብ አልፎ ወደ ፖለቲካ አመራሩ እያነጣጠረ ነው፣ ጎበዝ በአንድነት እንመክተው እንጂ በሌለን ልዩነት አንሟገት አሉ። የለውጥ መሪውቹ ነን ባዮችም ዶክተር አብይ ለጥቀው አለቃህን ተከተል ይመስል ምክትል ሊቀምበሩ ደመቀ መኮነን እንደሁሌም አይናቸውን አፍጥጠው የግምባራቸውን ቆዳ ሰብሰብ ዘርጋ እያደረጉ አንድ ነን ልዩነት የለንም አሉ። ምን ግድ አላቸው በቀጥታ ስርጭት አይተላለፍ። እዚህ አደራሽ ውስጥ ውሸት ይደሰኩሩና በኃላ በመግለጫ ይሸፋፉንታል። ህወሓት እንደዛ አልነበረም ብሎ መግለጫውን ሲቃወም ደግሞ ጆሮ ዳባ ይሉታል።

አዴፓዎች የሰጠንነው መግለጫ አሳፋሪ ነው። በስሜት ተገፋፍተን ነው። አንድ ላይ የታገለን ድርጅት እንደዛ ማለታችን እኛንም አርባ ዓመት እንደበግ ለምን እየተጎተትን ቆየን የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው አሉ። ገሚሶቹ የአዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የአዴፓ መግለጫን ስንሰማ ደነገጥን ይላሉ። መግለጫው የጋራ እንዳልነበረ ፍንጭ በሚሰጥ አነጋገር።

የህወሓት አባላትም መግለጫ ማውጣታችን በይዘትም በፕሮሲጀርም ትክክልና ወቅታዊ ነው አሉ። በአዴፓ ውስጥ የተፈፀመ መገዳደል ራሱን ያጥራ ማለታችን ትክክል ነው። የደቡብ ህዝቦችም በፓርላማ ጭምር በሃይል እንፈታዋለን የሲዳማ የክልል ጥያቄ ሲባል ትክክል አይደለም በሰላምና በህገመንግስት ይፈታ ማለት ጣልቃ መግባት አይደለም ይመለከተናል። ለሁሉም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የሚመለከት ነው ብለው እምነታቸውን ገለፁ።

አምስተኛ ሹክ። ክረምት አይደለ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ትልቅ ያልታሰበ ነጎድጋድ ድምፅ ተሰማ። አትደንግጡ። በኢህአዴግ ስብሰባዎች ለረዥም ጊዜ ድምፃቸው አሰምተው የማያቁት አቶ ለማ በድንገት ተናገሩ። ከሳቸው የለውጥ መሪ ያልተጠበቀ ንግግር ቤቱን በሁለት የከፈለ ሃሳብ አቀረቡ። ንግግራቸውን የጀመሩት በሊቀምበሩ ዶክተር አብይ በተዘጋጀው መወያያ ፅሑፍ አርእስትን በመቃወም ነበር። ‘ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት’ የሚለው አርእስት ተቀይሮ ሁኔታችን የሚገልፀው ‘አገር አጥፍተን እኛም እየጠፋን ነው’ ቢሆን ነው የሚሻላ አሉ። ኢህአዴግ ፈርሷል። የለም። ከአሁኑ የፈራረሰው ኢህአዴግና አገር ከለውጡ በፊት የነበረው ኢህአዴግና አገር ከነችግሮቹ ይሻላል አሉ። ከለውጡ በኃላ እየታዩ ያሉ ችግሮች በአገራችን ታሪክ ተከስተው ታይተው የማያቁ ናቸው። አገር የሚያጠፉ ናቸው። ዋናው ችግራችን ኢህአዴግ ባለመኖሩ ነው። ለውጡ ስለተጠለፈ (hijacked ስለ ተደረገ) ነው ችግር ላይ የወደቅ ነው። መዳን ከፈለግን ኢህአዴግ ወደ ነበረበት ቁመና እንመልሰው። ወይም በሰላማዊ መንገድ እንለያይ አሉ።

ከአቶ ለማ ንግግር በኃላ የአዴፓ፣ ደህዴን፣ እና የኦዲፒ ተናጋሪዎች ለማ ያለው ትክክል ነው ብለው ይጀምሩና ግን ኢህአዴግ አልፈረሰም። በጠና ታሟል ነው ማለት የምንችለው አሉ።

የህወሓት ተናጋሪዎች አቶ ለማን በመደገፍ ከአስር ወር በፊት ኢህአዴግ ፈርሷል ስንል ሰሚ አጣን። ያኔ ፈርሷል ስንል ዝርዝር ምክንያትና መገለጫዎቹም ገልፀናል አሉ።

ስድስተኛ ሹክ። ሁለተኛው አጀንዳ፣ የፓርቲ ውህደት አጀንዳ ቤቱ ሳይወያይበት ቀረ። ለምን እንደሆነ ሹክ ልበላቹህ። ዶክተር አብይ በዚህ አጀንዳ መወያየት ወቅቱ እንዳልሆነ ስላወቁ ተሎ ብለው በየደርጅቱ ተወያይታቹሁ ሪፖርት አድርጉ አሉ። በስብሰባው ወቅት ኢህአዴግ ከፈረሰ ቆይተዋል ብለው ከህወሓት ውጭ የለውጥ መሪ ነን ከሚሉ ሰዎች መነገሩ የፈረሰ ድርጅት ውህደት ያድርግ ብሎ መነጋገሩ ትርጉም የለውም። የመስመር ልዩነት አለን የሚል ክርክር በተነሳበት ወቅት ማን ከማን ሊወሃድ ብለው ሁለተኛው አጀንዳን አጠፏት። አጀንዳ ይሁን ብለህ አፀድቀህ ሳትወያይ ማለፍ ፕሮሲጀር ይፈቅዳል? የፕሮሲጀር ጠበቆች ይመልሱት።

ሰባተኛ ሹክ።
ሌላው በዚህ ስብሰባ የታየው ጉዳይ የደቡብ ህዝቦች የክልል እንሁን ጥያቄ በህገ መንግስቱና በህገመንግስቱ ብቻ ደህዴን እንዲመልስላቸው ተሰማመተዋል። ሳይንሳዊ ጥናት እየተባለ ጊዜ መውሰድ የለበትም እንደተባለ ተገልፃል።

ስምንተኛና የመጨረሻ ሹክ። የነሐሴው ስብሰባ ዶክተር አብይ የተደፈሩበት ስብሰባ ነበር። በህወሓት መደፈራቸው አዲስ ነገር አይደለም። መቼም አልተዋቸውም። እሳቸውም ፀረ ለውጥ ብለው ዘግተውት ቆይተዋል። ለምደውቷልም። አዲሱ ዝንባሌ የታየው ከአቶ ለማ ንግግር በኃላ ነው አሉ። የኦዲፒና ደህዴን አባላት የኢህአዴግ ሊቀመንበሩ ሲያጠቃልሉ ‘ደስ ያለህን አታጠቃልል። ይህንንም እኛ ባልነውና ቤቱ ባጠቃለለው ሂድበት’ አሉ አሉ። በለውጡ መሪ በንግግራቸው ጣልቃ ገብተው! በዛን ግዜ ሊቀመንበሩ ደንገጥ አሉ ይባላል። ከዛን ግዝ ጀምሮ ቀናቸው እየጨለመና ባንዴራቸው ዝቅ እያለ መሆኑን ያጤኑ ይመስላል ይላሉ ምንጮቻችን።

ከዚህ በኃላ ዶክተር አብይ ከአጀንዳ ውጭ የተናገሩትን ያልተጠበቀ ንግግር ለመሰናበቻ ሹክ ልበላቹህ። ከለውጡ በኃላ ህወሓትን ሲያመጉሱ ሰምቼ አላውቅም። እንዲህ አሉ። ህወሓት በ1977 እና 1993 ዓመተ ምህረት በድርጅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነቱን በውይይት ተከራክሮ በድምፅ ፈታው። መሳርያ ትጥቅ ስላልነበረው አይደለም። በሰለጠነ መንገድ በውይይት የመፍታት ብቃትና ባህል ስለነበረው ነው። አሁን ግን በደቡብ የምናየው ውይይት ትተው በድንጋይ አመራሩን ደበደቡ። በቅርቡ ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ አመራሩን በጥይት መግደል ተጀመረ። ለምን በውይይት አንፈታውም? አሉ አሉ። ቀጠሉ ከኃላ የሆነ ነገር ይገፋቸዋል። መንግስት መንግስት ነው። የፈለገውን ማድረግ ይችላል። ኮ/ል መንግስቱ መቶ ሃያ የለውጥ ሃዋርያ ሲያስቸግሩት የሚገደለውን ገድሎ ሌላውን ጥግ አስይዞ ይህችን አገር ቀጥ አድርጎ መርቷታል። አያስፈልግም እንጂ እዚህ ስብሰባ ጠርቻቹሁ ወታደሮች ጠርቼ ልገድላቹሁ እችላለሁ። ቤቱ ግማሹ አጉረመረመ። ግማሹ ይስቃል። በመሃልም እንዴት እንደዚህ ትላለህ ያሉም አሉ። ሊቀመንበሩ ቀጥለውም መርዝ በውሃ አድርጌ ልጨርሳቹህ እችላለሁ አሉ። ግን ምንም አያስፈልግም አሉ ተመልሰው። ውይይት ይሻላል አሉ። ሊቀመበሩ ከአንዱ አጀንዳ ወደ አንዱ እየዘለሉ ቀጠሉ። የኤርትራው ኢሳያስ አንስተው እብድ ነው ምን እንደሚያስብ አይታወቅም። ከሱ ጋር መስራት አስቸጋሪ ነው አሉ። እንፈራረም ብለው እሺ እያለ እያገተተው ነው አሉ። ካቢኔውን ሰብስቦ አያቅም። ምን እንደሚያስብ መገመት አይቻልም። ኤርትራ ውስጥ ለውስጥ ሰራዊቷን እያዘጋጀች ነው። ክረምቱ ሲያልቅ ወረራ ፈፅሞ ወደ ጦርነት ሊከተን ይችላል። ሱዳን እንደምንም ብለን አስማማናቸው ምንም ትምህርት የሌለው ግመል ነጋዴ የነበረ ጄነራል አስቸግሮን ነበር አሉ። አሁንም ማንም ሳይጠይቃቸው የጁቡቲው ኢስማኤል ገሌ ነው እያስቸገረን ያለው። ገና ከኤርትራ ጋር ታርቀዋል ብሎ፣ ወደብ አገልግሎትን ጥለው ይሄዳሉ ብሎ ፈርቶ ክፉኛ እያየኝ ነው። የትናንሽ አገር መሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው። ከአጀንዳ ውጭ ቀደዱ አሉ፡፡ ነገሪየው የትልቅ አገር መሪ ነኝ ቀለል ቀለል አታድርጉኝ ዓይነት ነው መልእክቱ።

ሹክ በማለቴ ፕሮሲጀር በወያኔ አነጋገር ዴሞክራሲያዊ ማከላዊነት ጥሼ ሊሆን ይችላል። ላይሆንም ይችላል ግን ህዝብ የማወቅ መብት አለው ብዬ ያደረጉት ስለሆነ ችግር ቢደርስብኝም እሸከመዋለሁ። ገበናችን ከህዝብ እንደብቅ የሚል፣ የለየልት ፀረ ዲሞክራሲና ፀረ ህዝብ ከሆነ ድርጅት ስብሰባ ማጋለጥማ የግድ ነው። ግን ሊቀመንበራችን መርዝ ወይም ጥይት እስኪያጠጡን ድረስ ነው። ሰላም ናፈቀኝ። ልማት ናፈቀኝ። ትያትሩ ይብቃ ለሚል ህዝብ ሹክ ማለት ትንሿ ግዴታዬ ናት ብዬ ይህንን የፈፅምኩት። ሹክ።

የኢትዮጵያ ሁኔታ ሌላ፣ የኢህአዴግ ፍርስራሽ የሚወያየው ሌላ ነው። ጥልቅ ተሃድሶ በስልጣን ናፋቂዎች በመቀማቱ አገራችን በከፍተኛና መግለፅ በሚከብድ ዘግናኝ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ነገ ዛሬ ፈርሳ ትበታተናለች ተብላ እየተጠበቀች ነው። ቁልፉ ጥያቄ አገር እንዴት እናድን ነው። አገር የሚድነው በህገ መንግስትና በህገመንግስቱ ብቻ ስንመራ ነው። አገር ሲኖር ነው ህገ መንግስቱን በህገመንግስቱ መሰረት ማሻሻል የምንችለው። ኢህአዴግ ሊያድናት አይችልም። የፈረሰ ድርጅት ሊያድነን አይችልምና። የዶክተር አብይ ዕቃ ዕቃ ጫወታ ገደል እየከተተን ነው። ሁሉም እውነተኛ የአገር ወዳጅ ተደራጅቶ መክሮ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጎን በመሰለፍ አገር የማዳን አጀንዳ ቀዳሚም ጊዜ የማይሰጥም ነው ብሎ ይነሳ።


አሁኑኑ አገራችን ከመፈራረስ እንታደጋት!

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by Dawi » 18 Aug 2019, 05:29

Revelations wrote:
18 Aug 2019, 04:32
መንግስት መንግስት ነው። የፈለገውን ማድረግ ይችላል። ኮ/ል መንግስቱ መቶ ሃያ የለውጥ ሃዋርያ ሲያስቸግሩት የሚገደለውን ገድሎ ሌላውን ጥግ አስይዞ ይህችን አገር ቀጥ አድርጎ መርቷታል። አያስፈልግም እንጂ እዚህ ስብሰባ ጠርቻቹሁ ወታደሮች ጠርቼ ልገድላቹሁ እችላለሁ። ቤቱ ግማሹ አጉረመረመ። ግማሹ ይስቃል። በመሃልም እንዴት እንደዚህ ትላለህ ያሉም አሉ። ሊቀመንበሩ ቀጥለውም መርዝ በውሃ አድርጌ ልጨርሳቹህ እችላለሁ አሉ። ግን ምንም አያስፈልግም አሉ ተመልሰው። ውይይት ይሻላል አሉ።
hehehehehehe!

Meles in the making!
Revelations wrote:
18 Aug 2019, 04:32
ለረዥም ጊዜ ድምፃቸው አሰምተው የማያቁት አቶ ለማ በድንገት ተናገሩ። ከሳቸው የለውጥ መሪ ያልተጠበቀ ንግግር ቤቱን በሁለት የከፈለ ሃሳብ አቀረቡ። ንግግራቸውን የጀመሩት በሊቀምበሩ ዶክተር አብይ በተዘጋጀው መወያያ ፅሑፍ አርእስትን በመቃወም ነበር። ‘ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት’ የሚለው አርእስት ተቀይሮ ሁኔታችን የሚገልፀው ‘አገር አጥፍተን እኛም እየጠፋን ነው’ ቢሆን ነው የሚሻላ አሉ። ኢህአዴግ ፈርሷል። የለም። ከአሁኑ የፈራረሰው ኢህአዴግና አገር ከለውጡ በፊት የነበረው ኢህአዴግና አገር ከነችግሮቹ ይሻላል አሉ። ከለውጡ በኃላ እየታዩ ያሉ ችግሮች በአገራችን ታሪክ ተከስተው ታይተው የማያቁ ናቸው። አገር የሚያጠፉ ናቸው። ዋናው ችግራችን ኢህአዴግ ባለመኖሩ ነው። ለውጡ ስለተጠለፈ (hijacked ስለ ተደረገ) ነው ችግር ላይ የወደቅ ነው። መዳን ከፈለግን ኢህአዴግ ወደ ነበረበት ቁመና እንመልሰው። ወይም በሰላማዊ መንገድ እንለያይ አሉ።
Is he talking about of his blunder of "demographic changes"?
Or is this the change agents gong back and forth before they make the final move?
Revelations wrote:
18 Aug 2019, 04:32
ኤርትራ ውስጥ ለውስጥ ሰራዊቷን እያዘጋጀች ነው።
If Eritrea is doing "military preparation" whose side is "መንግስት መንግስት ነው" of Ethiopia?

Make a Guess?
Revelations wrote:
18 Aug 2019, 04:32
የትልቅ አገር መሪ ነኝ ቀለል ቀለል አታድርጉኝ ዓይነት ነው መልእክቱ።
Better believe it! He is the man!

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by justo » 18 Aug 2019, 09:55

Revelations wrote:
18 Aug 2019, 04:32

የህወሓትን መልስ ያልጠበቁት የኢህአዴግ የለውጥ መሪ ነን ባዮች ፈጥነው ልዩነት የለንም አሉ።
አብዮታዊ ዲሞክራሲ መመርያችን ነው።
ህገ መንግስቱን በተለይ ፌደራሊዙም አማራጭ የሌለው ስርዓት ነው።
ምርጫም ማን አባቱ ያስረዝመዋል በወቅቱ ይካሄዳል ተባለ።
አዴፓዎች የሰጠንነው መግለጫ አሳፋሪ ነው።
በስሜት ተገፋፍተን ነው።
የህወሓት አባላትም መግለጫ ማውጣታችን በይዘትም በፕሮሲጀርም ትክክልና ወቅታዊ ነው አሉ።
ህወሓት በ1977 እና 1993 ዓመተ ምህረት በድርጅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነቱን በውይይት ተከራክሮ በድምፅ ፈታው።
መሳርያ ትጥቅ ስላልነበረው አይደለም።
በሰለጠነ መንገድ በውይይት የመፍታት ብቃትና ባህል ስለነበረው ነው።
አሁን ግን በደቡብ የምናየው ውይይት ትተው በድንጋይ አመራሩን ደበደቡ።
በቅርቡ ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ አመራሩን በጥይት መግደል ተጀመረ።
የኤርትራው ኢሳያስ አንስተው እብድ ነው ምን እንደሚያስብ አይታወቅም።
ከሱ ጋር መስራት አስቸጋሪ ነው አሉ። እንፈራረም ብለው እሺ እያለ እያገተተው ነው አሉ።
ምን እንደሚያስብ መገመት አይቻልም።
ኤርትራ ውስጥ ለውስጥ ሰራዊቷን እያዘጋጀች ነው።
ክረምቱ ሲያልቅ ወረራ ፈፅሞ ወደ ጦርነት ሊከተን ይችላል።
ጥልቅ ተሃድሶ በስልጣን ናፋቂዎች በመቀማቱ አገራችን በከፍተኛና መግለፅ በሚከብድ ዘግናኝ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።
ቁልፉ ጥያቄ አገር እንዴት እናድን ነው። አገር የሚድነው በህገ መንግስትና በህገመንግስቱ ብቻ ስንመራ ነው።
አገር ሲኖር ነው ህገ መንግስቱን በህገመንግስቱ መሰረት ማሻሻል የምንችለው።
kkkkkkk
way alemafer ... maferiawotch


Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by Dawi » 18 Aug 2019, 13:10

justo wrote:
18 Aug 2019, 09:55
የህወሓትን መልስ ያልጠበቁት የኢህአዴግ የለውጥ መሪ ነን ባዮች ፈጥነው ልዩነት የለንም አሉ።
አብዮታዊ ዲሞክራሲ መመርያችን ነው።
ህገ መንግስቱን በተለይ ፌደራሊዙም አማራጭ የሌለው ስርዓት ነው።
ምርጫም ማን አባቱ ያስረዝመዋል በወቅቱ ይካሄዳል ተባለ።
አዴፓዎች የሰጠንነው መግለጫ አሳፋሪ ነው።
በስሜት ተገፋፍተን ነው።
የህወሓት አባላትም መግለጫ ማውጣታችን በይዘትም በፕሮሲጀርም ትክክልና ወቅታዊ ነው አሉ።
ህወሓት በ1977 እና 1993 ዓመተ ምህረት በድርጅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነቱን በውይይት ተከራክሮ በድምፅ ፈታው።
Justo,

"ውይይት" On the the surface have the appearance of "civilized" however, the 1993 " ውይይት" was in the aftermath of the sacrifice of over 100,000 compatriots in their asinine war. Seyoum Mesfin/Ethiopia claimed victory over Eritrea after an independent tribunal at The Hague in the Netherlands handed down a ruling?

So Dr. Abiy is warning this morons if you keep pushing we shall have the final happy"ውይይት" in Asmara. ክርክሩን እንፈታዋለን እዚያ ተገናኝተን!

Abraha Belay should stop crying wolf in that video if Tigrai state don't stay as we know it today, after the final "ውይይት" in Asmara. They have been warned!

That is my take.
Revelations wrote:
18 Aug 2019, 12:15


[[..“That means the survival of Abiy in Addis Ababa depends on the survival of the peace deal with Eritrea, and the support he gets from Asmara.” It is now upon Dr Abiy to ensure that the thawing relations succeed...]]

So, what's going to be?

Is TPLF going to cooperate/allow Dr. Abiy do the ground work for the bigger picture to happen peacefully? "The East African Union" ? That bypasses mini ethnic conflicts here and there dogging the region.

Or Are they going to push the region to go to war first?

Without asking the above question, one can't say, "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው" . The opposite is likely.

justo
Member
Posts: 3178
Joined: 05 May 2013, 17:54

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by justo » 18 Aug 2019, 14:17

Dawi wrote:
18 Aug 2019, 13:10
Justo,
"ውይይት" On the the surface have the appearance of "civilized" however, the 1993 " ውይይት" was in the aftermath of the sacrifice of over 100,000 compatriots in their asinine war. Seyoum Mesfin/Ethiopia claimed victory over Eritrea after an independent tribunal at The Hague in the Netherlands handed down a ruling?

So Dr. Abiy is warning this morons if you keep pushing we shall have the final happy"ውይይት" in Asmara. ክርክሩን እንፈታዋለን እዚያ ተገናኝተን!

Abraha Belay should stop crying wolf in that video if Tigrai state don't stay as we know it today, after the final "ውይይት" in Asmara. They have been warned!

That is my take.
Dear Dawi, my take is the document is fake, written by a Woyane operative, to portray woyane in a better light. As professor Asmerom of Eritrea said, this people suffer from an incurable inferiority complex, they are trying to rebrand themselves, sometimes as something important, sometimes as something lawful, sometimes as something peaceful, sometimes as something powerful, while in reality they are none of these.

Degnet
Senior Member+
Posts: 25078
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by Degnet » 18 Aug 2019, 15:24

justo wrote:
18 Aug 2019, 14:17
Dawi wrote:
18 Aug 2019, 13:10
Justo,
"ውይይት" On the the surface have the appearance of "civilized" however, the 1993 " ውይይት" was in the aftermath of the sacrifice of over 100,000 compatriots in their asinine war. Seyoum Mesfin/Ethiopia claimed victory over Eritrea after an independent tribunal at The Hague in the Netherlands handed down a ruling?

So Dr. Abiy is warning this morons if you keep pushing we shall have the final happy"ውይይት" in Asmara. ክርክሩን እንፈታዋለን እዚያ ተገናኝተን!

Abraha Belay should stop crying wolf in that video if Tigrai state don't stay as we know it today, after the final "ውይይት" in Asmara. They have been warned!

That is my take.
Dear Dawi, my take is the document is fake, written by a Woyane operative, to portray woyane in a better light. As professor Asmerom of Eritrea said, this people suffer from an incurable inferiority complex, they are trying to rebrand themselves, sometimes as something important, sometimes as something lawful, sometimes as something peaceful, sometimes as something powerful, while in reality they are none of these.
Yehe sewye Abraha Belay eyale yalew 90% tekekel anew ahyaw Justo,ashasya hede derfu.Ab Mekelle hasas enbelom aynet seb,but hasas that drives auto.

Fed_Up
Senior Member+
Posts: 20617
Joined: 15 Apr 2009, 10:50

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by Fed_Up » 18 Aug 2019, 15:28

ያለው። ገና ከኤርትራ ጋር ታርቀዋል ብሎ፣ ወደብ አገልግሎትን ጥለው ይሄዳሉ ብሎ ፈርቶ ክፉኛ እያየኝ ነው። የትናንሽ አገር መሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው። ከአጀንዳ ውጭ ቀደዱ አሉ፡፡ ነገሪየው የትልቅ አገር መሪ ነኝ ቀለል ቀለል አታድርጉኝ ዓይነት ነው መልእክቱ።
ሽት!! "አሉ" ነው እንዴ? ይህንሁሉ ጊዜዬን ጨርሶ ... "አሉ" ይላል?

ለፃሃፊው "እናህትበዳ" ምንጨቢስ ግልብ ወያኔ በልልኝ:: ነገሩ ስራ አጥ እና ተስፋቢስ ሰነፍ በሞላበት አገር ... ይህ አይነት ነገር ብዙም ኣያስገርምም::

Revelations
Senior Member+
Posts: 33729
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by Revelations » 18 Aug 2019, 15:46

Please wait, video is loading...

sun
Member+
Posts: 9324
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by sun » 18 Aug 2019, 18:00

Revelations wrote:
18 Aug 2019, 01:28


Revelations,

Hmm... :P

Forget about your coffee house gossips and twerking for every passersby but instead thank the almighty for having such a a transformational and peace building leader who freed all Ethiopian prisoners from foreign and domestic jails and concentration camps and helped them and you too to come here and bark freely without any fear day and night non stop. Why don't you leave just few of the barking for the dogs because that is their mode of communication by birth and by design? :mrgreen:

Take your drooling Judas envious little self from the neck and go to lay on the floor and roll all over the places over and over again laughing loud for all the freedoms and other goodies the current new government have given to Mamma Ethiopia in 3000 years of Mamma history. Okay? Okay!
:P

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: "አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"

Post by EPRDF » 19 Aug 2019, 11:27

"አቢይ አህመድ ከሕወሃት ጋራ እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ነው"
ጋሽ revelations,

ከሕወሃት ጋር መስራት ኃጢያት ነው ተባለ እንዴ? ሕወሃት ለምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ተጭኖ የነበረውን የጭቆናና የስቃይ ቀንበር ያነሳ ኃይል እኮ ነው።

ጠባችን በስልጣን ከባለጉ ስግብግብ ሙሰኛ አባሎቹ ጋር ነው። አነኚያን ሆዳም ስግብግቦች ከስሩ መንጥሮ ለፍርድ አስካቀረበ ድረስ፣ ወደፊትም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት የሚጫወተው ሚና አዎንታዊነ ወሳኝ ነው።

Post Reply