Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12608
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must See ! Amhara region biggest scandal ever

Post by Thomas H » 17 Aug 2019, 17:24





ጋዜጠኛው፦ መጀመርያ ስሞትና የመጡበትን ቦታ ያስተዋውቁ፥

ሴትዮዋ፦ ትንጓለል ላቀው አያለው እባላለሁ የተወለድሁት ጎጃም ውስጥ ነው። በ14 ዓመት እድሜዬ ነው ወዳዲሳባ የመጣሁት። እዚሁ አዲሱ ገበያ ኗሪ ነኝ 60 ዓመትታ ኖሬያለሁ። ድሮ ተነፍገን ነበር ማንም አሸንድዬ እንድናከብር ረድቶን አያውቅም። በተለይ ላለፉት 27ዓመታት ታፍነን ነበር።

ጋዜጠኛ ፦ የዘንድሮ የአሸንዲዬ በዓል ከወትሮው ለየት የሚያደርገው እስከ ይንገሩን።

እማማ ትንጓለል፦ ''በጣም ደስ ብሎናል። ደስ የሚል ዝግጅትና ልምምድ እያደረግን ነው። እንደው ትግሬዎችን ሳንበልጣቸው እንቀራለን ብለህ ነው?''
ጋዜጠኛው፦ "የአሸንድዬ በዓል ማክበር የጀመሩት ከመች ጀምሮ ነው?"

እማማ ትንጓለል፦ "አሁንለታ ነው የጀመርነው። ድሮ አንዲት ትግሬ ጎሮቤታችን ነበሩ ስለ አሸንድዬ አውርተው አይጠግቡም ነበረና ደስ ይለኝ ነበር። አሁን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን መንግስታችን ስብሰባና ስልጠና ሰጥቶን እየጨፈርነው ነን"

ጋዜጠኛው፦ በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ፥

እማማ ትንጓለል፦ በጣም ደስ የሚል ልምምድ እያረግን ነው።
ሀገራችንን ሰላም ያርግልን
ክቡር መሪያችንን ይጠብቅልን
ለሴቶች ነፃነት በዓል ስልጠና ሰጥቶው ልምምድ እንድናረግ ላደረጉን የወረዳ 12ና የክፍለከተማችንን እንዲሁ የነባር ቀበሌ አመራሮቻችንን እናመሰግናለን።

ጋዜጠኛው ፦ አመሰግናለሁ።

እማማ ትንጓለል፦ እኛም እናመሰግናለን።
በዚህ እድሜያችን አሸንድዬ እንድንጨፍር ላደረጉን ሁሉ።