ዛሬ ቦሌ ወረዳ 3፣ ፒኮክ መናፈሻ አካባቢ ከባድ የደን ጭፍጨፋ እየተካሄደ እንደሆነ መረጃ ደረሰኝና ከደቂቃዎች በፊት ወደ ስፍራው ሄድኩ። እንደተመለከትኩት ከአውሮፓ ህብረት ጀርባ ያለው ይህ ጥቅጥቅ ደን ሙሉ ለሙሉ እየተቆረጠ ነው። እርግጥ ቆረጣው የተጀመረው ከሶስት ቀን በፊት እንደነበርና ይህ የባህር ዛፍ ደን እድሜው ከ40- 50 አመት እንደሚገመት የአካባቢው ሰዎች ነግረውኛል።
ቆረጣውን ሲያስተባብር የነበረውን ግለሰብም አግኝቼ ስለጉዳዩ ጠይቄው ነበር። የፍቃድ ደብዳቤ አሳይቶኝ እንዲህ ሲልም መለሰልኝ:
"እነዚህን ለመቆረጥ የደረሱ ዛፎችን እንድንቆርጥ እና ወደ 8,000 ካሬ የሚጠጋው መሬት ላይ መዝናኛ ፓርክ፣ የመኪና ማቆሚያ፣ ሲኒማ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ላይብረሪ፣ ካፌዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን እንድንሰራ የፈቀዱልን ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ናቸው። ዛፎቹን ቆርጠን እና ሸጠን ገቢውን ለአ/አበባ አካባቢ ጥበቃ እናስገባለን፣ ቦታውን ደሞ እኛ የአካባቢው ሰዎች እንጠቀምበታለን። ስለዚህ ህገ-ወጥ ቆረጣ እያካሄድን አይደለም። ዛፎቹም በእርጅና ምክንያት እራሳቸው እየወደቁ ነው።"
-
- Senior Member+
- Posts: 33732
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
-
- Senior Member+
- Posts: 33732
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: በታከለ ኡማ ፈቃድ ከባድ የደን ጭፍጨፋ በመሀል አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!
የአረንጓዴው ፉገራ ትክክለኛ ገፁ ይሄ ነው!
-
- Senior Member+
- Posts: 33732
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: በታከለ ኡማ ፈቃድ ከባድ የደን ጭፍጨፋ በመሀል አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!
ዛፍ መቁረጥ ፣ ቤት ማፍረስ ፣ ሕዝብ ማስራብ ......
-
- Senior Member+
- Posts: 26144
- Joined: 20 Apr 2013, 20:24
Re: በታከለ ኡማ ፈቃድ ከባድ የደን ጭፍጨፋ በመሀል አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!
ባህር ዛፍ መቆረጥ አለበት ያለበለዝያ ምን ጥቅም እናገኛለን። በተቆረጠው ምትክ ሲተከል ስራ ለተካዩ ይፈጥራል ጥቅም እንዳለው ስለሚታዋቅ እንክብካቤ የደረግለታል ። ባህር ዛፍ በከተማ ውስጥ በጣም አደገኛ ነው ባህር ዛፍ ዘይት አለው ። እናም ታውቃላቹሁ ዘይት እሳት ሲነካው እንደሚቀጣጠል ታድያ ቤንዚን ቤት ውስጥ እንደማስቅመጥ ነው የከተማ ውስጥ ጫካ ። በባህር ዛፉ ምትክ ጥዳን ውይራ የአገራችን ዛፎች መተከል አለባቸው።
ዋናው ቁምነገሩ አንድ ዛፍ ሲቆረጥ በምትኩ ፵ መተከል አለብት አለቀ ደቀቀ።
ዋናው ቁምነገሩ አንድ ዛፍ ሲቆረጥ በምትኩ ፵ መተከል አለብት አለቀ ደቀቀ።