Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by Meleket » 14 Aug 2019, 12:04

እንዲህ እንዲህ ላፍታም ቢሆን እስቲ የትጥቅ ትግል ወቅት ወጎችን እናጣጥም! ያኔ በዚያኛው ዘመን፡ እንደ አሸን የፈላው የደርግ ሰራዊት ኤርትራ ውስጥ ይርመሰመስ የነበረበት ግዜ፣ ያኔ ኤርትራ ውስጥ ነጭ ለባሾችና ሰላዮች የከተማ የውስጥ አርበኝነትን ትግል ለመደፍጠጥና ለመደምሰስ “ጀሮ ጠቢዎቻቸውን” በየአንዳንዱ ኤርትራዊ ቤተሰብ ደጃፍ ላይ ያሳድሩ በነበረበት ወቅት። ያኔ መሬት ቀውጢ ስትሆን ግዜ ባልባሌ ምክንያት “ውሃ ቀጠነ” እያሉ ለደርጉ እጃቸውን የሚሰጡ ወዶገቦች በተበራከቱበት ዘመን። ሻዕብያ፡ ኤርትራ ውስጥ በአንድ ስፍራ፡ የህዝብ አደረጃጀት ክፍል አባላቶቿንና ከተለያዩ ስፍራ የተሰባሰቡ የአካባቢያዊ(ዞባዊ) ሰራዊት ክፍሎች የተውጣጡ ታጋዮችዋንና አባላቶቿን በመሰብሰብ፡ ወደፊት ላሰበችው ረቂቅ ውጥን ትግባሬ፡ መላ ለመዘየድ አንድ ግዙፍ ስብሰባ ጠራች።

ከዚያስ . . .

ከዚያማ የናቅፋው ‘ግልገል አንበሳ’፣ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ የደርጉን 33 ጀቶችንና ሄሊኮፕተሮችን በ18 ደቂቃ ኦፕሬሽን ዶግ አመድ በማድረግ ያደባዮት የኤርትራዉያን ጥቂት ኮማንዶዎች የሚሊተሪ ኦፕሬሽን ስትራቴጂ ነዳፊና አስተግባሪዉ፣ የህዝብ አደረጃጀትና የዞባዊ ሰራዊት ክፍል ሃላፊዉ ታጋይ ስብሃት ኤፍሬም “ወዲ ኤፍሬም” ስብሰባዉን ከሚመሩት ታጋዮች መካከል፣አንዱ ነበር።
ስብሰባዉ እንደታሰበው በተወጠነለት ሰዓትና ቦታ ተጀመረ። ግሩም የሃሳብ ፍጭትም ተካሄደ። በስብሰባው መካከል ወዲ ኤፍሬም ለሁለቱ የስብሰባው ግዙፍ ክፍሎች ማለትም ለህዝብ አደረጃጀት(ድርጅት) ክፍልና ለሰራዊቱ ወኪሎች እስቲ የሚከነክናችሁና ሊብራራላችሁ የምትሹት ጥያቄ ካላችሁ ዕድሉን ለናንተ ሰጥቻለሁ ጥያቄዎቻችሁን አቅርቡ አላቸው።

የህዝብ አደረጃጀት ክፍል አባላት፣ በደርጉ ጥንግንግ የስለላና የነጭ ለባሽና በተለይም በ “ወዶ-ገባ” ሴራ ብዙ የስራ እንቅፋት ይፈጥርባቸው ስለነበር፣ በወኪላቸው አማካኝነት እንዲህ በማለት የሚቆጠቁጣቸውን ጥያቄ አቀረቡ፦

“እነዚህ ወዶ ገቦች ከኛ ጋር እንዳልታገሉና ብዙ ምስጢራችንን እንዳልተጋሩ ይሀው ወደ ደርጉ እየገቡ በዕለታዊ ስራችን ውስጥ ብዙ እንቅፋት እየፈጠሩብን ስለሆነ፣ ድርጅታችን አፋጣኝ ፈውስ ይፈልግላቸው፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም የማያዳግም እርምጃ ለምን አይወስድባቸው? አስቸገሩን እኮ! መፈናፈኛ ሊያሳጡን እኮ እየተወራጩ ነው!” በቁጭት ስሜት ወኪላቸው ጥያቄውን አቀረበ። አብዛኛው የ”ክፍሊ-ህዝቢ” ታጋይም በልቡ “እውነቱን ነው፡ እነዚህን ወዶገቦች ባንዴ ድምጥማጣቸውን በማጥፋት የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ነው ፈውሳቸው” እያለ አሰላሰለ።

ወዲ ኤፍሬምም ለቀረበለት እውነተኛ ጥያቄ መለሰ፡ እንዲህ ሲል፦
“አዪ ይህ አይነት መሰናክል ካልታከለበትማ ትግል መች ትግል ይባልና! እነዚህ ወዶ ገቦች እንደሆኑ ከአለቆቻቸው ጋር በተለያዩ ኢምንት ምክንያቶች እየተኳረፉ የሄዱ(የከዱ) እንጂ የፖለቲካ ብስለት ኖሯቸው ወደ ደርግ የገቡ አይደሉም። ሶቭየት ህብረትና ሌሎች አሉ የሚባሉ የአለም ሃያላን የሚያግዙት ግዙፉ ጠላታችን ደርግ ሊደፈጥጠን እያቆበቆበና ሳያሰልስ እየሰራ በሚገኝበት ቅጽበት፡ ለነዚህ በስሜት ለሚጋልቡ አንዳንድ ትርኪምርኪዎች ግዜና ጥይት አናጠፋም። ሲሆን ሲሆን በስራችን ላይ ይበልጥ ረቀቅ ያለ ዘዴና ብልሀትን አክለን፣ እነዚህን ወንድሞቻችንን በጥበብና በመላ አስተምረን ለዓላማችን ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ወይም ድልድዮች አድርገን እንጠቀምባቸዋለን፣ ስለሆነም ይልቅስ እንዴት አድርገን የኛን አላማ አስፈጻሚዎች እንደምናደርጋቸው ዘይዱ። ወዘተ” የሚል የቤት ስራን ለትጉዎቹ አባላቶቹ ሰጠ።

ቀጥሎም የተለያዩ ዞባዊ ሰራዊት ክፍሎች ወኪል ደግሞ ጥያቄያቸውን በወኔና በቆራጥነት፡ የአይበገሬነት ስሜት እየተናነቀው እንዲህ ሲል አቀረበ፦
“እኛን የሚገርመን ከደርግ ሰራዊት ጋር እስከመቸ ነው የምንፋጠጥ፣ በአሁኑ ወቅት ከመቸውም ግዜ በላይ ሞራላችን ሆነ ብቃታችን እጅግ አስተማማኝ ነው፣ ታድያ በፊታችን ተገትሮ ያለውን የጠላት ሰራዊት አብጠልጥለን አውቀነዋል፡ ስለሆነም ድምጥማጡን እንድናጠፋው ለምን አይፈቀድልንም፣ ሆ ብለን አንዴ ከተነሳን ሃያል ክንዳችንንና ብርቱ በትራችንን ሊቋቋም የሚችል ምንም ዓይነት ኃይል ሊገታን አይችልም፣ ስለዚህ በአፋጣኝ አንድ በሉን፡ ገስግሰን ይህን የደርግ ሰራዊት እንገርስሰው።” ይህ በወኔ የተሞላ የታጋዮች ወኪል ጥያቄውን አቅርቦ በተሰብሳቢዎችም ተጨብጥቦለት ተቀመጠ። ‘ወዲ ኤፍሬም’ ምን ብሎ ይመልስ ይሆን እያለ አሰፍስፎ ይጠብቅ የነበረው ተሰብሳቢም በጉጉት መልስ መጠበቅ ጀመረ።

ወዲ ኤፍሬም ቀጠለ
“ኣዪ ስታስቡት በጠበንጃ አፈሙዝ ይህን ሁሉ ሰራዊት ገለንና ማርከን የምንጨርስ ይመስላችኋልን? ስንት ሚሊዮን ብለን ገለን ልንጨርስ? እኛ እንደሆንን ከቁጥራችን አንጻር ወታደር መግደል ላይ ብቻ አተኩረን መስራት አያዋጣንም ይልቅስ ኳሷን ኢትዮጵያ ውስጥ ማስገባት ነው የሚያዋጣን? ኳሷ እዛ ከሄደች በኋላ የኛ ስራ ከበቂ በላይ ተከናውኗል ማለት ይቻላል፣ ከዚያ በኋላ ይህን ግዙፍ ሰራዊት እንዴት እንደምናደርገው ባይናችሁ ታያላችሁ፣ ‘ወዲ ኤፍሬም’ ምን ብሎ ነበር ትላላችሁ።”

ተሰብሳቢው ሁሉ “ፀጥ ረጭ” ሲል እያንዳንዱ ተሰብሳቢ ግን “እውነቱን ነው” እያለ በልቡ ያወጋ እንደነበር ሳይታለም የተፈታ ሓቅ ነበር።

እናማ ምን ለማለት ነው፡ ጀኔራሉ የዋዛ አይደሉም፣ ሁሉንም እንደየ አመጣጡ የመመለስ፡ አፈሙዝ ይዞ የመጣንም እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ባፍላው ዘመናቸው የፋርማሲ ተማሪ የነበሩ የኋላኋላ የአስተዳደርና የወታደራዊ ስትራቴጂ ፋርማሲስት ለመሆን የበቁ በሳል ሰው ናቸው ለማለት ነው። እንዲያው የዘመነ ትጥቅ ትግል ውሏቸውን ለግዜው ብናቆየው፣ ወያኔን እንኳ ስንት ግዜ አይደል ጀነራሉ በረቂቅ ጥበባቸው ‘መድኃኒቷን’ የሰጧት - የአስተዳደርና ወታደራዊ ስትራቴጂ ‘ፋርማሲስቱ’ ጄኔራላችን! ወዲ ኤፍሬም!!!


ከዚያኛው ዘመን ወግ! :mrgreen:

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by simbe11 » 14 Aug 2019, 12:42

እርግጥ ነው የ1984ቱ የአስመራ ኤርፖርት ኦፐሬሽን አስገራሚ ነበር።
ለቆራጥ ስውአት ክብር መስጠቱ አስፈላጊ ነው፤ መንጌም እንኳን አክብሮ ነው የቀበራቸው።
ነገርግን ወዲ ስብሃት አማራ መሆኑን ለምናውቅ ኤርትራዊ ጀግንነቱ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ክህደቱን ነው የምናውቀው።

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by Meleket » 15 Aug 2019, 03:33

ክቡር ወዳጃችን simbe 11
simbe11 wrote:
14 Aug 2019, 12:42
እርግጥ ነው የ1984ቱ የአስመራ ኤርፖርት ኦፐሬሽን አስገራሚ ነበር።
በምርጥ ኤርትራውያን ኮማንዶዎች ስለተከናወነው እንከን የለሽ የአስመራ ኤርፖርቱ ኦፕሬሽን ሰምተህ ታውቃለህ ማለት ነው? ነገሩ ነው እንጂ ያ ድንቅ ስራ ማንን ያላስገረመ! ዓለሙን በሙሉ አይደል እንዴ ያስገረመው!
simbe11 wrote:
14 Aug 2019, 12:42
ለቆራጥ ስውአት ክብር መስጠቱ አስፈላጊ ነው፤ መንጌም እንኳን አክብሮ ነው የቀበራቸው
ወዳጄ በዚህ ኦፕሬሽን አንድ ታጋይ ኮማንዶ ብቻ ነው የተሰዋው። ስሙም እምባየ ቅጽል ስሙም “ወዲ ረጋሂት” ይባላል። መንግስቱ በክብር ያስቀበረው ይህን ለዓላማው ሲል ተአምር ፈጽሞ የተሰዋን ታጋይ ነው። አንተ ግን “ስውእ” ከማለት ይልቅ “ስውኣት” እንዲሁም “አክብሮ የቀበረው” ከማለት ይልቅ “አክብሮ የቀበራቸው” አልክ፣ ሌሎች ታጋዮችም በዚያ ድንቅ ኦፕሬሽን ወቅት የተሰው አስመስለህ ሓቅን ልትቆለምም ሞከርክ! “ደቂ ምድሪ ባሕሪ” ደግሞ ከማንኛውም ነገር ውስጥ ሓቅን ፈልቅቀን ማውጣት ከነ ስብሃት ኤፍሬምና ከቀደምት አባቶቻችንና አያቶቻችን ወዘተ በደንቡ ስለተማርነው በመረጃና በማስረጃ ተደግፈን ሓቅንም ይዘን ይሀው ሞገትንህ!!
simbe11 wrote:
14 Aug 2019, 12:42
ነገርግን ወዲ ስብሃት ...
ወዳጃችን እኛ’ኮ እያወራን ያለው ስለ “ወዲ ኤፍሬም” እንጂ ስለ “ወዲ ስብሃት” አይደለም። “ወዲ ኤፍሬም” ሌላ፣ “ወዲ ስብሃት” ሌላ!
በመረጃ ብዙ ፍሬ ከሚያፈሩት ኢትዮጵያዉያን ወዳጆቻችን አንዱ እንዲህ ብሎ መክሮህ ነበር።
Horus wrote:
14 Aug 2019, 23:38
simbe11
ስለ ማታውቀው ነገር መናገር ኋላ ያሳፍራል። ….


ንሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ንጸላኢ ጥምረትና መሬት ነንገርግራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ ራ ራ!
:mrgreen:

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by simbe11 » 15 Aug 2019, 10:51

Nicely done picking all of my false/ wrong statements. But you omit the real question here. Is General Sibhat Ephrem real Eritrean or he is half Amhara? You should answer this question.

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by Meleket » 15 Aug 2019, 11:32

simbe11 wrote:
15 Aug 2019, 10:51
... real Eritrean or ....
ወዳጃችን simbe 11ያልገባዎት ነገር አለ! ኤርትራውነትን በተመለከተ “real” እና “unreal” ወይም “fake”የሚባል ነገር የለም።(አራት ነጥብ) እንቶኔ ½ ከእንትን ብሄር ነው፣ እንቶኔ ደግሞ ¼ ፣ 1/8 ፣ 1/16 ፣ 1/32 ወዘተ እያልክ ዜጎችን ለመከፋፈል የሚደረግ ሴራ ድሮ ድሮ ድሮ ቀረ። ኤርትራዊ ምንም ይሁን ማን፡ በኤርትራዉነት ህብረት የተጠመረና የተገመደ ነው። ይህን ጥምረት ለማላላት ሆነ ለማፍረስ የሚጥሩ አካላትን ደግሞ፣ “ነዚ ክትግዕታ’ዶ ትርህጻ” ወይም “ይችን ገንፎ ለማገንፋት ይህን ያህል ላበት!” እያለ ይሳለቅባቸዋል፣ ኤርትራዊ! :lol:

ንሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ንጸላኢ ጥምረትና መሬት ነንገርግራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ ራ ራ!
:mrgreen:

simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by simbe11 » 15 Aug 2019, 13:20

Meleket wrote:
15 Aug 2019, 11:32
simbe11 wrote:
15 Aug 2019, 10:51
... real Eritrean or ....
ወዳጃችን simbe 11ያልገባዎት ነገር አለ! ኤርትራውነትን በተመለከተ “real” እና “unreal” ወይም “fake”የሚባል ነገር የለም።(አራት ነጥብ) እንቶኔ ½ ከእንትን ብሄር ነው፣ እንቶኔ ደግሞ ¼ ፣ 1/8 ፣ 1/16 ፣ 1/32 ወዘተ እያልክ ዜጎችን ለመከፋፈል የሚደረግ ሴራ ድሮ ድሮ ድሮ ቀረ። ኤርትራዊ ምንም ይሁን ማን፡ በኤርትራዉነት ህብረት የተጠመረና የተገመደ ነው። ይህን ጥምረት ለማላላት ሆነ ለማፍረስ የሚጥሩ አካላትን ደግሞ፣ “ነዚ ክትግዕታ’ዶ ትርህጻ” ወይም “ይችን ገንፎ ለማገንፋት ይህን ያህል ላበት!” እያለ ይሳለቅባቸዋል፣ ኤርትራዊ! :lol:

ንሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ንጸላኢ ጥምረትና መሬት ነንገርግራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ ራ ራ!
:mrgreen:
Smart way of evading a simple question. All the above stated statements were supposed to be told to people like "Tarik" and "Fade-Up" who always cry pure blood Eritreans.
But going back to my question: Is he Amhara?
hmmmmm: I guess you don't want to answer this questions.

By the way the number of people who died in the 1984 mission is more than what is claimed. I have a reliable source who assured me that ‘Embaye‘ was not the only causality.

"Wedi- Shambel The insider", if it rings a bell !!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by Meleket » 16 Aug 2019, 09:51

ወዳጃችን simbe 11 እኛ’ኮ ለርስዎ መልስ ለመስጠት የሞከርነው፣ የዚያኛውን ዘመን ወግ ስናጣጥም እዚህ ድረስ ራስዎ በመምጣትዎ ነው። ራስዎ እርስዎ በሚሉት ርእስ ስር ያሻዎትን ቢሉ ኖሮ መልስ ባልሰጠንዎ ነበር፣ ምክንያቱም አንዳንዴ “አዉቆ የተኛን . . .” ወይም “ውሃን ቢወቅጡት . . .” ስለሚሆን ጉዳዩ።

ለምሳሌ እኛ ስለ “ኳሲቱ” ከአመታት በፊት ጥሩ አድርጎ ስለተነተነዉ ኤርትራዊ ታጋይ አገላለጽ ስንገልጥ፡ እርስዎ ደግሞ አሁን አሁንም
simbe11 wrote:
15 Aug 2019, 13:20
Is he Amhara?
ብለው ይጠይቁናል። ቀጥለዉም
simbe11 wrote:
15 Aug 2019, 13:20
I have a reliable source . . .
ይላሉ፣
እኛ እኛን ስለሚጠምረን ኤርትራዊነቱ በደንቡና በቅጡ በኩራት ስንነግርዎ እርስዎ ካለመኑን ታድያ
simbe11 wrote:
15 Aug 2019, 13:20
I have a reliable source . . .
ያሉትን ይጠይቁት እንጂ! :mrgreen:

ለመሆኑ ግን እርስዎ እነኝህን ጥያቄዎች እንዴት አድርገው ይሆን የሚመልሱልን?
አማራ ማለት ምን ማለት ነው? አማራ ማን ነው? በየትስ ይገኛል?
ቀጥለንም “እንግዲህ እንዳሻዎ አድርገው ኳሲቷን በሜዳዎ ያንከባሉ” ብንልዎ ደስ ላይልዎት ይችላል!
:mrgreen:

ንሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ንጸላኢ ጥምረትና መሬት ነንገርግራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ ራ ራ!
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ‘ኳሲቱ’ና ብልሀተኛው ታጋይ - የዚያኛው ዘመን ወግ

Post by Meleket » 17 Aug 2019, 05:24

እንግዲህ የዚያን ዘመንን ወግ ካነሳን አይቀር፡ በዚህ በመጀመሪያዉ የኤርትራዉያን ኮማንዶ የአስመራ ኤርፖርት ኦፕሬሽን ወቅት የተደባዩት አውሮፕላኖችን ዝርዝር ይህን እንደሚመስል ከታሪክ ማህደር ገለጥ አድርገን ብናነብ ምን ይለናል። ዝርዝሩ ይህ ነው፦
26 ሚግ 21 እና 23 የሚባሉ ተዋጊ አይሮፕላኖች፣
5 ሂሊኮፕተሮች፣
1 አንቴኖቭ 12፣
1 ኤሉጅን፣
በድምር 33 አይሮፕላኖች ዶግ አመድ ሆነዋል ይላል አንድ ያነበበው የኦፕሬሽኑን ሂደት በዝርዝር የሚገልጥ መጥሐፍ።

ኤሉጅን ማለት የሶቭየት ህብረት ስሪት የሆነች ሳብማሪን ዲተክተር ናት። በባሕር ውስጥ ለውስጥ ጠልቀው የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን ( ሳብማሪኖችን) ፎቶግራፍ እያነሳች የምታቀርብ ብዙ ዋጋ ያላት ልዩ አይሮፕላን። በዚያን ወቅትም እጅግ ስለሚጠነቀቁላትና ስለሚንገበገቡላት ስለሚሳሱላትም፡ ማታ ማታ ደቡብ የመን እየወሰዱ ያሳድሯት ነበር። እግዜሩ “ጥፊ ሲላት” ግን የኤርትራዉያን ኮማንዶዎች ኦፕሬሽን የተፈጸመ ለሌት፡ አሥመራ ኤርፖርት ነበረች። ይላል መጠሐፉ።

መጸሓፉ ስለ እምባየ ወይ ወዲ ረጋሂት ሓቀኛ ስሙ መብራህቱ ገብረሂወት መሆኑን ይገልጣል። (መብራህቱ ገብረሂወት ሲባል ደግሞ ከበረከት ስምዖን የቀድሞ ስም ጋር ተመሳሰለ አይደል! “አንዱ መብራህቱ ላገሩ፣ ሌላኛው መብራቱ ለተጋሩ” ሆነ አይደል ነገሩ!) እንቀጥል፦

እምባየ ወይ ወዲ ረጋሂት (መብራህቱ ገብረሂወት) በተሰዋበት ቦታ እንደተመዘገበው መረጃ፦ ቁመቱ 1.75 ሜትር ገደማ፣ ክላሽኑን በእግሮቹ መካከል ቀርቅሮ፣ አንዲት የላውንቸር ቦምብም አጠገቡ ተጋድማ ነበር። በደም የጨቀየውን አካላቱ ደርጎች ሲመረምሩትም ታፋው ላይ በጥይት መመታቱ ሲረጋገጥ፣ የሁለት እጆቹ ጣቶችና ደረቱ በእሳት ተለብልቦ ነበር፤ ይህን ታዝበውም ደርጎቹ “ራሱን በራሱ አጠፋ ማለት ነውን?” ብለው ተገርመው ነበር!

መንግስቱ ሃይለማርያምም ይህ ጀግና በወደቀበት ስፍራ ድረስ በመሄድ “ለዓላማው ሲል የተሰዋ ጀግና ነው ስለሆነም በአገባብ (በክብር) ቅበሩት . . . እያንዳንዱ ወታደርም ለአብዮታዊት እናት ሃገሩ ለኢትዮጵያ ይህን በመሰለ ጀግንነት ሊሰዋላት ይገባል” ብሎ በይፋ እንደተናገረ ይገልጣል መጠሐፉ።

በኤርትራዊ ታጋይ የተጻፈው መጠሓፍ አያይዞም ጀግና ኮማንዶዉን እንዲህ ይገልጸዋል፡

እምባየ፡ (መብራህቱ ገብረሂወት) እንኮ ስዉእ በዅሪ ስርሒት ኮማንዶ ማለትም በኮማንዶዎች የመጀመሪያ ኦፕሬሽን የተሰዋ ብቸኛው ታጋይ ኮማንዶ ብሎ ይጠቅሰዋል።

ይህን ስንል ታጋይ ስብሃት ኤፍሬም ይህን የመሰለውን እጅግ የተሳካ ኦፕሬሽን ሲነድፍና ሲተገብር ጎን ለጎን ደግሞ ለኤርትራ ነጻነት ሲሉ ኳሲቱን ወደ ሚመለከታት ስፍራ እየቀረቀቡ ያስጠጉ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዉያን ተሰማርተው ነበር።

ወዳጃችንን ክቡር simbe 11ን እንዲህ ብለን ጠይቀናቸው ነበር፣
Meleket wrote:
16 Aug 2019, 09:51

ለመሆኑ ግን እርስዎ እነኝህን ጥያቄዎች እንዴት አድርገው ይሆን የሚመልሱልን?
አማራ ማለት ምን ማለት ነው? አማራ ማን ነው? በየትስ ይገኛል?” ...
ንሓቂ ምስ ገለጽና ንሓሶት ነሸቝርራ፣
ንጸላኢ ጥምረትና መሬት ነንገርግራ፣
ፍለጡና በሉ ንሕና ኢና ኤርትራ ራ ራ!
:mrgreen:

Post Reply