Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

የአማራ ባንክ አ.ማ በይፋ ሸር መሸጥ ጀምሯል፣!!

Post by Maxi » 13 Aug 2019, 12:28

የአማራ ባንክ አ.ማ በይፋ ሸር መሸጥ ጀምሯል፣ መግዛት ትችላላችሁ!!



አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር (በምስረታ ላይ ያለ) አክሲዮን ሽያጭ መግለጫ

አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት በአክሲዮን ሽያጭ ላይ ነው። በዚህም መሰረት ማንኛውም የባንኩ ባለቤት መሆን የሚፈልግ ግለሰብ እና ድርጅት ከዚህ በታች ስማቸው በተገለፁት ባንኮች በኩል አክሲዮኑን መግዛት ይችላል፡፡

አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል የአክሲዮን ግዢ ቅፅ በአማራ ባንክ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ወይም በዓባይ ባንክ አ.ማ. በሁሉም ቅ/መቤቶች ማግኘት ይቻላል፡፡

1. የአንድ አክሲዮን መጠን ብር 1000 ( አንድ ሽህ ብር ) ሲሆን መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛ የአክሲዮን ብዛት 10 (አስር) ወይም 10,000 ( አሰር ሽህ ) ብር ነው።


2. አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት መግዛት የሚችለው ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ብዛት 100,000 (አንድ መቶ ሽህ) ወይም 100,000,000 (መቶ ሚሊዮን ብር) ነው።

3. የአገልግሎት ክፍያው ቃል የተገባውን ጠቅላላ አክሲዮን መጠን 5% ነው፡፡

4. አክስዮን የሚገዙ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች
ሀ) የአክሲዮን ግን ለመፈፀም አዲስ አበባ ካዛንቺስ ብሎምቴክ ሕንፃ (ጂፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጎን) ላይ በሚገኘው አማራ ባንክ ፕሮጀክት ጽ/ቤ ወይም ዓባይ ባንክ አ.ማ በሁሉም ቅርንጫፎች በመቅረብ የተዘጋጀውን የሽያጭ ቅፅ መሙላትና የተጠየቁትን መረጃዎች ማሟላት ይገባቸዋል፡፡
ለ) የሚገዙትን ጠቅላላ የአክሲዮን መጠን በዝግ ሂሰሳብ እና ቃል የገቡትን የአክሲዮን መጠን 5% የአገልግሎት ክፍያ በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ገቢ መደረግ ይኖርበታል።
ሐ) የአክሲዮን ግዢ የሚፈፀምባቸው ባንኮች ዝርዝር፦

1. . ዓባይ ባንክ አ/ማ

2. አቢሲንያ ባንክ አ/ማ

3. . አንበሳ ኢንተ. ባንክ አ.ማ.

4. ዳሽን ባንክ አ.ማ.

5. አዋሽ ኢንተ ባንክ አ.ማ.

6. ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አ.ማ.

7. ህብረት ባንክ አ.ማ.

8. ንብ ኢንተ.ባንክ አ.ማ.

9. የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ

10. ቡና ኢንተ ባንክ አ.ማ፣

መ) አክሲዮን ለሚገዙ ግለሰቦች

- የታደሰ መታወቂያ/ ፓስፖርት
- በልጆች ስም ለመግዛት የሚፈልግ የልደት ካርድ እና የአባት/እናት/ ወይም የአሳዳጊ መታወቂያ

ሰ) አክሲዮን ለሚገዙ ድርጅቶች/ ኩባንያዎች
-የድርጅቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ/ የንግድ ምዝገባ/ ግብር ክፍያ መለያ ቁጥር
-አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችል ህጋዊ ውክልና
-ማህበራትና እድሮች የተመሰረቱበትን የፈቃድ ሰርተፍኬት

ረ) የአክሲዮን ሸያጭ አከፋፈል በሁለት አማራጮች የቀረበ ሲሆን፤ ከቀረቡት አማራጮች በአንዱ ግዢ መፈፀም ይቻላል፡፡

አማራጭ-1 የአክሲዮን ግዥ ፎርም እንደተሞላ የጠቅላላ አክሲዮኖችን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል። አማራጭ-2 የአክሲዮን ግዥ ፎርም እንደተሞላ የጠቅላላ አክሲዮኖችን ዋጋ 50 % በመክፈል ቀሪውን ገንዘብ በሁለት ጊዜ በስድሰት ወር ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ማጠናቀቅ፡፡

ሰ) የተዘጋጀውን ቅጽ በሁለት ኮፒ ሞልተው የአክሲዮን ሽያጭም ሆነ አሰተዳደራዊ ወጪ መሸፈኛ 5% ገንዘብ በዓባይ ባንክ የሚያሰገቡ ከሆነ የሞሉትን ቅጽ አንዱን እና በተራ ቁጥር መ (ለግለሰብ ባለአክሲዮን) እና በተራ ቁጥር ሰ (ለድርጅት ባለአክሲዮን) የተዘረዘሩትን መረጃወች ፎቶ ኮፒ ለባንኩ ሰራተኞች ያሰረክባሉ፡፡ ነገር ግን የአክሲዮን ሽያጭም ሆነ አሰተዳደራዊ ወጪ መሸፈኛ 5% ገንዘብ ገቢ የሚያደርጉት በሌሎች በተጠቀሱት ባንኮች ከሆነ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በአዲሰ አበባ የአማራ ባንክ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቢሮ በግንባር በመቅረብ ያሰረክባሉ፡፡

ሸ) አማራ ባንክ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ. አድራሻ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ካዛንቺስ ብሎምቴክ ሕንፃ ( ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጎን)
2ኛ ፎቅ ነው።

ቀ) ከ 5 ሚሊዮን በላይ ለመግዛት ፍላጎት ያለቸው ግለሰብ / ድርጅት/ ብሩን ገቢ ከማድረጋቸው በፊት በቅድሚያ አዲስ አበባ የሚገኘውን ፕሮጀክት ጽ/ቤት ማነጋገር አለባቸው ።

ማስታወሻ፡-

ተጨማሪ ማብራሪያ ከአማራ ባንክ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በየአካባቢው ያሉ የአማራ ባንክ አደራጅ አባላት (አድራሻቸው በዓባይ ባንክ በሁሉም ቅርንጫፎች ይገኛል) መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ የሚገኘውን የፕሮጀክት ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0900780225 0912001819 / 0911248160 / 0911600388 / 0911133014 / 0941466607 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።


Amhara Bank S.C Facebook page: https://www.facebook.com/amharabanksc/

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: የአማራ ባንክ አ.ማ በይፋ ሸር መሸጥ ጀምሯል፣!!

Post by Ethoash » 13 Aug 2019, 12:36

የአማራ ባንክ አ.ማ በይፋ ሸር መሸጥ ጀምሯል፣!!
what! what !

ምን ማልትህ ነው ሽር ስትል። ምቅኝነት ማለትህ ነው ውይ። ድሮስ የዘር ማንዘርህ ነው ሽር ። ብትችረሽረው ምን ይገርማል

Post Reply