Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

የጎንደር ፓለቲካ፡ እሽክርክሪት እንደ ጭፈራው!

Post by Masud » 11 Aug 2019, 00:31

የጎንደር ፓለቲካ፡ እሽክርክሪት እንደ ጭፈራው!
=============================
ወያነ ሸዋ፡ ጎንደር፡ ጎጃም፡ ወሎ የሚባሉ ህዝቦችን አንድ ላይ ጨፍልቆ "አማራ" የሚባል የጋራ ስም ሰጠ፡ በአንድ መዋቅር ሰባሰባቸው፡፡ እንደ አንዱ ወዳጄ አነጋገር "አማራነትን" ለጨረታ አቀረበው፡፡ ጨረታውም ለአማራነት የበለጠ ቅርበት የለውም የሚባለው ጎንደር አሸነፈ፡፡ ሸዋም በጨዋነት ከዳር ሆኖ መመልከትን መረጠ፡፡ የጨረታው አሸናፊ ጎንደርም "አማራነቱን" ለማረጋገጥ በርከት ያለ ጠብመንጃ ( aka ርችት): ለሰርግ አገልግሎት የዋሉ ቦምቦችን ታጥቆ፡ አማራ ያልሆኑትን ቅማንቶችን ጨፈጨፈ፡ ተጋሩን ከቀያቸው አፈናቀለ፡፡ ሁኔታው አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛም የሚባለው አይነት ሆነ፡፡ የወዳጄን ጨዋታ እዚህ ላይ እንግታው እና ወደ ገደለው እንግባ፡፡ በዚህ ሁሉ ግርግር ሸዋ ኢንቨስትመንትን እየሳበ በ 1 አመት ብቻ 40 ቢልየን ገቢ አደረገ፡፡ ደብረብርሃን በ ልማት ስትፈካ ጎንደር በህገ ወጥ መሳርያ ገበያ ሞቀች፡፡ ጎንደር ግን ቅኝትዋም የተለመደው ጎንደራዊ ስሜት ይዞ ነጎደ

ቴዲ ቴዲ ብየ ሙት አልቀሰቅስም
በላይ በላይ ብየ ሙት አልቀሰቅስም
ይሄ ሁሉ አማራ ለወያኔ አያንስም

ብላ በቅዠት አለምዎ በላይ ዘለቀን ቀላቅላ ጎጃምን ለ እብደት ጠራችው፡፡ ጎጃምም የጨረታው አሸናፊ ከሆነው የጎንደር ሰልፍ ጋር ስልታዊ ግምባር ፈጠረች፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ወሎ እጇን ባፏ ጭና በአግራሞት እየተመለከተች ነው፡፡ "አቦ ምን ጉድ ነው የሰዴዴብኝ" እያለች ነው፡፡ የወሎ ህብረት ብላ የጨረታው አሸናፊው ሸቃቢው ሃይል በአግራሞት እያየችው ነው፡፡ ሸዋም ስራዋን እየሰራች ነው፡፡ በጎንደር እብደት ምክንያት የደብረሲና እና የደብረብርሃን የሙቀት ምንጭ የሆኑት የሰሜን ተጓዦች ናፍቀዋታል፡፡ በየቀኑ ገቢ ታደርገው የነበረ ሃብት አጥታለች፡፡

ጨዋታው እንደ ቀጠለ ነው

የሸዋ ብልሆች፡ የጎጃም ጥቂት ልባሞች፡ የወሎ አቻቻዮች " በጣት የሚቆጠሩ የጎንደር ስኩን ሰዎች "እንረጋጋ" ቢሉ ሰሚ አጡ፡፡ ባህርዳርም የእብደት እና የስካር ማእከል ሆነች፡፡ ህዝቡ "ሰላም" ይላል ሙርከኞች "እንዋጋ" ይላሉ፡፡ ህዝቡ " ታቦታችን አክሱም ነው" ይላል፡ ባለ ስልጣኖቹ " አክሱም ዋናው ጠላታችን ነው" እያሉ ድራማውን አራዘሙት፡፡ ትግራይም " ያላቹህ እድል ፎቶ መነሳት ወይም አለመነሳት ብቻ ነው" ብላ ቀለደችባቸው፡፡ እንደተገመተውም ቆቦ ላይ ከሃላቀር መሳርያዎቻቸው ጋር ሰልፊ ተነስተው ተመለሱ፡፡ የፎቶ አበላቸውም ብአዴን-አዴፓ ከፈላቸው፡፡ ፎቶው ፕሪንት ሳይደረግ "እንጨብጣታለን" ያሉ ሸፍቶች በስደተኛ ካምፕ ተጨብጠው ተገኙ፡፡ ትግራይም ለስደተኞች እርዳታ ሰጠች፡፡

አሁንም ድራማው ልብ አንጠልጣይ ሆኖ እንደቀጠለ ነው

ሸዋ ያስመዘገበው የኢንቨስትመንት መጠን በኩራት ሲናገር፡ ጎንደር ያከፋፈለችው የጥይት መጠን ሪፓርት አደረገች፡፡ ጎጃምም በባላሃብቱ አይተነው ወርቁ ድግስ ትንሽ ጥይት ወደ ሰማይ፡ በርከት ያለ ቶክስ ወደ ታዳሚው በመደገን አለኝታነትዎን አረጋገጠች፡፡ ጎንደር በስሜት ከአብይ ጁንታ ጋር እንዳልቆመች፡ አሁንም በስሜት ከአብይ ተለየች

የምን ለማ ለማ የምን ገዱ ገዱ
የምን አብይ አብይ የምን ገዱ ገዱ
ኮኔረል ደመቀ ና ወንዱ ና ወንዱ

ብላ ተልእኮውን በሚገባ ሁኔታ ያጠናቀቀው ትግራዋዩን ደመቀ ዘዉዱን መማለድ ስራዋ ሆነ፡፡ ጎንደር ቅማንቱን አፄ ቴድሮስ፡ ጉራጌውን ቴዲ አፍሮን በምታመልክበት አፍ ትግራዋዩን ደመቀ ዘውዱን "እርዳኝ ጌታየ" አለችው፡፡ (በጃንሆይ ግዜ "የትግራይ ባህል ቡዱን" ተቋቁሞ 3 ቅርንጫፎች ነበሩት፡ መቐለ (ዋና)፡ 1.አሰመራ፡ 2.አዲስ አበባና 3.ጎንደር) :: እናም ጎንደር ያልወለደችው ልጇ ና ወንዱ ብላ ተጣራች፡፡ ይህ የተለመደ የጎንደር የተማፅኖ ታሪክ አካል ነው፡፡ አፄ የውሃንስም አንገቱን የሰጠው ለጎንደር ሲል ነበር፡፡ የዩሃንስ ደርሶ-አዳኝነት ህወሓትም ደገመችው፡፡ ነብሰ በላው መላኩ ተፈራን ከጎንደር ነቀለችው፡፡

የተቀየረ የታሪክ ፍሰት የለም፡፡ ዉለታን ማስታወስ የሚል ነገር በጎንደር መዝገበ ቃላት የለም፡፡

የስካር ፓለቲካው በርከት ያሉ እብዶችና ሰካራሞች ለስልጣን አበቃ፡፡ ፉከራ ሞያ ሆነ፡ ቀረርቶ እና ጩሀት የብአዴን-አዴፓ የፓለቲካ ፕሮግራምን ተካ፡ ጎረቤቶችን መሳደብ፡ መተናኮስ የክልሉ መንግስት የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ ተደረገ፡፡ ልማት፡ ሰላም፡ በራስ ጉዳይ ሃላፊነት መውሰድ፡ ስክነት ከፓርቲው ጋር ቋሚ ፍቺ ፈፀሙ፡፡ አሉባልታ፡ ወሬ፡ ሃሜት የድርጅቱ እና የመንግስት ስራ ሆነ፡፡ መጠራጠሩ ሰፋ፡፡ መናናቁ ጫፍ ደረሰ፡፡ ተላለቁ፡ ተገዳደሉ፡፡ ገዳይም ተገዳይም እኩል ጀገኑ፡፡ የሞራል ሚዛኑ ተሰብሮ ከጠፋ ሰምበትበት ብሏል፡፡

አሁንም ቀነሰ እንጂ ጎንደር አረ ገዳይ ገዳየ እያለች ነው፡፡ ገዳይ አወዳሽ ገዳይ ይፈጥራል፡፡ ይገዳደላል፡፡ መከራው ለሁሉም ይተርፋል፡፡ የጎንደር ፓለቲካ ጎንደሬ የብአዴን አመራሮች ተለይተው ከተገደሉ በሃላ እንደ ሚዳቋ ደንገጥ ብሏል፡፡ ባይደነግጥም፡ የጎንደር ፓለቲካ የታወቀ ነው፡፡ በየመሽታ ቤቱ ይፎከራል፡ ወደ ሰማይ ይተኮሳል፡በየድግሱ ይተኮሳል፡ በሚድያ ይጮሃል፡ ከዛ ሽፍታ ያሰማራል፡ ሽፍታው ፎቶ ተነስቶ ይመለሳል አልያም ይገደላል፡ እንደገና በሽፍታው ቀብር ይፎከራል፡ ጥይት በከንቱ ተኩስ ይባክናል፡ አለቀ፡፡ ከዚህ ከፍ ያለ ፓለቲካ የላትም፡፡

በዚህ ሁሉ መሃል ህዝቡ ሰላሙን አጣ፡ የጥይት ራት ሆነ፡ በሃዘን አቆራመዱት፡ የሃፍረት ማቅ አለበሱት፡፡ ስርዓት አልበኝነት ስርዓት ሆነ:: እኛም ፁሁፋችን በዚህ ገታነ::

የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ናሁሰናይ በላይ እንደጻፈው