Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አንድ ካልቸር ጥሩ ነው ወይም መጥፎ የሚባለው በምን መለኪያ ነው?

Post by Horus » 09 Aug 2019, 01:02

እኔ ረጃጅም ሃተታዎች በመጻፍ ላሰለቻችሁ አልሻም ። ግን ሃስብ የሚቀሰቅሱ ጥያቄዎችን በማንሳት የናንተን ምርምር ማነሳሳት እፈልጋለሁ።

እንደ ምታቁት የጎሳ ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን አገርነት ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚያላዝኑት ጽንስ አለ፤ እሱም ካልቸር (እኔ ፍጥረ ግብር ብዬዋለሁ) ይባላል። ይሁንና በጠባቡ ባህል በሙሉ ጽንሱ ካልቸር ወይም ፍትረ ግብር ምንድን ነው? አንድ ካልቸር ጥሩ ነው የሚባለው ምን ስለሆነ ነው? ሌላውስ መጥፎ ካልቸር የሚባለው ምን ስለሆነ ነው? የጎሳ ወይም የዘር ማንነት አቀንቃኞች የተሻለ ካልቸር ይዘው ነው ወይ ኢትዮጵያን የሚቃወሙት?

ከጥቂት አመታት በፊት በኒው ዮርክ ከተማ ወስጥ በአሜሪካ አሉ የሚባሉት የተለያየ መስክ ምሁራን ማህበር ነበራቸው ስለ ልዩ ልዩ ትላልቅ ጉዳዮች የሚወያዩበት ። አንድ ያነሱት ጉዳይ ስለ ካልቸር ነበር ። የነሱ ጥያቄ ያንድ ጥሩ ካልቸር ባህሪያት ወይም መገለጫው ወይም መለኪያው ምንድን ነው የሚል ነበር ። የደረሱበት ግኝት የሚከተለው ነው።

ባንድ ቃል አንድ ካልቸር ጥሩ ወይም መልካም ባህል ወይም ፍጥረ ግብር ነው የሚባለው የዚያን ባልህ ባለቤቶች ግላዊም ሆነ ማህበራዊ ስርዓት ሲያረጋግጥ ማለትም ሶሺያል ኦርደር ሲያጸና፣ የሰውም ሆነ የማህበሩ ደህንነት ማለትም ዌል ቢኢንግ ሲያረጋግጥ እውቀታቸውን ሲገነባ፣ የማህበርተኞቹን ደስታ፣ ሃሴት ሲያበዛ ማለትም ሃብታብ ሲያረጋቸው፣ እና የፈጠራ፣ የዉበት፣ የእርካታ ምንጭ ሲሆን ነው። እነዚህ አራት መሰረታዊ የጥሩ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር ባህሪያት ሙሉ መጽሃፍ ያጽፋሉ ። ግን አሁን እየተነሳሱ ያሉት የኢትዮጵያዊነት ምሁራን ይስፋፉት እላለሁ ።

በተጻራሪው አንድ ባህል ሰራት አልባ ፤ ቀውሳዊ ከሆነ፣ ለደህነት አደጋ፣ እውቀት አልባ ከሆነ፣ የሃዘን የሰቆቃ የሞት የሽብር ምንጭ ከሆነ እና አስቀያሚ፣ አሳፋሪ፣ አግሊ ክስተቶችን የሚፈበርክ ከሆነ ያ መጥፎ የማይፈለግ ባህል ወይም ካልቸር ይባላ።

በተያያዘ ጉዳይ የመምህር ታየ ቦጋለ አስተምሮት እጅግ ተስማሚ ናቸው፣ ምስጋና ይድረሰው ! ኬር !!


Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ ካልቸር ጥሩ ነው ወይም መጥፎ የሚባለው በምን መለኪያ ነው?

Post by Horus » 09 Aug 2019, 01:59

አንድ ካልቸር በጣም ተፈላጊ ለመሆን ምን መምሰል እንዳለበት ጠቀስኩ።

አንድ ቤተሰብ በጣም ስኬታማ ቢህን ይህን ይመስላል፤ የዘር ቆሮቆች ይህን ያቃሉን?


Post Reply