Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 45804
Joined: 30 May 2010, 23:04

አማራ ክልል የሐሰት ምስክርነት ተስፋፍቷል ተብሏል።

Post by Halafi Mengedi » 08 Aug 2019, 10:50

አማራ ክልል የሐሰት ምስክርነት ተስፋፍቷል ተብሏል።

DW : የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር መጓደል፤ የሀሰተኛ ምስክርነትን አሁንም ያልተፈታ ችግር አድርጎታል ሲል የአማራ ምክር ቤት አስታወቀ። የሕግ ባለሙያዎች በበኩላቸው የንቃተ ሕግ ትምህርትን ማስፋት እና በሀሰት በሚመሰክሩ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አመልክተዋል።


ባለፉት በርካታ ዓመታት የሀሰተኛ ምስክርነትን ለመቀነስ የተለያዩ የንቃተ ሕግ ሥራዎች የተከናወኑ ቢሆንም ችግሩ ግን አሁንም መቀነስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል ምክር ቤት አስታውቋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ ሰጤ ለዶይቼ ቬለ DW እንዳረጋገጡት የሀሰተኛ ምስክርነት በተለያዩ በጎበኟቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፣ ይህም የሆነው የፍትህ አካላት ተቀናጅተው እና ተናብበው ባለመሥራታቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ በፌደራልና በክልል የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሙሉዓለም ዘውዴ በበኩላቸው የሀሰተኛ ምስክርነት በሙያው ላይ ያሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ብዙ ሰው የሚያውቀው ጉዳይ እንደሆነ ይናገራሉ።

አቶ ሙሉዓለም በሐሰት በሚመሰክሩ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ ቅጣት እንደሚስፈልግ ያምናሉ። የሀሰተኛ ምስክርነት የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ የክልሉ ምክር ቤት አቅጣጫ ማስቀመጡንም የምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትህና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ በዝርዝር አስቀምጠዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዓለምሸት ምሕረት ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ እስካሁን በርካታ የንቃተ ሕግ ሥራዎች ቢሠሩም ችግሩ ሊቀንስ እንዳልቻለ ጠቁመው በቀጣይ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በተለየ ሁኔታ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራው እንደሚቀጥል አመልክተዋል። ኅብረተሰቡ ሀሰተኛ ምስክርነት ነውር እና ኢስነምግባራዊ መሆኑን እንዲረዳ ትምህርት ተጠናክሮ እንዲሰጥ የፍትህ አካላትም በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ የሕግ ባለሙዎቹ አሳስበዋል።


አሳፋሪው የዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር በሚሊኒየም አዳራሽ ያደርጉት መላው ኢትዮጵያውያንን ያስከፋ መሆኑን ተነገረአሳፋሪው የዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር በሚሊኒየም አዳራሽ ያደርጉት መላው ኢትዮጵያውያንን ያስከፋ መሆኑን ተነገረMereja
ፖሊስ ሊያጣራው ያልፈቀደውና የኢንጂነሩን ግድያ የሚያመለክት የተባለለት መረጃ ይፋ እየሆነ ነው።ፖሊስ ሊያጣራው ያልፈቀደውና የኢንጂነሩን ግድያ የሚያመለክት የተባለለት መረጃ ይፋ እየሆነ ነው። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ አደለም የተገደለው ከተገደለ ቡሃላ ሬሳው ነው መስቀል አደባባይ የመጣው። በኢንጂነሩ ግድያ ከ አስራ አንድ ሰው በላይ ተሳትፏል መቀሌ ሆኖው ትዛዝ ከሚሰጡት ሰዎች ውጭ።