Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33732
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

Post by Revelations » 06 Aug 2019, 16:06

ዛሬ የለም ስለሚለው አማራ የጻፈው መጽሃፍ!



Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

Post by Maxi » 06 Aug 2019, 16:50

አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

ዛሬ የለም ስለሚለው አማራ የጻፈው መጽሃፍ! ከዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል!!



https://ethiodocs.files.wordpress.com/2 ... -to-to.pdf

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

Post by Maxi » 06 Aug 2019, 17:00

ከራሱ ጋር የተጣላ አንዳርጋቸው ጽጌ!!

አንድርጋቸው ጽጌ "የአማራ ህዝብ ከዬት ወዴት"
ብሎ ከፃፈው መጽሃፍ ገፅ 7 ላይ የተወሰደ




simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

Post by simbe11 » 06 Aug 2019, 19:47

The guy works for TPLF. He was an EPRDF official in Addis. And it’s been know for so long that TPLF takes the dumbs with little or no moral.

The eat the country and spend a few months of talking and call themselves elites.

I have really hard time trusting people who worked for TPLF.
Maxi wrote:
06 Aug 2019, 16:50
አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

ዛሬ የለም ስለሚለው አማራ የጻፈው መጽሃፍ! ከዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል!!



https://ethiodocs.files.wordpress.com/2 ... -to-to.pdf

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

Post by Maxi » 06 Aug 2019, 19:58

የአንዳርጋቸው ጽጌ ነገር. . .
አቻምየለህ ታምሩ

አንዳርጋቸው ጽጌ በትናንትናው እለት ከአባይ ሜዲያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ነው ያለውን «የዘር ፖለቲካ» ሲያወግዝ ሰምተነዋል። ይገርማ! ነገሩ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ ይላል አይነት ሆነብኝ። የኢትዮጵያን ፖለቲካ የዘር ፖለቲካ በማድረግ ከበከሉት ተውሳኮችና ጸረ አማራ ፖለቲካን በሁለት እግሩ እንዲቆም ካደረጉት የ ያ ትውልድ አባላት መካከል በግንባር ቀደምትነት ከሚሰለፉት ሰዎች መካከል አንዳርጋቸው ጽጌ ቀዳሚው ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ በ1970 ዓ.ም. ከማንም በፊት የፋኖ ትግል የጀመረው አማራን የማጥፋት አላማ የያዘ «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» የሚባል ሕወሓት የመሰረተለትን ድርጅት በመምራት ነበር።

ወረድ ብዬ ብዙ ሰው የማያውቀውን የአንዳርጋቸው ጽጌን ጸረ አማራነትና በ1970 ሕወሓት ስለመሰረተለት የኢሕዴንና የብአዴን እናት ድርጅት ታሪክና አንዳርጋቸው ጽጌ ሌላውን ዘረኛ ብሎ ጣቱን ወደሌላ ሊያስጠቁም የሚያስችል የኋላ ታሪክና ዛሬም ላይ ቢሆን የሞራል ልዕልና እንደሌለው የሚያስረግጡ እውነታዎችን ማቅረብ እሻለሁ።

አንዳርጋቸው ገና በጧቱ የኢሕአፓ ፋኖ ሆኖ በወያኔ ተማርኮ ወደ ሕወሓት እንደገባ ወያኔዎች ያቋቋሙለትን ጸረ አማራ ድርጅት ይመራ ነበር። በሌላ አነጋገር ወያኔ ኦሕዴድን፣ ብአዴንን፣ ደሕዴንን፣ ወዘተ ሳይመሰርት ለመሰሪ አላማው ድርጅት ያቋቋመው ለአንዳርጋቸው ጽጌ ነበር። አንዳርጋቸው ጽጌ ከአንድ አመት ተኩል በላይ ወያኔ ባስቀረጸለት ማሕተምና በሰጠው ቢሮ እየኖረ አድዋ ውስጥ ከአንድ አመት ተኩል በላይ የመራው ወያኔ ያቋቋመለት ድርጅት «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» ይባል ነበር።

ይህ በአንዳርጋቸው ጽጌ ይመራ የነበረው የሕወሓት ድርጅት የሕወሓትን ጸረ አማራ የፖለቲካ ፕሮግራም ቃል በቃል ፕሮግራሙ በማድረግ የተመሰረተ ሲሆን ወያኔ ይህን ድርጅት አቋቁሞ አንዳርጋቸውን መሪ ያደረገው ለመሀል አገሩ ትግል በመሳሪያነት ሊጠቀምበት ነበር። አንዳርጋቸው ጽጌ በኢሳት ሎንዶን ስቱዲዮ ከወንድማገኝ ጋሹ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የትግሬዎችን ደግነት ሲያወራ ትግራይ ከወያኔ ጋር ሲታገል «ተቅማጥ ታምሜ በነበረበት ወቅት መጸዳዳች አልችል ብዬ በሰገራየ ላይ ስወድቅ አንድ የትግራይ ልጅ ሰገራየን ጠረገልኝ» ሲል ያወሳው ታሪክ ሕወሓት ያቋቋመለትን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ ሲመራ በነበረበት ሰዓት ያጋጠመውን ነበር። ሰገራየን ጠረገልኝ ያለው ወጣትም ሕወሓት የመደበልትን ሰላይ ነበር።

አንዳርጋቸው ጽጌ ድርጅቱን አንድ አመት ተኩል ከመራ በኋላ ወደ ሱዳን ሄዶ ሳይመለስ በመቅረቱ አንድ አመት ያህል ከጠበቁት በኋላ ሌላ ሰዎችን አሰባስበው አንዳርጋቸው ይመራው የነበረውን «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» እንዲረከቡ አደረጉ። ይህ የሆነው በ1973 ዓ.ም. ነው። በዚህ መሰረት በ1973 ዓ.ም. አንዳርጋቸው ጽጌ ይመራው የነበረውን «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» በድርጅቱ ስም ላይ የአንድ ቃል ለውጥ በማድረግ ማለትም «አብዮታዊ» የምትለዋን ቃል «ዲሞክራሲያዊ» በሚል ቀይረው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ [ኢሕዴን] ወይንም የዛሬውን ብአዴን በነ በረከት ሰምዖን ፊት አውራሪነት እንደገና እንዲቋቋምና የአንዳርጋቸው ጽጌው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» የተፈጠረለትን አላማ ይዞ የወያኔን ጸረ አማራ ፕሮግራም ወደ ተግባር እንዲያወርድ ተደረገ።

ይህ ከሆነ ከአስር አመታት በኋላ አንዳርጋቸው ጽጌ በ1983 ዓ.ም. ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ከሚኖርበት ሎንዶን ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ኢሕዴንን የተቀላቀለው እንደ አዲስ ድርጅት ሳይሆን ከጅምሩ ሲመራውና ወደ ነበረውና ጥሎት ወደሄደው እናት ድርጅቱ ተመልሶ እንዲገባ ግብዣ ቀርቦለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ ብአዴን ውስጥ የገባው በዘር ፖለቲካ ስለሚያምን ነው። ምንም እንኳ ቁም ነገር ባይሆንም አንዳርጋቸው ጽጌ የአማራ ድርጅት ውስጥ የገባው ግን እህቱ እንደነገረችን ዘሩ አማራ ሳይሆን ነው። የአንዳርጋቸው ጽጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ከሶስት ዓመት በፊት «ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ» በሚፍ በጻፉት ማስታወሻ ስነ አንዳርጋቸው የሚከተለውን ጽፈው ነበር፤ «አንዳርጋቸው የቤተሰባችን የመጀመረያ ወንድ ልጅ ስለነበረ ብርቅዬ መሆን የጀመረው የካቲት 1 ቀን 1947 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሆስፒታል ከእናታችን ከወ/ሮ አልታዬ ተሰማ ሮቢ እና ከአባታችን ከአቶ ፅጌ ሀብተማርያም ጨሜሳ ከተወለደ ቀን ጀምሮ ነው።» ይህ የእህቱ ምስክርነት ነው። እንደሚታወቀው ባገራችን ዘረኞች መስፈር ዘር የሚቆጠረው ባባት ነው። በዚህ መስፈር ነው እንግዲህ አባዱላ ገመዳ እናቱ አማራ ሆና የኦሮሞ ድርጅት መሪ የሆነው ዘሩን ባባቱ ቆጥሮ ነው።

እንግዲህ! አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ ላይ ራሱን ከደሙ ነጻ አድርጎ በሁለት እግሩ ያቆመውን በዘር ላይ ተመሰረተ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የመተቸት የሞራል ልዕልና የለውም። ከአማራ አንጻር መቆም የዘር ፖለቲካ አራማጅ አያደርግም፤ ሰዎች ሲያደርጉት ሐጢያት፤ እሱ ሲያደርገው ግን ጽድቅ ካልተባለ በስተቀር የዘር ፖለቲካን የሚተቸው አንዳርጋቸው ጽጌ ራሱ ያኔ ፋኖ በነበረበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላይም ጭምር ከጸረ አማራ አስተሳሰብ ያልተላቀቀ የዘር ፖለቲካ አራማጅ ነው። ይህን በማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ።

አንዳርጋቸው ጽጌ በ1970 ዓ.ም. ሕወሓት ያቋቋመለትን «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» ሲመራ ይመራበት የነበረው የፖለቲካ ፕሮግራም የምናውቀው ጸረ አማራው የሕወሓት ፕሮግራም ነበር። አንዳርጋቸው ይህንን ሕወሓት ያቋቋመለትን ጸረ አማራ ድርጅት ተለይቶ ለአመታት ሎንዶን ቢቆይም ፋኖ የሆነበት ጸረ አማራ አመለካከቱ ግን አልለቀቀውም ነበር። ወያኔም ጥሪ ያደረገለት የቆየውን ጸረ አማራ አመለካከቱን ስለሚያውቅና ወደ አቋቋሙለት ጸረ አማራ ድርጅት መመለስ እንደሚችል ማረጋገጫ ስለሰጣቸው ነበር። በዚህም መሰረት በ1983 ዓ.ም. ወደ እናት ድርጅቱ የቀድሞው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ»፤ የኋላው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ» እና የአሁኑ ብአዴን ከተመለሰ በኋላ በፋኖነት የታገሉለትን ጸረ አማራ አጀንዳ በመንግሥትነት ከተሰየሙ በኋላ ለማስፈጸም በድርጅቱ ፕሮግራም ጸረ አማራ አቋማቸውን በማስፈርና ይህንንም በማርቀቁ ረገድ በቀዳሚዎቹ የወያኔ ሎሌዎች መካከል አንዱ አንዳርጋቸው ጽጌ ነበር። በዚህ የድርጅቱ ፕሮግራም መግቢያ ላይ እንደሰፈረው ወያኔ «የአማራ ክልል» በሚል ከፈጠረው ክልል ውጭ የሚኖሩ አማሮችን «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና «ሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ሲል ይገልጻቸዋል፤ የነ አንዳርጋቸው ጽጌ ድርጅትም እነሱንም እንደማይወክል ይነግረናል።

ባለፉት ሀያ ሰባት የመከራ አመታት በሐረር፣ በኢሉ አባቦራ፣ በመተከል፣ በጅማ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በጉራ ፈርዳ፣ወዘተ. . . ይኖሩ የነበሩ አማሮች ቤታቸው እየተቃጠለ፣ ንብረታቸው እየተወረሰ፣ ያለፍርድ እየተገደሉ፣ እጃቸው እየተቆረጠና ቤት ተዘግቶባቸው እየተቃጠሉ እንዲፈናቀሉ ሲደረጉ በአማራ ስም የተቋቋመው ብአዴን ዝም ብሎ ያየውና ሽርጣም እያሉ ይሰድቧችኋል እያለ ሲያስጨፈጨፍና ዝም ብሎ ሲያይ የኖረው እነ አንዳርጋቸው ጽጌ በጻፉት ፕሮግራም እየተመራ ነበር።

የአንዳርጋቸው ጽጌ ጸረ አማራነት በዚህ አያበቃል። ግንቦት ሰባትን ከመሰረተ በኋላም ድርጅቱ በልሳኑ ቁጥር 25 ጥቅምት 27 2001 ዓ.ም. በርዕሰ አንቀጹ የወጣውን ጸረ አማራ አቋም መውሰድ እንችላለን። በዚህ ርዕሰ አንቀጽ ለዘመናት ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያን ሲገዛ የኖረው የአማራው ኤሊት ያለውን ካሁን በኋላ ሥልጣኑን ለኦሮሞውና ለደቡቡ ማስረከብ እንዳለበት፤ ድርጁቱም ለዚህ እንደሚታገል ያትታል።ይህን ጸረ አማራና ጸረ ዴሞክራሲ የሆነ የግንቦት ሰባት ርዕሰ አንቀጽ የጻፉት አንዳርጋቸው ጽጌና ሌላ ለጊዜው ስሙጥ መጥቀስ የማልፈግለው ሰው እንደሆነ ባደረግሁት ማጣራት ለማረጋገጥ ችያለሁ። በሌላ አነጋገር የአንዳርጋቸው ጽጌ ግንቦት ሰባት የሚታገለው አማራን ከፖለቲካ ስልጣን ለማግለል ነው ማለት ነው። ሕወሓትም ሆነ የቀድሞው የአንዳርጋቸው ጽጌ ድርጅት «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» ያደረጉት ይህንን ነበር። አንድ እሳቤ ከአማራ አንጻር ሲሆን ዘረኛነት አይሆንም ካልተባለ በስተቀር ከዚህ በላይ ዘረኛነት ምን ኖሮ ነው አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ ላይ ሌሎችን በዘረኛነት የሚከሰው?

ምን ይኼ ብቻ! አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንደተፈታ በኢሳት ሎንዶን ስቱዲዮ ቀርቦ በሰጠው ቃለ ምልልስ «የሸዋ መንግሥት» ሲል የጠራውን የኢትዮጵያ መንግሥት የአማራ መንግሥት አድርጎ በማቅረብ ወያኔዎች በትግሬነት ተደራጀተው ከመሰረቱት የሕወሓት አገዛዝ ጋር አንድ አይነት አድርጎ በማቅረብ የመንግሥትነት ተራው ለሁሉም እንዲደርሰው ሲል እየተናገረ ነበር። አንዳርጋቸው ጽጌ ከወያኔ በፊት የነበሩትን የኢትዮጵያ መንግሥታት የአማራ መንግሥታት አድርጎ ያቀረባቸው ካሁን በኋላ የሚደረገው ለውጥ ከአማራ አንጻር መሆን እንዳለበት ሲነግረን ነው። በርግጥ ይህ እሳቤ የአንዳርጋቸው ጽጌ እሳቤ ብቻ ሳይሆን የ ያ ትውልድ በሙሉ የግራ ፖለቲካ ትርክት ነው።

ባጭሩ የአማራ ልጆች በአማራነት የተደራጁት አንዳርጋቸው ጽጌና የትውድል አጋሮቹ ባደረጉት ጸረ አማራ የዘረኛነት ትግልና በወለዱት ፖለቲካ የዘር ማጥፋት ሰለባ የሆነውን አማራን ለመከላከል እንጂ እንደነሱ የዘረኛነት ትግል ለማድረግ አይደለም። ስለዚህ አንዳርጋቸው ጽጌ የአማራን ልጆች በአማራነት መደራጀትና መታገል በዘረኛነት ፈርጆ ማውገዙን ማቆም አለበት። ሕሊና ካለው ወደ ውስጥ በመመልከት ከፍ ሲል የዘረዘርሁትንና ያጎነጠውን ጸረ አማራ አቋሙን አስተካክሎ የአማራን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት። የእሱ እሳቤ ሰለባ የሆንነውን እኛን ግፉዓንን በዘረኛነት መክሰሱ ነውረኛነት ብቻ ነው።

ከታች የታተመው[ያሰመርሁበት] ሕወሓት የመሰረተለት «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ንቅሳቄ» የሚባለው የአንዳርጋቸው ጽጌ ድርጅት ታሪክ circumstantial evidence ነው። የታተመው ማስረጃ ገብሩ አስራት ከጻፈው «ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ» መጽሐፍ የተገኘ ነው።

ውድ አንባብያን በዚህ ጉዳይ አቶ አንዳርጋቸው ምላሽ ከሰጡ የምናስተናግድ መሆኑን አስቀድሞ ለመግለጽ እንወዳለን።



Revelations
Senior Member+
Posts: 33732
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ አፍ 77 ምላስ!

Post by Revelations » 07 Aug 2019, 08:35

ይድረስ ለአንዳርጋቸዉ ጽጌ
----------------------
ከሸንቁጥ አየለ

------------------

1. "የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙም እርስ በርሱ አልተቀላቀለም::አልፎ አልፎ መቀላቀል ያለዉ በከተሞች ነዉ:: በመሆኑም ከአማራ እና ከሌላ ብሄር በከተማ የተወለዱ እና አማርኛ ቋንቋ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ አማራ ይሁኑ::አማራ ብሄረተኝነቱን ማምጣት የሚችለዉ ኢትዮጵያ ከሚባለዉ ሀገር ማዕቀፍ እራሱን ሲያወጣ ነዉ::ኢትዮጵያ በወረራ እና በቅኝ ግዛት የተፈጠረ ሀገር ነዉ::አማራዉ ሌሎች ነገዶችን ወሮ ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር በመፍጠሩ ስህተት ሰርቷል::የአማራ ብሄርተኝነትን ያኮላሸዉ የኢትዮጵያ መፈጠር ነዉ::ኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ ያለዉ ሀገር ስለሆነ ቢፈርስ ሁሉም ነገድ የየራሱን ክልል ይዞ መሄድ ይችላል::

አማራም የራሱን ክልል ይዞ ቢሄድ የአማራ ብሄረተኝነት በደንብ ያብባል::እኔም አማራ ነኝ እና የአማራዉ ህልዉና ስለሚያሳስበኝ አማራ ከዬት ወዴት የሚለዉን መጽሃፍ ለመጻፍ ተነሳሁ::" አቶ አንዳርጋቸዉ አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ የተረተዉ ነዉ::አቶ አንዳርጋቸዉ ይሄን መጽሃፉን የጻፈዉ የወያኔ/ኢህአዴግ የአዲስ ከተማ ጽ/ቤት አፈ ጉባኤ በነበረበት ጊዜ ከስልጣኑ ተባሮ ባሉት ጥቂት ወራት ዉስጥ ነዉ::የዚህ ጽሁፍ ዋና ፍሬ ሀሳብም የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ከሆነዉ ከአንዳርጋቸዉ አ ዕምሮ የፈለቀ የተኮረጀ ሀሳብ መሆኑን መጽሃፉን እንደዋጣ በግል ጋዜጦች ላይ መጽሃፉን ተችቼ ሀሳቤን ሰንዝሬ ነበር:: አንዳንድ ሰዎች ግን አማራ የሚባለዉ ቃል ስለተጠራላቸዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የአማራ ጠበቃ ነዉ እያሉ እንብር እንብር ሲሉ እንደነበረም አስታዉሳለሁ::እረ አሁን ድረስ የሚሉም ነበሩ::

2. የአንዳርጋቸዉ ጽጌ ሁለተኛ መጽሃፉ "ነጻነት እማያዉቅ ነጻ አዉጭ የሚል ነዉ::በዚህኛዉ መጽሃፉ ከአማራ እና ኦሮሞ ነገድ እንደሚወለድ አብራርቶ ጽፏል:: ይሄ መጽሃፉ ከወያኔ ተጽኖ በተወሰነ ደረጃ የተላቀቀበት ወቅት እና ወደ ቅንጅት አስተሳሰብ ያዘነበለበት ወቅት ላይ ስለነበረ መላክም ሀሳቦችን ይዟል ማለት ይቻላል::አንዳንድ ትንታኔዎቹም ጠንካራ የሚባሉ ናቸዉ::የሚያሳዝነዉ ግን የዚህ መጽሃፍ መቋጫም የሚደመደመዉ የተዋህዶን ሀይማኖት በመሳደብ እና ተዋህዶን ደናቁርት አቢዮተኞች ላጠፉት ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ በማድረግ ነዉ::ይሄ የድንዛዜ አካሄድ በአብዛኞቹ የዚያ ትዉልድ ፖለቲከኞች እራሳቸዉን እንዳዋቂ ለማሳያነት የሚተቀሙበት ስልት ነው::

የእግዚአብሄርን ቤት በመሳደብ እራስን አዋቂ ማድረግ ትልቁ ስልታቸዉ ነዉ::እናም አንዳርጋቸዉም ነጻነት የማያዉቅ ነጻዉጭ በሚለዉ መጽሃፉም ተዋህዶን አርክሶ እና ኮንኑ የትንታኔዉ መቋጫ አድርጓታል:: በእሱ ትንታኔ መሰረትም ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዳያብብ ትልቅ እንቅፋት የሆነዉ የቤተክህነት ባህል እና ስነልቦና ነዉ::ከአቢዮታዉያኑ ኢ አማኞች ጋር ቤተክህነትን በምን ገመድ ጎትቶ እንዳገናኛት ግን ሳይገልጽልን አልፎታል::

አስቂኙ ነገር ታዲያ አንድ የተዋህዶ ሰባኪ ነኝ የሚል ወዳጄ የአንዳርጋቸዉን መጽሃፍ አነበብኩት ብሎ ማብራሪያ ሰጠኝ::ተዋህዶ ላይ ያለዉን እይታ እንዴት አገኘህዉ ብለዉ "መቼም ግሩም ገልጾታል" ብሎኝ ቁጭ::ይሄ ሰባኪ ነኝ ባይ መጽሃፉን እንዳላነበበዉ ወይም መጽሃፍ አንብቦ እንደማይረዳ ሲገባኝ ከትከት ብዬ ስቄቤት እንደነበረ ትዝ ይለኛል::ለምን ትስቃለህ ቢለኝ "መቼም እናንተ ዲያቢሎስ ቢሰድባችሁ አትቆጡም::የክርስቶስን ቤት የሚሳደብን ሁሉ ታደንቃላችሁ አይደል?" ብዬ ብለዉ የመለሰለኝ መልስ እስካሁን ያስቀኛል::"እንዴ ? አንዳርጋቸዉ ተዋህዶን ሰደበ እንዴ?" ብሎኝ ቁጭ::በቁጥሩ ቀላል የማይባል ሰዉ እንዲህ ይመስለኛል::ነገር ከመመርመር ጩህት እደመቀበት እሚረግሙት ዳስ ዉስጥ ገብቶ ከበሮ የሚደልቅ::

3. አንዳርጋቸዉ አሁንም ሶስተኛ መጽሃፉን አሳትሟል:: ይሄ መጽሃፉ ደግሞ በተለዬ ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ የጻፈዉ ይመስላል::በአንድ መልኩ እስር ቤት እያለ የጻፈዉ ታሪክ እና ከ እስር ቤት ከወጣም ብኋላ አሁን በኦነጋዉያን ተጽዕኖ ዉስጥ ወድቆ የጻፈዉ መጽሃፍ የቀደሙትን የራሱን ትርክቶች ደምስሷቸዋል:: ዋናዉ ማንነቴ ነዉ ሲል አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ ያተተዉንም ፍልስፍናዉን እና ማንነቱንም ፍቆ በመጣል አማራ የሚባል ህዝብ የለም::እኔም ኦሮሞ ነኝ ብሎ ቁጭ ብሏል::እኔ ኦሮሞ ነኝ ማለቱ አንዳች ክፋት የለዉም::አስገራሚዉ ነገር ከኔ በላይ አማራ የለም ሲል አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ የተረከዉን ማንነቱን በመፋቅ እንዴዉም አማራ የሚባል ህዝብ የለም ማለቱ ነዉ ነዉ::
----------------------------------------------------------
-----------------------------------
ከላይ የተነሱ ሶስት የሰልቦና ቀዉሶችን እንዉሰድ እና አላማቸዉ ምን እንደሆነ እንይ
-------------------------
1.አማራ ከዬት ወዴት የሚለዉ መጽሃፍ የተጻፈዉ እኔም አማራ ነኝ::አማራን ወክዬ ስልጣን እይዛለሁ የሚል ትልምን ተንተርሶ ነዉ::ይሄ ሀሳብ አይከፋም ነበር::ክፋቱ ግን አማራ ያልሆኑ የከተማ ሰዎችን ሁሉ አማርኛ ስለሚናገሩ ብቻ አማራ ይሁኑ::ኢትዮጵያም ትፍረስ::ኢትዮጵያ ስትፈርስ የአማራ ብሄረተኝነት ይቀጣጠላ የሚለዉ ሸዉራራ ሀገር አፍራሽ ህሳቤ ነበር::የዚህ ሸዉራራ ህሳቤ መነሻዉም ከአማራ በላይ አማራ ሆኖ ለመገኘት የታቀደ መሰረት የሌለዉ ስሁት ስነልቦናዊ ቀመር ነበር::
2. በሁለተኛዉ መጽሃፉ ደግሞ ኦሮሞነቱን እና አማራነቱን ለማሳዬት ከሁለቱ ነገዶች መወለዱን ለማታቀስ የተገደደበት ሁኔታ ነበር::ይሄዉም ቅንጅት ህብረ ብሄራዊነትን እያገነነዉ ስለመጣ ነበር::በዚህ ህብረ ብሄራዊነት ምህዳር ዉስጥ በሁለቱ ትልልቅ ነገዶች ተወክሎ መሪነቱን ለመጨበት እና ከኔ በላይ ወካይ የለም የሚል ታሳቢን ያነገበ ነዉ::

3. አሁን ነገሮች ሲገለባበጡ እና የኦሮሞ ብሄረተኝነት ጉልበት ሲያገኝ ደግሞ ሌላ የስልታን ጎዳና ስልጥ መቀዬስ አስፈላጊ ሆነ::እኔ ኦሮሞ ነኝ::አማራ የሚባል ነገድ የለም ብሎ ቁጭ::ይሄንንም በማለት አሁንም በስልጣን ወንበር ስር የማድፈጥ ስትራቴጅ ስልት እንጅ የኦሮሞን ህዝብ በተለዬ የመዉደድ ባህሪ ኖሮት አይደለም::የስልታን መንገዱ እጅግ ዘወርዋራ እና ብዙ መሆኑን አልሞ የተነሳዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ሁሉንም ስልቶች እየቀያዬር እየሞከራቸዉ ይመስላል:: ሁሉም የከተማ ሰዎች እና የአማራ ክልል ህዝብ አማራ ይሁን ሲል አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ ያወጀዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ አሁን ደግሞ አማራ የሚባል ህዝብ የለም ብሎ እርፍ::

አንዳርጋቸዉ ጽጌ እና ግንቦት ሰባት በዚሁ አጋጣሚ የከረረ ጸብ ዉስጥ የገቡትን የአማራ ብሄረተኛ ሀይል የመበቀያ ስልትም ያገኙ መስሏቸዉ ሊሆን ይችላል አማራ የለም የሚለዉን ትርክት ይዘዉ የመጡት::አማራ የለም ካልን የአማራ ብሄረተኝነት ይዳከማ ብለዉ አስበዉ መሆኑ ነዉ::

የሽህ እና ህሽ አመታት የአማራ ታሪክን ካለማወቅ የሚመነጭ ሸዉራራ ህሳቤ እና ፈጥኖ ደራሽ ሀሳብ ሁሌም ስሁት ነዉ::የአማራ ህዝብ እንዲህ በቀላሉ የሚፈረካክሰስ ህዝብ አይደለም::የአማራ ህዝብ ሰላም እና እረፍት እስካላገኘ ድረስም የአማራ ወጣቶች እንደ አማራ ብሄረተኛ ወይም እንደ ኢትዮጵያ ብሄረተኛ ወይም በሌላ መልክ ሆነዉ ትግል ከማድረግ አይቆሙም::ስለዚህ መፍትሄዉ የችግሩን ስር ማድረቅ እንጅ ሀሰተኛ ትርክ መፍጠር አልነበረም::
---------------------
የመደምደሚያ ምክር ለአንዳርጋቸዉ ጽጌ
-----------------
ከሁሉም የሚበልጠዉን ኢትዮጵያዊ ማንነት በምልዓት ብትለብሰዉ እንዲህ የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ አትገባም ነበር::የኢትዮጵያም ስልጣን እግዚአብሄር ከፈቀደልህ ያንተ ይሆን ነበር::ስልጣን ከእግዚአብሄር እንጂ ከዘርህ ወይም ከፓርቲህ አይመነጭም::ሃሃሃሃ...ለኮሚኒስቶች የሚያስቅ የካህን-ንጉስ ፍልስፍና ነገርኩህ አይደለም?

ለማንኛዉም ኢትዮጵያዊነት ከሁሉም ማንነቶች በላይ መሆኑን ብታዉቅ: አንተም ከሁለቱ ነገዶችም ተወልደህ ቢሆን: ወይም ከኦሮሞ ብሄር ብቻ ተወልደህ ቢሆን: ወይም ቀድሞ አማራ ነኝ እንዳልከዉ ከአማራ ብሄርም ተወልደህ ቢሆን ከንኡስ ማንነትህ የሚበልጠዉ አምንነት ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ ነዉ::ከአማራነትም: ከኦሮሞነትም የሚበልጠዉን ኢትዮጵያዊ ማንነት በእምነት ብትለብሰዉ ከሁሉም በላይ ትከብር ነበር::

እንዲህ አንዴ አንዱ የነገድ ማንነትህ ትዝ ሲልህ ሌላ ጊዜ እንደሌለ ሲጠፋብህ: ሌላ ጊዜ ከሁለት መወለድህ ሲታሰብህ ባትተህ እና ዋትተህ መመላለስህ ያሳዝናል::እንደ ኢትዮጵያዊ ወንድሜ ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ የአዳም ልጅ ወንድሜ የማንነትህ ነገር እንዲህ እስከ አንጥንትህ ድረስ ለምን እንደ በላህ ሳስበዉ አሳዘንከኝ::

የሆኖ ሆኖ ተለይቶ የዘር ማጥፋት እየተደረገበት ያለበትን የአማራ ነገድ የለም ስላልክ የምታተርፈዉ የፖለቲካ ትርፍህን አንተዉ ታጭደዋለህ::የአማራ ነገድ በዚህ ወቅት የለም የሚለዉ ሰዉ ሳይሆን የሚፈልገዉ አማራን ለይታችሁ አታጥቁ:ፍትህ አድርጉ:ሁሉንም ኢትዮጵያዉያን እኩል የሚያደርግ ሀገር ፍጠሩ:ሁሉንም ነገዶች እኩል የሚያስተናግድ ፍጠሩ የሚል ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ነበር የሚፈልገዉ::

ለማኛዉም ኢትዮጵያዊነትን መቶ አመት ነዉ እድሜዉ ብለህ በቅኝ ግዛት የተፈጠረ ሀገር ነዉ ብለህ ብትክደዉም መጽሃፍ ቅዱስ ግን የሚተርክልን ኢትዮጵያዊ ማንነት ከማንኛዉም የነገድ ማንነት በላይ መሆኑን ነዉ::በመጽሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር እራሱ ኢትዮጵያዊ ልጄ ነዉ ብሎ መስክሯል እና::

ኢትዮጵያዊነትን ለኢትዮጵያዊ ሁሉ የሰጠዉ እራሱ እግዚአብሄር ነዉና::የሚቀበለዉ ኢትዮጵያዊ መልካም አደረግ::የማይቀበለዉም ኢትዮጵያዊ መብቱ ነዉ:: ከእዉነቱ ስትቆረጥ ይዘህዉ የምትመጣዉ ትንታኔ ሁሉ ሀስት እና እርስ በርሱ የሚምታት ነዉ::አንዴ አማራ ነኝ: አንዴ አማራ እና ኦሮሞ ነኝ: አንዴ አማራ የሚባል ህዝብ የለም እያልክ መከራህን ታያለህ::አንዴ በስልታን ጥም: አንዴ በበቀል: አንዴም በግል ተራ ፍልስፍና ስትዋልል ትዉላለህ::

ኢትዮጵያዊነት ተፈልጎም የማይገኝ ማንነት ነዉ::ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለዉ ህዝብ እንኳን ቢጥለዉ ሌላ ወገን ያነሳዋል::ጥቁሩ አለም የነጻነት: የእኩልነት: በእግዚአብሄር መንፈስ መወደድን እና በ እግዚአብሄር አይን የታወቀ ህዝብ መሆኑን ማረጋገጫ ቢፈልግ የሚያገኘዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ነዉ::
ስለዚህ ዛሬ ኢትዮጵያ የተባለዉ ህዝብ ኢትዮጵያዊነትን አዉልቆ ቢጥለዉ ሌላዉ ወገን አንስቶ ይልብሰዋል::

ኢትዮጵያ ጥሎባት እናንተ ከወያኔ ጋር ሆናችሁ በቀየሳችሁት የነገድ ፖለቲካ ስር ገብታለች እና ገና ብዙ በርካታ ዉጥንቅጦች እና የማምንነት ቀዉሶችን የተሸከሙ ዜጎች ታስተናግዳለች:: አንዴ ይሄኛዉን ነኝ::ሌላ ጊዜ ያኛዉን ነኝ የሚሉ የማንነት ቀዉስ ዉስጥ የሚዳክሩ በርካታ ዜጎች የሚተራመሱባት ሀገር::

በነገራችን ላይ ኢሳያስ አፈወርቂ በአንድ ወገን ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ጥሎ ነዉ ኤርትራዉያንን ከወንድሞቻቸዉ ኢትዮጵያዉያንን የነጣጠላቸዉ::መለስ ዜናዊም በአንድ ወገን ኤርትራዊ ማንነቱን ክዶ ነዉ ኢትዮጵያዉያንን ከወንድሞቻቸዉ ኤርትራዉያንን የነጣጠሏቸዉ::ይሄም ሁሉ የክፋት እና ስልጣን መያዝን እንደ ግብ የመዉሰድ የተሳሳተ ፍልስፍና ነዉ::

የሆነ ሆኖ እግዚአብሄር የታመነ ነዉና ህዝቤ ያለዉን እና የተወደደ ኢትዮጵያዊነት የተላበሰዉን ህዝቡን ያድናል::

Post Reply