Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5626
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

አብይ መሀመድ እያዳለጠህ ወደማጥ ከመገባት ተስተካከል፤ ተቃዋሚዎች ልብ አውጡ፤ ጋዜጠኞች የወያኔ ግዜ ዳንሳችሁን ለማሳየት አትሟሟቁ

Post by TGAA » 25 Jul 2019, 23:02

በአሁኑ ሰአት ሁለት የሚታዩ ጉድፍቶች በአብይ አሰተዳደር ውስጥና በተቃዋሚ የሚባሉት ውስጥ እንዲሁም በሀገሪቱ የሚገኙት ሚድያ አውታሮች ውስጥ እነዚህ የሚታዩ አስተዳደራዊ እንዲሁም አቃማዊ እንዲሁም ዘገብን በሚመለከት የሚታዩ ግድፍቶች ናቸው፡፡ በግዜው እነዚህን ቀርፈን ካላስወገድን ሀገራችንን ወደ ዲሞክራሲ ሳይሆን ወደ አምባገነን አሰተዳደር ነው የምንወስዳት ፡፡ መጀመሪያ ላይ የአብይን አስተዳደር እንመልከት ፤ መጀመሪያ ላይ የወሰዳቸው እርምጃዎች የህዝቡን ልብ ትርታ ያዳመጡ ናቸው ፤ ነገር ግን ወዲያው የአፍ መግለጫውና አብይ የሚመራው ድርጅት መግለጫዎች በግልጽ እየተቃረኑ መጡ፤ አብይ የመረጠው መንገድ አልሰማሁም ፤ አላየሁም ፤ የምናገረውን ስሙኝ እመኑኝ ብቻ ሆነ፤ በባላአደራ ላይ በአከታታይ የወሰደው እርምጃ ፤ ከዚያም በቅርቡ በአማራና መሀከል ሀገር በተፈጸመው ወንጀልን ግልጽ በሆነ ሁኔታ የፖሊስ ምርመራ እንደማድረግ ከመንግስት ይወጣ የነበረው በጣም ግራ የሚያጋባ መግለጫዎች አሁንም ልክ እንደወያኔ ጊዜ ህዝብን ግራ ለማጋባት ተመሳሳይ ካርታ እየተጫወተ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲወድ ብዙ የሚያያቸውን ነገሮች ከችግር በዛት አንጻር እያየ በትግስት ይጠብቃል እንጁ ሁሉንም የሚሰራውን ነገር ይገነዘባል ፡፡ አብይ ግን የህዝቡን ፍቅር ማክበሩን ማሳየት የሚችለው ህዝቡን በቀጥታ ያለው ችግር ምን እንደሆነ በግልጽ ማድረስ ሲችል ነው ፤ አሁን በቅርብ ግዜ በቲፎዞነት ደጋፊ ነን እያሉ ግልጽ የሆነውን ስህተት የሚያለባብሱለት ሁሉ ከመንግስቱ ግዜ ጀምሮ መለሰን ተሻግሮ የመጣ መሪ ለማስደሰት ጭራን የማውለብለብ ልማድ ነው፤ አይጠቅመንም ፤ መልሶ እዛው የነበርንበት ነው የሚደፍቀን ፤ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ተመለሶ ወደዚያ ይሄዳል ብሎ የሚያስብ ካለ በጣም ስልጣን ያደደበው ሰው ብቻ ነው፡፡ ህግን ለማስከበት ህግንና ፖለቲካን መለያየት ያስፈልጋል ፤ ማንኛውም ህገ ወጥ ስራ ፤ ህግ በሚያስከብሩ ፍርድ ቤትና በህዝብ ደህንነት ጠባቂዎች እንዲሁም ፖሊሶች ነው ማለቅ ያለበት፡፡ አብይ ይህን የህግ ተቋም በራሱ ቆሞ ህገን በተመለከተ እርምጃ እንዲወስድ እንደማረግ ፤ የወያኔ የሴራ ፓለቲካ መጽሀፍ አውጥቶ ሊጠቀምበት እየፈለገ ይመስላል፡፡ ትልቅ ስህተት ነው ቶሎ ማቆም አለበት፡፡ ሰሞኑን ትንሽ እየተሻላቸው የመጡ ይመስላሉ ነገር ግን የተቃውሞ ፓርቲዎች እንደዚህ አይነት ህገ ወጥነት በመንግስት በኩል ሲታይ ዝም ማለት እንደማበረታታት ነው የሚቆጠረው ፡ ማንኛውንም ህገ ወጥ እርምጃ ገና ከመሬት ሳይነሳ ነው መቆም ያለበት ፤ ባለደራስ ላይ ይህ ሁሉ ጸረ ህግ የሆነ ስራ ሲሰራ ዝም ፤ አሁን ደግሞ አብንና ባልደራስ ላይ እንዲህ አይነት አይን ያወጣ ስራ ሲሰራ ዝም ይህ አይነት አስጠሊታ መሽኮርመም ነገ የሚያመጣውን ነገር መገንዘብ ያስፈልጋል ፡ አብይ ጥሩ ነው ብላቸሁም የምታምኑ ካላቸሁ መንገድ ሲስት በአደባባይ ትክክል እንዳልሆነና በቶሎ እንዲያርም በመንገር ነው መደገፍ የምትችሉት ፡፡ ከዚያ ደግሞ ሚድያ የሚባሉት ልክ በወያኔ ግዜ ያደርጉ እንደነበረው ግልጽ የሆነ የአንባገነነነት ጸረ ዲሞክራሲያዊ ስራ ሲሰራ የተሰራውን ጉድፍ ስራ በግልጽ ሪፖርት እንደማድረግ በተንሻፈፈ አማርኛ ማለባበስ ይወዳሉ፡፡ ለምሳሌ ባልድራስ በጀርመን የሚያደርገውን ስብሰባ በተመለከተ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤንባሲ ተሰብሳቢዎቹ ላይ የማስፈራርያ ማስታወቂያ ሳወጣ የመረጃ ጋዜጣ አርእስት “በጀርመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት እሰጥ አገባ!” ዲሞክራሲያው የመሰብሰብ መብትን ጀርመን ድረስ ሄደው ኢትዮጵያዊያንን ለማሽማቀቅ እንዲህ አይነት መግለጫ በኢትዮጵያዊን ገንዘብ ተቀጥረው የሚስሩ የማስፈራርያ መግለጫ “እሰጥ አገባ” ነው ብሎ ሪፖርት ማድረግ ወራዳ የጋዜጠኝነት ተግባር ነው፡፡

Revelations
Senior Member+
Posts: 33729
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አብይ መሀመድ እያዳለጠህ ወደማጥ ከመገባት ተስተካከል፤ ተቃዋሚዎች ልብ አውጡ፤ ጋዜጠኞች የወያኔ ግዜ ዳንሳችሁን ለማሳየት አትሟሟቁ

Post by Revelations » 25 Jul 2019, 23:33

Please wait, video is loading...


Post Reply