Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
fana-solo
Member
Posts: 528
Joined: 11 Jun 2019, 01:43

በመሰረቱ "ኤርትራ" የውሸት ስምና ማንነት ነው። ሲጀመር ጀምሮ "ኤርትራዊነት" የፉገራ ማንነት ነው።

Post by fana-solo » 24 Jul 2019, 18:23




በመሰረቱ "ኤርትራ" የውሸት ስምና ማንነት ሲሆን፤የጣል-ያን ወራሪ ጦር በ፲፱ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ላካባቢው የሰጠው ስያሜ ነው። ይኼ ቦታ - ምድረ ባሕሪ፣ መረብ ምላሽ፣ ባህረ ነጋሽ አንዳንዴም ባሕር በመባል ነበር የሚታወቀው። በተጨማሪም ነዋሪዎቹ በየአውራጃቸው ስም የሚጠሩበትም ጊዜ ነበር - ሐማሴን፣ አካለ ጉዛይ፣ ሰራዬ፣ መንደፈራ፣ ሰንዓፌ ፣ በጎስ/ከርን...ወዘተርፈ... ተብለው በተናጠል ይታወቁ ነበር። ባጠቃላይ ሲጀመር ጀምሮ "ኤርትራዊነት" የፉገራ ማንነት ቀጥሎም አስቂኝ ዜግነት ሆኖ ነበር የከረመው። "ኤርትራ" የሚለው ስያሜ ራሱ መጥፎ እና ከይሲ የሆነ መንፈስ ባገሬው ነዋሪዎች ላይ እንዲሰረፅ ለማድረግ ከአንድ ምዕተ-ዓመት በላይ ብቸኛውን ሚና ተጫውቷል። በኢትዮጵይያ የውጭ ጠላቶች ጥንሰሳ እና ኩትኳቶ እዛው የሰሜኑ ግዛታችን አካባቢ የተተከለው የጥላቻ ርዕዮተ አለም፣ዋናው ግቡ ኢትዮጵያን ከባህር በር ለማራቅ እንጂ ራሷን የምትችል አዲስ አገር ለመፍጠር ታልሞ አልነበረም። እዛ አካባቢ ያለው ህዝብ ታሪኩ ከኢትዮጵያ መደበኛ ታሪክ እምብዛም የተለየ ሆኖ ወይም ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ የአገዛዝ በደልም ደርሶበት አያውቅም። በከረረው ዕብደታቸው ምክንያት ከተገነጠሉ በኋላም ከኢትዮጵያ ጀርባ ላይ ፈፅሞ ወርደው አያውቁም ነበር፤እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ነው ያሉት።በአፄ ኃይለስላሤም ሆነ በጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ሃይለማርያም ጊዜ የምድረባሕሪ ትግሬዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ተንቀባረው ይኖሩ ነበር። በዘመነ ትግሬ/ ዘመነ አረብ ደግሞ ዘመዶቻቸውና የእብደት አጋሮቻቸው የሆኑት ትግሬዎች መንጥረው ከኢትዮጵያ አባረሯቸው። በቀድሞዎቹ የመንግስት ስርዓቶች ጊዜ ያልተፈፀመውን የበደል አይነት፤ እብደት በገነነበት በትግሬዎቹ ዘመን ደግሞ ትግሬው በትግሬው ላይ ፈፅሞታል። እንግዲህ ይኼ ዕውነታ ከዘመነ ትግሬ/ዐረብ ትሩፋቶች ውስጥ አንዱና ጉልሁ ነው። አሁን ደግሞ መልሰው በገፍ እያስገቧቸው፣ እየተንከባከቧቸው፣ እያስተማሯቸው፣ ከሁሉም የበለጠ ደግሞ ከአለም አቀፍ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ለሚለገሰው የገንዘብ ድጎማ ማስገኛነት እየተጠቀሙባቸው ነው። ይኼንንም ማድረግ ከጀመሩ አስር አመት ሳይሞላቸው አይቀርም። ትግሬ አገር ውስጥ ራሱ ፭ የስደተኛ ጣቢያዎች ለምድረባህሪዎች ተመድበው ይገኛሉ። አንዳንዴም ያገሬው ትግሬዎች "ኤርትራ" የሚል የባርያ ስም ይዘው ከነዚህ ስደተኞች ጋር ወደ ሶስተኛ አገር በስደተኛነት ይጓዛሉ። የምድረ ባሕሪ ነዋሪዎች አጭር የህይወት ገፅታ በዚች የትዕይንተ ኩነት ቅንብር ትጠቃለላለች።የመጀመሪያው የዚህ ትዕይንተ ኩነት ክፍል የምድረ ባሕሪ ነዋሪዎች እንደሰርዲን በትንሽ ጀልባ ታጭቀው በባህር ላይ ሲንቀዋለሉ ሲያሳይ፤ የሚቀጥለው ክፍል ደግሞ ከባርነት ያመለጠች አንዲት ምስኪን ፍሬ ልጅ፣ ቅዥቢው መሪያቸው የሚፈፅምባቸውን በደል በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ትተርካለች። የሚገርመው ግን የምድረባሕሪ ነዋሪዎች አሁን አለንበት በሚሉት በዘመነ "ናፅነት" ጊዜ፣ "ባርነት" እና "ባርያ" የሚሉት ቃላቶች በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለነሱ ዋነኛ መገለጫ ስንኞች ሆነው መገኘታቸው ነው። ወይ መዓልቲ አለ ትግሬ........ይኼንንስ መቼ ለማየት እንበቃለን ብለን አሰብን - የሞተ ተጎዳ ፣ የሰነበተ ታዘበ እንዲሉ።