Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum



Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by Ethoash » 24 Jul 2019, 17:16


#etv በባዮቴክኖሎጂ ምርምር እስከ አርሶ አደሩ የሚደርሱ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡
የምግብ ዋስትናና የግብርና ምርምር በዘር ተኳር።።።።።።።።።።።።።this is state of the art ግብርና

gadaa2
Member
Posts: 2178
Joined: 15 Oct 2013, 15:40

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by gadaa2 » 24 Jul 2019, 18:19

Revelations wrote:
24 Jul 2019, 17:09
Interesting, except Oromo most Ethiopian ethnics exist in this map. Can you tell us when the so called Oromo/G arrived from Madagascar, how many submarine, or airplane was assigned who kicked them by millions from there(I mean Madagascar is island, and not possible to swim, aha, they are fish, some where it says they are fish and swam to Ethiopia, 5000 km ocean, what a surprise. I lost that skill of swimming now I should go back to my ocean. Yes we came out of Ocean too. Additionally, on which terimanl was Aba Baharey sitting to report a 500 years (he must have the age of Muse) of journey of the Cushite Oromo to Cush land. Aba Bahery doesn't exist just from all this report. As for the map, I can send you all to Yemen. We better respect each other and live in peace.

Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by Revelations » 24 Jul 2019, 18:34

ባጠቃላይ የኦሮሞ ጎሳዎች በፊት ከነበሩበት መኖሪያቸው ተነስተው በቡድን በቡድን በመሆን (በጎሳ) አዲስ ቦታዎችን ሲቆጣጠሩ የዛን ቦታ መጠሪያ በመቀየር በራሳቸው ጎሳ ስም ይጠሩታል። ለምሳሌ በጥንት ጊዜ አርሲ፣ ወለጋ፣ ኢሊባቦር፣ ወሎ ወዘተ የጎሳ ስሞች እንጂ የቦታ ስሞች አልነበሩም። በመሆኑም እነዚህ አካባቢዎች በኦሮሞ ጎሳዎች ከመያዛቸው በፊት የነበራቸው መጠሪያ ስም የተለየ ነበር ማለት ነው።

በንጉስ ዘርዓ ያዕቆብ ፣ በአፄ በእደ ማርያም፣ በአፄ ገላውዲውስ እና በአፄ ሰርፀ ድንግል ዜና መዋዕሎች ውስጥ የተጠቀሱትንና ነገስታቱ በኢትዮጵያን የተዘዋወሩባቸውን የቦታ ስሞች ብንመለከት የብዙዎቹ መጠሪያቸው ተቀይሯል። ለምሳሌ፦

– በፊት ፈጥጋር ይባል የነበረው አሁን አርሲ ተብሎ ይጠራል።

– በፊት ቢዛምና ዳሞት ይባል የነበረው አሁን ወለጋ ተብሎ

ይጠራል

– በፊት እናርያ የነበረው አሁን ኢሊባቦር ተብሎ ይጠራል።

– በፊት ላኮመልዛ የነበረ አሁን ወሎ ተብሎ ይጠራል።

– በፊት በፊት አንጎት የነበረው አሁን ራያ ተብሎ ይጠራል።

– በፊት ሽምብራ ቆሬ የነበረ አሁን አዳማ (ናዝሬት) ተብሎ

ይጠራል ወዘተ።




Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by Revelations » 24 Jul 2019, 18:44

ማስታዎሻ፦ የአካባቢ መጠሪያ ስሞች በኦሮሞ ጎሳዎች ፍልሰትና መስፋፋት ብቻ አልነበረም የሚቀየሩት ወይም የተቀየሩት። ለምሳሌ፡ ከጣልያን ወረራ በፊት ትግራይ እና ኤርትራ የሚባል የቦታ መጠሪያዎች አልነበሩም።

ትግራይ አንደ አንድ የአካባቢ መጠሪያ ክ 13ኛ ከፍለዘመን ጀምሮ አንደሚ ታወቅ ካርታው ያሳያል:: አፄ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ንጉሰነግስት ስለነበሩ አንደ የትግራይ ገዢ በታሪክ አልቀረቡም :: ኤርትራ የሚባለው አካባቢ ከትግራይ የተወሰደ አውራጃ ነው:; ከ 1896 ዓም በፊት አንደ ፈረጆቹ አቆጣጠር ኤርትራ የሚባል አካባቢ አይታወቅም: (ካርታዉና ጭማሪ ከአክሱም ፖስት )

*ትግራይ የሚለው መጠሪያ በአጼ ዮሐንስ iv ጊዜ እንኳን ያልነበረ የቅርብ ጊዜ ግኝት ነው። ከዛ በፊት “ትግሬ” በአውራጃ ደረጃ ነበር የሚታወቀው። በጠቅላይ ግዛት ስም “ትግሬ” ብለው መጥራት የጀመሩት ቀ/ኃ/ሥላሴ ናቸው። በወቅቱ ትግሬ የሚባለው በአሁኑ ሰዓት ትግራይ ተብሎ የሚጠራው ሁሉም ሳይሆን ሽሬ እና አድዋ ብቻ ነበሩ። ዛላንበሳ፣ ይሮብ፣ ተምቤ፣ አክሱም፣ አጋሜ እራሳቸውን ችለው በተናጠል የሚተዳደሩ ሲሆን ዘራቸውም (ጎሳቸው) አንዳቸው ኩሸ ሌላቸው ሴማዊ ናቸው። ሁሉም ትግሬ አይባሉም ነበር። የትግርኛው ቋንቋ ተናጋሪው የቀሩትን በተለይየመንገድ አፍኖ ስለያዛቸው እንጂ በትግራይም ሆነ በኤርትራ ውስጥ ትግርኛ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቋንቋዎች ይነገራሉ። ትግርኛ የሚናገር ሁሉ ትግሬ እንዳልሆነ ሁሉ ከአንድ በላይ ቋንቋዎችን ማለትም የኩናማ ቋንቋ፣ ትግርኛ፣ ትግረ ወይም የሳሆ ቋንቋዎችን መናገር ስለቻለ ያ ሰው ትግሬ ነው ብሎ መደምደም አይቻልም። አሁን ትግራይ በሚባለው ክልል የሚገኙት ኩናማ፣ ኢሮብ (ሳሆ)፣ ተምቤን፣ እንደርታ (አጋሜ) የሚባሉት አካካቢ የሚኖሩ ህዝቦች የአገው ወይም የኩሽ ህዝብ ዘሮች እንጂ ትግሬ (ሴሜቲክ) አይደሉም። ለምሳሌ ጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋ ዘራቸው (ጎሳቸው) ከአገው የሚመዘዝ እንጂ ከትግሬ አይደለም። ኤርትራ የሚለውን መጠሪያን ስንመለከት ደግሞ ከፋፋዩ ፋሽስት ጣሊያን ህዝቡን ለማደናገር የባህሩን ስም (Red Sea or Eritrea Sea) ለመሬቱ የሰጠው ነው። ማለትም ቀድሞ ባህረ ነጋሽ እየተባለ ለሚጠራው አካባቢ ጣሊያን ኤርትራ ብሎ አዲስ ስም አወጣለት ከጊዜ ወደ ጊዜ ህዝቡ የድሮውን እየረሳ አዲሱን እየለመደ ሄደ። ኤርትራ የባህር እንጂ የመሬቱ መጠሩያ አልነበረም። ሌላው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ኤርትራ የሚለው ቃል የቀይ ባህር (የውሃው) መጠሪያ እንጂ የሃገሩ ወይም የመሬቱ መጠሪያ አይደለም። ነብዩ ሙሴ እስራኤላውያንን ባህሩን ከፍሎ አላሻገራቸውም አንጂ በግብፅ መሬት ላይ ነበር።

የደቡቡን የሃገራችንን ክፍል ስንመለከት ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን። ለምሳሌ ቀደም ባሉት ዘመናት በጅማና አካባቢው፣ በከፋ፣ እናርያ (ኢሊባቦር)፣ ከንባታ፣ ሃድያ፣ ሲዳማ፣ አርሲ (ፈጥጋር)፣ ወላጋ (ቢዛምና ዳሞት) እና የመሳሰሉት አካባቢዎች እንደ ዘመኑ ከአክሱም kingdom ጀምሮ፣ በላስታ፣ በጎንደር እና በሸዋ መቀመጫውን ላደረጉት የኢትዮጵያ ዘውዳዊ መንግስታት ስር የሚተዳደሩ ነበሩ። በተለይ ከኦሮሞ ምስፋፋትና ስደት በፊት የሸዋ ዘውዳዊ መንግስት፣ ከንባታ፣ ሃድያ፣ ፈጥጋር (አርሲ)፣ ዳወሮ፣ ሜቶሎሜ (ዳማት) ግዛቶች እርስ በርስ በቀጥታ የሚገናኙ ኩታ ገጠም ነበሩ።

እዚህ ላይ ለማስታወስ ያህል በ14 ኛው ክፍለ ዘመን የሃገራችን ንጉስ የነበሩት የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ባለቤት ንግስት እሌኒ ከሙስሊም ቤተሰብ የሚወለዱና የዘር ሃረጋቸው ከደቡብ የኢትዮጵያ ከሃድያ ብሔረሰብ ነው። ግራኝ አህመድ ከኦቶማን ቱርክ ባገኘው እርዳታ ሃገራችንን ከላይ እስከ ታች ባመሰበት ጦርነት በርካታ የአማራ ሰራዊት በኢትዮጵያ ምድር ከጫፍ እስከ ጫፍ ደማቸውን ያላፈሰሱበት ቅንጣት መሬት አይገኝም። በዛ ወቅት የሃድያ ተወላጇ ንግስት እሌኒ አሊ ነበሩ ከፓርቹጋሎች ጋር በመጻጻፍ ወታደራዊ እርዳታ እንዲገኝ ያደረጉት። ስለዚህ ከአህመድ ግራኝ ወረራም ሆነ ከኦሮሞ ጎሳዎች ወደ አካባቢው ከመስፋፋታቸው በፊት ጀምሮ ሃድያ በሸዋ ነገስታት ስር መሆኗን እዚህ ላይ ማስተዋል ተገቢ ይሆናል። አጼ ምኒሊክ ወደነዚህ አካባቢዎች ያደረጉት ዘመቻ የወያኔና የኦነግ ካድሬዎች እንደሚያስወሩት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን የሸዋ ነገስታት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ከነዚህ አካባቢዎች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት ስለነበራቸው፣ በተለያየ ጊዜ የደም መስዋእትነት የከፈሉበት የአባቶቻቸው ሃገር ስለሆነም ጭምር ነው። በታሪክ ተጽፎ እንደምናገኘው እነ አፄ ገላውዲዎስ፣ እነ ራስ ሐልመልማልና የመሳሰሉት የተሰውበት ነገር ግን በቀነ ጎደሎ ግዛቶቹ ከአማራው የተነጠቁበት (የተነጠሉበት) ስለነበር ታሪካዊ ያባቶቻቸውን ግዛቶች ለማስመለስ፣ ዘመዳሞችን ለማገናኘት፣ የተቃጠሉና የወደሙ ገዳማትና አብያተ ቤተ ክርስቱያናትን ዳግም ለማቆም፣ ባጠቃላይ ተበታትና የነበረች ሃገርን የማሰባሰብና የማቅናት ዘማቻ ነበር።

አፄ ምኒልክ ወደ አንድ አካባቢ ሲዘምቱ “ሕዝብ በከንቱ እንዳያልቅና ሀገር እንዳይጠፋ አባቶችህ ለአባቶቼ እንደገበሩት አንተም በሰላም ለኔ ገብር፣ ይህንን ካደረክ ስልጣንህን እባርክልሃለሁ፣ በፍቅር እንኖራለን” የሚል ጥሪ አስቀድመው ለአካባቢው ገዢ/ ባላባት ይልኩ ነበር እንጂ በሰራዊታቸው ብዛት ታብየው በስሜትና በጀብደኝነት የሚነዱ አልነበሩም። የአካባቢው ገዢ ጥሪያቸውን በሰላም ከተቀበለ ስልጣኑን ባርከውለት አመታዊ ግብሩን ለመንግስት እንዲያስገባ አሳስበውት ሾመው ሸልመውት ይመለሱ ነበር። አጼ ምኒሊክ ወደ ጦርነት የሚሄዱት ሰላማዊው መንገድ ሲሟጠጥ ብቻ ነበር። እምቢ ባዩን ባላባት በመረጠው መንገድ በጦርነት ገጥመውት ከማረኩት በኋላ እንኳን ለሁለተኛ ጊዜ በሰላም እንዲኖር እድል ይሰጡት ነበር። ለምሳሌ የወላይታው ንጉስ ጦና እምቢ ብሎ ውጊያ ገጠመ። ተሸነፈ፣ በምኒልክ ተማረከ። ምህረት አደረጉለት። እሱም ዳግም እንደማይበድል ቃል ገባ፣ እሳቸውም ንግስናውን መለሱለት። ንጉስ ጦናም እስከ ህይወቱ ፍጻሜ ድረስ ከምኒልክ ጋር በፍቅር ኖሩ።

እንደሚታወቀው ጸረ አንድነቶች መልካም መልካሙን ታሪካችንን እየደበቁ ክፉ ክፉውን እያጋነነኑና እየቀጣጠሉ ስለሚነግሩን ነው እንጂ፣ ሃገርን በፍቅርና በስምምነት መምራት ተቀዳሚ ስራቸው ያደረጉት አፄ ምኒልክ በመነጋገር (በዲፕሎማሲ) ያለ ጦርነት ወደ አንድነቱ ህብረት ዳግም ያመጧቸው የኢትዮጵያ ግዛቶችና የጎሳ መሪዎች እጅግ ብዙ – ብዙ ናቸው።

ለምሳሌ ያህል በወለጋ፣ በጅማ፣ በአፋር፣ በምዕ/ምስ እና በደቡብ ሸዋ ይኖሩ የነበሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በየመንደሩና ጎጡ የሚገኙ በርካታ ባላባቶችን፣ የጎሳ መሪዎችን እና ገዢዎችን ያለምንም ጦርነት በሰላም የአጼ ምኒሊክን ንግስናን የተቀበሉና ወደ አንድነቱ ህብረት በፍቃዳቸው የተቀላቀሉ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አብዛኛዎቹ የምኒሊክ ወታደሮች ኦሮሞዎች እንደነበሩ ማስታወስ ተገቢ ነው።

የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ፣ የተለያየ ባህልና እምነት ያላቸውን ቁጥራቸው ከ80 በላይ የሆኑ የኢትዮጵያ ጎሳዎችን ያውም በዛ ኋላ ቀር በሆነበት ስልክም፣ ራዲዮም ሆነ ዘመናዊ መጓጓዣ በሌለበት ሁኔታ እነዚህን ህዝቦች አሰባስቦና አስማምቶ ሁሉንም የሚያካትት የጋራ ሀገር መገንባት እጅግ ውስብስብና ከባድ ነገር ነው። ከዚህ አንጻር አፄ ምኒሊክ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች (ጎሳዎችን) አሰባስበው አንድ የጋራ ሀገር መገንባታቸው ሳያንስ እነዛኑ በየጎጥ ታጥረው በትንሹ እያሰቡ እርስ በርስ ሲተራመሱ የነበሩ የአካባቢ ገዢዎችንና የጎሳ መሪዎችን ለትልቅ ሃገራዊ ራዕይ እና ለአንድ አላማ አሳምነውና አስተባብረው የአውሮፓ ቀኝ ገዢ ወረራዎችን መመከታቸው እጅግ የሚያስመሰግናቸው አኩሪ ሥራ ነው።

አፄ ምኒልክ ሀገር የማቅናትና የማደራጀት ከፍተኛ የሆነ ስራ በሚሰሩበት ጊዜ አውሮፓዉያን ሃገራችንን ጨምሮ መላው አፍሪካን በቀኝ ግዛት ለመቀራመት ያሰፈሰፉበት ወቅት መሆኑን ማስታወስ ይገባል። ስለሆነም ለአንድ አፍታ ያንን ጊዜ ለማሰብ ብንሞክር ንጉሱ ምን ያህል እጅግ ፈታኝ ጊዜ ውስጥ እንደነበሩና ያጋጠማቸውን ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች በጥበብና በትእግስት እንዳሸነፉ እንረዳለን። በጀግንነታቸው ብቻ ሳይሆን ባላቸው መልካም ስብእና እንኮራባቸዋለን።

የወለጋ ባላባቶችና የጎሳ መሪዎች ያለጦርነትና ኮሽታ የምኒልክን ንግስናን በሰላም የተቀበሉና ወደ አንድነቱ ህብረት በስምምነት የተቀላቀሉ ናቸው። አጼ ምኒልክም ቢሆኑ አማርኛንና ኦሮምኛን አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ፣ በምኒልክ የስልጣን እርከን ውስጥና በተዋጊነት እንዳልተሳተፉ ዛሬ ልጆቻቸው የኦሮሞ ህዝብ በምኒልክ እንደዚህ ተደርጓል በማለት በፈጠራ ታሪክ መጠመዳቸው፣ የንጉሱንና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት መቀባታቸው እጅግ የሚያሳዝን ነው። በአርሲ፣ በሐረርጌ … በዚህ ወይም በዚያ አካባቢ በሚኖሩ ኦሮሞዎች ላይ አጼ ምኒልክ ይህንን ተፈጽመዋል በማለት ያለመረጃ በቅብብሌሽ ወሬ ከሳሽ የመሆናቸውን ሚስጥር ከሚጠቁሙን ውስጥ የመጀመሪያው የኦነግ፣ የወያኔና የሻቢያን ግንኙነት ምክንያትን ማጥናት ሲሆን ሌላው ደግሞ በወለጋና አካባቢው የነበሩ የጀርመን ፕሮቴስታንት ሚሽነሪዎችን ታሪክ መመርመር ስንችል ነው።

ወለጋ አካባቢ ለረጅን ጊዜ በመኖሩ የኦሮምኛ ቋንቋ መናገር የሚችል ዮሐን ክራፍት የሚባል የጀርመን ፕሮቴስታንት ሚሽነሪና ሰላይ መጽሐፍ ቅዱስን ጀርመንኛን በሚጽፍበት በእንግሊዘኛ ፊደል (በላቲን ፊደል) በመጠቀም በኦሮምኛ ቋንቋ ተረጎመ (በነገራችን ላይ የቁቤ መነሻው ይህ ነው)። ይህ ዮሐን ክራፍት የተባለ ሚሽነሪ (ወንጌላዊ) ለተወሰነ ጊዜ ሸዋ ተቀምጦ በነበረበት ሰዓት ለአውሮፓ ቀኝ ገዢዎች ሲሰልል ተደርሶበት ከሃገር የተባረረ ቢሆንም ዳግም በኬንያ ሞምባሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገባ ነው። ከተወሰነ ጊዜ ሃገር ውስጥ ከቆየ በኋላ ተመልሶ ወጣ። የዮሐን ክራፍትን ዱካ ተከትለው የመጡ ሌሌች ሚሽነሪዎች (ወንጌላውያን) በእሱ መንገድ በመጓዝ በወለጋ ክርስትናን መስበክ እንደጀመሩ ህዝቡ ታቦት እያለ ቢያስቸግራቸው 10ቱን ህግጋት በእንጨት ላይ እየጻፋ ቤተ ክርስቲያን በማስቀመጥ ሰዎችን መሳብ ቻሉ። ት/ት ቤቶችን ከፈቱ። ት/ት ቤት መክፈቱ ባልከፋ ነገር ግን በርካታ የዘረኝነትና ጸረ ኢትዮጵያ መርዝ ተከሉ። የኦሮሞ ብሔረተኛ አስተሳሰብ ያላቸው ጽንፈኛ እንደ ኦነግ ዓይነት ያሉ ድርጅቶች መስራቾች አብዛኛዎቹ በወለጋ በዮሐን ክራፍት በተቋቋሙ የጀርመን የሚሽነሪ ት/ት ቤቶች ተኮትኩተው ያደጉ ናቸው።

ሌላው ደግሞ ግራኝ መሃመድ በሰሜኑ የክርስቲያን መንግስት ላይ የጀሃድ ጦርነት በማወጅ ያካሂድ ለነበረው ጦርነት አብዛኛውን ተዋጊ ወታደሩን ይመለምል የነበረው በምእራብ ሐረርጌ፣ በአርሲና በሃድያ (ባሌ) አካባቢ ከሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ነበር። እንደ ወለጋው የዮሐን ክራፍት ዓይነት ሃገርን ከማፍረስ ጎን ለጎን ቤተ ክርስቲያንን ማቃጠል ይሰበክበት ከነበረው አካባቢ ነበር የዛሬው የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኛ የሆነው ጁሃር መሐመድና ጓደኞቹ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አካባቢ ነው።

የኦሮሞ ፍልሰት ወይም መስፋፋት ከመጀመሩ በፊት ባሌ፣ አርሲ፣ የሸዋና አካባቢዎቹ ድረስ ይኖሩ የነበሩት አማሮች፣ ሃዲያዎች፣ ከንባታዎች፣ ጉራጌውምችና ሌሎች ጎሳዎች ነበሩ። በገዳ ባህላዊ ሥርዓት የሰለጠኑ የኦሮሞ ተዋጊዎች በጎሳ በጎሳ እየተደራጁ ወደዚሁ አካባቢ በመምጣት የቀድሞ ነባር (Native) ነዋሪዎችን በሃይል በማፈናቀል ወይም “ሞጋሳ” እና “ጉዲፈቻ” በተባሉ የኦሮሞ ባህል የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦችን ወደ ኦሮሞነት በመለወጥ (Oromization) መሰረት በርካቶች ኦሮሞ ሆኑ። ባጠቃላይ የሞጋሳና የጉዲፈቻ ባህል ኦሮሞነት ከዘር ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሚያሳይ ሲሆን ይህም ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ ያለውን የአካባቢውን ህዝብ የአሰፋፈርና የቋንቋው ሁኔታ (Demography) እጅጉን ቀያየረው።

ሌላው ደግሞ በወሎ የሚገኙ የየጁ ኦሮሞዎች ከአርሲ የመጡ ሙስሊም ኦሮሞዎች ናቸው። የአርሲ ኦሮሞዎች ታሪክ ወደ ኋላ ሄደን ከስር መሠረቱ ስንፈትሽ ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን። ከዚህ በላይ እንደተገለጸው ከኦሮሞ መስፋፋት ቀደም ብሎ የአርሲ አካባቢ ቀደምት ነዋሪዎች የጉራጌና የከንባታ ህዝቦች ነበሩ። እነዚህ የጉራጌና የከንባታ ህዝቦች በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ወደ ኦሮሞነት የተቀየሩ ናቸው። ከዛ ቀድሞ ብሎ እነዚህ የጉራጌና የከንባታ ህዝቦች በአህመድ ግራኝ ወረራ ወቅት ወደ እስልምና የተቀየሩ መሆናቸውንና፣ በኦሮሞ መስፋፋት ደግሞ ወደ ኦሮሞነት ተቀየሩ፣ በመጨረሻም ከአርሲ ወደ ሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ወደ ሆነው ወሎ በቀድሞ አጠራሩ ላኮሞንዛ በመሰደድ የጁ የሚባል ቦታ ሰፈሩ።

ወደ መካከለኛውና ምዕራባዊ የኢትዮጵያ አቅጣጫ ስንሄድ ደግሞ ወለጋን፣ ጎጃምን፣ ሰላሌንና ሸዋን ብንመለከት ተመሳሳይ የሆነ ታሪክ እናገኛለን። አሁን ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ የሙገር ወንዝን ይዞ፣ ኖኖና አማያን አካቶ እስከ ጅማና ጊቤ በርሃ ድረስ ይኖሩ የነበሩ ጋፋትና ዳማት (ቤቶሎሚ) የሚባሉ ጎሳዎች (Kingdom) ይኖሩ ነበር። ይህ ሁሉ የሚያሳየን እኛ ኢትዮጵያውያን በሃይማኖት፣ በዘር፣ በባህል፣ በቋንቋና በመሳሰለው የተደበላለቅን መሆናችንን ነው።

አሁን ካለው ወደ 35 ሚሊየን ከሚገመተው የኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ከላይ ከዘር ማንዘሩ ማለትም ከኦሮሞ መስፋፋትና ስርጭት በፊት ጀምሮ “ቅልቅል የሌለው ንጹህ ኦሮሞ” ነው ተብሎ የሚገመተው 7ሚሊዮን ቢሆን ነው የሚል ግምት እንዳለ የታሪክ ምሁር የሆኑት ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ በቅርቡ ከSBS ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ ገልጸዋል። ለምሳሌ ለኦነግ ወይም ኦህዴድ ስብስባ ከተገኙ 100 የኦሮሞ ብሔር አባላት ተሰብሳቢዎች ውስጥ 20 ብቻ ናቸው “ቅልቅል የሌላቸው ንጹህ ኦሮሞዎች” እንደማለት ነው። (ከ5ሰው 1ሰው ወይም 20%)።

አሁን ላለው የኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው ስለ ኦሮሞ ህዝብ ከኦሮሞ ውጭ ሌላው ኢትዮጵያዊ አይመለከተውም የሚል ካለ “አክሱም ለወላይታው ምኑ ነው” እንደማለት ያህል ነው። ስለ ኦሮሞ መናገርና መቆርቆር መብቴ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞና የአማራ አባቶች ዘመናዊት ኢትዮጵያን በጋራ አበጅተው የሰጡን የጋራ ውርሳችን ናት። ጽንፈኞቹ የፈለጉትን ቢቀባጥሩም የእኔ አቋም ግን ስለ ኦሮሞ ለመናገር መብት የሰጠኝ ኢትዮጵያዊነቴ ነው፣ አሁን ስላለችው ኢትዮጵያ ያለ ኦሮሞ ልገልጻት አልችልም። የኦሮሞ ህዝብ በአስተዳደሩ፣ በውትድርናው፣ በዘፈኑ፣ በስፓርቱ፣ በፓለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊ ህይወቱ ባጠቃላይ በዘመናዊ ኢትዮጵያ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ከአማራው ጎን ከፍተኛ ድርሻ አለው።

ኢትዮጵያን የጠሉ ሁሉ ምኒሊክን እየጠሉ ተቸገሩ እንጂ አፄ ምኒልክ በወሬ ሳይሆን በተግባር ለሃገራቸን ኢትዮጵያ እድገት፣ ብልጽግና እና ነጻነት ብዙ የደከሙ፣ ለዘመናዊነት በር ከፋች በመሆን በርካታ ስልጣኔ ወደ ሃገራችን ያስገቡ ታላቅ ንጉስ ናቸው። ዓለም አልሰለጠነም በሚባልበት በዛ ጊዜ ከ80 በላይ የሆኑ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችን በፍቅር አስማምተውና አስተባብረው የመሯትን ሃገር ዓለም በሰለጠነበት በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ወያኔና ኦነግ ዓይነት ጽንፈኛ ድርጅቶች ነገር ሲያምሱና ህዝብን እርስ በርሱ ከማጋጨት ውጭ ለትውልድ የሚጠቅም ነገር ሲሰሩ አልታዩም። ወያኔ/ህወሃት አጼ ምኒልክ በገነቡት በ4ኪሎ ቤተ መንግስት ተጎልቶ ስማቸውን ከማጥፋት ውጭ በአግባቡ ህዝብና ሃገር መምራት አልቻለም። =======//======

ደረጀ ተፈራ

(ውድ አንባቢያን፦ ይህ ጽሁፍ የግል ማስታወሻዬ ስለሆነ ስህተት ከተገኘበት ለማስተካከል ዝግጁ ነኝ)


Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by Revelations » 25 Jul 2019, 07:28

Inheritance

The rules of inheritance as given by d'Abbadie and de Salviac are as follows :
Among uterine brothers the eldest son is normally the heir to all his father's property,
the others getting no more than their father gives them in his lifetime. If there are
sons by different mothers, each gets something : the eldest two-thirds, and the others
two-thirds of what is left after each inheritance has been allocated ; for example, a
man leaves 54 cows and four sons ; the eldest son gets 36 cows, the second 12, the
third four, and the youngest two. Women cannot normally inherit, though it seems
that in the middle of the 19th century in Enarya, and also in Gera (where there was
a queen), women had authority over property and could inherit. 71 The inheritance
of other things, according to Azais and Chambard, is regulated as follows among
the eastern Galla : a man leaves to his eldest son his spear, a jar of milk, and a
heifer ; this bequest is called kolu. The eldest son also inherits his father's social
position and most of his authority over the rest of the family. Cecchi records that in
the Gibe States everything, including a man's title, is left to the eldest son ; other
sons lived in separate homesteads with the goods given to them by their father on marriage,
or by the king as rewards for bravery in war. When a man had no sons or
nephews, his property passed to the king.

Revelations
Senior Member+
Posts: 33713
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by Revelations » 25 Jul 2019, 12:05

MAIN CULTURAL FEATURES

Warriors wear on the forehead the genitals of enemies they have killed ; these may
also be hung over the door and left till they drop off.
18 For the most part the Galla
dp not wear ear-rings, 19 but Arusi men wear small copper rings in their ears, 20 and
Mata who kill elephants give gold ear-rings to their wives. 21 Necklaces range from
simple strings of beads to broad bands composed of numbers of such strings ; Arusi
women wear neckbands of hippopotamus hide. Men may wear a plain gut cord round
the neck. 22 Armlets are much worn, and ivory and horn armlets on a man always
denote recognition of bravery. The armlet called maldd may be worn only by those
who have killed five men, five buffaloes, and five lions 23 ; that called irbora or ilbora
is worn on the upper arm by men who have killed an elephant 24 or an enemy. 25 In
Wallaga both men and women wear circular ivory armlets of distinctive patterns,
some of those worn by men having alternating rings of white and darkened ivory ;
women were seen with six armlets of ivory and 42 of brass. 26 Arusi women wear
copper neck rings and necklaces of glass beads 27 ; men wear copper toe-rings and
large tin rings on the thumbs. 28

The Galla are fond of anointing their bodies with [deleted]. A man, however, must
earn the right to this practice ; not even his first success in battle gives him the right,
and in fact after this he is called ballesa (“ blunderer ”) till he succeeds in performing
a second act of bravery. Hence ballesa are much feared because of their eagerness
to acquire the coveted right to anoint their bodies. 29


mitmitaye
Member
Posts: 680
Joined: 29 Mar 2018, 15:18

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by mitmitaye » 29 Jul 2019, 08:38

gadaa2 wrote:
24 Jul 2019, 18:19
Revelations wrote:
24 Jul 2019, 17:09
Interesting, except Oromo most Ethiopian ethnics exist in this map. Can you tell us when the so called Oromo/G arrived from Madagascar, how many submarine, or airplane was assigned who kicked them by millions from there(I mean Madagascar is island, and not possible to swim, aha, they are fish, some where it says they are fish and swam to Ethiopia, 5000 km ocean, what a surprise. I lost that skill of swimming now I should go back to my ocean. Yes we came out of Ocean too. Additionally, on which terimanl was Aba Baharey sitting to report a 500 years (he must have the age of Muse) of journey of the Cushite Oromo to Cush land. Aba Bahery doesn't exist just from all this report. As for the map, I can send you all to Yemen.We better respect each other and live in peace.

MasbokatuN yeQoyiNa, Aba Bahrey did exist and reported about the ormo migration from Southern Ethiopia. His report is valid to this day.

European and Arab writers have also mentioned the tribes that lived in shewa and the south before Oromo migration.. anyway you can deny it all as a fable. But history books tells us there was Oromo migration to the north.

I never believed that 'Oromos came from Madagascar'. Oromos and somalis were part of Ethiopia. Lou tribe of Kenya, somalis and Oromos are Ethiopians.

The Ethiopian empire had expanded and shrunk through out history. But the nucleus of it, is what's to day Ethiopia. The Horne of Africa and some part of Kenya were part of Ethiopia.

You could see on the map around the southwest and southern areas of Ethiopia. There is lou, somal & Orma tribes. In this map, Kaffa was in Damot Empire, but around 17/18 century??, Kaffa had it's own kingdom..

So, borders do no mean much when it comes to define people's origin and their relation to their immediate neighbors 😉 human beings have moved around throughout history. It's the basic survival skill :idea: :idea:

mitmitaye
Member
Posts: 680
Joined: 29 Mar 2018, 15:18

Re: "ሞጋሳ - የዘር እና የባህል ማሳሻ መደምሰሻ ወይስ የወንድማማችነት ድልድይ?" - ክፍል ፩

Post by mitmitaye » 29 Jul 2019, 08:42

gadaa2 wrote:
24 Jul 2019, 18:19
Revelations wrote:
24 Jul 2019, 17:09
Interesting, except Oromo most Ethiopian ethnics exist in this map. Can you tell us when the so called Oromo/G arrived from Madagascar, how many submarine, or airplane was assigned who kicked them by millions from there(I mean Madagascar is island, and not possible to swim, aha, they are fish, some where it says they are fish and swam to Ethiopia, 5000 km ocean, what a surprise. I lost that skill of swimming now I should go back to my ocean. Yes we came out of Ocean too. Additionally, on which terimanl was Aba Baharey sitting to report a 500 years (he must have the age of Muse) of journey of the Cushite Oromo to Cush land. Aba Bahery doesn't exist just from all this report. As for the map, I can send you all to Yemen.We better respect each other and live in peace.

Masbokatu yeQoyiNa, Aba Bahrey did exist and reported about the ormo migration from Southern Ethiopia. His report is valid to this day.

Europeans and Arab writers have also mentioned the tribes that lived in shewa and the south before Oromo migration.. anyway you can deny it all as a fable. But history books tells us there was Oromo migration to the north.

I never believed that 'Oromos came from Madagascar'. Oromos and somalis were part of Ethiopia. Lou tribe of Kenya, somalis and Oromos are Ethiopians.

The Ethiopian empire had expanded and shrunk through out history. But the nucleus of it, is what's to day Ethiopia. The Horne of Africa and some part of Kenya were part of Ethiopia.

You could see on the map around the southwest and southern areas of Ethiopia. There is lou, somal & Orma tribes. In this map, Kaffa was in Damot Empire, but around 17/18 century??, Kaffa had it's own kingdom..

So, borders do no mean much when it comes to define people's origin and their relation to their immediate neighbors 😉 human beings have moved around throughout history. It's the basic survival skill :idea: :idea:

Post Reply