Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
fasil1235
Member
Posts: 1314
Joined: 01 Jul 2018, 08:58

FANO Vs ADP in Amhara

Post by fasil1235 » 23 Jul 2019, 13:18

FANO Vs ADP DEBATE


Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: FANO Vs ADP in Amhara

Post by Assegid S. » 23 Jul 2019, 15:16

በ“ለውጥ ማምጣት” እና በለውጥ ተጠቃሚ በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። መቼም አዴፓ ህይወቱም ሆነ ሞቱ ከሆዱ ጋር ክፉኛ የተቆራኘ ነውና … ለራበው ሰው፦ ምግብ በማብሰልና ያበሰለውን ምግብ በመመገብ መካከል ትልቅ ልዩነት እንዳለ ይገባው ይሆን? አሁን ትላንትና የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ሹመት ላየ ህዝብ ... የአዴፓ አደርባይነት “ያለፈ ታሪክ ነው” ተብሎ ይዋሻል ... በዋሺራው?

አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ “የፋሲል … የጣና … የአባይ … ወዘተ” እያሉ ለኣማራው ምክር-ቤት ጆግራፊና ታሪክ ሲያስጠኑ፣ "ሲላ፣ ተኩላ" ብለው ሲተርቱ፥ ተልኳቸውን ብቻ ሳይሆን ላኪያቸውንም አሳብቆባቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በየክልሉ ሲዞሩ በተለይም ደግሞ ደቡብ ላይ ያደረጉትን ንግግር በደንብ ላዳመጠ፦ በአቶ ተመስገን እና በጠቅላይ ሚንስትሩ የቃላት አጠቃቀምና የዓረፍተ-ነገር አደራደር ላይ ቀጥተኛ፣ በጣም ተቀራራቢ የጽሑፍ pattern ያወጣል። ምናልባት ልዩነቱ የበሬና የበግ፣ የጅብና የተኩላ፣ የሐይቅና የተራራ … እያለ ይቀጥላል። የእኔ መላምት እንግዲህ ሁለት ነው፦

ኣንድ፦ የአቶ ተመስገን ጽሑፍ ደራሲ / editor እራሳቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ ናቸው፤ አለበለዚያም
ሁለት፦ የጠቅላይ ሚንስትሩንም ሆነ የእኚህን ሰው ንግግር የፃፈው ሰው አንድ ግለሰብ ነው።

እንግዲህ ጥቅም ነውና … ቻለው ፋኖ። እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፥ አቶ ደመቀ መኮንንም ልጆቻቸውን አስተምረው፣ ኩለው፣ እስኪድሩ እዳህ ነውና “ጽናቱን ይስጥህ!” ልበልህ። ባይሆን ያኔ … ቤተሰቦቻቸውን ቦታ ቦታ ካስያዙ ቦኃላ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ይለቁልህ ይሆናል። እስከዛው ግን አሳርህን ብቻ ሳይሆን አስክሬንህንም ትቆጥራለህ።

አንድ የ Yoruba / የኣፍሪካ ምሳሌያዊ አነጋገር አለ፦ when the axe entered the forest, the trees said, "look, the handle is one of us!". “መጥረቢያ ወደ ጫካው ሲገባ፥ ዛፎች “ተመልከቱ … የመጥረቢያው ዛቢያ የእኛው አካል ነው አሉ” ነው ትርጉሙ። ወደ ግል ፍቺዬ ስመልሰው ደግሞ፦ ቆራጭ መጥረቢያ ወደ ጫካ ሲገባ፥ ዛፎች እጀታውን ብቻ ተመልክተው … ከስለቱ ጋር መዋሀዱን (ባንዳነቱን) ረስተው … “የእኛው አካል ነው!” ሲሉ ተረጋጉ። መታሰቢያነቷ ለአቶ ተመስገን ጥሩነህ



cartoon credited for: pbfcomics.com

Post Reply