Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12589
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

A lesson from Emperor Haileselassie to PM Abiy

Post by Thomas H » 22 Jul 2019, 18:04

ችግኝ ተክሎ ፎቶ መነሳት ብቻ ሳይሆን ችግኙን ውኃ ማጠጣትም ያስፈልጋል

Thomas H
Senior Member
Posts: 12589
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: A lesson from Emperor Haileselassie to PM Abiy

Post by Thomas H » 24 Jul 2019, 10:00

ዓብይ እና ችግኞቹ
ጉድጓድ ተቆፍሮ ይጠብቅሀል ፣ ባስ ኮንትራት ተይዞ ነዳጅ ተሞልቶ ከባልደረቦችህ ጋር ከከተማ ወጣ ወዳለ ስፍራ ትሄዳለህ ፣የታሸገ ውሃ በብዛት ተይዞ በመንገድ ላይ ሰልፊው ለጉድ ነው።

እዛ ስትደርስ የተዘጋጀልህን ምንነቱን የማታውቀው የዛፍ አይነት በተዘጋጀልህ ጉድጓድ ውስጥ ጣል አድርገህ ከባልደረቦችህ ጋር አየተሳሳቅክ ፎቶህን ተነስተህ በመኪናህ ትመለሳለህ ። ከተማ ውስጥ የምሳ ግብዣ ይኖራል። እሱን ጥብስቅ አድርገህ በልተህ እለቱ የስራ ቀን ቢሆንም እና ደሞዝህ የተከፈለህ ቢሆንም “በጣም ደክሞሀል” እና እረፍት ታደርጋለህ።

በዚህም ለሀገርህ ትልቅ ውለታ እንደሰራህላት “አረንጓዴ አሻራ ” እንዳሳረፍክ እየተሰማህ በከንቱ ኩራት ትወጠራለህ።

እነዚህ ጥያቄዎች ወደ ህሊናህ እንዲመጡ አትፈልግም…
– ጉድጓዶቹን የቆፈረው ጉልበት ሰራተኛ ለምን ችግኞቹን አይተክልም ነበር? የእኔ እጅ የተለየ ሀይል አለው?
– በእለቱ ለእኔ የወጣው ወጪ ለስራ ፈላጊ የጉልበት ሰራተኛ ተከፍሎት ቢሆን ከእኔ በተሻለ ሀላፊነት እና ጥራት ችግኞቹን ሊተክል እና ሊያለማ አይችልም ነበር?
–በዛ ቀን እንደልቤ እየጠጣሁ እንዳሻኝ የጣልኩት የውሃ ፕላስቲክ ምን ብክለት አስከትሎ ይሆን?
– የተከልኩት ችግኝ የሚገኝበት ስፍራ ተመልሼ የምሄደው መቼ ነው? ነገ ቦታው ለመኖርያ ቤቶች ወይም ለባለሀብት ላለመመራቱ ምን ማረጋገጫ አለኝ? አምና የተከልንበት ቦታ ተመንጥሮ ሼድ አልተሰራበትምን?

Post Reply