Page 4 of 4

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 01 Sep 2019, 00:36
by Horus
በኢትዮጵያ የጎሳ ፌዴሬሽን መፍጠር አይቻልም

በጎሳ ፌዴሬሽን ወስጥ መተማመን በፍጹም ሊኖር አይችልም። በኢትዮጵያ ውስጥ ፌዴሬሽን የሚለው ቃልና ጽንሰ ሃሳብ ምናልባት ከ60 አመታት በላይ እድሜ አለው፤ ከኤርትራ ፌዴሬሽን እንኳ ብንጀርምር። በአሁን ሰአት በየቀኑ ይህን ቃል ሳንሰማ አንውልም። ነገር ግን አንድም ቦታ ስለዚህ ቃል ሆነ ስንጸ ሃሳብ እውነተኛ ትርጉም ሲጠቀስ ስምቼ አላውቅም ።

ፌዴሬሽን ምን ማለት ነው? የቃሉ ስረ ምንጭስ ምንድን ነው? ለመሆኑ የጎሳ ፌዴሬሽን በእውን በተግባር ሊኖር ይችላልን?
ፈደረ ማለት አመነ ማለት ነው፤ ማለትም ፈደርነት እምነት፣ ኪዳን፣ ማመን፣ አንድን ነገር እንደ እውነት መቀበል፣ አንድን ነገር ማተለቅ፣ ማግነን፣ ማክበር ማለት ነው። ሰው ከአምላኩ ጋር ያለው አንድነት በኪዳን፣ በፈደር፣ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው። ማህበርተኞች እቁብ የሚጠጡት በፈደር፣ በእምነት ላይ ተመስርተው ነው። ስለዚህ ያለ እምነት፣ ያለ መተማመን ፌዴሬሽን የሚባል ጽንስ፣ ልምድም ሆነ ንድፈ ሃሳብ በአለም የለም።

ስለሆነም በአላማ፣ በቁጥር፣ በባህል፣ በራእይ ሆነ በፍላጎት የተለያዩ ብቻ ሳይሆን የሚጠርጠሩ፣የሚፎካከሩ፣ የሚጣሉ ጎሳዎች በእምነት፣ በኪዳን በመተማመን ቃል ኪዳን ላይ የተመሰረተ ህብረትም ሆነ መንግስት ሊያቆሙ አይችሉም። ራሱ የፌዴራላዊ ህብረትም ሆነ የጋራ መንግስት ሊያቆሙ የሚችሉት በፈጣሪም ሆነ በሕግ ፊት እኩል የሆኑት የኢትዮጵያ ግለሰቦች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈለገው አይነት ፌዴራሊዝም ሊቆም ሊጽና የሚችለው በኢትዮጵያ ዜጋዎችና በዜጋ ፍልስፍና፣ በዜጋ ፖለቲካ ንድፈ ሃሳብ እና በዜኘት ካልቸር ላይ ነው።

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 07 Sep 2019, 21:17
by Horus
..……………………………………………………………………………...

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 10 Sep 2019, 23:20
by Horus
ይህን ራሱን ያስተማረ ድንቅ ምሁር ከዳር እስከ ዳር ስሙት !!! በዚህ ሃረግ ከላይ ያነሳትህን ችግር እምርቱ ላይ እሳየን ነው


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 16 Sep 2019, 23:52
by Horus
የጠ/ሚ አቢይ የከፋ ውሎ ሙሉውን ተከታትዪዋለሁ ! የከፋ ህዝብ ስልጡንነትና መረጋጋት እጅግ ደስ ይላል !! ያዲሱ ካልቸር ምልክት !!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 21 Sep 2019, 01:51
by Horus

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 24 Sep 2019, 12:54
by Horus
..……………………………………………………………………...

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 03 Feb 2020, 23:34
by Horus
ዛሬ 2020 አ/ም ነው ። ይህን ነገር የጻፍኩት የዛሬ 25 አመት አካባቢ ነው ። ይዛሬን ያቢይ ያፓርላማ ው ሎ ስከሰማሁ በኋላ አሁንም እንድታነቡት ወደ ላይ ስቤዋለሁ


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 08 Feb 2020, 01:02
by Horus
እዚህ አስተያየት ውስጥ ለማለት እንደ ሞከርኩት የጎሳ ርዕዮትና የጎሳ ፖለቲካን ወደ ትክክለኛ አቅሙ ለማውረድ እና ዘረኘትን ከፖለቲካ መድረክ ለማውረድ የኢትዮጵያ ሕዝብ እያንዳንዱ በመስኩ ቆራጥ ትግል ማንሳት ግድ ይለዋል ። እንሱም በእምነት፣ በካልቸር፣ በቋንቋ፣ በንግድ፣ በፊሎሶፊ፣ በሙዚቃ ፣ቲያትር ወዘተ: ወዘተ


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 03 Mar 2020, 23:48
by Horus
እኔ እንደ ዛሬም ደስ ብሎኝ አያውቅም ። የዚህ ሃረግ ትችት የጻፍኩት በሴጵቴምበር 2፣ 1995 (በፈረንጅ) ነበር ። ከ24 አመት በኋላ ያነሳሁት ችግር እንዳለ ስለነበር ከ8 ወር በፊት እዚህ ላይ ፖስት አደረጉት ። አሁን የት/ት ካሪኩለም ማሻሻያ ተደርጎ የሚከተለውን ሰማሁ ። ይህ ትልቅ ዜና ነው። አገራችህን ተስፋ አላት ። ኬር !!!
viewtopic.php?f=2&t=211630