Page 2 of 4

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 28 Jul 2019, 01:33
by Horus
beekaa

ትራይብ ሁሉ አገር ዪሆናል የሚለው ካውሮፓ መጽሃፍ የተወሰደ እንጂ ከኢትዮጵያ ትራይቦች የተወሰደ እውነታ አይደለም። አበሻ ስለ ራሱ ሲጠየቅ ሁል ግዜ ያውሮፓን ልምድ እንደ አቢነት ይጠቅሳል ። ይህ አይሰራም ። ያፍሪካ ትራይቦች ኔሽን ስታተ የሆኑ የሉም። ኔሽን ስቴት እምነት ነው እንጂ የዘር ጎሳ ስብስብ አይደለም። አፊካዎች ኔሽን ስቴት የመሆን እምነት ሊያሳድጉ ብዙ የቀራቸዋል ። የኢትዮጵያም ምሁራን ገና ትምህርት ይወሳዳሉ !

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 28 Jul 2019, 03:39
by Horus
ጎሳ፣ኔሽን፣ ወዘተ ያንድ ህዝብ እምነት ነው። እምነት የሌለው ሕዝብ ምንም አይደለለም። አትዮጵያ አንድ ትልቅ ገናና አገር የምትሆነው እኛ ያ እንድትሆን ስለምናምን ነው ።

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 28 Jul 2019, 05:11
by Degnet
Horus wrote:
20 Jul 2019, 01:57
(ይህ ሃተታ በ9/2/1995 ለER መጽሄት ልልከው ከጻፍኩት በኋላ ተረስቶ ዛሬ እንዳጋጣሚ ሳነበው አሁንም ያለውን ሁኔታ ስለሚያሳይ ምንም ሳልቀይር እነሆ ከ24 አመታት በኋላ። ሃተታው ረጅም ስለሆነ ለመደምደምያው ታገሱ)

የጽሁፉ መቋጫ የቀድሞ ኢትዮጵያም የቀድሞ ጎሳዎችም ወደ ዘመናዊነት በሚደረገው አድካሚ ጉዞ ይለወጣሉ፤ አሁን የምናየው ሁሉ ግዜያዊ ነው። በዚህ የሽግግር ውጥንቅጥ መሪና አሸናፊዎቹ እጅግ አዲስና ያልታየ መፍትሄ ማመንጨት የሚችሉት ፈላስፎች፣ ነዳፊዎች፣ ሃሳቢዎችና የኪነት ፈጣሪዎች ናቸው የሚል ነው ።

ኢትዮጵያ መሰረታዊ የውድመትና የድቀት አደጋ አለባት እላለሁ ። ይህን ስል ምን ማለቴ ነው?

አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአካል አይወድሙም፤ አይጠፉም። እንዲያውም በሚቀጥሉት ሰላሳ አምስት አመታት ወስጥ የሕዝባችን ቁጥር ከ55 ሚሊዮን ወደ 140 ሚሊዮን ያድጋል። የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ ስርዓታት ተሽካሚዎችና አንቀሳቃሾች ይህ ሕዝብ ነው። ሆኖም አሁን ካለው ሕዝብ የተወሰኑት በሽግግሩ ወቅት ይጠፋሉ። ሽግግር ስል ግዙፉን ወደ ዘመናዊነት የሚደረገው አስቸጋሪና ዝብርቅርቅ ሽግግር ማለቴ ነው ። በሽሽግሩ የሚወድሙት ግን ከፊሉ ብቻ ናቸው።

በኢትዮጵያ ካሉት ብዙ ጎሳዎች አኳያ ወደ ዘመናዊነት በሚደረገው ሽግግር ወቅት የሚወድሙት ማህበረ ሰቦች የተኞቹ ናቸው? ከወድመት የሚድኑት ከመጥፋት የሚተርፉት በምን በምን ምክንያቶች ነው? በመሰረለቱ ከውድመት የሚድኑት ሕዝብ ሆኑ ጎሳዎች አሁን ከሚያምኑበት የጥፋትና የቀውስ ባህል እየከዱ ወደ አዲስ አስተሳሰብና ባህል የሚዞሩት ናችው። ይህን መሰል እውቀትና ችሎታ የሌላቸው ግለሰቦች፣ ጎሳዎችና ቡድኖች ወዳሚዎች ናቸው። ስለዚህ የዘመኑ ቀውስና ብሶት የሚጠይቀውን ለውጥ ለማድረግ ችሎታ ያላቸው ክፍሎች ግዙፉን ሽግግር ያልፋሉ፤ ያልቻሉት ይወድማሉ። አሁን ያለው ሞራሉ የላሸቀው ሰው አዲስ ነገር አይፈጥርም።

ሁለተኛ፣ ስለ ኢትዮጵያ ውድመት በሚጠቀስበት ወቅት ሌላው ግልጽ ነገር ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ የፈጠሯቸው ቁሳዊ ባህላት፣ ቁሳዊ ግንባታዎች ሁሉ አይደመሰሱም። የፈጠሩት ሳይንስ ሆነ ቴክኒክ ሁሉ አይወድምም። ሆኖም ከቁሳዊ ባህላችን፣ ከልማት ውጤቶች ከፊሉ በሽግግሩ ጦርነት፣ አብዮት፣ አናርኪና ሁከት ይወድማሉ። ከውድመት የሚድኑት ቁሳዊ (ለምሳሌ ቤቶች፣ መንገዶች፣ መኪናዎች) ከእሴታዊ ምንነት ጋር ብዙም የተቋለፉ አይደሉም። ለምሳሌ ለዘውድ አገዛዝ የታነጸው ቤተ መንግስት ለኮሚኒስት ፓርቲና ለወያኔ መሰብሰቢያ ያገለግላል። ፈንጂ ለጥፋትም ለማእድንም ያገለግላል። ስለዚህ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ የተፈጠሩት ቁሳዊ ባህላት ሆነ ተቋማት አሁን ለጎሳ ስርዓት ግንባታ መገልገያ ተደርገዋል። ምንነትና እሴት እና የነሱ ተሸካሚ የሆነው ቁሳዊ መሳሪያ ያላቸው አንድነት እጅግ የላላ ነው። ቴሌቪዝን ሃይማኖትም ሌብነትም የሰበክበታል። እነዚህ ቁሳዊ መሳሪያዎች የአዲሱ ስርወ እሴት አገልጋይ ይሆናሉ።

ሶስተኛ፣ ከዚህ ቀደም በፌውዳሉ ስርዓት ስር ተዋቅሮ የነበረው የመላ ኢትዮጵያ ስርወ እሴት መዝቀጥና መፍረስ የሁሉም ባህልና ማህበራዊነት መፍረስ ወይም መበታተን አይደለም። ቀድሞ ያልተዋሃደ ነገር ሊበተን አይችልም። ስለዚህ የዘመኑ የጎሳ ስርወ እሴት ድሮ የነበረውን የጎሳዎች ልዩነት አጽድቋል፣ አጠናክሯል፤ እስከ ተወሰነ ድረስ እያደጉ የነበሩ የመላ ኢትዮጵያ እሴቶችን ሰባብሯል። ሆኖም ተጽዕኖው የተወሰነ እንጂ ጠቅላላ መበታተንና ዝቅጠት ሊሆን አይችልም። ጠበብ ብሎ በሴምና ባማራው ዙሪያ ያደገው ባህል ስሜታዊ ሆነ ሳይንሳዊ እስከ ተወሰነ ድረስ ተለውጦ ስፋት እያገኘ ነው። ግን ይህ ምን አይነት ባህል ነው?

አራተኛ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እሴትና ምንነት ወይም ማንነት በጎሳ እሴትና ማንነት እየተተካ ሲሄድ ወይም መሄድ ማህበረሰባዊና ባህላዊ ፈጠራን ማለትም ስልጣኔን ቀጥ አድርጎ አቁሟል፤ ያቆማልም። የተፈጥሮ ስይንቲስቶች እና ቁሳዊ ፈጣሪዎች የሚሰሩለት አገራዊ ፋይዳ ሆነ ትርጉም ከጠፋ ወዲህ ስራ አቁመዋል። በመንቀሳቀስ ላይ ያለው የጎሳ ባህል፣ ተረት፣ ታሪክና አፈታሪክ የሚቆፍረው ጠባቡ የሶሻል ሳይንስ ምሁር ብቻ ነው። በአንጻሩም ለኢትዮጵያዊነት የሚሟገተው የሶሻል ሳይንስ ምሁር ፖለቲካዊና ታሪካዊ ክርክር ያደርጋል። ክዚህ ውጭ የጎሳ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂ የሚባል ነገር ስለሌለ ሳይንሳዊ ፈጠራ ከእሴትና ምንነት እጦት የተነሳ ወድቋል። ይህ መቼም ትልቁ ቀውስ ነው። ይህም ሆኖ በተፈጥሮ ሳይንስ ዙሪያ እያቆጠቆጠ የነበረው ምሁር ሲበተን ጠንካራ ብሄራዊ ምሁራን በሃይማኖት፣ በፍልስፍና በስነ ፖለቲካ ዙሪያ ተነስተው ብሄራዊ ፈጠራ ሊያደርጉ አልቻሉም።

ይህ ሁለገብ ዝቅጠት እጅግ አሳሳቢው ቀውስ ነው። በኢትዮጵያ ወስጥ ለብዙ ግዜ ብሄራዊ ሳይንሳዊ የፈጠራ እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም፤ አገራዊ እሴትና አለኝታ ጠፍቷልና። በማህበራዊ ፍልስፍና መስክም ተመሳሳይ ቀጥ የማለት አደጋ አለ ። በአጠቃላይ አገራዊ የሆኑት የፍልስፍና መሰረቶች ማለትም የግለሰቡ ሰብአዊነት፣ እና መደባዊ ህብራዊነት በዘር ጽንስ ስለተሻሩ ጎሳ በተሰኘው የቡድን ጽንስ ዙሪያ አንድም የረባ ፍልስፍና ሊነሳ አይችልም ። የጎሳ ጽንስ ቅድመ ፍልስፍና ስለሆነ፣ ቅድመ ሰብአዊነት ስለሆነ። ስለሆነም ሶሺያ ፊሎሶፊም ከፍተኛ ዝቅጠት ወስጥ ይግኛል። ሌላው ቀርቶ መንፈሳዊ ፍልስፍና እንኳን ሊያቆጠቁጥ አልቻለም።

አምስተኛ፣ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሳይንስ ቀውስ አለ። የጎሳ ጽንሰ ሃሳብም ሆነ የጎሳ እንቅስቃሴ ማህበራዊ ወይም ሶሺያል ሳይንስ የለውም። ይህ አዲስ ተብዬ ፖለቲካም በጭለማ ውስጥ የሚደረግ ሙከራ ነው። ጠባብ የፖለቲካ መሃንዲሶች የሚያጨማልቁት ሙከራ ነው። ብሄራዊ ሶሺያል ሳይንሱ ስረው መሰረቱን በደንብ ለውጦና ግልጽ አድርጎ የፈጠራ ንቅናቄ ማድረግ ተስኖት ቆሟል። የሶሺያ ሳይንስ ቀውሱ የጀመረው በሃይለ ስላሴ ዘመን ነበር። የዘውድ አገዛዝን ዘመናዊ ለማድረግና ለምዕራብ ተቀባይነት ለመስጠት ሲሞከር የተፈጠረ ውዥንብር ነበር። ስለዚህ በዘውድ አስተሳሰብና በሊብራል ዴሞክራሲ መካከል የተነሳው ቀውስና ውዥንብር እልባት ሳያገኝ የአብዮቱ ዘመን መጥቶ ሁለቱም (የመለኮታዊም ሆነ የሕዝባዊ ሃይል አስተሳሰብ) ከመድረክ አስወገዳቸው።

ሶሺያሊዝም እየተባለ ይታወቅ የነበረው የተሳሳተ ወታደራዊ አገዛዝ በአንድ ቃል የፖለቲካ ሃተታ ወይም ትንተና ከህብረተሰቡ እንዲጠፋ አደረገ። ወታደራዊ የቡድን አገዛዝ ከሶሻሊዝም ጋር እንደ ተምታታ ሁሉ ዛሬ ደግሞ የጎሳ አስተሳሰብና ርዕዮት ከዴሞክራሲ ጋር እየተምታታ ቀርቧል። ስለሆነም በጎሳ አስተሳሰብ መግነን ሳቢያ አዲሱ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ትልቅ ቀውስ እንዲወድቅ ተደርጓል። ዘመናዊ ዴሞክራሲና ጎሰኝነት እስካልተለያዩና ዴሞክራሲ ከጎሰኘነት እስካልጸዳ ድረስ በኢትዮጵያ የሶሺያል ሳይንስ ቀውስ አያበቃም።

ሌላው ትልቁ የኢትዮጵያ ቀውስ የስነ ጥበብ ውድቀት ነው። እነሱም ስዕል፣ ጠረባ፣ ሙዚቃ፣ ስነጽሁፍ፣ ውዝዋዜ፣ ቲያትር፣ ሲኒማ፣ ዚቅ፣ አርኪቴክቸር ወዘተ ። ቀደም ሲል የነበሩት ጠቢባን እያለቁ ነው። አዲስ የሚፈጠሩት አብዛኞቹ ዋጋ ቢስ ናቸው፤ ጥልቀትና ንቃት የላቸውም። ብሄራዊ ራዕይና ስረው እሴት ላይ የተመሰረተ ፈጠራ ሳይሆን ከዚህም ከዚያ የተለቃቀመ፣ ከምዕራብ የተገለበተ የተቀዳ ስራ ነው ።
የቀረው ከጎሳዎች ግላዊ ባህል፣ ሙዚቃ ወዘተ ጋር የተያያዘ ነው ። የኪነትና የስነት መስክ በውራጅ ፈጠራ ተጥለቅልቋል ። እዚህ ላይ ተደጋግሞ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ኪነትና የኢትዮጵያ ስነ ጥበብ የሚባል ነገር አለ ወይ የሚለው ነው? ወይስ የ90 ብሄረ ሰቦች ስብስብ ጥርቅም ስነ ጥበብ? ይህ ያልተመለሰውና አወዛጋቢው ጥያቄ ነው።

ሌላው ትልቁ የኢትዮጵያ ቀውስ ሕግና ስነምግባር (ኤቲክስ) የተመለከተ ነው። በአንደኛ ደረጃ ዘመናዊ ወይም በተዋሃደ መልኩ የኢትዮጵያን ሕግና ስነምግባር የምንላቸው በምዕራቡ ግፊት የገባው እጅግ አለማዊና አምባገነን ባህል ሳቢያ ለብዙ አመታት የተከሰተ ኢሕጋዊነት ወይም የሕገወጥነት ክስተት አለ። ይህ የሕገወጥነትና የስነ ምግባር (ሞራል) ብልሹነት በአገሪቱ ለዴሞክራሲ አለመኖር ብቻ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ በብሄረሰቦች መካከል የነበረውን ግንኙነት የመነጨም ነው። በተለይ ስነምግባር በተመለከተ የ90ቹ ጎሳዎች ግላዊ ኤቲክስ አለመዋሃዱና አንድ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ስነምግባር አለመፈጠሩን ያመለክታል።

በዚህ መስክ ያለው ቀውስ እጅግ አሳሳቢ የሚሆነው የተለያዩ የብሄረ ሰብ ሴራዎችና ስነምግባራት መኖራቸው ብቻ አይደለም። የሕግ አለመከበር፣ የሃይል መግነን፣ በስልጣን መባለግና ፍርደገምድልነት፣ እኔባይነት ሌሎችን ማፈን በሃይል ሌሎችህን ማንበርከክ የዛሬን ጥቅም ባይነት ብቻ (ሄደኒዝም) እና አፍራሽነት የደምሳሽነት አመለካከት (ኒሂሊዝም) የመሳሰሉት የሁሉንም ብሄረሰብ አኗኗር ስለሚያቃውሱ አደገኛነታቸው ህብረባህል ከመሆን የባሰ ነው።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ቀውሶችን እናስተውላለን። አንደኛው የመላ ኢትዮጵያ አንድ ወጥ ስርዓት፣ እሴት፣ ባህል፣ ለማስተባበር ለማዋሃድ የሚሞክረው አዝማሚያ ነው። ይህ አዝማሚያ የተበተነና አቅጣጫ የለሽ መሆኑ ነው። ሁለትኛው የእያንዳንዱ ጎሳ እሴትና ባህል ቁንጽል ብቸኛ መሆንና በሌሎች ተቀባይነትን ማጣት እንዲሁም በዘመናዊነት መመታቱ ነው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ እሴት የላትም፤ ያለውም በምዕራብ ዘመናዊነት ተቃውሷል። የጎሳው እሴት አንዱም ለብሄራዊነት ብቃት ማጣቱ ብቻ ሳይሆን እሱም በዘመናዊነት ተቃውሷል። በሶስተኛ ድረጃ በኢትዮጵያ እሴትና (ካለ ማለት ነው) በጎሳው እሴት መሃል ያልተቋለጠ ግጭት ይካሄዳል። እነዚህ ሶስት ክስተቶች ሕግን፣ ስነምግባርን፣ ዴሞክራሲን፣ አስተዳደርን፣ አደረጃጀትን፣ ወዘተ ሁሉ ያካልላሉ። ለዚህ ደግሞ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ የለንም።

በሌላ ደረጃ እየተከሰተ ያለ መሰረታዊ ችግር አለ። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ ብሔራዊ እሴትና ባህል አለመፍጠሯ፣ በ90 ብሄረሰብ ባህሎችና በብዙ ሃይማኖቶች መከፋፈሏ ብቻ ሳይበቃ በተለይ ከምዕራቡ ዘመናዊነት ጋር የተቃመሱት የጎሳ ባህላትም የስሜታዊነት ጥራዝነጠቅነት ብልሽት ደርሶባቸዋል። ያጭር ግዜ ድል፣ ደስታ፣ ተንኮልና አፍራሽነት በሁሉም ባህላት ዘንድ እሴቶች ሆነዋል። ስለዚህ ስርወ እሴት ያጣው የኢትዮጵያዊነት ባህል (ካልቸር) ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ጎሳም ተመሳሳይ ቀውስ አጋጥሞታል። ከዚህ ሁለገብ የሆነ ቀውስ ለመውጣት ሰዎች ግዙፍ የሆኑ የእምነት፣ የአንድነት፣ የትብብር፣ የፍቅር እሴቶችን ከመሻት ይልቅ በግላዊና ቡድናዊ የታሪክና የህላዌ ምርምር ወይም ቁፋሮ ላይ ስለተጠመዱ እጅግ ቅጥ ያጣ የአመለካከት ጥበትና ውዥንብር በህብረተሰቡ ሰፍኗል። ስለሆነም ኢትዮጵያ የረዥም ግዜና መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችላት ብሩህ አመለካከት፣ ብሩህ ራዕይ የላትም፤ በምሁሮችዋ ማለት ነው።

ስለዚህ ግዙፉ የኢትዮጵያ ሽግግር ከየት ወዴት የሚሄድ ሽግግር ነው? የሚለው በፍጹም ግልጽ አይደለም። ከአንድነት ወደ መበተን ወይስ ከመበተን ወደ አንድነት? ወደ አለማዊነት ወይስ ወደ መንፈሳዊነት? ከእምነት ወደ ሳይንስ ወይስ ከሳይንስ ወደ እምነት? ከጎሳዊነት ወደ ዜግነት ወይስ ወደ ባሰ ዘረኝነት? ከኢሰባዊነት ወደ ሰባዊነት ወይስ ሌላ?

ይህን ግዙፍ ሽግግር ለምፍጠር በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፊሎሶፊ፣ በሶሺያል ሳይንስ በተለይ በፕለቲካ ሳይንስ፣ በስነ ጥበብ፣ በሕግና ስነምግባር መስኮች ሊመሩ የሚችሉ የሃይማኖት፣ የሳይንስ፣ የስነት፣ የስነ ህብረተሰብ መሪዎች ኢትዮጵያ የሏትም። መፈጠር ያለበትና ሊፈጠር የሚታሰበው እምነትና ንድፈ ሃሳብ መብላላት አልጀመረም፤ ሲብላላ አይታይም።

ከላይ የቀረበው ሃተታ የሚያመለክተው ጉዳይ ቀደም ሲል በትንሹም ቢሆን በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትና በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ ተገንብቶ የነበረው የባህልና እሴት መለኪያ (ደረጃው) እጅግ መዝቀጡን ነው። የብሄረሰቦች ፉክክር ከሰፈነ ወዲህ አገሪቱ ባህላዊና እሴታዊ ህብረተሰብ መሆኗ ጠፍቶ የምዕራብና የምስራቅ ሸቀጣ ሸቀጣዊ ባህል በገፍ የሚራገፍባት ገበያ ሆናለች። በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እንጂ አገር መሪዎች የሉም። የዜጋዎች ደህንነት ባገር አቀፍ ድህነት ማለትም የእምነት ድህነት፣ የፍልስፍና ድህነት፣ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና የፈጠራ ድህነት፣ የሶሻልና ፖለተካ ሳይንስ ድህነት፣ ተዉጧል። በስነ ጥበብ ማለትም በስዕል፣ ጠረባ፣ ሙዚቃ፣ ስነጽሁፍ፣ ቲያትር፣ ውዝዋዜ፣ ስነሲኒማ፣ ስነፎቶ ሁሉ ድህነት፤ በሕግና ስነምግባር ድህነት ጭምር የታጠረ ሁኖዋል። ህብረተሰቡ በጥቂት ያልተማሩ ሃብታሞችና በብዙሃን ያልተማሩ ድሆች ተከፋፍሏል። ከላይ የተዘረዘሩትን መስኮች ሊፈጥር የሚችለው ምሁር ወይም ተሰዷል፣ አለያም ፈጽሞ የለም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን በአይምሮዋቸው የሚሰሩ ሕዝቦች ሳይሆኑ መደባዊ ክፍፍሉ በሚበሉና በሚራቡ ሰዋዊ እንስሶች መካከል ነው። ይህ ሰቆቃ (ትራጀዲ) እንጂ ሽግግር አይደለም።

ከዚህ መቀመቅ እንዴት እንደሚውጣ የሚያሳይ ብርሃን አለን? ለኢትዮጵያ ወድቀትና ወድመት ምክንያት አገሩ ቀውስ መሆኑ ብቻ ኣይደለም። ከፍተኛ ያስተሳሰብና የመመራመር ድርቀት አለ። ከፍተኛ የፈጠራ አልባነት ጭለማ ሰፍኗል። ትልቁ ችግር የድንቁርና መስፈን ነው። በዚህ ጭለማ ወስጥ ከምዕራብ በሚመጣ ውራጅ ሸቀጥና ባህል አንድም ፋይዳ ለመፈየድ አይቻልም።

ስለሆነም አዲስ ቅድመ መርህ (አዲስ ፓራዳይም) አዲስ መርሃ እሴት (ቫልዩ ፕሪንሲፕል) መፈልሰፍ አለበት ። ይህን መሰል የሃሳብና የፈጠራ ብርሃን በኢትዮጵያ ምሁራን ሁሉ ይሞከራል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። የጎሳ ፖለቲካ የምሁራንን አንድነት አፍርሷል። ተያይዞም ብሄራዊ (አገራዊ) የሃሳብ አንድነት ፈርሷል። በመሆኑም ሙሉ ባህል ወይም አሞሌ ካልቸር፣ የኢትዮጵያ ምልአተ ባህል ሊፈጥሩ አይችሉም፤ እንዳይፈጠር አድርገዋል። የኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊና ወሳኝ ቀውስ (ችግር) መከፋፈል፣ መበታተን ነው። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ብትንና የቅውስ (ኬዎስ) ስርዓት ነው። ከሃይማኖት እስከ ተራ ሕይወት ሁሉም ብትን ስርዓት ነው።

ኢትዮጵያ ብትን ስርዓት እስከ ሆነች ድረስ ምልአተ ባህል፣ እሴተ ተዋህዶ ያለው ብሄራዊ ሴራ መፍጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን የተበታተኑት ክፍሎች እርስበርሳቸው ይጋጫሉ፣ ይጣላሉ፣ ይወድማሉ። ከላይ የተዘረዘሩት የባልና የፈጠራ መስኮች የሚንቀሳቀሱት በሰዎች፣ በቡድኖች፣ በሕዝብ ነው። እነዚህ የባህል ተሸካሚዎች እስከተበጣበጡ ድረስ አንድ ወጥ ነገር ለመፍጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን ምንም ነገር ሊፈጥሩ አይችሉም፤ አንዱ ሌላውን ስለሚያፈርሰው። ኢትዮጵያ ብትን ስርዓት ብቻ ሳትሆን የግጭት ስርዓት ነች ። የእርስበርስ መጠፋፋት፣ መዋደም፣ የእልቂት ስርዓት ንች ። ይህን መሰል ህብረተሰብ ወደ ታች እንጂ ወደ ላይ አይሸጋገርም። ለዚህ ሁሉ መሰረቱ ኢትዮጵያዊያን ማንም ይሁኑ ከየትም ይወለዱ፣ በአንድ ፈጣሪ የሚያምን፣ በሰው ልጅ ሰባዊነትና ልዕልና የሚያምን፣ በኢዮጵያዊያን ሁሉ ወንድማማችነት የሚያምን አንድ ሕዝብ አለመሆናቸው ነው። ይህን መሰረት፣ ይህን ቅድመ መርህ፣ ይህን ፓራዳይም እውን የሚያደርገው ትውልድ ገና የለም።

ያልኳቸውን ነገሮች በትንሹ ለመድገም፣ ኢትዮጵያ በማንኛውም መስክ ብትለካ ማለትም በሃይማኖት፣ በፍልስፊና፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሶሺያል ሳይንስ፣ በስነ ጥበብ፣ በሕግና በስነ ምግባር በሁሉም መስክ ቁርጭራጭ ስርዓት ነው። እነዚህ እጅግ ብዙ ቁርጭራጮች በግለ ህልውናቸው ፋይዳቢስ ሲሆኑ በህብረ ህልውናቸው ተጻራሪ፣ ተዋዳሚ፣ ተፋላሚና የግጭት መነሾዎች ናቸው። ስለዚህ ለየብቻም በህበረትም ዋጋቢሶች ናቸው። በግል ለድህነትና ለድንቁርና ተጋልጠዋል፤ ከተባበሩ ይተላለቃሉ ። መውጫ የለሽ ዙሪያ ጥምትም ማለት ነው።

ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች በኢትዮጵያ ግለሰቦች እና ቡድኖች አይምሮ ላይ ወይም አስተሳሰብ ዘንድ የሚያስከትሉት ተጽዕኖዎች አሉ። የግለሰቦች፣ ብሄረሰቦችና ቡድኖችን የማንነት ትርጉም ለውጠዋል፣ አናግተዋል። እነዚህ የምንነትና የማንነት ትርጉሞች ተበታትነዋል፣ ተፍረክርከዋል፣ ተቃውሰዋል፣ ተዘባርቀዋልም። ተያይዞም እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ያሏቸው፣ የነበራቸው እሴቶች ወይም ሰርዓተ እሴቶች፣ አስተሳሰብ፣ መርሆችና እምነቶች ተበታትነዋል፣ ተፍረክርከዋል፣ ተቃውሰዋል። የሞራል ስነስርዓታቸው ላሽቋል፣ ወድቋል። ማለትም ደግና ክፉ፣ ጥሩና መጥፎ፣ ትክክልና ስህተት፣ ፍትህና ግፍ፣ ጠቃሚና ጎጂ፣ ገምቢና አፍራሽ፣ እድገትና ወድቀት፣ ልማትና ወድመት፣ ነጻነትና ባርነት፣ ትልቅነትና ትንሽነት፣ ክብርና ውርደት፣ ራዕይና መታወር፣ ብርሃንና ጭለማ፣ ፍቅርና ጥላቻ፣ የሰላምና ሽብር፣ ስርዓትና ቀውስ በአንድ ቃል ደህንነትና ድህነትን የሚለይ የግምትና የህሊና ተቋማቸው ወይም ችሎታቸው ተቃውሷል። ከላይ የተጠቀሰው መበታተንና መጋጨት የግለሰቦችን አስተሳሰብና ሰነምግባር በመበታተን ላይምሮና የሞራል አናርኪ ዳርጓቸዋል። ማሀበራዊ አናርኪና ያስተሳሰብ ምስቅልቅልነት አይነጣጠሉም። አንዱ ሌላውን ይወልዳል፤ እንዲያውም ያስተሳሰብና የሞራል ስርዓት ሳይኖር ማህበራዊ ስርዓት ሊኖር አይችልም። ብትን ሃይማኖት፣ ብትን ፍልስፍና፣ ብትን እሴት፣ ብትን ፖለቲካ፣ ብትን ስነት፣ ወዘተ የሚፈጥሩት ብትን ህብረተሰብን ነው።

ያስተሳሰብ፣ የህሊናና የሞራል ቀውስ ወይም አናርኪ ውጤቱ የተፋፋመ ቅራኔ ፣ ግጭት፣ ሁከትና ጦርነት ነው። በኢትዮጵያ የሃይልና የጉልበተኝነት ሚና እየገነነ ይሄዳል። ጦርነት፣ አብዮት፣ አመጽ፣ ወንጀል፣ ሕግ አልባነት በአገሪቱ ይስፋፋሉ። በሰው ሕይወት ላይ እልቂት ይከተላል። የሕዝቦች ቁሳዊ መደላደል (አኗኗር) ይፈርሳል። ያገሪቱ ቁሳዊ ሃብት ይወድማል። ይህ የመጨረሻ ወድመትና ጥፋት ከሚከተሉ ሶስት አዝማሚያዎች አንዱን ሊወስድ ይችላል።

አንደኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በብትንትንነቱና በቀውሱ ለረጅም ዘመን ሊቀጥል ይችላል። ይህም ማለት አገሪቱ ምንም አይነት መሰረታዊ መፍትሄ ሳታገኝ በሞትና በህይወት መካከል አሳዛኝ የሆነው ህልውናዋ እንደ ተንጠለጠለ ሊቀጥል ይችላል።

ሁለተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በተወሰኑ ሰፋፊ መሬቶች ፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ግዛቶች፣ ተከፋፍሎ በአዲስ ፌዴራላዊ ወይም ኮንፌዴራላዊ ስብስብ ሊቀጥሉ ይችላሉ። ኢትዮጵያ በብዙ አገሮች የምትከፋፈለቅ ይህ አዝማሚያ እውን ከሆነ ነው።

ሶስተኛው አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ መሰረታዊ ያስተሳሰብና የእስትራተጂ ለውጥ አድርጎ ስርወ እሴታችን የአንድ ፈጣሪ ገናናነት፣ የሰው ልጅ ልዕልናና የኢትዮጵያዊያን አንድ ቤተሰብነት ሆኖ አገሪቱ ከውድቀት ልትድን ትችላለጭ

ከነዚህ ሶስት አዝማሚያዎች የትኛው እውን እንደሚሆን የሚወሰነው በኢትዮጵያ ምሁራን መካከል ባለው የሃይል ሚዛንና የማሰብ ችሎታ ነው። ለምሳሌ ያንድነትም ሆነ የብሄረሰብ ምሁራን ከደከሙና አዲስ መፍትሄ ማቅረብ ካልቻሉ ወይም አንዱ ከለላው በልጦ ማሸነፍ ካልቻለ አንደኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

የብሄረሰብ ምሁራን የበላይነት ይዘው የጎሳ ክፍፍል አሁን ባለው ቀጥሎ ካደገና ካሸነፈ ሁለተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል። የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ከጠነክሩ ሶስተኛ አዝማሚያ እውን ይሆናል።

ለምሳሌ ሶስተኛው አዝማሚያ ሃይማኖትን በተመለከተ የኢትዮጵያዊያን እምነት ሆነ አምልኮ መሆን ያለበት እግዚአብሄር፣ ክርስቶስ፣ አላህ፣ ያዌ፣ ጂሆቫ፣ ዋቃ፣ ሌላም ሌላም በሚል መናቆር ሳይሆን በአንድ ፈጣሪ ማመን ነው። ቤተ እምነት ሆነ ቤተ አምልኮ ሁሉ የአንድ ፈጣሪ ቤተመቅደስ ሆኖ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የአንድ እምነት አማኝ አንድ ሕዝብ መሆናቸውን መቀብለና ያንን ማስተማር አለበት ። የኢትዮጵያ ብሄረሰብ ግለሰቦች ሁሉ ማለትም ኢትዮጵያዊ ሰው ሁሉ የአንድ ፈጣሪ ፍጡራን እንደ ሆኑ። እነሱም አንድ ኢትዮጵያዊ ብሄር እንደሆኑ ተቀብሎ የኢትዮጵያ ጎሳ እንደሆኑ ማመንና ማስተማር አለበት ። በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አንድ ቤተሰብ ፣ ወንድማማች እንደሆኑ ማመንና ማስተማር አለበት ።

በእነዚህ ሶስት ስረወ እሴቶች መሰረት የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ የፍልስፍና፣ የስነ ጥበብ፣ የማህበራዊ ሳይንስ፣ የሕግና የስነ ምግባር ውህደቶችን የሚያንጸባርቅ ባህል፣ ፈጠራ፣ ንድፈ ሃሳብ መቀመር ግድ ይላል። የኢትዮጵያ አንድነት ምሁራን ይህን ማድረግ ካልቻሉ የጎሳ ምሁራን አሁን በጀመሩት አጀንዳ ቀጥለው ሕዝቡን በብዙ አማልክጥ በብዙ ጎሳዎች፣ በብዙ ቋንቋዎች፣ በብዙ ባህሎች በመከፋፈል ይህም ውሎ አድሮ ወይ ኢትዮጵያ መከፋፈል ወይም ወደ ኢትዮጵያ ወድመት ማምራቱ አይቀሬ ነው።

ይህን ያልኩት የዛሬ 24 አመት ነበር
Bezih meketel alebegn teru tsehuf new,kemiakerakeregn neger hulu reke erasen le tekem mawal new,Horus endetsafew.

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 29 Jul 2019, 13:16
by Horus
ይሀው ዛሬ ሃምሌ 2011 ነው። ከላይ የነሳዋቸው 3 አዝማሚያዎች 3ቱም አሉ፤ አንደኛ ሙሉ በሙሉ እውን ሆኖ አልወጣም። ሆኖም የልኡል ዜጋ ወይም የግለሰቡ ልዕልና አስተሳሰብ ያልው ድምጽ በጣም በመሰማት ላይ ይገኛል። በዜጋ ፖለቲካ ዙሪያ መደራጀት አድጓል። ያንድነትና የዜጋነት ምሁራን በርክተዋል። የጎሳ ወይም የመንጋ አስተሳሰብ ድክመት በሰፊው በመነገር ላይ ነው።

ብሌላ በኩል መንጋነትና ቀውስም በየቦታው አሉ። ሚዲያው በበዛና በተለያዩ መስኮች ወስጥ የሚሰሩ ምሁራን መሰማት መጀመራቸው ያንድነት፣ የዜጋ ልዕልና ህሳቤ ይበልጥ እያደገ ነው ለማለት ይቻላል። ለምሳሌ ይህን ቃለ ምልልስ ተከታተሉጥ


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 30 Jul 2019, 13:15
by Horus
ይሀው በሰሞኑ የሚደረገው 2 ቢሊዮን ዛፍ ተከላ ለ25 አመት የተካሄደውን ከባቢ የማውደም የጥፋት ባህል አዝማሚያ ሊለወጥ የሚችህል አዲስ አመለካከት ነው። ደስ የሚል አዝማሚያ !!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 31 Jul 2019, 01:31
by Horus
እኛ ኢትዮጵያዊያን ካልቸር ለሚለው ጽንሰ ነገር ብቁ ሆኖ የሚገልጽ ቃል የለንም። ባህል ከካልቸር የጠበበ ጽንስ ነው። ዘይቤ፣ ወግ፣ ዘዴ፣ ብልሃት፣ እሴት እና ሌሎችም ከካልቸር የጠበቡ ናቸው።

በእኔ ግምት ቻልቸርን ሙሉ በሙሉ የሚገልጽ ጽንስ 'ፍጥረ ግብር' የሚለው ነው። ካልቸር ማንኛውም የሰው ልጅ ቡድንም ሆነ ማህበር በማደራጀት ተፈጥሮ ከፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ ውጭ የሰው ልጅ በተግባር፣ በግብር፣ በስራ የሚፈጥራቸው ነገሮች ሁሉ ካልቸር ይባላሉ። ማለትም ካልቸር ሁለት ክፍሎች አሉት ። የመጀመሪያው 'ፈጠራ፣ መፍጠር፣ ፍጥር' የሚለው ነው። ካልቸር ሰው የፈጠረው ነገር ማለት ነው። ሁለተኛው ጽንስ ግብር፣ ስራ፣ ተግባር የሚለው ነው። ማለትም ካልቸር የስራ፣ የተግባር ውጤት ነ። ስለዚህ ትክክለኛ የካልቸር ቃል ፍጥረ ግብር ነው እላለሁ ።


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 01 Aug 2019, 18:32
by Horus
In my view this tree planting initiative is perhaps one of the most significant leadership act of PM Abiye because this national effort will have the unintended effect of national purposefulness, and national unity. It will produce a culture of prudence, that is the culture of caring for the future and creativity. For this to happen public intellectuals need to expand of the metaphor of planting something live, the notion of well- being the total Ethiopian ecology or Eco-system.

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 03 Aug 2019, 01:13
by Horus
አንድ ጽንሰ ነገር ተቀርጾ፣ ተተክሎ፣ ለምቶ እስኪያብብ በድጋሚ በድጋሚ እንክብካቤ ይሻል። ስለ ኢትዮጵያ ማህበረ ሰብ፣ ስለ ኢትዮጵያ ፍጥረ ግብር ወይም ካልቸር ስናስብ ያለው ሃቅ ተመሳሳይ ነው።
እንደ ገና ልድገመው፤ ሁላችንም የምታኮራ፣ ተወዳጅ ኢትዮጵያ ላይ ለመስማማት ሶስት ስርወ እሴቶች ወይም ኮር ቢሊፍስ ላይ እንስማማ። ሁላችንም በአንድ ፈጣሪ እንመን ። ያ አንድ ፈጣሪ በተለያዩ ስሞች መጥራታችንን ተቀብለን በስም ልዩ በይዘት አንድ እምነት እንዳለን እንቀበል። ከዚያም ይህ አንድ ፈጣሪ የፈጠረውን የሰው ልጅ ማለትም አንድ ግለ ሰብ ፍጹም ልኡል፣ ፍጹም ነጻ የሆነ ሰብአዊነቱም ከፈጣሪው ያገኘው መሆኑ ላይ እንስማማ። ይህም ስለሆነ ኢትዮጵያዊያን ሰው በመሆናቸው ብቻ ወድማማች በመሆናቸው እንስማማ። ይህ ነው ያንድ ትልቅ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር መሰረቱ። በዚህ መሰረት አንድ ኢትዮጵያዊ ካልቸር (ፍጥረ ግብር) ይፋፋል።
ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ አጀንዳ ላይ መጣላታችን ያበቃል።

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 03 Aug 2019, 01:27
by Horus
ከዚያስ ኢትዮጵያን እንደ አንድ ድርጅት፣ እንደ አንድ ለአላማ የቆመ ነገር አድርገን ብናያት ያሏት አጀንዳዎች፣ ግቦች፣ ተለእኮዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

እነሱም የሚከተሉት ናቸው ፤

አንድነቷ የጸና የተረጋጋችና ጠንካራ አገር መሆን
ደሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ ማህበረ ሰብ መሆን
ሃብታም፣ የተማረና ጤነኛ ሕዝብ ምሆን
ፍጣሪ፣ ከባቢ ጤና፣ መንፈሳዊ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር መገንባት

በቃ ይህ ነው የኢትዮጵያ ፋይዳ !!!

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 03 Aug 2019, 01:55
by Horus
እዚህ ከላይ ባልኩት ሃተታ ውስጥ የአናርኪና የኒሂሊዝም ካልቸር ያልኩትን ዐቢይ ሲያብራራ ስሙ። ግን አቢይም የመንጋ ፖለቲካን የዜጋ በማስመሰል ሁለቱን ፈረሶች ሊጋልብ ይጥራል።

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 03 Aug 2019, 22:56
by Horus
በሃተታዬ ወስጥ የኢትዮያን ምላተ ካልቸር (ፍጥረ ግብር) የሚገነቡት የሃይማኖት፣ የፍልስፍና፣ ታሪክ፣ ስነ ማህበር፣ ስነ ፖለቲካ፣ ስነ ጥበብ፣ ስነ መረጃ፣ ስነ ምግባር፣ ሕግ እና ሌሎች ምሁራን ወይም ልሂቃን የነበሩበት ድክመት ጠቅሼ ነበር። በአሁን ወቅት በተልይም ከኢሳት ዘመንና ከአቢይ ግዛት ጀምሮ ብዙ ተስፋ ሰጭ ጮራዎች እየታዩ ነው።

በእኔ ግምት የፍትህ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ሳይሆን ፖለቲካል ሂስቶሪያንና ሶሺያል ሂስቶሪያን ነው፤ እጅግ አስፈላጊ የጊዜውን የፖለቲካና ማህበራዊ ታሪክ ወብ በሆነ ሃተታና ክሪቲክ እየዘገበ ነው።

በጥሞና ስሙት፤


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 04 Aug 2019, 00:05
by Horus
ለምሳሌ የጠ/ሚ ዐቢይን ያገዛዝ ስልት እንመልከት ። ተመስገን ደሳለኝ ከላይ ብዙ ብዙ ነገር አንስቷል፤ ስለ አቢይ ባህሪ፣ የመሪነት ዝግጅት፣ የተግባር አፈጻጸም ስልቶች፣ ሌሎችም።

ኒኮሎ ማኪያቬሊ ልዕኡሉን ሲማክረው መስፍኑ አንድ ጥልቅ ጥያቄ ይጠይቀዋል። በስኬት ለመግዛት ወይም ባሁኑ ዘመን አባባል ለመምራት የሚሻለው ፣ ሕዝቡ ቢወድደኝ ነው ወይስ ቢፈራኝ? ማኪያቬሊ ቢቻል ቢቻል በመወደድ መግዛትን ይመረጣል፤ ካልሆነ ግን በፈራት መግዛት አለብህ ሲል ይመክረዋል።
አቢይ እርካብና መንበር የተባለው መጽሃፉን ሲያዘጋጅ የማኪያቬሊን ሃሳብ እንደ ተጠቀመ ተመስገን ነግሮናል።

አሁን ጥያቄው አቢይ የሚገዛው በመወደድ ነው ወይስ በመፈራት የሚለው ነው።

አቢይ ሁለቱንም በማፈራረቅ ይጠቀማል። እርግጥ ስልት ከተግባር አላማና ውጤት ጋር ይያያዛል። ቢሆንም አንድ ግብ በተለያየ ስልት ይተገበራል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ አንድነት፣ መረጋጋትና ጥንካሬ መወደድ ካልሰራ መፈራትን ጥቅም ላይ ማዋል ግዴታ ነው።

ዞሮ ዞሮ አቢይ መለካት ያለበት ከዚህ በታች ባለው የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው።

ኢትዮጵያን እንደ አንድ ድርጅት፣ እንደ አንድ ለአላማ የቆመ ነገር አድርገን ብናያት ያሏት አጀንዳዎች፣ ግቦች፣ ተልእኮዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

እነሱም የሚከተሉት ናቸው ፤

አንድነቷ የጸና የተረጋጋችና ጠንካራ አገር መሆን
ደሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ ማህበረ ሰብ መሆን
ሃብታም፣ የተማረና ጤነኛ ሕዝብ ምሆን
ፍጣሪ፣ ከባቢ ጤናማ፣ መንፈሳዊ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር መገንባት ናቸው።

በቃ ይህ ነው የኢትዮጵያ ፋይዳ

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 04 Aug 2019, 01:22
by Horus
ለምሳሌ ይህ አንድ እጅግ ከፍተኛ ካልቸራል ፣ ከፍተኛ ፍጥረ ግብራዊ እንቅስቃሴ ነው። የሰው ልጅ እንዲህ እንዲህ እያለ ነው አይማኖት፣ እምነት፣ ሳይንስ የሚጀመረው !!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 04 Aug 2019, 02:54
by Horus
ወደ ፊት የሚሆን ነገር ሁሉ በመሰረቱ ድብቅ ነው። ድብቅ ማለት አይታይም ማለትም ያልሆነ ነገር ሁሉ አይታይም። ስላልሆነ ማለት ነው። ግን ነገን የሚፈጥሩት ዛሬ የምናያቸው አሉ። ያ ነው የኢትዮጵያ አንዱ አዝማሚያ የምንለው ። ሮቤል ባምላክ ቅድመ መርህ ወይም ፓራዳይም ነው !!!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 05 Aug 2019, 12:39
by Horus
ኢትዮጵያዊነት መልካምነት የሚል ራዕይ አንግቦ አገር እያቆመ ያለው የኩራታቸን ምንጭ ጆሲ (ዮሴፍ ገብሬ) በሆዴ ውስት ያለውን ቃል ነው ሚናገረው። በእርግጥ የኢትዮጵያ ልጆች እየተነሱ ነው ! እምነት የሁሉ ነገር መነሾ ነው ። ይህ ነው የኢትዮጵያ ስርወ እሴት ማለት !!!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 05 Aug 2019, 18:28
by Medo
You and your likes are parts of a problem not a solution. Whatever you say or claim can't change that. Go and find yourself. Absent mind.

Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 05 Aug 2019, 22:39
by Horus
ውድ አንባቢያን፣ በእርግጥ ኢትዮጵያዊ የሆናችሁ ከዚህ በታች የሚቀርበውን አሳዛኝ፣ አስደማሚ፣ አስደናቂ፣ አስተማሪ እጅግ ምርጥ ትችትና ማረሚያ ተከታተሉት። ይህን ነው የዛሬ 24 አመት ግዙፍ ባልላዊ (ካልቸራል ወይም ፍጥረ ግብር) ቀውስ ያልኩት ። እዚህ የቀረበው የቋንቋና የጽሁፍ ግብረገብ ወይም የጽሁፍ ስነ ምግባር አንዱ ትልቅ ብሩ ምሳሌ ነው። የብሄራዊ ቀውሱን የሚክሙት ልሂውቃን እየተሱ ነውና እልል እንበል !!!!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 07 Aug 2019, 23:07
by Horus
እኔን ለሚመስሉ ኢትዮጵያን ከልብ የሚወዱ እልፍ አእላፍ ሚልዮኖች እንደ ምናየው የጎሳና የዘረኝነት ፖለቲካና ትርክት ከየአቅጣጫው በተለያዩ መስክ በረቀቁ ምሁራን ልሂቃን እየተምታ ነው ።

በሃይማኖት መሪዮች
በትንሹም ቢሆን በፍልስፍና ተማሪዎች (ኢትዮጵያ እከሌ የሚባል ፈላስፋ ስለሌላት
በታሪክ ምሁራን እንደ ታየ ቦጋለ ያሉ
በስነ ፖለቲካ
በስነ ማህበር
በስነ አኮኖሚ
በተለይ በኪነትና በስነ ጠቢባን
በሰባዊ ግብረ ሰናያን
በሚዲያ ዘርፍ
ሌላም
ሌላም
በሃኪሞች
በስይኮሎጊስቶች
በአንድ ቃል የኢትዮጵያ ልጆች በዚህ ከቀጠልን በጥቂት አመታት ወስጥ ክላይ የዘረዘኳቸው ቀውሶችን እንፈታለን !!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 09 Aug 2019, 00:26
by Horus
እኔ ረጃጅም ሃተታዎች በመጻፍ ላሰለቻችሁ አልሻም ። ግን ሃስብ የሚቀሰቅሱ ጥያቄዎችን በማንሳት የናንተን ምርምር ማነሳሳት እፈልጋለሁ።

እንደ ምታቁት የጎሳ ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን አገርነት ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚያላዝኑት ጽንስ አለ፤ እሱም ካልቸር (እኔ ፍጥረ ግብር ብዬዋለሁ) ይባላል። ይሁንና በጠባቡ ባህል በሙሉ ጽንሱ ካልቸር ወይም ፍትረ ግብር ምንድን ነው? አንድ ካልቸር ጥሩ ነው የሚባለው ምን ስለሆነ ነው? ሌላውስ መጥፎ ካልቸር የሚባለው ምን ስለሆነ ነው? የጎሳ ወይም የዘር ማንነት አቀንቃኞች የተሻለ ካልቸር ይዘው ነው ወይ ኢትዮጵያን የሚቃወሙት?

ከጥቂት አመታት በፊት በኒው ዮርክ ከተማ ወስጥ በአሜሪካ አሉ የሚባሉት የተለያየ መስክ ምሁራን ማህበር ነበራቸው ስለ ልዩ ልዩ ትላልቅ ጉዳዮች የሚወያዩበት ። አንድ ያነሱት ጉዳይ ስለ ካልቸር ነበር ። የነሱ ጥያቄ ያንድ ጥሩ ካልቸር ባህሪያት ወይም መገለጫው ወይም መለኪያው ምንድን ነው የሚል ነበር ። የደረሱበት ግኝት የሚከተለው ነው።

ባንድ ቃል አንድ ካልቸር ጥሩ ወይም መልካም ባህል ወይም ፍጥረ ግብር ነው የሚባለው የዚያን ባልህ ባለቤቶች ግላዊም ሆነ ማህበራዊ ስርዓት ሲያረጋግጥ ማለትም ሶሺያል ኦርደር ሲያጸና፣ የሰውም ሆነ የማህበሩ ደህንነት ማለትም ዌል ቢኢንግ ሲያረጋግጥ፣ የማህበርተኞቹን ደስታ፣ ሃሴት ሲያበዛ ማለትም ሃብታብ ሲያረጋቸው፣ እና የፈጠራ፣ የዉበት፣ የእርካታ ምንጭ ሲሆን ነው። እነዚህ አራት መሰረታዊ የጥሩ ካልቸር ወይም ፍጥረ ግብር ባህሪያት ሙሉ መጽሃፍ ያጽፋሉ ። ግን አሁን እየተነሳሱ ያሉት የኢትዮጵያዊነት ምሁራን ያስፋፉት እላለሁ ።

በተያያዘ ጉዳይ የመምህር ታየ ቦጋለ አስተምሮት እጅግ ተስማሚ ናቸው፣ ምስጋና ይድረሰው ! ኬር !!


Re: የዘመናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀውስ

Posted: 09 Aug 2019, 01:31
by Horus
ኦቦ ያቤሎ
መምህር ታየ ቦጋለ የኩራትህ ምንጭ መሆን ይገባል ፣ ሆኖም የሚጥምህን አንተ ታቃለህ ። ይህ የቦረና ልጅ ድንቅ ኢትዮያዊ አንተ ብትክደው 110 ሚልዮን የኛ ሁን የሚሉት አሉ !!! ትንሽ ምንግዜም ትንሽ ነው። ያቤሎ አቢይን ሊገድሉት የሚሹትኮ ኦሮሞች ናቸው። ተስማማን !!! ከዘር ፓራዳይም ነጻ ሳትወጣ የቁላ ዘውድ አኮፍሰው በዚያው ወደ ዚያኛው አለም ት ዘልቃለው። መምህር ታየ ግዙፍ የኢትዮያ ሂስቶሪካል አናሊስትና ክሪቲክ እየሆነ ነው ። አንተ ግን ምንም ነህ !! አትርሳ !! ኢትዮጵያ የትም አትሄድም ። ነገ ኢትዮጵያ ግፍን አንተን ሳይሆን የቦረናው ልጅ እያለ የሚያውቀው ታየ ቦጋለን ነው ። ነጋቲ !!!