Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 26 Feb 2020, 10:27

ፋሺዝም * ናዚዝም * ኮምዩኒዝም
Fascism * Nazism * Communism

ቃላት፦
1) ፋሺዝም፡- “ፋሸስ” (Fasces) ከሚል የላቲን ቃል የተወሰደ ነው። ሮማውያን ሲጠቀሙበት ደግሞ ትናናሽ እንጨቶች በአንድ ላይ ተጠምረው፡ አንድ መጥረቢያ በመካከሉ የሚታይበት ምልክት ነው፣ ይህ የሚሰጠውም ለትልልቅ ባለሥልጣኖች ሆኖ፣ በሕይወትና በሞት መካከል ሥልጣን ያለ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው። በ20ኛው ክፍለ ዘመን፣ ሙሶሊኒ የመሰረተው የፋሺዝም ፓርቲ ምልክት ሆነ።
2) ናዚዝም፦ ይህ ደግሞ “ናሲዮናል-ሶሲያሊዝሙስ” National sozialismus ከሚል፡ የጀርመን መሪ ከተከተለው አመለካከትና፣ ፖለቲካዊ ፓርቲው የያዘው ማኅበራዊ አመለካከት ያመለክታል።
3) ኮምዩኒዝም፦ በጋራ ንብረትና እኩልነት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ነው።
ፋሺዝም፦
የፈረንሣይ ሣልሳይ ሪፖብሊክ የተባለ መንግሥትና ቅድስት መንበር ስምምነትና የጋራ ግንዛቤ ላይ ለመድረስ እንደተግባቡ፣ ቫቲካን ማለት ቅድስት መንበርና የጣልያን መንግሥት ወዲያውኑ አንድ የስምምነት ውል ላይ ደረሱ። ይህም የላተራን ኮንኮርዳት የሚባል በ1929 የተከናወነ ነው። በዚህ መሠረትም የጣልያን መንግሥት በ1870 በኃይል የወሰደው፣ በጳጳስ ለሚተዳደር የጣልያን መካከኛ አውራጃ ክፍል፣ ማካካሻ ሮማ ውስጥ የሚገኝ ቫቲካን ልዑላዊ ሃገር እንዲሆን ተደረገ።

ይህ አዲስ የቫቲካን ልዑላዊነት፡ ነጻና በዓለም መድረኽ ውስጥ ደግሞ ገለልተኛ የሆነ መስመርን እንዲከተል ተፈለገ። ከዚህም ጋር አንስተኛ ስፋት ያለው መሬትን የያዘ፡ ራሱን የቻለ መንግሥተ-ሃገር መልክና የአደረጃጀት ሥርዓት እንዲይዝ ሆነ። ከዚህ ከላተራን ስምምነት ጋር የተያያዘ ሌላ ከጣልያን መንግሥት ጋር የተደረገ የስምምነት ውል እንደሚያመለክተውም፣ አብዛኞቹ ካቶሊካውያን በተቀመጡበት አንድ ሃገር፣ የቤተክርስትያንና የመንግሥት ግንኙነት እንዴት መሆን እንዳለበት በመሠረተ-ሓሳብ ይሁን በተግባር መመሪያ የሚሰጥ ውል ተነደፈ።

በዚህ ሰነድ ውል እንደተነደፈው፡ ካቶሊካዊ እምነት ሃገራዊ ሃይማኖትና ቤተክርስትያን እንደሆነ የሚያስብ መሆኑ ይታያል፤ በተለይም አንቀጽ 7 “መንግሥትና ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እያንዳንዳቸው በየተልእኳቸውና ሥርዓቶቻቸው ነጻና ልዑላዊ መብት አላቸው፣ ግንኙነታችውን በተመለከተም በላተራን ውል ያለው መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል። ሁለቱም ወገኖች የተስማሙበት ማሻሻያ ሲኖር፣ (constitutional revision) ሕጋዊ ግምገማና ዳግመ-ግምት ማድረግ አያስፈልገውም።

አንቀጽ 34 ደግሞ እንደ ግዴታ ይታይ የነበረን ሲቪላዊ ትዳርን፣ ለማስወገድ “የትዳርና የቃልኪዳን መሠረት ቤተሰብ እንደመሆኑ መጠን፣ የካቶሊካዊ ሕዝብ ትውፉት ጋር በሚስማማ የክብርና የማዕረግ መልኩ እንዲፈጸም የጣልያን መንግሥት ፍላጎት በመሆኑ፡ ያ በቤተክርስትያን ሕገ ቀኖና የተፈጸመ ምሥጢረ ተኽሊል (ቃልኪዳን) በጣልያን ሲቪላዊ ሕግም ሙሉ በሙሉ የጸናና ተቀባይነት ያለው ይሆናል” ተባለ።

ቤተክህነትና፡ በምናኔ የሚኖሩ አካላቶቿ ደግሞ ከዓለማዊና ሃገራዊ አገልግሎት ነጻ እንደሆኑ በመንግሥት ታመነበት። አንቀጽ 36 ደግሞ እንዲህ ይላል፦ “ትምህርተ ክርስትያን ማስተማር ከካቶሊካዊ ትውፊት ጋር በሚስማማ መልኩ ለይፋዊው የመንግሥት ሥርዓተ ትምህርት አጋሩና ምንጩ መሆኑን የጣልያን መንግሥት ይስማማበታል።” ይህ አንቀጽ በሌላ አንቀጽ 43 ላይም ድጋፍን አግኝቷል “ካቶሊካዊ ተግባር የተባለ እንቅስቃሴና፡ በእሱ የተመረኮዙ እንቅስቃሴዎች፣ እንደ የቅድስት መንበር ውሳኔ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውጭ የሚሰሩ ሲሆኑ በቀጥታ ከቤተክርስትያን መሪዎች ስር ሆነው ካቶሊካዊ መመሪያዎችንና ትምህርትን ለመዘርጋት እንደሚተጉ ሁሉ በጣልያን መንግሥት ተቀባይነት አላቸው።”

ከላተራን ውል መፈረም በኋላ (1929) ለፋሺዝም መሪ ሙሶሊኒ ከቤተክርስትያን ጋር ያጋጨው ይህ መጨረሻ ላይ የተጠቀሰው ጕዳይ ነው። ቢያንስ ቢያንስ እንደ የሙሶሊኒ ስነሓሳብ መሠረት ኢጣልያ ውስጥ ሊተክለው ወይ ሊመሠርተው የሚሻ ሥርዓት ወይ መንግሥት “ቶታሊታሪያን” (Totalitarian) የሚባል አምባገንና፣ በማንኛውም የኅብረተሰብ ሕይወት ውስጥ እጁን ሊያስገባ የሚሻ፡ ሁሉንም ነገር እሱ ራሱ ብቻ ሊያንቀሳቅስ የሚሻ እንጂ ለግለሰቦች ዕቅድና ሓሳብ ነጻነት የማይሰጥ ሥርዓትን ነው።

በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወኪሎችና በፋሺዝም መሪዎች መካከል እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 1926 ዓ.ም. ውል ተፈረመ። ሙሶሊኒም ስለ ላተራን ውል ወይ ስምምነት ለጣልያን ሃገር ሸንጎ ባቀረበው ሪፖርት እንደሚከተለው አለ፦ “እንግዲያውኑስ ሁለቱ ልዑላዊ አካላትና የየራሳቸው መንገድና፣ የእርስ በርስ እውቅናና ተቀባይነት ያላቸው ናቸው። ቢሆንም ግን በመንግሥተ-ሃገር (State) አንጻር ሲታይ ቤተክርስትያን ልዑላውነት የላትም፡ ነጻም አይደለችም፣ ምክንያቱም በተቋሞቿና በሰዎቿ በኩል አድርጋ ለውስጣዊው የመንግሥተ-ሃገር ሕግና ለውሉ ልዩ መመሪያዎች መገዛት አለባት። …ክርስትና በፍልስጤም ተወለደ፣ ሮማ ውስጥ ግን ካቶሊክ ሆነ። ፍልስጤም ውስጥ ብቻ ተከልሎ ቢቀር ኖሮ አንድ እዚህ ግባ የማይባል ትንሽ ቡድን ብቻ ሆኖ በቀረ ነበር …ዕጣውም ምንም ዱካ ሳያስቀር መጥፋት ብቻ በሆነ ነበር፣… ምድራዊውን (ግዚያዊውን) የጳጳስ ግዛት ቀበርነው እንጂ፣ አላሥነሳነውም …ማንኛውም እንደኛ ያለ መንግሥት፡ የታዳጊ ትውልዶቹን ትምህርትና አስተዳደግ በሚገባ መኮስኮስን አይመለከተኝም ሊል አይችልም። ይህንን በተመለክተ እኔ ፍንክች የማይል አቋም ነው ያለኝ፣ የወጣቶቻችን ትምህርት ከእጃችን ሊያመጥ አይገባም። ልጆቻችን በፖለቲካዊ እምነታችን መሠረት ሊያድጉና ሊኮተኮቱ ሊመለመሉ ይገባል። ይህንን ትምህርት ሙሉና ብቁ ማድረግ ይጠበቅብናል፣ ስለሆነም ለልጆቻችን የጀግንነትና የደፋርነት፡ እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን በደንብ አድርገው እንዲችሉ አድርገን ማሰልጠን ይገባናል …”።

ከዚህ የሙሶሊኒ ንግግር ማግስት፣ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተቃውሞ ተከተለው። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 11ኛ እንዲህ በማለት መለሱለት፡ “መንግሥት ለወጣቶች ትምህርት መቆርቆሩ ትክክል ቢሆንም ቅሉ፣ ማንኛውንም የቤተሰቦች መብትና ዕድልን ግን መንግሥት ሊቆጣጠረው አይገባም። መንግሥት ቤተሰብን ሊቆጣጠር መሻቱ ተቀባይነት የሌለውና ከባሕርያዊ ሕግ ተጻይ ወይ ተቃራኒ ነገር ነው። ለምን ቢባል ከመንግሥትና ከኅብረተሰብ በፊት ሊተኮርበትና ሊቀድም የሚገባው ቤተሰብ ነው። ስለሆነም መንግሥት የቤተሰብ ስራን ሊያሳድግና ሊያበረታታ እንዲሁም ከወላጆች ፍላጎት ጋር የሚስማማ ዕቅድን ሊያወጣ በተጨማሪም የቤተክርስትያንን መለኮታዊ መብትን ማክበር እንጂ መተናኮል የለበትም። መንግሥት በትምህርት ተቋሞቹ ውስጥ፡ በሚያሰራጨው ሃሳቦችና ፕሮግራሞቹ፣ ገዢዎችንና የግዛት ተስፋፊዎችን ሊያበረታታና እነርሱን የመሰሉትን ሊያሞካሽ ካሰበ ይህን መሰሉ ሃሳብ በጭራሽ አንቀበለውም። ሥልጣን ላይ የወጣና ኃይል አለኝ ያለና በረታሁ ያለ አንዱ መንግሥት እንዲህ ካደረገ ሌሎችም እንዲህ ማድረጋቸው አይቀሬ ይሆናል። ሁሉም መንግሥታት በየፊናቸው ለመግዛት መሻትንና ግዛትን የማስፋፋት ዓላማን አንግበው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ታድያ ምን ዓይነት ትርኢት ነው ልናይ የምንችለው? ይህን የመሰለው አስተዳደርና የአመላመል ትምህርትስ ለዓለማችን ሰላምና መረጋጋት ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል? በአምላክና በሕገ-ባሕርይ ለቤተክርስትያን ሆነ ለቤተሰብ በትምህርትና በአስተዳደግ በኩል የተሰጠንን መብት የሚገታና የሚነፍግ ማንኛውንም ዓይነት ተግባር ልንስማማበት አንችልም። ይህን በመሰለው ጕዳይ ላይ አንደራደርም። ሁለት ሲደመር ሁለት አራት መሆኑ ፍጹም የሚያከራክር አይደልም። አምስት ወይም አሥር አለመሆኑ የኛ ስሕተት አይደለም። መብታችንና መሠረታዊ መመሪያችን ድርድር ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም። ንቅንቅ የማይለውን ጽኑ አቋማችንን ተግባር ላይ ለማዋል የሚያግዝ ግዙፍ ኃይል ወይ መሣርያ የለንም፣ ይህ ግን የሚያሳስብ ወይ ወንጀል ወይ በደል አይደለም። ምክንያቱም ሓቅና መብት ኃይልና ጉልበት ኣያስፈልጋቸውም።”

የፋሺዝም መልስ L’Impero በተባለው ልሣኑ ወጣ። “ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እጅጉኑ ወደ ታች ወርደው በጋዜጣ ክርክር ውስጥ ገብተው “መሪን”(Il Duce) ያህል ሊያርሙና ሊያስተምሩ የፈለጉ ይመስላሉ። “ዱቸ”ን ሆነ አመለካከቱን ጥያቄ ውስጥ የሚያገባ አንዳችም ጕዳይ የለም። እሱን የሚቃወም የለም፤ እሱ ራሱም ለገዛ ራሱ አይቃወምም …ፋሺዝምን ሊወቅስ ወይም ሊቃወም የሚችል ፋሺዝም ብቻ ነው፤ “ዱቸ”ን መንቀፍ ያለበት ወይም የሚነቅፍ አንዳችም ሰው መገኘት የለበትም። እምናምነው በሱ ነው፣ እሱ የዕድገታችን መሠረት ነው። ሙሶለኒ ማለት፣ እግዚአብሔር በርሕራሔው ወደኛ የላከልን ሰው መሆኑን፣ ማንኛውም ሰው ሊረሳው የማይገባ ሓቅ ነው።” ይህን የመሰለውን ሽብርም አንዳንድ ሰዎች ደገፉት ተከተሉትም፤ አንዳንድ የቤተክህነት አካላትም ተደፈሩ፣ አንዳንድ የቤተክርስትያን ተቋማትም ፋሺዝምን በሚያደንቁ ደጋፊዎቹ ተዘረፉ።

አምባገነኑን ሥርዓት (totalitarianism) ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የኮነኑበትና የተቃወሙባት ሰነድ “አያስፈልገንም” (non abbiamo bisogno) ብላ የምትጀምር ሓዋርያዊ መልእክታቸው ነች። በዚያች መልእክታቸውም ለመላው ዓለም እንዲህ ብለዋል፦ “ወጣቶችን የገዛ ራሱ ንብረት ሊያደርጋቸው ከሚጥር አምባገነን ሥርዓት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠን እንገኛለን፤ .. ይህ ትንንሾችን የመቆጣጠር አዝማሚያ፣ ፓርቲውንና መንግሥቱን ብቻ እንዲያገለግሉ ማድረግ፣ ለራሱ አረማዊ አምልኮን ለሚሻ ሥርዓትና ሃሳብ ለማንሰራፋት ለሚጓዝ መንግሥት፣ ጭራሹኑ አገርን እንዲያመልኩ የሚያደርግ ጥረት ነው። ይህ ደግሞ የቤተሰብን ባህርያዊ ወይ የተፈጥሮ መብት የሚቃወም፣ የቤተክርስትያንንም መልዕልተ ባሕርያዊ መብት የሚጻረር ነው፣… ይህ መጥቶብን ያለው ጉድ ላይኞቹን ወይ ትልልቆቹን የመንፈስ መሪዎቻችንን የሚቃወም አንዳች ዓይነት ሃይማኖት ነው … “ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መወገድ አለበት፡ መሞት አለበት” የሚሉ አካላትም ሳይቀሩ ይደመጣሉ። …ይህ ዓይነቱ ሓሳብ ከካቶሊካዊ ትምህርተ-እምነትና ተግባራዊ ሕይወት ጋር ጭራሹኑ የማይጣጣም ነው።

ስለሆነም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ የፋሺዝም ወጣቶች የተመደበላቸውን የማሕላ ሥርዓት “ኢሕጋዊ” በማለት ተቃወሙት፤ የማህላው ቃላቶችም እንደሚከተለው ነበሩ፦ ““የዱቸን” ትእዛዞችና ቃላትን ምንም ዓይነት ጥያቄ ሳላነሳ ልታዘዝና የፊሺዝምን አብዮት ዓላማ ሁለመናየን በመሥጠት መሥዋዕት ልሆን በሁሉም ኃይሌ አስፈላጊም ከሆነ በደሜ ምስክር ለመሆን እምላለሁ።”
የሚል ነበር።በዚህ ዓይነት ሙሶሊኒ ዲክታተር ወይ አምባገነን መሆኑ በይፋ ታየ። መጨረሻው ግን አላማረም።

በቀጣዩ ክፍል “የ ጀርመን ናዚዝም [National Socialism]” የሚለውን ንኡስ ክፍል እንመለከታለን። :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 21 May 2020, 08:17

የ ጀርመን ናዚዝም [National Socialism]

ኢጣልያ ውስጥ የፋሺዝምን የአምባገነናዊነት እርምጃ የገታው ካቶሊካዊነት ነበር፣ ይህም ማለት ማንኛውም ካቶሊካዊ አካባቢና ስፍራ ይህንን አምባገነናዊነት ጭራሹኑ አልተቀበለውም ማለት ነው። የናዚ ጀርመን ግዛት ግን ካቶሊካዊያን ያልሆኑ ሰዎች የበዙበት አካባቢ ነበር። አልፍረድ አይንሽታይን የተባለ ታዋቂ ሳይንቲስት፣ በአዶልፍ ሂትለር ምክንያት ካገሩ ሊሰደድ ሲገደድ፣ በሃይማኖት የማያምን (agnostic) ሰው ነበር። ያም ሆኖ ግን በሰጡት ምስክርነት ምክንያት በጀርመን ሃገር የሁለቱም የሃይማኖት ጎራዎች ማለትም ካቶሊኮችም ሆኑ ፕሮቴስታንቶች የናዚን የግዛት አካሄድና አሰያየምን(ሢመት) በመቃወማቸው ምክንያት ያሞግሳቸዋል። የዚህ ምክንያት ደግሞ እነዚያ ምሁሮች የስነጽሑፍ ሰዎች አሳታሚዎችና የፖለቲካ ሰዎች ሁሉም እጃቸውን ሲሰጡና፣ የናዚ ሥርአት መሳሪያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ የጀርመን ክርስትያኖች ግን በድፍረትና በጀግንነት ሲቃወሙት ታዩ።

ለጀርመኑ ናዚ ከካቶሊክ ቤተክርስትያን የቀረበበት ይፋዊ ተቃውሞ በ1930 ይጀምራል። ሂትለር ከቅድስት መንበር ጋር የገባውን ውል (1933) እንደማይጠብቅ ግልጽ ሲሆን ግዜ፣ በ1934 ወዲያውኑ የሮዘንበርግ (Rosenberg’s Myth) ውጥን ወይ ትልም በአጠቃላይ በቤተክርስትያን በኩል የተወገዘ ጽሑፍ ሆነ፣ በ1935 ደግሞ የናዚ ጀርመን ያስከተለው ስደትና ትንኮሳ በጀርመኑ መሪ በቢስማርክ ግዜ ከካቶሊክ ቤተክርስትያን አንጻር ተነስቶ ከነበረው ትንኮሳና ስደት ጋር ተለይቶ (የ 1870 “ለሥልጣኔ ትግል” KulturKampf) እንደማይታይ ተገለጸ።።

የጀርመን መንግሥት የገባውን ውል እንደጣሰ የሚያመልክትና የሚያወግዝ የሚኮንን መግለጫ በካቶሊካውያን አቡናት በየግዜው ወጥቷል፤ ነሓሴ 20 1935፣ መስከረም 10 1936፣ ነሓሴ 19 1938። እ.አ.አ. በ1937 ዓ.ም. ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 11ኛ የ”ናዚ”ን ትምህርት ባወገዙበት መግለጫ እንዲህ በማለት ገልጸዋል፦ “በጥልቀት የማያስብ አእምሮ ካልሆነ በሥተቀር፣ ይህ ሃገራዊ ጣዖትነት ወይም ሃገራዊ ሃይማኖት የሚል ሓሳብን የሚያነሳሳ ሰው ባልኖረ ነበር፤ ወይም ለአምላክ ለፈጣሪ ዓለም፡ የሁሉም ሕዝቦች ንጉሥና ሓጋጊ የሆነ፡ በፊቱ ሁሉም ልክ እንደ የውሃ ጠብታ የሆኑ፡ ይህን የመሰለውን አምላክ በደንበር ከልሎ ለኔና ለቀየየ ወይ ለዘሬ ወይ ለሕዝቤ ብቻ ብሎ ሊወስነው ወይ ሊያግተው የሚፈልግ አንድም ሰው …ባልተገኘ ነበር። ያም ሆኖ ግን ያቺ የሓርነት ቀን ትመጣለች፣ የክርስቶስ ጠላቶችን ብቁ ያልሆነ መዝሙርና ዜማን የሚተካ፣ የአምላክ የምስጋና መዝሙር (ስብሓተ ኣምላክ) የሚዜሚባት ዕለት ትመጣለች።” “Mit brennender Sorge” (=በሚነድ/በሚያቃጥል ፍቕር/ሓልዮት)።

ይህን የመሰሉት ግልጽ መግለጫዎች በናዚ-ጀርመን በኩል አንዳችም ግምት አልተሰጣቸውም። ስለሆነም ፕዮስ 11ኛ ሌላ ቃላትና መግለጫዎችም ግምት እንደማይሰጣቸው ሲገነዘቡ፣ መቀጠል የሚገባው ተግባራዊ እርምጃ፣ የሥርዓቱ ሰለባዎች ለሆኑ ስደተኞችና ግፍ የተፈጸመባቸው ሰዎች ተገቢውን ብቁ አገልግሎት መስጠት እንደሚሻል ተረዱ። የናዚ-ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እስከሚሸነፍ ግዜ ድረስ ደግሞ ቅድስት መንበር ይህንን ተልእኾና ተግባር በብቃት አራመደችው።

በቀጣዩ ክፍል “ኮሚዩኒዝም” የሚለውን ንኡስ ክፍል እንመለከታለን
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 18 Oct 2022, 07:35

ኮሚዩኒዝም

በ20ኛው ክፍለዘመን ከተነሱት አምባገነን ሥርዓቶች (totalitarianism) መካከል ለረዢም ግዜ የቀጠለውና የተስፋፋው የኮምኒዝም ሥርዓት ነው። ከሃይማኖት እምነት ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ለሰው ልጆች ጥቅም የታሰበ የኮሚኒስት ዓላማ፣ መልእልተ ባህርያዊ ከሆነው የቤተክርስትያን ዓላማ ጋር የማይጣጣም ሆኖ ተገመተ። ስለሆነም ቤተክርስትያንና ሁሉም ዓይነት ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች “ለሕዝብ መርዙ ነው/ ሕዝብን የሚያደነዝዝ ነው” (ኦፒዩም) ስለተባለ እንዲወገድ ተፈረደበት።

የሩሲያው ኮሚዩኒስታዊ አብዮት እጅግ ቀፋፊ የሆነ የደም መፍሰስን አስከትሏል። ከ 1918 እስከ 1920 ብቻ 26 የሚሆኑ አቡናትንና 1200 ካህናት ተገደሉ። ከ 1917 እስከ 1941 ደግሞ የሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን አቡናት ከ 130 ወደ 28፣ ካህናት ደግሞ ከ 50,000 ወደ 5,000 ወረዱ። በዚህ ግዜ የነበሩ ካቶሊካውያን ከሁለት ካህናት በስተቀር ሌሎች አቡናትና ካህናት ተገደሉ አሊያም ታሰሩ ወይም ከሃገር እንዲሰደዱ ተደረገ።

በሩሲያ የኮሚኒዝም እንቅስቃሴ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወላፈን እንዳንዣበበት ለሃገር ድሕነት ሲል ከሩሲያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ጋር ስምምነትና መተጋገዝ ላይ ለመድረስ ተገደደ። ስለሆነም ሩሲያ ውስጥ ሃይማኖት የሚያስፈልግ ከሆነ ኦርቶዶክስ ብቻ ሊሆን እንደሚቻል ለካቶሊክ ግን ምንም ዓይነት ቦታ እንደማይፈቀድና እንደማይኖር ተደረገ። ከዚህ ሁሉ ጋርም የመንግሥት ይፋዊ ጸረ-አምላክና ጸረ-እምነት አመለካከት ጭራሹኑ ለውጥ አልተደረገበትም ብቻ ሳይሆን አልተነካም እንደነበረውም ቀጠለ። ስለሆነም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በሩሲያ ሆነ የኮሚኒስት ካምፕ ውስጥ ከነበሩት ሃገራት፣ የካቶሊክ ቤተክርስትያንን ለማዳከም፣ ጭራሹኑም እንድትጠፋና እንድትደመሰስ ለማድረግ ብዙ ተጣረ።

ለፕሮፓጋንዳ እንዲመች ተብሎም፣ በሃገሪቱ ውስጥ ብዛት ያላቸው ካህናት እንዲንቀሳቀሱ ተደረገ፣ ተግባር ላይ ግን ክህነታዊ አገልግሎታቸው በጣም የተገደበ ወይ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ሁኔታ ላይ ከቤቶቻቸው እንዳይወጡም ሳይቀር እንደ እስረኛ የተከለከሉ ነበሩ። ማንኛውም ዓይነት ካቶሊካዊ ስብሰባ ወይ ማኅበር ጭራሹኑ ታገደ። ምንም እንኳን ሁሉም መእመናን ባይታሰሩና ባይገደሉም፣ አዳዲስ ተከታዮችን ለማፍራት የሚደረገው ጥረት ጭራሹኑ ተከለከለ፣ መእመናን በሃይማኖታቸው የጸኑ ከሆኑ ደግሞ በፓርቲው ሆነ በሃገሪቱ መንግሥት ውስጥ ምንም ዓይነት ስፍራ ሆነ ዕድገት አይሰጣቸውም ነበር።

ቻይና፡ ልዩ ሁኔታ፥ ቻይና ውስጥ ቤተክርስትያን በኮሚኒስታዊው ሥርዓት ምክንያት ከሁለት ተከፍላ ትገኛለች። በሥርዓቱና በፓርቲው የምትተዳደር አንዲት ሃገራዊት ቤተክርስትያን (Patriotic Church) ስትኖር፣ ይህንን ሂደት የማትቀበል ግን ደግሞ ከእንተ ላዕለ ኩሉ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ጋር የምትጓዝ፣ መንግሥት የማያውቃት ከቻለም ሊያጠፋት የሚጥር፣ እንድትኖርም የማይፈቀድላት ቤተክርስትያንም አለች። ልዩነታቸው ምንድን ነው ከተባለ፣ በእምነት-ሃይማኖት አንድ ናቸው፣ ነገር ግን የሃገራዊቷ ቤተክርስትያን አቡናት የሚሠየሙት በመንግሥት ነው፣ ማንኛውም ዓይነት አካሄዷም በመንግሥት መመሪያ ቁጥጥር ስር ነው። ባጀቷ ሆነ ማንኛውም ወጭዋ ከመንግሥት ነው፣ ስለሆነም ነጻ ቤተክርስትያን አይደለችም።

በሌላ በኩል ደግሞ “ድብቋ” ቤተክርስትያን ደግሞ ከሮማ መንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላትን ግንኙነትና አንድነት ትጠብቃለች፣ ካህናቶቿን በድብቅ መልምላ ክህነትን ታለብሳለች፣ አቡኖቿ በድብቅ የሚንቀሳቀሱና በመንበረ ጴጥሮስ የሚሰየሙ ናቸው። በቅርቡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ሃገራዊዋን ቤተክርስትያን ለማቀራረብ ብዙ ጥረዋል፣ ነገር ግን አልተሳካላቸውም።

በቀጣዩ ክፍል “የርእሰ ሊቃነጳጳሳት ማስጠንቀቅያ” የሚለውን ንኡስ ክፍል እንመለከታለን።
:mrgreen:

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Assegid S. » 18 Oct 2022, 08:52

ሰላም መለከት;

ከአስተማሪ ጵሁፎችህ የማላውቀውን አውቄ የጎደለኝንም ሞልቼበታለሁና ምስጋናዬ ብዙ ነው። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ይህ forum ለእንዲህ አይነቱ መማማሪያና መተራረሚያ መድረክ ይሆን ዘንድ ነውና በድጋሚ እናመሰግንሀለን።

ቻይናን በሚመለከት፦ ከጥቂት ዓመታት ጀምሮ የቻይናን ሰማይ "ከመስቀል የፀዳ" ለማድረግ የኮሚኒስት አመራሩ እየወሰደ ያለውን ... ከየቤተክርስቲያኑ ላይ የመስቀል ምልክትን የማውረድ (የማንሳት) ተግባር ግን የትኛውም ምክንያት ቢሰጠው ፍፁም ሊዋጥልኝ ያልቻለ ተግባር ነው። እኔ እንደ ግለሰብ ባልስማማበትም፥ ኣንዳንዶች ቻይና በተለያየ አጋጣሚ ለሚደርስባት ማህበረሰባዊ መቅሰፍት (የ corona ቫይረስን) ጨምሮ ምክንያት የሚያደርጉት ይህን አይነቱን ፀረ-ክርስቲያናዊ አቋም ነው። የሆኖ ሆኖ ግን የሚቀጥለውን “የርእሰ ሊቃነጳጳሳት ማስጠንቀቅያ” ጽሑፍህን በጉጉት እንጠብቃለን 8)

Chinese officials remove crosses from churches amid coronavirus for being 'higher than the national flag'

ከይቅርታ ጋር ደግሞ እነዚህን ሁለት የ Roman fasces ምስል እንድለጥፍ ይፈቀድልኝ 8)

መልካም ሳምንት ... ወንድም Meleket




Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 19 Oct 2022, 02:56

ወንድም Assegid S.ስለ ማበረታታትህ እኛም ከልብ ኣመስግነናል። ይህን ጽሑፍ ለመማማሪያነት ስናጋራ፡ በጽሁፉም ጭምር የጎደለ ካለ እንድንሞላበት እና የእውቀት አድማሳችንን ለማስፋት ይረዳን ዘንድ በማለም ነው። የለጠፍከውን የRoman fasces ምስል፡ ብዙዎች ኣናውቀው ይሆናል፡ ኣሁን ግን ይህን ምስል "ፈላጭ ቆራጭ" ከሚለው ኣባባል ጋር እያመሳሰልን እናስታውሰዋለን። ሌሎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ተመሳሳይ ኣስተማሪ ጽሑፎችን በማጋራት የእውቀት አድማሳችንን እንድናሰፋ ቢያግዙን መልካም ነው እንላለን።

ቀጣዩን ጽሁፍ በቀጣይ ከጥናታዊው ጽሁፍ ቀንጭበን እናቀርባለን። ለአንባቢዎች ሁሉ መልካሙን ሁሉ እየተመኘን።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 26 Oct 2022, 03:37

የርእሰ ሊቃነጳጳሳት ማስጠንቀቅያ

እ.ኤ.አ. በ1937 ዓ.ም. ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 11ኛ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት ማስጠንቀቂያ፣ ይህ የኮሚዩኒዝም የተጋነነ ጥራዝ ነጠቅ አካሄድ አደገኛ መሆኑን፡ ይህ ለራሱ አስቀድሞ ከነበረው እጅግ ኋላቀር አስተሳሰብ የከፋ በመሆኑ ይህንኑ ለመቃወም መሆኑን አመለከቱ። “አሁን ላለው ዓለም፡ ይህን ነጻ በሆነ አስተሳሰብ የቆሰለውን (liberal) ዓለም ሊፈውስ የሚችል፣ ያ የሰራተኛው መደብ ሓሳብ አይደለም፣ ፍራቻንና ሽብርን ማንገሥም አይደለም፣ የመንግሥት ፈላጭ ቆራጭነትም አይደለም፣ ይልቁንስ በማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ ሥርዓት፡ ማኅበራዊ ፍትሕና ቅንነትን ያማከለ ክርስትያናዊ ፍቅር እንዲሠርጽ ማድረግ ነው … ትክክለኛና ሓቀኛ የሆነ ዕድገትና ሥልጣኔ ሊመጣ የሚችለው ማንኛውም ነገር በፍቅርና በስምምነት የጋራ ጥቅም በሚያጎናጽፍ አመራር ሲካሄድ ብቻ መሆኑን ገልጸናል … ለነፍሳት ጥቅም፣ መንግሥተ-ሃገር ከዚህ ከቤተክርስትያን መንፈሳዊ ውጥን ጋር ተስማምቶ መጓዙ የግድ ይለዋል። ይህ ማለት ደግሞ ሃገሮች በደንበራችው ውስጥ ፀረ-አምላክ የሆነ አመለካከት የኅብረተሰብን መሠረት የሚያናጋ አደገኛ አስተሳሰብንና አላማን እንዳይፈቅዱ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ማለት ነው። የመለኮታዊው መምህር ሥልጣን ከሌለ በዚህ ምድር ውስጥ ምንም ዓይነት ሥልጣን ባልኖረ ነበር፣ ያ በሕያው አምላክ ስም የሚደረግ ማሕላ ካልሆነ በስተቀር ማሕላ የሚባል ነገር ባልኖረ ነበር፣ “ክርስቶስ ፍቅር ነው” (Caritate Christi) https://www.vatican.va/content/pius-xi/ ... pulsi.html በሚል አርእስት ስር በወጣው ሓዋርያዊ መልእክታችን እንደገለጽነው አሁንም እንደግምላችኋለን “ማንኛውም ዓይነት ዋስትናና የሕሊና ሁኔታ በሌለበት አኳኋን ምን ዓይነት ውል ነው ሊፈጸም የሚችለው? ምን ዓይነት ማሕላስ ነው ሊጠበቅና ሊጸና የሚችለው? ማንኛውም ዓይነት ውልስ ምን ዓይነት ዋጋ ሊሰጠው ይችላል? ፈሪሓ እግዚአብሔርና፡ አምላኽን ማመን በሌለበት ስፍራ እንዴት አድርገን ስለ የኅሊና ዋስትና ልንናገር እንችላለን? ይህንን መሠረት ካስወገድን፣ ማንኛውም ሞራላዊ ሕግ አብሮት ነው የሚወገድና የሚደመሰስ ....መንግሥት ቤተክርስትያንን ሙሉ በሙሉ መንፈሳዊና መለኮታዊ ተግባሮቿን እንድትፈጽም ነጻ ሊተዋት ይገባል።” (Divini Redemptoris)። https://www.vatican.va/content/pius-xi/ ... toris.html

በቀጣዩ ክፍል “ሃይማኖትን የሚቃወሙ መንግሥታት” የሚለውን ንኡስ ክፍል እንመለከታለን።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 06 Feb 2023, 05:44

ሃይማኖትን የሚቃወሙ መንግሥታት፦

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ምስራቅ ኤውሮጳ በኮሚዩኒዝም በመያዙ ሃይማኖትን የሚቃረነው አካሄድ ካቶሊካዊነት በተስፋፋባቸው ሃገሮች ውስጥም ገብቶ በመንሰራፋቱ፣ አቡናትና ቤተክርስትያን በዚህ ገደብን ባበጀ ዕንቅፋት የሆነ መጤ ሁኔታ ችግር ውስጥ ተገኙ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 12ኛ ደግሞ፣ በሚከተለው ሁኔታ መልሳቸውን ሰጡ፣ “ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በግዙፍ የቤተክርስትያን ሕንጻ በአራት ግድግዳዎች ውስጥ ብቻ ተዘግታ እንድትቀር አትፈቅድም በጭራሽም አትቀበለውም። በዕለታዊ ሕይወትና በእምነት መካከል በቤተክርስትያንና በዓለም መካከል እያልክ የሚከፋፍል ውጥንን መፍጠር ከክርስትያናዊና ካቶሊካዊ ሓሳብ ጋር የሚጻረር ነው”(የ፵ ጾም ስብከት 1946)።

በ1949 በሃንጋሪያዊው ሊቀጳጳሳት ካርዲናል ሚንድዘንቲን ለመወንጀል በተደረገ እጅግ በተቀናበረ የፍርድ ዝግጅት ወቅት እኒህ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 12ኛ እንዲህ ይላሉ “ያ ሁሉንም ሊጠቀልል የሚሻና (totalitarianism) አምባገነን እንዲሁም ፀረ ሃይማኖት የሆነ መንግሥት፣ ቤተክርስትያን ትናገር ዘንድ ድምጿንም ታሰማ ዘንድ ተገቢ ሆኖ እያለ፣ ዝም ትል ዘንድ ይሻል፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ድምጿን ከፍ አድርጋ ልታውጀው ሲገባት፡ ከሰዎች ፍላጎት ጋር እንድታዳቅለው ይሻል፣ ስለሆነም ሰዎች የኅሊና ጭቈናና ሥቃይ ሲያጋጥማቸው ጠበቃ የማትሆናቸው ልሣን የማትሆናቸው መብታቸው ሆነ ሓርነታቸው ሲነካ ጠበቃ የማትሆን ቤተክርስትያን “ሂዱ ሁሉንም ሰዎች በጎደናዎች አስተምሯቸው” የሚል ትእዛዝን ከክርስቶስ የተቀበለች ቤተክርስትያን በአራት ግድግዳዎች መሃል ታጥራ ከቀረች ኃላፊነቷን አልተወጣችም ማለት ነው። ስፍር ቁጥር የሌላቸው በርካታ የአማንያንና የሰማዕታትን ውርስ የተቀበላችሁ የተወደዳችሁ ልጆቻችን! ይህች የምትረከቧትና የምታፈቅሯት ቤተክርስትያን በአራት ግድግዳ ውስጥ ብቻ የታጠረች ናትን? በዚህች ቤተክርስትያን ውስጥ የእናታችን ቅድስት ቤተክርስትያንን ፊት ታያላችሁን? ይህ ከላይ የተጠቀሰውን ፀረ ሃይማኖት የሆነን ተግባር የሚጠይቅ መንግሥትን የሚቀበል የጴጥሮስ ምትክ ወይም ተኪ በአእምሯችሁ ሊሳል ይችላልን?”

በ1950 በተከበረ ቅዱስ ዓመተ-ድኅነት፣ በሶቪየት ሩሲያና በምዕራቡ ዓለም መካከል በነበረው “ቀዝቃዛው ጦርነት” ስለሚባለው ጕዳይም ጠቅሰው ገልጸዋል። እኒህ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፕዮስ 12ኛ ይህ ቀዝቃዛው ጦርነት ያከትም ዘንድ የሚከተለው ቃላቸውን ሰጥተው ነበር፦ “ግድግዳዎችና መጋረጃዎች ይወገዱ! የእሾህ ሽቦ አጥሮችም ይፍረሱ፣ እያንዳንዱ ሕዝብ የሌላኛው ሕዝብን ሕይወትና ሁኔታ እንዲያውቅ ዕድሉ ይሰጠው፤ አንዳንድ ሃገሮች ከሰለጠነው ዓለም የተነጠሉ መሆናቸው፡ ለዓለም ሰላም እጅግ አደገኛና አስጊ በመሆኑ ይህ ተነጽሎ ሊወገድ ይገባል!! በሕዝቦች መካከል ወንድማማቻዊ የትብብር ስምምነት ያድግ ዘንድ ቤተክርስትያን ለዚህ ትግባሬ የሚሆን ዕድል ለማመቻቸት ምን ያህል ያልጣረችና ያልተመኘኝ!! በቤተክርስትያን ቋንቋ ምዕራብና ምሥራቅ ማለት ተቃራኒ ኃይሎች ወይ ጎራዎች ማለት ሳይሆን፣ የጋራ ውርስ ያላቸው፣ ለወደፊቱም ይህን የጋራ ውርስና ሃብት በጋራ ሊሰራበትና ልንገለገልበት እንደሚገባ አድርጋ ነው የምታስበው። በተሰጣት መለኮታዊ ተልእኮ መሠረት ቤተክርስትያን የሁሉም ሕዝቦች እናት ነች፣ ለሁሉም ሰላም ፈላጊዎች ደግሞ ታማኝ ጓደኛና ጥበበኛ መሪ ነች።” የሚገርመው ግን ይህን የመሰለ የቅዱስ ዓመት ማሳሰቢያ እየተሰጠ፡ በምዕራብና ምሥራቅ ኮርያ መካከል የተካሄደው ውጊያ በዚሁ ዓመት ተቀጣጠለ/ተፏፏመ።




ፈጣሪ ሰላም ወዳድ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ይባርክ!
:mrgreen:

Post Reply