Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 12 Jul 2019, 02:17

ይህ ጽሑፍ Hidmona H Rights ከጻፉት መጸሐፍ የተቀነጨበ ነው። መንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነታቸው ምን እንደሚመስልም በጥንቱ ዘመን በመካከለኛው ዘመንና በዘመናዊው ዓለም ይተነትንንልናል። ይህን ታሪኽ ጠንቅቀው ያልተገነዘቡ የዘመናችን ፖለቲከኞች ጽንሰ ሃሳቡን ጠንቅቀው ካለመረዳታቸው የተነሳ የተሳሳተና የተወላገደ ትርጓሜ ሲሰጡት ስለሚታዩ እስቲ ይህን ሳይንሳዊ ጥናት “ኣልቦ ነገር ወኣልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎም፡. ውስተ ኵሉ ምድር ወፅኣ ነገሮሙ፡. ወእስከ ኣጽናፈ ዓለም በጽሓ ነቢቦሙ።” እያልን ደራሲዎቹን እያመሰገንን እንማማርበት። መልካም ንባብ። https://www.amazon.com/%E1%8D%96%E1%88% ... 1771365498

የሃይማኖትና የፖለቲካ (መንግሥት) ግንኙነት - በታሪክ አኳያ

“እነኝህ ሁለት ዓይነት ፍቅሮች ናቸው፤ የመጀመሪያይቱ መንፈሳዊት ነች፣ ሁለተኛዋ ግን መልካም አይደለችም (መጥፎ ነች)፣ የመጀመሪያይቱ ማኅበራዊ ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን ግላዊና ስስታም ነች፣ ለኔ ብቻ ባይ ናት፣ የመጀመሪያይቱ ስለ ሰማያዊቷና መንፈሳዊቷ ማኅበር ስትል የጋራ ጥቅምን ስትመለከት፣ ሁለተኛይቱ ግን በስግብግብነት ሁሉንም ማኅበራዊ ጉዳዮች ለራሷ ለግሏ ብቻ ልትወርስ ወይ ልታግበሰብስ ትፈልጋለች፣ ምክንያቱም በትዕቢት የተወጠረች ስለሆነች ነው። የመጀመሪያይቱ በአምላክ ስር የምትኖር ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን የአምላክን ህልውና ከናካቴው የምትጻረር ነች፤ የመጀሪያይቱ የተረጋጋች ስትሆን ሁለተኛይቱ ግን በጥባጭና በሁከት የተመላች ነች፤ የመጀመሪያይቱ ሰላማዊት ስትሆን፤ ሁለተኛይቱ ግን ነውጠኛ ነች፣ የመጀመሪያይቱ የተሳሳቱ ሰዎች ከሚያሞካሿት ይልቅ ሓቅን ትመርጣለች፣ ሁለተኛይቱ ግን በፈለገው አኳኃን ይምጣ በውሸት የሚያሞካሻትንና ከንቱ ውዳሴን ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ትሻለች። የመጀመሪያቱ ትሕትና የተመላችና ተወዳጅ ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን ቅናታም ነች። የመጀመሪያይቱ እሷ ለራሷ የምትሻውን ለማንኛውም አካል ትመኛለች፣ ሁለተኛይቱ ግን ማንኛውንም አካል ለማንበርከክ ትሻለች። የመጀመሪያይቱ ለጓደኛዋ ወይ ጎረቤቷ መልካም እንዲሆንለት ስትጥር፣ ሁለተኛይቱ ግን ጓደኛዋን ወይም ጎረቤቷን እንደ መገልገያነት ትጠቀምበታለች።

በሰው ልጆች መካከል ሁለት ከተሞች አሉ። እነርሱም ሊለካና ሊደረስበት በማይችለው የአምላክ በጎ ርህራሄ ስር ይገኛሉ። አምላክ ማንኛውንም ፍጡር የሚያስተዳድር ነው። የመጀመሪያዋ ከተማ የቅኑዎችና የጻድቃኖች ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን በመንፈስ የደነዘዙት ከተማ ነች። እነዚህ ሁለት ከተሞች ለግዜው የተደበላለቁ ቢመስሉም፣ በመጨረሻው የፍርድ ዘመን ግን ይለያያሉ ይህም ማለት መለያየታቸው አይቀሬ ነው . . .” (ቅዱስ ኣጎስጢኖስ -De Genesi ad Litteram XI, XV. 20; Augustine’s Quest of Wisdom 249)

ይህ ትልቅ መምህር፣ የኅብረተሰብን አውታሮች(እርከኖች) ከሁለት መድቦታል፣ ክርስትናዊና አረማዊም ብሎታል። ሥልጡን የነበረው የሮማዊያን ግዛት ተሸንፎ፣ ሮማም እ.ኤ.አ.በ410 ዓ.ም. አላሪክ በተባሉ የሰሜን ወራሪዎች እንደተያዘች፣ አጎስጢኖስ “የእግዚአብሔር ሃገር” ወይም “ሃገረ እግዚኣብሔር” (The City of God) የተሰኘች መጸሓፉን ደረሰ። በዚችው መጸሓፉም በታሪክና በታሪክ ጉዞ ላይ ያለውን አመለካከት አነጥሮና ኣብራርቶ ይገልጻል። መንፈሳዊቷ “የእግዚአብሔር ሃገር ወይ ከተማ” እንዴት እንደተቆረቆረችና እንዳደገች (ምንጯንና አስተዳደጓን ወይም አበለጻጸጓን)፣ እንዲሁም ዓለማዊዋና (ዓላዊት/ወዳቂዋ/ ተሳሳቿ) “የሠይጣን ከተማ ወይ ሃገር” በሚለዋወጠውና በሚገለባበጠው ሥልጣኔ መካከል እንዴት አድርጋ እንደምትበቅልና እንደምትታይ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይዘረዝረዋል። ሮማውያን የነበራቸውን ባሕሪያዊና መንፈሳዊ ኃይል እንዳጠፉ፣ ተንገዳግደውና ተሰነካክለው ወደቁ፣ የሮማውያን ሥልጣኔ ቢደመሰስም እንኳን፣ ክርስትያናዊቱ ከተማ ግን በሕይወት እንደምትኖርና እንደምትቀጥል የአጎስጢኖስ የማይናወጥ ግንዛቤ ነበር።

ስለሆነም የሮማ ግዛትና ሥልጣኔ እንዳለፈ፣ አዲስ የመካከለኛው ዘመን ክርስትያናዊ ግዛት ተከሰተ፣ ተስፋፋም፣ ማእከሉንም በተለይ በአውሮፓ እምብርት (በጀርመን) አካባቢ አደረገ። ያም ሆኖ የአጎስጢኖስን ጹሁፎች ያነበቡ ሰዎች ትኩረታቸው ሁሉ፣ “አጎስጢኖስ ያለው ሁሉ መች ይሆን የሚፈጸም??” የሚል ይመስል ነበር። ይህም ሌላ ውጥረትን ፈጠረ፤ ዓለማዊቷን ከተማ፣ በሮማውያን መንግሥት ከወከልናት፣ አዲስቷን ክርስትያናዊ መንግሥትንስ ታድያ በምንድን ነው የምንወክላት/የምንገልጻት (እንዴት ልናያት ነው)? ይህም ስለሆነ አንድ አዲስ አይነት አመለካከት ተከሰተ፣ ይሀውም -
 እንዲያው በደፈናው መንግሥተ-ሃገርን (the State) ከዓለማዊቷ ከተማ ጋር ማመሳሰል እንደማይገባ፣
 ስለሆነም መንግሥትና ቤተክርስትያን፣ አንዲት የ“ አምላክን ከተማ” ማቆም/መመስረት አለባቸው የሚል ሓሳብ ገነነ፡ አንሰራፋም።
 አንድ “ክርስትያናዊ ኅብረት” (Christian Commonwealth) ሆነውም መንፈሳዊና ምድራዊ፣ የቤተክርስትያንና የዓለም (ፖለቲካዊ አኳኋን) የሚወሃሃድበትና፣ ግን ደግሞ ሁለቱ የተለያየ ችሎታና ጥበብ/አመለካከት መሆኑም ታወቀ።

ከዚህ አስተሳሰብም የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ኅብረትና አንድነት፣ ሁለቱም ተፈጠረ። ቤተክርስትያንና መንግሥት፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ጭራሹኑ ተደበላለቀ ተዳቀለም። አሁን አሁን በሁሉም በበለጸጉ ሃገሮች ያለው - “ የመንግሥትና የቤተክርስትያን መለያየት” (Separation of Church & State) ከሚባለው ዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር የሚጋጭ ሓሳብና አመለካከት ተስፋፋ ገነነም። ሆኖም ግን ይህን ፍጹም የሆነ ልዩነት የሚል አመለካከትን ባጠናከርክ ቁጥር፣ መንግሥትና ቤተክርስትያን ፍጹም ከተለያዩ፣ አስቀድሞ ወደተጠቀሰው የአጎስጢኖስ ሃሳብ ወይ አመለካከት እንደ መመለስ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ቤተክርስትያን ከዕለታዊና የወትሮ የኅብረተሰብ ህላዌ አኳያ፣ ልትገለል ወይ ልትነጠል ነው ማለት ነው፤ የመጭው ዓለምና መንፈሳዊ ወገን ብቻ ተደርጋ ትታሰብ የነበረቸው፣ በኅብረተሰብ ዕለታዊ ሕይወት ውስጥ ልትፈጽመው የሚገባት ሚናና ሊኖራት የሚገባ ተጽዕኖና ልትሰጠውና ልታበረክተው የሚገባት ብርሃንን እንድታበረክት ዕድል አይኖራትም ማለት ነው። በሌላ አኳያ ደግሞ ይህ አመለካከት ዓለማዊውን መንግሥት ወይም ፓለቲካዊውን ወገን ብቻውን ራቁቱን የሚያስቀር፣ ማንኛውም ከመንፈሳዊ ወገን ሊያገኘው ይችል ከነበረ ብርሃንና ድጋፍን እንዳያገኝ የሚያስደርግ፣ ስለሆነም ለብቻው ተገልሎ፣ ወደ ስስታምነትና አረመኒያውነት፣ አጎስጢኖስም ሳይቀር ወደገለጸው ዓለማዊነት ሁኔታ አያመራምን? የሚል ጥያቄን አነሳሳ።

በእምነት የተሞሉ ምሁራንና ተሞክሮ ያላቸው ሰዎችም ሊያስሱት የሚገባቸው፣ ይህን ቀላል መልስ የማይገኝለትን ጥያቄ ሊያስቡበት እንደሚገባ ነው። ስለሆነም ይህን ልንረዳ እንችል ዘንድ እንዲያግዘን፣ ወደ ኋላ ተመልሰን የታሪክን ጉዞ መፈተሽ ይገባናል። የቤተክርስትያንና የመንግሥት ግንኙነቶች ባለፉት ዘመናትና፣ አሁን ደርሶበት ያለ ሁኔታን ማየት ያስፈልገናል። ምክንያቱም ታሪክ የሕይወት መምህር ነችና።

በቀጣዩ ክፍል በዘመነ አረመኒያዉያን ይህ የመንግሥትና የሃይማኖት ግንኙነት ምን ይመስል እንደሆነ እንቃኛለን። :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 12 Jul 2019, 11:27

በዘመነ አረመኔነት

ክርስቶስ ከመምጣቱ አስቀድሞ፣ “የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር” የሚለውን ትምህርቱን ከመዘርጋቱ በፊት፣ የነበሩት እንደ ሮማዊያን ያሉ ትልልቅ መንግሥቶች፣ መንፈሳዊንና ፖለቲካዊ ኃይልንና ዘዴን አጣምረው የሚጓዙ ነበሩንጉሥ በመንፈሳዊ ጉዳይም ውስጥ ዋና ሆኖ፣ ሕዝባዊ አምልኮንም ሳይቀር የሚያከናውን እሱ ራሱ ነበር። ምክንያቱም ይህን የመሰለው ሥርዓትና አገባብ ከአርበኝነት ጋር ይያያዝ ስለነበር ነው። በክርስቶስ ግዜ ግን ይህ አገባብ መልኩንና አፈጻጸሙን ቀይሮ፣ ንጉሥ ሕዝቡን ወደ አምልኮ የሚመራ መሆኑ ቀርቶ፣ እሱ ራሱ የሚመለክ፣ ወይም አምልኮና ስግደትን የሚቀበል፣ እንዲያው ባጭሩ “አምላክ” ሆኖ ተገኝ:mrgreen:

ይህም በምስራቅ ወገን ጀምሮ፣ በሮማዊ ግዛት ውስጥም የታየው በአውግስጦስ ቄሥር ዘመን (ከ31 ቅ.ል.ክ. እስከ 14 ዓ.ም.) ሲሆን፣ ይህ ልማድ የኋላ ኋላ አድጎና ተስፋፍቶ፣ ንጉሥን የማምለክ ሁኔታ ለንጉሥ ይሰጠው ከነበረው የአርበኛነት ስሜት ጋር ተወሃህዶ ተገኘ። እንዲያ ሲሆንም፣ እንግሊዛዊው ሎርድ ኣክተን ያለው ቃል መፈጸሙ የግድ ሆነ፦ “ሥልጣን፣ በተለይም ወሰን ወይ ገደብ የሌለው ሥልጣን፣ ወሰን ወይም ገደብ የሌለው ሙስናን ይፈጥራል ወይም ያስከትላል”። ይህን ለመሰለው ጨቋኝነትና አፋኝነት እንዲሁም አምባገነንነት (Oppressive Totalitarianism) ቀደምት የክርስትያን መሪዎችና የሥነ-መለኮት መምህራንና፣ የቤተክርስትያን አበው ሽንጣቸውን ገትረው ታጥቀው ተዋግተውታል

እኒያ የቤተክርስትያን የመጀመሪያዎቹ መምህራን እምንላቸው (አበው) በሐዋርያት በኩል አድርጎ ወደ እነርሱ የደረሰውን አዲስ የክርስቶስ ትምህርት ለማቀብና ለማስተላለፍ ጣሩ። ስለሆነም “የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር” የሚለውን የክርስቶስ መመሪያ፣ እንዲሁም “ማንኛውም ሰው ለበላዮ ወይም በሱ ላይ ለተሾመው ባለ ሥልጣን ይገዛለት፣ ምክንያቱም ከአምላክ ካልሆነ በስተቀር፣ ሌላ ሥልጣን የለምና። እነኝህ በሕይወት ያሉ ባለ ሥልጣኖችም በአምላክ የተሾሙ ናቸው፣ ስለሆነም ባለ ሥልጣንን የሚቃወም፣ አምላክ የሾመውን ነው የሚቃወም ማለት ነው”። (ሮሜ 13፡1) ለማቀብና ለማሸጋገር ጣሩ።

በቀጣይ ክፍል ይህን በተመለከተ አበው የቤተክርስቲያን መምህራን እነ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ ምን ይላሉ የሚለውን ክፍል እንመለከታለን።
:mrgreen:

AbebeB
Member
Posts: 4144
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by AbebeB » 12 Jul 2019, 11:30

Why you insult us? Please avoid: “ኣልቦ ነገር ወኣልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎም፡. ውስተ ኵሉ ምድር ወፅኣ ነገሮሙ፡. ወእስከ ኣጽናፈ ዓለም በጽሓ ነቢቦሙ።”

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 12 Jul 2019, 11:50

AbebeB wrote:
12 Jul 2019, 11:30
Why you insult us? Please avoid:.....
አቶ AbebeB እንዴ ቀስ በል እንጂ፣ ምን ነካህ ሰው ይታዘበኛል አትልም እንዴ! ይህ ትምህርት ቤት እንጂ ጠጅ ቤት እኮ አይደለም! :lol: አንተንና መሰል ‘ረቂቅ ፖለቲከኞቻችንን’ ለማስተማር ነው የምርምሩን ውጤት እዚህ ያመጣነዉ እኮ! :mrgreen:

Degnet
Senior Member+
Posts: 23433
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Degnet » 12 Jul 2019, 11:54

Meleket wrote:
12 Jul 2019, 02:17
ይህ ጽሑፍ Hidmona H Rights ከጻፉት መጸሐፍ የተቀነጨበ ነው። መንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነታቸው ምን እንደሚመስልም በጥንቱ ዘመን በመካከለኛው ዘመንና በዘመናዊው ዓለም ይተነትንንልናል። ይህን ታሪኽ ጠንቅቀው ያልተገነዘቡ የዘመናችን ፖለቲከኞች ጽንሰ ሃሳቡን ጠንቅቀው ካለመረዳታቸው የተነሳ የተሳሳተና የተወላገደ ትርጓሜ ሲሰጡት ስለሚታዩ እስቲ ይህን ሳይንሳዊ ጥናት “ኣልቦ ነገር ወኣልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎም፡. ውስተ ኵሉ ምድር ወፅኣ ነገሮሙ፡. ወእስከ ኣጽናፈ ዓለም በጽሓ ነቢቦሙ።” እያልን ደራሲዎቹን እያመሰገንን እንማማርበት። መልካም ንባብ። https://www.amazon.com/%E1%8D%96%E1%88% ... 1771365498

የሃይማኖትና የፖለቲካ (መንግሥት) ግንኙነት - በታሪክ አኳያ

“እነኝህ ሁለት ዓይነት ፍቅሮች ናቸው፤ የመጀመሪያይቱ መንፈሳዊት ነች፣ ሁለተኛዋ ግን መልካም አይደለችም (መጥፎ ነች)፣ የመጀመሪያይቱ ማኅበራዊ ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን ግላዊና ስስታም ነች፣ ለኔ ብቻ ባይ ናት፣ የመጀመሪያይቱ ስለ ሰማያዊቷና መንፈሳዊቷ ማኅበር ስትል የጋራ ጥቅምን ስትመለከት፣ ሁለተኛይቱ ግን በስግብግብነት ሁሉንም ማኅበራዊ ጉዳዮች ለራሷ ለግሏ ብቻ ልትወርስ ወይ ልታግበሰብስ ትፈልጋለች፣ ምክንያቱም በትዕቢት የተወጠረች ስለሆነች ነው። የመጀመሪያይቱ በአምላክ ስር የምትኖር ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን የአምላክን ህልውና ከናካቴው የምትጻረር ነች፤ የመጀሪያይቱ የተረጋጋች ስትሆን ሁለተኛይቱ ግን በጥባጭና በሁከት የተመላች ነች፤ የመጀመሪያይቱ ሰላማዊት ስትሆን፤ ሁለተኛይቱ ግን ነውጠኛ ነች፣ የመጀመሪያይቱ የተሳሳቱ ሰዎች ከሚያሞካሿት ይልቅ ሓቅን ትመርጣለች፣ ሁለተኛይቱ ግን በፈለገው አኳኃን ይምጣ በውሸት የሚያሞካሻትንና ከንቱ ውዳሴን ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ትሻለች። የመጀመሪያቱ ትሕትና የተመላችና ተወዳጅ ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን ቅናታም ነች። የመጀመሪያይቱ እሷ ለራሷ የምትሻውን ለማንኛውም አካል ትመኛለች፣ ሁለተኛይቱ ግን ማንኛውንም አካል ለማንበርከክ ትሻለች። የመጀመሪያይቱ ለጓደኛዋ ወይ ጎረቤቷ መልካም እንዲሆንለት ስትጥር፣ ሁለተኛይቱ ግን ጓደኛዋን ወይም ጎረቤቷን እንደ መገልገያነት ትጠቀምበታለች።

በሰው ልጆች መካከል ሁለት ከተሞች አሉ። እነርሱም ሊለካና ሊደረስበት በማይችለው የአምላክ በጎ ርህራሄ ስር ይገኛሉ። አምላክ ማንኛውንም ፍጡር የሚያስተዳድር ነው። የመጀመሪያዋ ከተማ የቅኑዎችና የጻድቃኖች ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን በመንፈስ የደነዘዙት ከተማ ነች። እነዚህ ሁለት ከተሞች ለግዜው የተደበላለቁ ቢመስሉም፣ በመጨረሻው የፍርድ ዘመን ግን ይለያያሉ ይህም ማለት መለያየታቸው አይቀሬ ነው . . .” (ቅዱስ ኣጎስጢኖስ -De Genesi ad Litteram XI, XV. 20; Augustine’s Quest of Wisdom 249)

ይህ ትልቅ መምህር፣ የኅብረተሰብን አውታሮች(እርከኖች) ከሁለት መድቦታል፣ ክርስትናዊና አረማዊም ብሎታል። ሥልጡን የነበረው የሮማዊያን ግዛት ተሸንፎ፣ ሮማም እ.ኤ.አ.በ410 ዓ.ም. አላሪክ በተባሉ የሰሜን ወራሪዎች እንደተያዘች፣ አጎስጢኖስ “የእግዚአብሔር ሃገር” ወይም “ሃገረ እግዚኣብሔር” (The City of God) የተሰኘች መጸሓፉን ደረሰ። በዚችው መጸሓፉም በታሪክና በታሪክ ጉዞ ላይ ያለውን አመለካከት አነጥሮና ኣብራርቶ ይገልጻል። መንፈሳዊቷ “የእግዚአብሔር ሃገር ወይ ከተማ” እንዴት እንደተቆረቆረችና እንዳደገች (ምንጯንና አስተዳደጓን ወይም አበለጻጸጓን)፣ እንዲሁም ዓለማዊዋና (ዓላዊት/ወዳቂዋ/ ተሳሳቿ) “የሠይጣን ከተማ ወይ ሃገር” በሚለዋወጠውና በሚገለባበጠው ሥልጣኔ መካከል እንዴት አድርጋ እንደምትበቅልና እንደምትታይ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይዘረዝረዋል። ሮማውያን የነበራቸውን ባሕሪያዊና መንፈሳዊ ኃይል እንዳጠፉ፣ ተንገዳግደውና ተሰነካክለው ወደቁ፣ የሮማውያን ሥልጣኔ ቢደመሰስም እንኳን፣ ክርስትያናዊቱ ከተማ ግን በሕይወት እንደምትኖርና እንደምትቀጥል የአጎስጢኖስ የማይናወጥ ግንዛቤ ነበር።

ስለሆነም የሮማ ግዛትና ሥልጣኔ እንዳለፈ፣ አዲስ የመካከለኛው ዘመን ክርስትያናዊ ግዛት ተከሰተ፣ ተስፋፋም፣ ማእከሉንም በተለይ በአውሮፓ እምብርት (በጀርመን) አካባቢ አደረገ። ያም ሆኖ የአጎስጢኖስን ጹሁፎች ያነበቡ ሰዎች ትኩረታቸው ሁሉ፣ “አጎስጢኖስ ያለው ሁሉ መች ይሆን የሚፈጸም??” የሚል ይመስል ነበር። ይህም ሌላ ውጥረትን ፈጠረ፤ ዓለማዊቷን ከተማ፣ በሮማውያን መንግሥት ከወከልናት፣ አዲስቷን ክርስትያናዊ መንግሥትንስ ታድያ በምንድን ነው የምንወክላት/የምንገልጻት (እንዴት ልናያት ነው)? ይህም ስለሆነ አንድ አዲስ አይነት አመለካከት ተከሰተ፣ ይሀውም -
 እንዲያው በደፈናው መንግሥተ-ሃገርን (the State) ከዓለማዊቷ ከተማ ጋር ማመሳሰል እንደማይገባ፣
 ስለሆነም መንግሥትና ቤተክርስትያን፣ አንዲት የ“ አምላክን ከተማ” ማቆም/መመስረት አለባቸው የሚል ሓሳብ ገነነ፡ አንሰራፋም።
 አንድ “ክርስትያናዊ ኅብረት” (Christian Commonwealth) ሆነውም መንፈሳዊና ምድራዊ፣ የቤተክርስትያንና የዓለም (ፖለቲካዊ አኳኋን) የሚወሃሃድበትና፣ ግን ደግሞ ሁለቱ የተለያየ ችሎታና ጥበብ/አመለካከት መሆኑም ታወቀ።

ከዚህ አስተሳሰብም የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ኅብረትና አንድነት፣ ሁለቱም ተፈጠረ። ቤተክርስትያንና መንግሥት፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ጭራሹኑ ተደበላለቀ ተዳቀለም። አሁን አሁን በሁሉም በበለጸጉ ሃገሮች ያለው - “ የመንግሥትና የቤተክርስትያን መለያየት” (Separation of Church & State) ከሚባለው ዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር የሚጋጭ ሓሳብና አመለካከት ተስፋፋ ገነነም። ሆኖም ግን ይህን ፍጹም የሆነ ልዩነት የሚል አመለካከትን ባጠናከርክ ቁጥር፣ መንግሥትና ቤተክርስትያን ፍጹም ከተለያዩ፣ አስቀድሞ ወደተጠቀሰው የአጎስጢኖስ ሃሳብ ወይ አመለካከት እንደ መመለስ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ቤተክርስትያን ከዕለታዊና የወትሮ የኅብረተሰብ ህላዌ አኳያ፣ ልትገለል ወይ ልትነጠል ነው ማለት ነው፤ የመጭው ዓለምና መንፈሳዊ ወገን ብቻ ተደርጋ ትታሰብ የነበረቸው፣ በኅብረተሰብ ዕለታዊ ሕይወት ውስጥ ልትፈጽመው የሚገባት ሚናና ሊኖራት የሚገባ ተጽዕኖና ልትሰጠውና ልታበረክተው የሚገባት ብርሃንን እንድታበረክት ዕድል አይኖራትም ማለት ነው። በሌላ አኳያ ደግሞ ይህ አመለካከት ዓለማዊውን መንግሥት ወይም ፓለቲካዊውን ወገን ብቻውን ራቁቱን የሚያስቀር፣ ማንኛውም ከመንፈሳዊ ወገን ሊያገኘው ይችል ከነበረ ብርሃንና ድጋፍን እንዳያገኝ የሚያስደርግ፣ ስለሆነም ለብቻው ተገልሎ፣ ወደ ስስታምነትና አረመኒያውነት፣ አጎስጢኖስም ሳይቀር ወደገለጸው ዓለማዊነት ሁኔታ አያመራምን? የሚል ጥያቄን አነሳሳ።

በእምነት የተሞሉ ምሁራንና ተሞክሮ ያላቸው ሰዎችም ሊያስሱት የሚገባቸው፣ ይህን ቀላል መልስ የማይገኝለትን ጥያቄ ሊያስቡበት እንደሚገባ ነው። ስለሆነም ይህን ልንረዳ እንችል ዘንድ እንዲያግዘን፣ ወደ ኋላ ተመልሰን የታሪክን ጉዞ መፈተሽ ይገባናል። የቤተክርስትያንና የመንግሥት ግንኙነቶች ባለፉት ዘመናትና፣ አሁን ደርሶበት ያለ ሁኔታን ማየት ያስፈልገናል። ምክንያቱም ታሪክ የሕይወት መምህር ነችና።

በቀጣዩ ክፍል በዘመነ አረመኒያዉያን ይህ የመንግሥትና የሃይማኖት ግንኙነት ምን ይመስል እንደሆነ እንቃኛለን። :mrgreen:
This is another good article.Knowledge is power.

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 16 Jul 2019, 03:15

"መንግሥትና ሃይማኖት" በሚል ርእስ የቀረበው ሳይንሳዊ ጥናት ይቀጥላል፣ መልካም ንባብ!

አበው፣ የቤተክርስትያን መምህራን - ምን ይላሉ?

የሮማ ነገሥታት አረማውያን እስከነበሩበት ግዜ ድረስ፣ የክርስትናን ብቃትና ሓቀኝነት ለማስረዳት ይጥሩ የነበሩት ምሁራን (apologetes)፣ በአንድ በኩል ክርስትናን ሊያጠቁት ከሚነሱ አካላት እየተከላከሉለት፣ ጎን ለጎን ደግሞ ክርስትያን ለመንግሥታቸው ያላቸውን እምነት በመግለጽ፣ ንጉሥን እንደ አምላክ በመቁጠር ማምለክን ግን፣ በጭራሽ የሚኮንኑት ጉዳይ ነበር። በዚህ ምክንያትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ ንጉሥ የተሾመ እንዲመለክና እንዲሰገድለት ሳይሆን፣ በተገቢው መልኩ እንዲከበር ነው፤ ምክንያቱም እሱ በአምላክ የተፈጠረ ሰው እንጂ፣ አምላክ አይደለም” (To Autolycus 1፡11)።

በ 2ተኛው ምእተ ዓመት የነበረው ታሲያን የተባለ ሌላ ክርስትያን ደራሲም - “ንጉሥ እየጠየቀን ያለው ቀረጥ/ግብር እንድንከፍል ነውን? እኔ በበኩሌ ይህን ቀረጥ ወይ ግብር ለመክፈል ዝግጁ ነኝ። አስተዳዳሪው ወይ ገዢው እንዳገለግለው ወይም እንድላከው ነውን የሚጠይቀኝ ያለው? መልካም! በሱ ግዛት ስር (የሱ) በመሆኔ፣ በሱ ስር መሆኔን ሳላወላዳ የምቀበለው ጉዳይ ነው። (against the Greeks 4) ተርቱሉያንም ቢሆን፣ “ክርስትያን የማንኛውም ወገን ጠላት አይደለም፣ የሮማውንም ንጉሥ አይጠላውም” ይላል። (ወደ ስካፑላ 2)።

ክርስትያኖች ንጉሥን ለማምለኽ ፈቃደኞች ስላልሆኑ፣ እንደ “ፀረ-አምላክ” (“atheist”) እንደ “የሰው ልጆች ጠላቶች” ተገምተዋል ወይ ተቆጥረዋል፣ አቻ የማይገኝለት ስደትና ሰማዕትነትን እንዲቀበሉም ተገደዋል። ለንጉሥ መስዋዕት ማቅረብና አለማቅረብም ዋነኛው መፈተኛቸው ነበር፣ ክርስትያኖች ይህንን ድርጊት በማያሻማና በማያወላውል መልኩ ተቃወሙት። ይህ የተባለው ስደት ግን በሁሉም መስክ አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ አልነበረም፤ ስለሆነም አንዳንድ ክርስትያኖች በየግል ሲታዩ(ሲገመገሙ)፣ ቅኑዎች አርበኞችና ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆኑ ነፍጠኞች መሆናቸውን አስመሰከሩ። ምክንያቱም ሠራዊት ውስጥ መሰለፍ ወይም የሠራዊት አባል መሆን ብቻ ሳይሆን፣ በፍላጎት የሠራዊት አባል መሆንም አልነበረም አይባልም።

እኒያ የክርስትና ሰማዕታት ያሳዩት የነበሩት ድፍረትና ጀግንነት፣ ለቀሪዎቹ በሕይወት ለተረፉት ሲያበረታታቸው፣ እንዲህ ያለን ድፍረትንና ጀግንነትን ለመፈጸም የምታበረታታ ሃይማኖት፣ አስፈላጊ መሆን አለባት የሚል ግምገማና ትንታኔ፣ በአረማውያኖቹ ሓሳብና አስተሳሰብ ውስጥ ዳበረ። ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ (Constantine the Great) የክርስትና ሃይማኖትን ነጻ ያወጣበት “የሚላኖው አዋጅ” (The Edict of Milan 313 ዓ.ም.) በመባል የሚታወቅ ሰነድ ነው። ዡልያን ከሓዲው (Julian the Apostate) የተባለው ንጉሥ (361-363)፣ እሱ ራሱ ወደ አረመኔነቱ ተመልሶስ፣ መላው ኅብረተሰቡንም ጭምር ወደ አረመኔነት ለመመለስ (ለመለወጥ)፣ ያችን ሰዓት የኋሊዮሽ ለመዘወር ጥረት አላደረገም አይባልም። ይህ ግን “በከንቱ ጻመውከ ኤሣው” የተባለ ሆነ። ከዚህ በኋላም መንግሥቱ ራሱ፣ ከ 382 በኋላ አረመኔነቱና አረመኒያዊ አመለካከቱ እየተዳከመና እየጠፋ ሄደ

በቀጣዩ ክፍል ቄሣረ-ጵጵስና (Caesaro-papism) የሚለውን ክፍል በጥቂቱ እንቃኛለን።
:mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 20 Jul 2019, 01:20

ቄሣረ-ጵጵስና (Caesaro-papism)

ይህ ቄሣርነትና ጵጵስናን ያጠቃለለ (Caesaro-papism) ሥርዓትና አገባብ፣ እኒያ እስከዚህ ግዜ ድረስ በሁሉም ነገር ላይ ሥልጣን የነበራቸውን የክርስትና-ነገሥታት መብትና ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ወይም እንዲተው፣ ዝግጁዎች እንዳልነበሩ የሚያሳይ ነበር። ስለሆነም ነገሥታት ራሳቸውን እንደ የሃይማኖት ጠበቆች አድርገው ስለሚገምቱና ስለሚቆጥሩ ልክ አቡኖች እንደሆኑ ይታሰቡ ነበር። ለምሳሌ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ፣ እሱ ራሱ “የቤተክርስትያን የውጭ ግንኙነት መስክም ሳይቀር አቡን” ሆኖ እንዲታይ የሚያደርግ አስተሳሰብ ነበር። ቀዳማዊ ንጉሥ ተዮዶስዮስ ደግሞ በ382 እ.ኤ.አ. ባወጣው አዋጁ/ድንጋጌው፣ ክርስትናዊ ቅኑ እምነትና ትምህርት አስፈላጊ እንደሆነና፣ ከዚህ ቅኑ እምነት ያንገራገረ ወይ አሻፈረኝ ያለ በሕገ መንግሥት እንደሚያስጠይቀው አወጀ። ስለሆነም ከመናፍቓን አንጻር የሚወጣ ሕግ ሲበዛና ሲሰፋ ታየ። 57 ዓመታት ባደረገው የዳግማዊ ተዮዶስዮስ ግዛት፣ 68 አዋጆችን አወጀ (408-450)። በነዚህ አዋጆች ግልጽ የተደረገው “ዋነኛውና ተቀዳሚው የንጉሥ ተግባር፣ እውነተኛዋን ሃይማኖት መጠበቅና ማቀብ ሲሆን፣ ያች ሃይማኖት የምታቀርበው ስግደትና አምልኮ ደግሞ ከትክክለኛው ሰብአዊ እድገትና አካሄድ ጋር የተሳሰረ እንዲሆን” መጣር ያለበት መሆኑን የሚያስረዳ ነው። ይህ የቄሣርና የጳጳስ (Caesaro-papism) ሃላፊነቶች መጣመር አድጎ ጫፉ ወይ ጠርዙ ላይ የደረሰበት፣ በዘመነ ታላቁ ንጉሥ ዡስቲንያን (527-565) ነው። በዚህ ንጉሥ አክራሪ ሕጎችና አዋጆች ውስጥ ደግሞ፣ ንጉሥ ውሳኔ ከሚሰጥባቸው የቤተክርስትያን ተልዕኾዎች መካከል አንዳንዶቹ የሚጠቀሱት ናቸው፣ - የጳጳሳት አሰላለፍ፣ ቅደም ተከተልና የሃላፊነት ደረጃ፣ ሢመተ ጳጳሳትን የሚመለከቱ ጉዳዮች ... ውሳኔ መስጠት፣ ሥነ-መለኮትንና (Theology) ሥነ-ኣምልኾን (Liturgy) የሚመለከቱ መመሪያዎች መስጠት፣ የንጉሥ መብት እንደሆኑ አድርጎ ያስቀምጠዋል ወይም ያቀርበዋል።

በቀጣይ ክፍል ይህን ለመሰለው የቄሣረ-ጵጵስናዊ አካሄድ በወቅቱ አበው የቤተክርስትያን መምህራን ያቀረቡትን ተቓውሞ እንቃኛለን። :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 23 Jul 2019, 04:52

አበው የቤተክርስትያን መምህራን ቄሣረ-ጵጵስናን (Caesaro-papism) በተመለከተ ያቀረቡት ተቓውሞ

ይህን ለመሰለው በቤተክርስትያን ውስጥ ገደብየለሽ የንጉሥ ጣልቃገብነትን፣ አንዳንድ አበው፣ በተለይም በምሥራቕ ወገን የነበሩ ጳጳሳት አልተቃወሙትም አይባልም (ተቃውመውታል)። ምክንያቱም ይህን በ 330 እ.ኤ.አ. ቍስጥንጥንያ ውስጥ ላደገው ንጉሣዊ ማእከል፣ አገልጋዮች መሆን ለቤተክርስትያን መሪዎች አልተዋጠላቸውም። በ350 አካባቢ የኮርዶቫ (ስፐይን) አቡን ሆሲዮስ፣ ኢየሱስ የቄሣርን ግብር በተመለከተ የተናገረው ጠቅሰው፣ ንጉሥ ኮስታንታንሲዮስ ዳግማይን እንደሚከተለው አሉት - “አምላክ መንግሥታትን በእጅህ አስረከበህ፣ ለኛ ደግሞ የቤተክርስትያንን ጕዳይ አደራ ሰጥቶናል...፣ ምድራዊውን ሥልጣን ለማካሄድ ለኛ አልተፈቀደልንም፣ ለእርስዎም ጌታየ! ዕጣን (=ቤተመቕደስ) እንዲያጥኑ የተሰጥዎት ችሎታ የለም”።

የሚላኖው ጳጳስ ቅዱስ አምብሮዝዩስ (374-397) ደግሞ ይህን በመሰለው ግልጽና የማያወላዳ አገላለጽ - “ግብርን መክፈል የሚገባን በእርግጥ ለቔሣር መሆኑ አያጠራጥም፣ ቤተክርስትያን ግን የእግዚአብሔር ነች፤ ስለሆነም ለቔሣር ልትሰጥ/ልትወሰን (በቔሣር ስር ልትሆን) አይገባትም፤ ምክንያቱም የአምላክ-ቤት የቔሣር አይደለም ... ይህን እያልኩ ያለሁት፣ ለንጉሥ ካለኝ አክብሮትና አድናቆት ጋር መሆኑ ማንም የሚቃወመው አይደለም። ለሱ (ለንጉሡ) የቤተክርስትያን ልጅ ከመሆን በላይ ሌላ የሚያገኘው ትልቅ ክብር የለውም፣ ... ስለሆነም ንጉሡ ቤተክርስትያን ውስጥ በስሯ እንጂ፣ የበላይዋ ሊሆን አይችልም”።(Against Auxentius)

በሌላ ወቅትም አብምሮዝዩስ፣ የእምነት ጕዳይ ከንጉሥ ሥልጣን ውጭና ንጉሥን የማይመለከት መሆኑን ሲያሳይ እንዲህ ይላል፦ “የእምነትን ጕዳይ በተመለከተ፣ አንድ ማንም ዓለማዊ ሰው በሌላ አንድ አቡን ላይ የበላይ ሆኖ ውሳኔ የሚሰጥበት ጉዳይ የት ነው ሰምታችሁ የምታውቁ (ተሰምቶም አይታወቅ)? እናማ እኛስ በሰዎች ተሞኝተንና ተደልለንስ፣ ለክህነት በዋነኝነት የተሰጠውን መብትና ግዴታዎች፣ አምላክ የሰጠንን ክብርና ልዕልና ለሌሎች አሳልፈን ልንሰጠውና፣ ራሳችንን ልናዋልርድ ማለት ነውን? ... ቅዱሳት መጻሕፍትንና ያለፈውን ግዜያት ተሞክሮ ስናጤን ደግሞ፣ የእምነት ጕዳይን በተመለከተ፣ -እምነትን በተመለከተ ነው እያልኩ ያለሁት፣- አቡናት/ጳጳሳት ናቸው በነገሥታት ላይ የሚፈርዱት እንጂ፣ ክርስትያን ነገሥታት በአቡናት ላይ ሆነው እንደማይወስኑ መታወቅ አለበት፣ ይህንን ሓቅስ ማነው እኮ ማነው ሊሽረው የሚችል? (መልእ. 21)።

እነርሱ በሚያቀርቡት ሙግት፣ ስለ ሁሉም ነገር መወሰንና መመሪያ መስጠት የንጉሥ ሕጋዊ መብቱ ነው፣ ለምን ቢባል ሁሉም በሱ ስር ስለሆነ፡ ይላሉ። መልሴ እንደሚከተለው ነው - ኦ ንጉሥ! በመለኮታዊ (መንፈሳዊ) ጉዳዮች ወይ ነገሮች ላይ ሥልጣን አለኝ ብለህ አታስብ፤ ይህን የመሰለ ጉጉትና ምኞትም አይኑርህ፣ ረጂም ዘመነ ሥልጣንን ከፈለግክ ራስህን ከአምላክ ስር አስገዛ። የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር፣ የቄሣርን ለቄሣር የሚል ጽሑፍ አለ። የመንግሥት አዳራሽ የሚገባው ለንጉሥ ነው፣ አብያተ ክርስትያን ደግሞ ለካህን ነው የሚገባው። ላንተ የተሰጠህ ሥልጣንና መብት፣ በመንግሥታዊ ሕንጻዎች ላይ እንጂ፣ ቅዱስና መንፈሳዊ በሆኑት ነገሮች ላይ አይደለም”፣(መል. 20)።

በዚህ በ 20ኛ መቶ ክፍለ ዘመን (ምእተ -ዓመት)፣ ከሃገራቸው የኮሚኒስት መሪዎች ጋር የተጋፈጡት የፖላንድ ሊቀጳጳሳት ካርዲናል ቪሽንጽኪ (Cardinal Wyszynski)፣ ይህን የአምብሮዝዩስ ሓሳብ የሚያንጸባርቅ ሃሳብ፣ ለእኒያ ለኮሚኒስቶች ገልጠውላቸዋል - “እናንት ቄሣሮች ወይንም የቄሣር ልጆች ለአምላክ እንጂ ለሌላ ለማንም ልትገዙ አይገባችሁም”። ቅዱስ አብሮዝዩስ ይህንን ያለውን ቃላትና የሰጠውን ትምህርት፣ ከንጉሥ ተዮዶስዩስ አንጻር በተግባር ላይ አውሎታል። ካሊኒኩም በተባለ ቦታ ላይ ስለነበረው የአይሁድ ምኵራብና፣ ሳሎኒካ ላይ በተፈጸመው የሰዎች ኅልቀትም፣ ቀዳማዊ ንጉሥ ተዮዶስዩስን በብርቱ ቃላት ኮንኖታል ወቅሶታል አውግዞታልም። እንደ አምብሮዝዩስ ሁሉ በምሥራቕ ወገንም፣ ታላቁ ባስልዮስንና፣ ዮሓንስ አፈወርቅን የመሰሉ፤ አቡናት፣ ነገሥታት ስለሆኑ(በመሆናቸው) ብቻ ይህን የቤተክርስትያንን አስተዳደር መውረስ ማለትም (Caesaro-papism) የሆነ ዝንባሌያቸውን፣ ያለ ምንም ማመንታት በቀጣይነት ተቃውመዋቸዋል።

“አምላክን ሳትቀበልና፣ እሱኑ ሳታውቅ የፍትሕን ጕዳይ በሚገባ መፈጸምና መጠበቅ ይቻላል” የሚልን አመለካከት፣ ሳይሰሮ (ወይም ቺቸሮ Cicero) የተባለ ላቲናዊ ደራሲ ያመጣውን/ያነሳሳውን ሓሳብ፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ አበርትቶ ተቃውሞታል። እንዲያውም በአንጻሩ፣ አንድ መንግሥት ፍትሓዊ ሆኖ፡ የፍትሕን ጉዳዮች በተግባር ላይ ሊያውል ከሆነ፣ የእምነት ጉዳዮችንና ሃይማኖትን የሚያከብርና የሚቀበል መሆን አለበት። አረማዊው መንግሥተ-ሃገር (state) ብቁና ቅኑ እምነትና-ሃይማኖት የሌለው ስለሆነ ፍትሕን ለማንገሥ ዓቅምና ብቃት የለውም።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጀላስዩስ ደግሞ የቤተክርስትያንና የመንግሥትን (የሃይማኖትንና የፖለቲካን) ግንኙነት የሚመራ ጥንታዊና ዘመናዊ ትምህርትን አበርክቷል። ሁለቱም ጎን ለጎን የሚሄዱ፣ አንዱ ከአንዱ ነጻ የሆነ፣ በየራሱ መንገድና ማሳ ላይ የሚሠራ ሥልጣንና ችሎታ ነው። በማለትም እንዲህ ያስቀምጡታል፦ “ዓለም የሚመራባቸውና የሚገዛበት ሁለት ነገሮች አሉ፤ መንፈሳዊ (የተቀደሰ) የጳጳሳት ሥልጣንና፣ የነገሥታት ሥልጣን ናቸው። ከነዚህ ከሁለቱ የከበደውና ክቡሩ፡ ያ የካህናትና የጳጳሳት ሥልጣን ነው፤ ምክንያቱም ነገ በአምላክ የፍርድ ዙፋን ፊት ቀርበው፣ ነገሥታትንም በተመለከተ ጕዳይ ሳይቀር የሚጠየቁ በመሆናቸው ነው።ኦ! የተፈቀርክና ሞገስ የሞላህ ልጃችን! አንተ በሥልጣንህ ከሰው ልጆች ላይ ላቅ ያልክ ብትሆንም እንኳን፣ መንፈሳዊ (መለኮታዊ) ነገሮች ላይ ሥልጣን ባላቸው ሰዎች እግር ስር፣ ራስህን እንታጎነብስ (ትሑት እንድትሆን)፣ ከእነርሱም ለድኅነትህ የሚያስፈልግህን ነገሮች እንደምትለምን ... ታውቃለህ። ... አቡኖችም ቢሆኑ አምላክ የሰጠህን ንጉሣዊ ሥልጣን አውቀውልህ፣ መንግሥታዊ ጕዳዮችንና ምድራዊ ነገሮችን በተመለከተ፡ የምታወጣቸውን ሕጎችህንና ድንጋጌዎችህን የሚታዘዙ ከሆኑ ዘንድ፣ አንተም ታድያ ለእኒያ መንፈሳዊና የተቀደሰ የአምላክ ምሥጢራትን ለማደል የተቀቡትን/የተመረጡትን አባቶች፣ ምን በመሰለ መንፈሣዊ ቅንዓት ነው መታዘዝ የሚገባህ!!”(መልእ.12)።

በቀጣዩ ክፍል “የመካከለኛው ዘመን (Middle Age) ክርስትያናዊ ሥርዓት” ምን ይመስላል የሚለውን ክፍል በከፊል እንቃኛለን! :mrgreen:

Degnet
Senior Member+
Posts: 23433
Joined: 16 Feb 2013, 11:48

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Degnet » 23 Jul 2019, 06:39

Meleket wrote:
12 Jul 2019, 02:17
ይህ ጽሑፍ Hidmona H Rights ከጻፉት መጸሐፍ የተቀነጨበ ነው። መንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነታቸው ምን እንደሚመስልም በጥንቱ ዘመን በመካከለኛው ዘመንና በዘመናዊው ዓለም ይተነትንንልናል። ይህን ታሪኽ ጠንቅቀው ያልተገነዘቡ የዘመናችን ፖለቲከኞች ጽንሰ ሃሳቡን ጠንቅቀው ካለመረዳታቸው የተነሳ የተሳሳተና የተወላገደ ትርጓሜ ሲሰጡት ስለሚታዩ እስቲ ይህን ሳይንሳዊ ጥናት “ኣልቦ ነገር ወኣልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎም፡. ውስተ ኵሉ ምድር ወፅኣ ነገሮሙ፡. ወእስከ ኣጽናፈ ዓለም በጽሓ ነቢቦሙ።” እያልን ደራሲዎቹን እያመሰገንን እንማማርበት። መልካም ንባብ። https://www.amazon.com/%E1%8D%96%E1%88% ... 1771365498

የሃይማኖትና የፖለቲካ (መንግሥት) ግንኙነት - በታሪክ አኳያ

“እነኝህ ሁለት ዓይነት ፍቅሮች ናቸው፤ የመጀመሪያይቱ መንፈሳዊት ነች፣ ሁለተኛዋ ግን መልካም አይደለችም (መጥፎ ነች)፣ የመጀመሪያይቱ ማኅበራዊ ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን ግላዊና ስስታም ነች፣ ለኔ ብቻ ባይ ናት፣ የመጀመሪያይቱ ስለ ሰማያዊቷና መንፈሳዊቷ ማኅበር ስትል የጋራ ጥቅምን ስትመለከት፣ ሁለተኛይቱ ግን በስግብግብነት ሁሉንም ማኅበራዊ ጉዳዮች ለራሷ ለግሏ ብቻ ልትወርስ ወይ ልታግበሰብስ ትፈልጋለች፣ ምክንያቱም በትዕቢት የተወጠረች ስለሆነች ነው። የመጀመሪያይቱ በአምላክ ስር የምትኖር ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን የአምላክን ህልውና ከናካቴው የምትጻረር ነች፤ የመጀሪያይቱ የተረጋጋች ስትሆን ሁለተኛይቱ ግን በጥባጭና በሁከት የተመላች ነች፤ የመጀመሪያይቱ ሰላማዊት ስትሆን፤ ሁለተኛይቱ ግን ነውጠኛ ነች፣ የመጀመሪያይቱ የተሳሳቱ ሰዎች ከሚያሞካሿት ይልቅ ሓቅን ትመርጣለች፣ ሁለተኛይቱ ግን በፈለገው አኳኃን ይምጣ በውሸት የሚያሞካሻትንና ከንቱ ውዳሴን ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ትሻለች። የመጀመሪያቱ ትሕትና የተመላችና ተወዳጅ ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን ቅናታም ነች። የመጀመሪያይቱ እሷ ለራሷ የምትሻውን ለማንኛውም አካል ትመኛለች፣ ሁለተኛይቱ ግን ማንኛውንም አካል ለማንበርከክ ትሻለች። የመጀመሪያይቱ ለጓደኛዋ ወይ ጎረቤቷ መልካም እንዲሆንለት ስትጥር፣ ሁለተኛይቱ ግን ጓደኛዋን ወይም ጎረቤቷን እንደ መገልገያነት ትጠቀምበታለች።

በሰው ልጆች መካከል ሁለት ከተሞች አሉ። እነርሱም ሊለካና ሊደረስበት በማይችለው የአምላክ በጎ ርህራሄ ስር ይገኛሉ። አምላክ ማንኛውንም ፍጡር የሚያስተዳድር ነው። የመጀመሪያዋ ከተማ የቅኑዎችና የጻድቃኖች ስትሆን፣ ሁለተኛይቱ ግን በመንፈስ የደነዘዙት ከተማ ነች። እነዚህ ሁለት ከተሞች ለግዜው የተደበላለቁ ቢመስሉም፣ በመጨረሻው የፍርድ ዘመን ግን ይለያያሉ ይህም ማለት መለያየታቸው አይቀሬ ነው . . .” (ቅዱስ ኣጎስጢኖስ -De Genesi ad Litteram XI, XV. 20; Augustine’s Quest of Wisdom 249)

ይህ ትልቅ መምህር፣ የኅብረተሰብን አውታሮች(እርከኖች) ከሁለት መድቦታል፣ ክርስትናዊና አረማዊም ብሎታል። ሥልጡን የነበረው የሮማዊያን ግዛት ተሸንፎ፣ ሮማም እ.ኤ.አ.በ410 ዓ.ም. አላሪክ በተባሉ የሰሜን ወራሪዎች እንደተያዘች፣ አጎስጢኖስ “የእግዚአብሔር ሃገር” ወይም “ሃገረ እግዚኣብሔር” (The City of God) የተሰኘች መጸሓፉን ደረሰ። በዚችው መጸሓፉም በታሪክና በታሪክ ጉዞ ላይ ያለውን አመለካከት አነጥሮና ኣብራርቶ ይገልጻል። መንፈሳዊቷ “የእግዚአብሔር ሃገር ወይ ከተማ” እንዴት እንደተቆረቆረችና እንዳደገች (ምንጯንና አስተዳደጓን ወይም አበለጻጸጓን)፣ እንዲሁም ዓለማዊዋና (ዓላዊት/ወዳቂዋ/ ተሳሳቿ) “የሠይጣን ከተማ ወይ ሃገር” በሚለዋወጠውና በሚገለባበጠው ሥልጣኔ መካከል እንዴት አድርጋ እንደምትበቅልና እንደምትታይ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይዘረዝረዋል። ሮማውያን የነበራቸውን ባሕሪያዊና መንፈሳዊ ኃይል እንዳጠፉ፣ ተንገዳግደውና ተሰነካክለው ወደቁ፣ የሮማውያን ሥልጣኔ ቢደመሰስም እንኳን፣ ክርስትያናዊቱ ከተማ ግን በሕይወት እንደምትኖርና እንደምትቀጥል የአጎስጢኖስ የማይናወጥ ግንዛቤ ነበር።

ስለሆነም የሮማ ግዛትና ሥልጣኔ እንዳለፈ፣ አዲስ የመካከለኛው ዘመን ክርስትያናዊ ግዛት ተከሰተ፣ ተስፋፋም፣ ማእከሉንም በተለይ በአውሮፓ እምብርት (በጀርመን) አካባቢ አደረገ። ያም ሆኖ የአጎስጢኖስን ጹሁፎች ያነበቡ ሰዎች ትኩረታቸው ሁሉ፣ “አጎስጢኖስ ያለው ሁሉ መች ይሆን የሚፈጸም??” የሚል ይመስል ነበር። ይህም ሌላ ውጥረትን ፈጠረ፤ ዓለማዊቷን ከተማ፣ በሮማውያን መንግሥት ከወከልናት፣ አዲስቷን ክርስትያናዊ መንግሥትንስ ታድያ በምንድን ነው የምንወክላት/የምንገልጻት (እንዴት ልናያት ነው)? ይህም ስለሆነ አንድ አዲስ አይነት አመለካከት ተከሰተ፣ ይሀውም -
 እንዲያው በደፈናው መንግሥተ-ሃገርን (the State) ከዓለማዊቷ ከተማ ጋር ማመሳሰል እንደማይገባ፣
 ስለሆነም መንግሥትና ቤተክርስትያን፣ አንዲት የ“ አምላክን ከተማ” ማቆም/መመስረት አለባቸው የሚል ሓሳብ ገነነ፡ አንሰራፋም።
 አንድ “ክርስትያናዊ ኅብረት” (Christian Commonwealth) ሆነውም መንፈሳዊና ምድራዊ፣ የቤተክርስትያንና የዓለም (ፖለቲካዊ አኳኋን) የሚወሃሃድበትና፣ ግን ደግሞ ሁለቱ የተለያየ ችሎታና ጥበብ/አመለካከት መሆኑም ታወቀ።

ከዚህ አስተሳሰብም የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ኅብረትና አንድነት፣ ሁለቱም ተፈጠረ። ቤተክርስትያንና መንግሥት፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ ጭራሹኑ ተደበላለቀ ተዳቀለም። አሁን አሁን በሁሉም በበለጸጉ ሃገሮች ያለው - “ የመንግሥትና የቤተክርስትያን መለያየት” (Separation of Church & State) ከሚባለው ዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር የሚጋጭ ሓሳብና አመለካከት ተስፋፋ ገነነም። ሆኖም ግን ይህን ፍጹም የሆነ ልዩነት የሚል አመለካከትን ባጠናከርክ ቁጥር፣ መንግሥትና ቤተክርስትያን ፍጹም ከተለያዩ፣ አስቀድሞ ወደተጠቀሰው የአጎስጢኖስ ሃሳብ ወይ አመለካከት እንደ መመለስ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ቤተክርስትያን ከዕለታዊና የወትሮ የኅብረተሰብ ህላዌ አኳያ፣ ልትገለል ወይ ልትነጠል ነው ማለት ነው፤ የመጭው ዓለምና መንፈሳዊ ወገን ብቻ ተደርጋ ትታሰብ የነበረቸው፣ በኅብረተሰብ ዕለታዊ ሕይወት ውስጥ ልትፈጽመው የሚገባት ሚናና ሊኖራት የሚገባ ተጽዕኖና ልትሰጠውና ልታበረክተው የሚገባት ብርሃንን እንድታበረክት ዕድል አይኖራትም ማለት ነው። በሌላ አኳያ ደግሞ ይህ አመለካከት ዓለማዊውን መንግሥት ወይም ፓለቲካዊውን ወገን ብቻውን ራቁቱን የሚያስቀር፣ ማንኛውም ከመንፈሳዊ ወገን ሊያገኘው ይችል ከነበረ ብርሃንና ድጋፍን እንዳያገኝ የሚያስደርግ፣ ስለሆነም ለብቻው ተገልሎ፣ ወደ ስስታምነትና አረመኒያውነት፣ አጎስጢኖስም ሳይቀር ወደገለጸው ዓለማዊነት ሁኔታ አያመራምን? የሚል ጥያቄን አነሳሳ።

በእምነት የተሞሉ ምሁራንና ተሞክሮ ያላቸው ሰዎችም ሊያስሱት የሚገባቸው፣ ይህን ቀላል መልስ የማይገኝለትን ጥያቄ ሊያስቡበት እንደሚገባ ነው። ስለሆነም ይህን ልንረዳ እንችል ዘንድ እንዲያግዘን፣ ወደ ኋላ ተመልሰን የታሪክን ጉዞ መፈተሽ ይገባናል። የቤተክርስትያንና የመንግሥት ግንኙነቶች ባለፉት ዘመናትና፣ አሁን ደርሶበት ያለ ሁኔታን ማየት ያስፈልገናል። ምክንያቱም ታሪክ የሕይወት መምህር ነችና።

በቀጣዩ ክፍል በዘመነ አረመኒያዉያን ይህ የመንግሥትና የሃይማኖት ግንኙነት ምን ይመስል እንደሆነ እንቃኛለን። :mrgreen:
Entay waga alewo anta bruk hawe seb ne teuy neger gedi zeybelu koynu.

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 29 Jul 2019, 05:20

የመካከለኛው ዘመን (Middle Age) ክርስትያናዊ ሥርዓት

በመካከለኛው ዘመን እያደገና እየጎለበተ የሄደው አካሄድ ደግሞ ለየት ያለ ሥእልን ይሰጠናል። አሁንም እንደ አብነት የምንጠቅሰው፡ በአውሮፓዊ የታሪክ መድረኽ የተከሰተውን ፍጻሜ ነው። ክህነትና ንግሥነት ላቅ ባለ ደረጃ፣ በጵጵስናና በመንግሥት መልክ የተቆራኙበት ዘመን ነው። ተሳስረውና ተቆራኝተው ግዛታቸውን ያደላደሉበት ዘመን ነው የነበረው። በተለይም የአውሮጳ የመካከለኛው ዘመን ታሪኽ ሲቃኝ፣ ዋንኛ ተልእኾውና (መደቡ) ሥነሓሳቡን፣ የካቶሊኽ ቤተክርስትያን ተጽዕኖና ሚና የበረከተበትና የገነነበት ግዜ መሆኑ ነው የሚታወቀው።

ክርስትና፡ ከቆየው የሮማውያን መንግሥትና ግዛት ጋር ሲነጻጸር፣ በስፋትም ሆነ በዕድሜ እርዝማኔ እጅግ አጭር ወይም ትንሽ ነው። በሜድትራንያን አካባቢ በሁሉም አቅጣጫዎች ያሉ ሃገሮች በክርስትና ስር ቢገቡም፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ሚናው ቢስፋፋም እንኳን፣ የሮማውያን ግዛት፣ ልማድና ሥርዓት የሚንጸባረቅበት ሁኔታ እጅግ የተስፋፋው ግን፣ ወደ ማእከላዊና ሰሜናዊ አውሮጳ በኩል ሲሆን፣ ከሮማዊ ግዛትና ከክርስትና አንጻር ሲታይ ደግሞ እጅግ ጠባብ ሆኖ ተገኘ። በመሆኑም የሜዲተራንያንን አካባቢ እንደለወጠው ሁሉ፣ አብዛኛውን የአውሮጳ ክፍል (የሮማ ግዛት)ንም ጭምር መለወጥ ነበረበት፣ ነገር ግን ይህ ቀላል ሆኖ አልተገኘም። ያ የለውጡ ሂደትም ቀስ በቀስ ተካየደ።

የጀርመን ዝርያዎችና አካባቢያቸው (Teutons) ወደ ክርስትና እንደገቡ አዲስ ክስተት ተፈጠረ ሊባል ይችላል። እነኝህ ብዙውን ግዜ እንደ ጀርመን የሚታወቁ “ተውቶን” ወደ ክርስትና እንደገቡ፣ ሊያወሃህዳቸው የሚችልና እምነትንና ሥነሕንጻን በተመለከተ (Culture) የኛ ነው የሚሉት የኅብረተሰብ ሥርዓትና ወግ አልነበራቸውም። እነሱ ክርስትናን የተቀበሉበት ወቅት ደግሞ፣ የሮማውያን ባህልና ሕንጸት ወደ መዳከም አቅጣጫ ይጓዝ በነበረበት ግዜ ነበር። የሮማውያኑን ባህልና ሕንጸት መልካም መልካሙንና የተሻለውን አበርክቶ አንኳር አንኳሩን ያቀበች አካል ብትኖር ቤተክርስትያን ነች። ቤተክርስትያን ውስጥ የዳበረው፣ ሕጋዊ አካሄድና አደረጃጀት ለምሳሌ ከሮማዊ ልምድ የተወሰደ ነው። ስለሆነም የግሪኽንና የሮማውያኑን ሥልጣኔና ዕድገት ዋናዋናውን በደመቀ ሁኔታና በጥልቀት ወደነዚህ ተውቶኖች ያመጣው ክርስትና ነው። ስለሆነም በዚ በአዲሱ ክርስትናና፣ ክርስትና ከግሪኽና ከሮማውያን ሥልጣኔ ጨምቆና መርጦ ያቀበውን ሥልጣኔና አስተሳሰቦች ሁሉ፣ እነኝህ የሰሜንና የመካከለኛው አውሮጳ ሕዝቦችን በአዲስ መልኩ አደራጃቸው፣ ወደላቀ ግንዛቤም ወሰዳችው አወሃሃዳቸውም፣ የኛ ነው የሚሉት ስነ ሕንጸት (Culture) ወይም ባህል ያላቸው ሆኖም ተሰማቸው። በመሆኑም ይህንን የመሰለውን እምነትንና የስነሕንጸትን ሃብት ያወረሰቻቸውን ቤተክርስትያንን ደግሞ፡ ልክ እንደ መንፈሳዊት እናታቸው ማሰባቸውም ባህርያዊ ክስተት ሆነ። በምድራዊ ጉዟቸው ያካበቱት ሁሉ እርምጃቸውና ድላቸውም በቤተክርስትያን አማካኝነት ያገኙት ነበር፡ ይህም- ትምህርት፣ ሕግ፣ ስነሕንጸት፣ ግዙፍ ማተርያላዌ ሥልጣኔና ቴክኒካዊ ሙያንም ሳይቀር የሚያጠቃልል ነበር፣ ይህም ማለት አቡናት ስብከተወንጌልን ለማከናወንና ለማጎልበት ሲሉ፣ መገናኛ መንገዶችንና መሸጋገሪያ ድልድዮችን ሲያሳንጹ፣ አበምኔቶች (የገዳም መሪዎች) ጭምር እርሻን ለማጎልበት የተለያዩ መመሪያዎችንና ድርጊቶችን ሲያከናውኑ ተስተውለዋል።

ስለሆነም እነዚህ አካላት ውስጥ የቤተክርስትያን ስራ የተሳካ ቢሆንም፣ እነዚህ ሕዝቦች ግን ባለፈው ግዜ፡ የኛ ነው የሚሉት ልዩ ሥልጣኔና ዕድገት፣ ልዩ እምነትና ስነሕንጸትን ያላዳበሩና ያልተቆራኙ ስለነበሩ፣ ለቤተክርስትያን ሥራ መሳካት፡ እንደ አንድ ሳይታረስ ድንግል ሆኖ የቆየ መሬት ሆነው ተገኙ። ልክ እንደ ግሪኾችና ሮማውያን ያለ፡ ጥልቕና ረቂቕ ባህል እምነትና ስነሕንጸት አልነበራችውም። ስለሆነም ቤተክርስትያን በዕለታዊ ሕይወታቸው ውስጥ ዋና ምሰሶ እንድትሆን፣ ከማንኛውም ግዜያዊና መንፈሳዊ፣ ምድራዊና መንፈሳዊ ሕይወታቸው ውስጥም ተሰሚ ድምጽ ሊኖራት መቻሉ ባሕርያዊ ጕዳይ ሆነ። ይህን የመሰለው የቤተክርስትያን ልዕልና፣ የበላይነትና ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም ደግሞ፣ ማእከላዊውን ዘመን እንደ የክርስትያናዊ ሥርዓት (Christendom) ሲያስቆጥረው ይገኛል። በመካከለኛው ዘመን አውሮጳ፣ ለክህነት ለጵጵስናና ለመንፈሳዊ ወገን የሚሰጥ አክብሮት፣ የማንኛውም ማኅበራዊ ድርጊት መሠረት ነበር ልንልም እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ይህን ከመሰለው አክብሮትና አድናቆት (ከክህነትና ጳጳስነት አኳያ) ካልሆነ በስተቀር፣ ያ ሁሉ በቤተክርስትያንና በቤተክርስትያን ሰዎች አማካኝነት የተካሄደውን ተልእኾና ሚና፣ ሌላ ይህ ነው የሚባል ብቁ መግለጫ ሊገኝለት አይችልም።

ክርስትያናዊ ወንድማማችነት (ትብብር) መተሳሰብ፣ ለዓለም- አቀፋዊና አህጉራዊ ትግግዝና መልካም ግንኙነት ኃያልና ጽኑ መሠረቱና ዋንኛ ሓሳቡ ነው። ያም ሆኖ መተሳሰብ ወይ ወንድማማችነት ሲባል፣ የጋራ አባትነትም አለ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ወንድማማቾች ነን የሚሉ ሰዎች ካሉ፣ የጋራ አባት፣ ወይም የጋራ እናት አሉን ማለታቸው ነው። ያ በዓይን የማይታየው አባት፡ እግዚአብሔር አምላኽ ሲሆን፣ እናታቸው የምትሆናቸውን ቤተክርስትያንን የሚመሩት ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ደግሞ፣ በዚህ ምድር ላይ ልክ እንደ አባታቸው አድርገው ሊያስቧቸው የግድ ይላል/ሆነ። እኒህ አባትም ሙሉ የአባትነት ሥልጣን እንዳላቸው በእነኝህ ልጆቻቸው ዘንድ የታወቀ ሆነ።

በቀጣይ ክፍል “ፈራጅና(ዳኛና) መሪ” የሚለው ንኡስ ክፍል ይቀጥላል።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 13 Aug 2019, 10:44

ፈራጅና(ዳኛና) መሪ፦

እኒህ የተባሉት አባት ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ ካላቸው ምኞት የተነሳ፣ የእልህና የጥላቻ ስሜቶች በልጆቻቸው መካከል ተነስቶ ሲጣሉ፣ ይህን ቅራኔያቸውን እልባት ላይ በማድረስ የሚፈርዱና እርቅን የሚያመጡ፣ እኒህ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆኑ። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም፣ ምድራዊ ህልውናቸውንና ድሕነታቸውን በተመለከተም ምክራቸውንና አባታዊ ቡራኬያቸውን ሊሰጧቸው፣ ከማያምኑት ጠላቶቻቸው ጋርም እንዴት አድርገው እርስበራሳቸው እንደሚጠባበቁ መመሪያዎችን ሲለግሷቸው ተስተዋሉ። ሓቅን ያውቁ ዘንድ ስለሚሹም ለልጆቻቸው እኒህ አባት ትምህርትን አስፋፉላቸው፣ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎችንም ቀየሱላቸው፣ ስሕተት ሰርጎ እንዳይገባም ጠበቃ ሆኗቸው፣ በተለይም እምነትን በተመለከተ ጕዳይ ስሕተት በተከሰተ ቅጽበት እኒህ አባት እየተከታተሉ ይህንን ስሕተት አረሙላቸው ነቀሉላቸውም። በዚህ ምድርም ከሳቸው በላይ ሊታይና ተሰሚነት ሊኖረው የሚችል አካል እንደሌለ፣ ውሳኔያቸውና ትምህርታቸው ደግሞ እሰማይ ላይ ከሚደረገው ጋር ሳይቀር፣ ግንኙነት ያለው አድርገው ክርስትያን የአባታቸው ልዑል ሥልጣን መሆኑን እንደሚረዱ ታመነበት። በዚህ ምድር ላይ ከእርሳቸው በላይ ሥልጣን ኑሮስ፣ እርሳቸውን ከሥልጣን ሊያወርዳቸው የሚችል ማንም የለም፣ ስለሆነም እርሳቸው በዚህ ምድር ውስጥ በማንኛውም ሥልጣን ስር አይደሉም።

በ 501 እ.ኤ.አ. ፓልም ውስጥ የተደረገው ሲኖዶስ ባሳለፈው ውሳኔ፣ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ላይ ውሳኔ ወይም ፍርድ የሚሰጥ አካል ኢሕጋዊ ብቻ ሳይሆን የማይቻል ነው በማለት ወሰነ። አጠቃላይ ክርስትያናዊ አመለካከትና ስሜትም የማይቀበለውና የማይዋጥለት ጕዳይ ነው። ስለሆነም እኒህ የጋራ አባት በኅብረተሰብ ውስጥ ሕግና ፍትሕን፣ በንግድና ልውውጥ ሂደት ውስጥም ርትዕ ይኖር ዘንድ መምሪያዎችን ማውጣታቸው ተቀባይነት አለው። በማንኛውም የሞራላዊ ጕዳዮች ላይም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመጨረሻውን ብያኔና ቃል የሚሰጡ፣ በየአቅጣጫውም ተራ መእመናንን ከማንኛውም ፖለቲካዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጭቈናና ተጽዕኖ የሚከላከሉላቸውና የሚታደጓቸው ሆኑ። አንዳንድ ግዜ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ውሳኔዎችና መመሪያዎችን የሚቃወሙ አካላት ቢኖሩም፣ በአጠቃላይ ሲታይ መሠረታዊ ጕዳዮች ላይ ግን፣ ማንን እንደምትጠይቅና ማንን እንደምታማክር፡ ማንን ነው የምንጠይቅ? ... በሚባልበት ወቅት፣ ከእኒህ የክርስቶስ ወኪል በስተቀር፣ ከእኒህ የጴጥሮስ ምትክ ሌላ እንዳልነበራቸው ሁሉም የሚስማሙበት ነጥብ ነበር።

ሞራልን በተመለከተ ጕዳዮች ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የበላይ ዋና መምህርና ወሳኝ አካል መሆናቸው ካቶሊካዊያን የሚቀበሉት ሲሆን፣ በመካከለኛው ዘመን የነበረው አከራካሪ ጥያቄ ግን፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከምድራዊ አስተዳደርና ከዓለማዊ ጕዳያት አኳያ የሚኖራቸው ሥልጣንና ተጽዕኖ ወይ ሚናን በተመለከተ ነው። አንዳንዶች የሥነመለኮት መምህራን፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዚህ ባላቸው መንፈሳዊ ስልጣን አማካኝነት፣ በምድራዊ ነገሮችና ግዚያዊ ጕዳዮች ላይም ቀጥታዊ የሆነ ሕጋዊ ሥልጣን አላቸው የሚሉ ነበሩ፤ ይህ ዓይነት ሓሳብ ግን በአሁኑ ወቅት ሰሚ የማያገኝ አመለካከት ነው። ሆኖም ግን ቅዱስ አብሮዝዩስ እንደሚያስተምረው፣ አቡናት ወይ ጳጳሳት ለሁሉም የክርስትና አማንያን፣ ማዕረጋቸው የፈለገው ዓይነት ይሁን፣ ለነገሥታትም ጭምር፣ ሞራላዊ መመሪያ ሊሰጡ፣ ሊያስተምሩና ሊቆጣጠሩ ሥልጣን አላቸው።

በቀጣዩ ክፍል “ቀጥታዊ ያልሆነ ሥልጣን” (Indirect Power) በሚል ንዑስ ርእስ ሥር የሰፈሩ ሓቆችን እንጋራለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 29 Aug 2019, 04:00

በዚሁ መጸሐፍ “የመካከለኛው ዘመን (Middle Age) ክርስትያናዊ ሥርዓት” በሚል ርእስ ስር የሚከተለውን ንኡስ ርእስ ይዘት እንመልከት።

“ቀጥታዊ ያልሆነ ሥልጣን” (Indirect Power)፣

እኒያ ማንኛውንም ነገር ለመፈጸም ቃል የሚገቡና የሚምሉ መእመናን፣ ከዚያ ከገቡት ቃል ወይ ማህላ ነጻ የሚያደርጋቸው፣ ወይም እንዲለውጡ የሚያስችላቸው የክህነት ሥልጣን ነው። በዚህ ምክንያትም በአንዳንድ የምድራዊ ጕዳዮች ውስጥም፣ ክህነት/ጵጵስና በምድራዊ መኳንንትና ባለሥልጣኖች ላይ “ቀጥታዊ ያልሆነ ሥልጣን” እንዳላቸው ተቀባይነት ያለው አመለካከት ሆነ። ግብርን በተመለከተ ጕዳይም፣ በየአካባቢው በተደረሰበት ስምምነት በጸደቀ ሕግ መሠረት፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን በምድራዊ ነገሮች ላይ ሳይቀር ዋንኛውና ወሳኙ ፈረጅ አካል አድርገው ተቀበሏቸው።

ለምሳሌ በስጳኛ/ስጴን (Spain)፣ ቶለዶ ላይ በተካሄደው የቤተክርስትያን ሰዎችና፣ የንግሥናው አማካሪዎች የተሳተፉበት 6ተኛ ጉባኤ (በ 636 እ.ኤ.አ.) መሠረት፣ “ማህላውን እስካልፈጸመ ድረስ፣ ማንኛውም ንጉሥ ወደ ዙፋን እንዳይወጣ፣ ሌላው ቅድመ ሁኔታ ደግሞ፣ በግዛቱ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት መናፍቕነት እንዲንቀሳቀስ እንዳይፈቅድ” የሚል ይገኝበታል።

መላጣው ሻርል (Charles the Bald) የተሰኘው የፈረንሣይ ንጉሥ ደግሞ (843-877) ራሱ በገዛ ራሱ የተቀበለው መመሪያ እንደሚከተለው ይላል - “በእነርሱ ሥልጣንና ተልእኮ መሠረት ንጉሥ ሆኘ የተቀባሁ፣ በነዚህ አቡናት ግምገማና ፍርድ ካልሆነ በስተቀር፣ በሌላ በማንኛውም ይሁን አካል ከዚህ ልዑል የንጉሥነት ዙፋን ልወርድ አልችልም”።

ኤድዋርድ “ታማኙ/ተኣማኒ”(Edward the Confessor) የተባለ የእንግሊዝ ሃገር ንጉሥ (1042-1066) ካወጣቸው ሕጎች መካከል፣ 14ኛው አንቀጽ እንዲህ ይላል- “..ንጉሥ ቤተክርስትያንን ሊያከብራት ይገባዋል፣ ከሚያቆስሏት ሊከላከልላት፣ መጥፎ ተግባር የሚያደርጉትን ሊያባርርላት፣ አረ እንዲያውም ከነ ጭራሹ ሊደመስስላት ይገባዋል። እንዲህ ካላደረገ ንጉሥ ለሚለው ማዕረጉ ብቁ አይደለም ማለት ነው ...”።

የ 13ኛው መቶ ክፍለዘመን (ምእተ ዓመት) የጀርመን ሕግ (የሽዋብ ሕግ በመባል የሚታወቀው) ሕግ ደግሞ፣ “ንጉሥ የመምረጥ መብት ለጀርመናውያን የተሰጠ ነው፣ ...በመራጮቹ ፍላጎት መሠረት ንጉሡ ተቀብቶ ዘውዱንም ደፍቶ በኣኸን ዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ፣ የንግሥነት ሥልጣንና ስሙን ይሰጣል። ያም ሆኖ በመላው የግዝኣተ-መንግሥቱን (empire) ሙሉ ሥልጣን የሚጨብጠው ግን፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲቀቡት ብቻ ነው፣...ንጉሡን ሊያወግዙና ሊያግዱት የሚችሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው...”።

በእንዲ ዓይነቱ ምድራዊና ግዜያዊ ጕዳይ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሕዝብ ወኪል ሆነው መስራታቸው፣ በ1871 በነበሩት ፕዮስ 9ኛ ተቀባይነትን ያገኘ ጕዳይ ሆነ፣-“...ኃይል ባለው የጋራ ሕግ መሠረት፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን እንደ የክርስትያን የበላይ መሪና ፈራጅ አድርገው በሚቀበሉ ወገናት ስምምነት፣..ነገሥታትን ከሥልጣናቸው ወይም ከዙፋናቸው ማውረድ፣ በምድራዊ ነገሮች መሪዎችና መንግሥቶች ፍርድ ውሳኔ መስጠት፣ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣን ነው። ነገር ግን አሁን ያለው ሁኔታና ህልውና ጭራሹኑ የተለየና የተለወጠ ስለሆነ፣ በአሁኑ ግዜ እንደዚያ ማድረግ ማለት፣ የባሰውኑ ክፋት አምጥቶ እነዚህን ልዩልዩ ነገሮችንና ጊዜያትን ግርግርና ብጥብጥ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው”።

“የተለያየ አተረጓጎም” የሚለውን ክፍል በቀጣይ እንኮመኩማለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 09 Sep 2019, 04:59

የተለያየ አተረጓጎም

እ.ኤ.አ. በ800 ዓ.ም. የልደት በዓል ወቅት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልዮን 3ተኛ በንጉሥ ሻርልማኝ (Charles the Great) ራስ ላይ ዘውድ የደፉበት ዕለት ነበር። ይህ ተግባርም የተለያየ ትርጉም ተሰጠው። ይህ የተለያየ አተረጓጎምና ግንዛቤም ቀጥሎ በነገሥታትና በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ጭቅጭቅን ፈጠረ። መሠረተ ሓሳቡ ግን ልክ በላተራን ቤተክርስትያን ሥእል(ሞዛይክ) ላይ እንደሰፈረው ነው። በሥእሉ ላይ እንደሚታየው፣ ክርስቶስ ለጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማይን ቁልፍ ሲያስረክበው ይታያል። ከዚህም ጎን ለጎን በትረ-መንግሥትን ለንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲያስረክበው ይታያል። ይህም እኒህ ሁለቱ የቤተክርስትያንና፣ የምድራዊ መንግሥትን ሥልጣን መጨበጣቸውን ያመለክታል። ቆይቶም ቅዱስ ልዮን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትም እንደ የጴጥሮስ ምትክ መጠን፣ ንጉሥ ሻርልማኝ ደግሞ የቆስጢንጢኖስ ምትክ ሆነው፣ እነዚህን የተጠቀሱትን ምልክቶች እንደተቀበሉ የሚያሳይ ነው።

እነኝህ ሁለቱ ሥልጣኖች ወይ ችሎታዎች በመካከለኛው ዘመን፣ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 22፡38 እንደተጠቀሰው፣ የሓዋርያት ሁለት ሰይፎች ተመስለው እናገኛቸዋለን። አልኩዊንን የመሰሉ የንጉሥ ሻርልማኝ (768-814) አማካሪዎች ደግሞ፣ ንጉሡ ሁለቱንም ሥልጣኖች እንደጨበጠ ወይ እጁ ውስጥ እንዳስገባ፣ ሁለቱንም ሠይፎች እንደያዘ፣ የመንፈሳዊዉን ወገን ግን ንጉሡ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደሰጣቸው አድርገው ተገነዘቡት። የቅዱስ ጀላስዩስን አስተሳሰብ የሚጋራና የሚከተል ቅዱስ በርናርዶስ ዘክሌርቮ (የ12ተኛው መቶ ክፍለዘመን)ግን፣ ጳጳስና ንጉሥ የየራሳቸው ሰይፍ ያላቸው፣ አንዱ ከሌላኛው ነጻ ሆኖ፣ ግን ደግሞ በፍቅርና በስምምነት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ይገልጻል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቦኒፋቺዩስ 8ተኛ (1294-1303) ደግሞ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሁለቱንም ሰይፎች እንደያዘና፣ ምድርን የሚመለከተውን ጕዳይ ደግሞ ለዓለማዊው ገዢ፣ ለንጉሥ ሰይፉን እንደሰጠ አድርጎ በማሰብ፣ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኃይልና ሚና እጅግ የላቀ መሆኑ ይታሰብበት የነበረ ግዜን ያመለክታል። ከዚህ በላይ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ሥልጣንና ኃይልን የሚገልጽ፣ ይህም ማለት በመካከለኛው ዘመን ከዚህ በላይ የዚህ ሥልጣን ምልክቶች ከአንዱ ወገን ወደ ሌላኛው የተጓዘበት ግዜ አልነበረም ማለት ይቻላል።

እንደ ንጉሥ ሻርልማኝ ያለ፣ በምዕራብ (አውሮጳ) አካባቢ ንጉሣዊ ሥልጣኑን በደንብ አድርጎ ያደላደለና ያጸና ሲገኝ/ሲመጣ፣ ቀስ በቀስ ቄሣረ-ጳጳስ (Caesaro-papism) የሚል አስተሳሰብና አመለካከት እየሰፋ ሄደ። ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምክርና ሃሳብ የሚሰጥ፣ ለአቡናትና ካህናት መመሪያ የሚያወጣ፣ ለመነኮሳንና ደናግል ሕጎችን የሚደነግግ፣ ዓለማውያን በዓላትን እንዲያከብሩ የሚያስገድድ፣ የቤተክርስትያንን ዜማና ማኅሌት የሚቆጣጠር ...ሆኖም ተገኘ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉና ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጊቶች ከሻርልማኝ ሞት በኋላ የሚከታተለው አልተገኘም። ስለሆነም ይህ ድርጊት በሻርልማኝ የግል ሁኔታና አማካሪዎች የተመረኮዘ ክስተት ነው የነበረው። ቀጥሎ የነገሠው ንጉሥ ሉዊስ መንፈሳዊውም (814-840) ለክህነትና ጵጵስና ታላቅ አክብሮቱን ሲሰጥ፣ ከካህን እግር ስር ተደፍቶ ንስሓ የፈጸመበት ግዜ እንደነበረውም ይታወቃል። በዘመነ ሉዊስና ቀጥለው በነበሩት ተኪዎቹ፣ ያ ኀያል የነበረው የሻርልማኝ መንግሥት (Carolingian) ተዳክሞና ተበታትኖ የፊውዳሊዝም ዘመን እንደደረሰበት እናውቃለን።

በቀጣዩ ክፍል “ፊውዳሊዝም” በሚል ንኡስ ርእስ የተካተተውን ታሪክ እንመለከታለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 24 Sep 2019, 03:27

ፊውዳሊዝም፦ ፊውዳሊዝም ሲባል፣ የተወሰነ የኔ የሚለው አደረጃጀትና ዓላማ ስር የቆመ፣ እንደ አንድ መደበኛ ሥርዓት ተደርጎ ሊታይ አይችልም(አይበቃም)። ምክንያቱም ሥርዓትና ሕግ እንዲሁም መሪ የሌለው፣ ሁሉም እንደየ ኃይሉና ሥልጣኑ በማን አለብኝነት የሚራመድበት - የሥልጣን የለሽ ወይም የ“አናርኪ” (anarchy) ግዜ ነበር ሊባል ይችላል። ስለሆነም በትልልቆቹ የማኅበራዊ ግንኙነቶች፣ በወጉ ሕዝባዊና መንግሥታዊ ሥልጣን እንዲኖር ከመጣር ይልቅ፣ በግላዊ ውሎችና፣ በአድርባይነት በሚፈበረክ አካሄድ ተተክቶ እናገኘዋለን። ሥልጣንን መያዝ ከመሬት ይዞታ ጋር ተሳሰረ፣ መሬት የማንኛውም ዓይነት ሥልጣንና ዓላማ ምትክ ሆነ። ፖለቲካዊ ዋስትና የሚኖርህ፣ መሬት ካለህ፣ ወይ ደግሞ ከባለ መሬት ጋር ስትተሳሰር ሆነ። ይህም በበኩሉ አንዳች ዓይነት ጭቆናን ፈጠረ፣ ምክንያቱም አንድ ሰው፡ እሱው ገዢህ እሱው የሚያሰራህ፣ እሱው ራሱ ባለመሬት (እየከፈልከው የምታርስለት)፣ እሱው ራሱ ፈራጅህ ... የሚሆንበት ሁኔታ ተፈጠረ።

እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ያ ምስኪን ጭቍኑ ሰው ወዴት ይጠጋል? ምንስ ያደርጋል? ምንስ ይበጀዋል? ሁሉም ነገር በአንድ ወይም በጥቂቶች ብቻ ተይዟል። ስለሆነም ስሞታ ሊቀርብባት የሚችል ወይም አንዳች ነገር ልታደርግ የምትችል ቤተክርስትያን ብቻ ሆና ተገኘች። ያም ሆኖ ራሷ ቤተክርስትያንም ሳትቀር በዚህ የፊውዳል አካሄድ ተጽዕኖ ስርም የነበረችበት ወቅት ነበር። ምክንያቱም አቡኖችና አበምኔቶች ከዓመጸኞችና ከኃያል ሽፍቶች ዋስትናን ያገኙ ዘንድ በማለት፣ ራሳቸውን በሌሎች ስርና በሌሎች ላይ አደረጉ፣ የቤተክርስትያን መሬትም ለዚህ ተግባር ዋለ። አንዳንድ ግዜ ከሌሎች ለሚያገኙት ጥበቃና ዋስትና፣ ምላሹ ወይ ለውጡ በሚያሳርጉት ጸሎትና መንፈሳዊ አገልግሎት ሲካካስ አብዛኛውን ግዜ ግን፣ ጥበቃ ለሚያደርግላቸው መሪና ለሠራዊቱ ዕጥቅና ስንቅ ማዘጋጀት ላይ ተሳተፉ።

ይህን የመሰለው፣ መሣፍንቶች አቡኖች የሚሆኑበት፣ ወይም አቡኖች መሣፍንት የሚሆኑበት አካሄድ፣ ሙስናን አስከተለ ሊባል ይቻላል፣ ይህን ቦታ ወይ ስፍራ ወይ ሥልጣን ለመያዝም ኃያል ፉክክር፣ ህልክና ውድድር ተከሠተ። ይህ ነው እንግዲያውኑስ “ዘመነ-ጸልማት” ወይም “የጨለማው ዘመን” (Dark Ages) ለሚባለው ዘመን ጥርጊያ መንገድ የከፈተው። ይህ ተግባር መጥፎ የሆነ አካሄድን በማምጣቱ፣ አቡኖችን ካህናቶችንና አበምኔቶችን ተራ ዓለማውያኑ እንዲሾሟቸውና እንዲሽሯቸው አስደረገ። በዚህም ምክንያት፣ በተለይም ባልተማረው ተራ ሕዝብ ኅሊናና አእምሮ ውስጥ፣ መንፈሣዊ ሥልጣን ምንጩ ከወዴት እንደሆነ አደናጋሪ ሆነ። ምክንያቱም አንድ ባለመሬት፣ አንድ አቡንን ወይም አበምኔትን ስልጣን የመጨበጥ ምልክት የሆነውን ዘውድ ወይም በትረ-ኖላዊ ሊያስይዘው፣ ወይም አንድ ካሕንን ፍትሓት ማድረግንና ቤተክርስትያን ውስጥ መገኘትን ወዘተ የቤተክርስትያን ንብረት በዓለማውያን ሰዎች እንዲመዘበርና እንዲወሰድ፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ ሥልጣን ሰጭ፣ ሿሚና ሻሪ ሆነው ተገኙ። ስለሆነም አንዳንዴ ለማይመለከታቸው ሰዎች መንፈሳዊ ኃላፊነት ሲሰጡ፣ አንዳንድ ግዜ ደግሞ ለሚገባቸውና ለሚመለከታቸው ሰዎች ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ሲያርቋቸውና ሲያገሏቸው ተስተዋሉ

ከዚህ ሁሉ መጥፎ ረገረግ ጭቃ ለመውጣት በቤተክርስትያን ውስጥ ኃይለኛ እንቅስቃሴ ተነሳሳ። ይህም በ 10ኛው ክፍለዘመን የተጀማመረ ነው። አነሳሾቹና ጀማሪዎቹም የክሉኒ መነኮሳት ሲሆኑ፡ እንዲሁም የሎረይን ቤተክርስትያንም ነበሩ፣ ፍጻሜ ላይ ያደረሱት ግን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ልዮን 9ኛ እንዲሁም ጎርጎርዮስ 7ኛ ናቸው። አዲስ ማኅበራዊ ሥርዓትም ጀመረ፣ ይህም “ተዮክራሲ” (Theocracy= አምላካዊ አስተዳደር) የተሰኘ፣ ማንኛውም ነገር በመንፈሳዊ ሥልጣን ስር ይሁን፣ በእሱም ስር ይተዳደር የሚል ባህል ነው። በተለይም የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ኃላፊነትና ሚና፣ በዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጕዳዮች ውስጥ፣ እንደ የበላይ ዳኛና ነገሮችን እልባት ላይ የሚያደሱ አድርጎ የሚገምት አካሄድ ነው። ሄፌለ የተባለ የታሪክ ጸሓፊ እንደሚለው - “ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ፣ በመላው ዓለም የተዘረጋ ወይ የተስፋፋ፣ በመንፈሳዊ ሥልጣን ስር የሚተዳደር፣ (Theocracy) ሁሉንም የክርስትና መንግሥታት የሚያጠቃልል መሠረታዊ መመሪያው ደግሞ ዓሠርቱ ትእዛዛት መሆን ያለበት ነው። እንዲህ ያለው የሃገሮች ኅብረትና ስምምነት ውስጥ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የበላይ መሪ ይሆናሉ። ፀሓይ አጠገቧ ሆና ለጨረቃ ብርሃንን እንደምትሰጣት ሁሉ፣ መንፈሳዊ ሥልጣንም ምድራዊው ሥልጣን አጠገብ ሆኖ፣ ኃይልና ብርሃንን ሊለግሰው ይገባል። ይህም የሚሆነው ምድራዊውን ሥልጣን ሆነ፣ እኒያ መሣፍንቱን ሳይደመስስ፣ ሉዑላዊነታቸውን ሳይነካ በመጠበቅ የሚተገበር” ነው።

ይህ አዲስ ሓሳብና ዓላማም፣ ወይም ያ የቀድሞ ሓሳብ በአዲስ መልኩ ተግባር ላይ ሲውል የታየው ግን፣ ጀርመናዊውን ንጉሥ ሄንሪ 4ተኛ (1056-1106) ከሥልጣን የማስወገድ ሂደት ሲሆን፣ ይህም እጅግ ወደ ከረረ ሁኔታ የደረሰው፣ በ1077 ላይ በካኖሳ ፍጻሜ አማካኝነት ነው። ንጉሥ ሄንሪ 4ተኛ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይቅርታና ምሕረትን እንዲያገኝ ሦስት ቀናት በውጭ ብርድና ውርጭ ላይ ተጋልጦ ንስሓውን እንደፈጸመ ይታወቃል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 7ተኛ ይህን የመሰለው ነገሥታትን የማንበርከክ ተግባሩን ትክክለኛነት ለማስረዳት፣ ወደ የቅዱስ አጎስጢኖስ ሃሳብ ነው የሚያመራው፤ እንደ አጎስጢኖስ ግንዛቤ “ዓለማዊ ሥልጣን፣ ምንጩ ሠይጣን ነው”፣ ሰብአዊ ግዛት ወይም መንግሥት ደግሞ የአዳም-ኃጢአት ውጤት መሆኑን ነው የሚቀበል።

በ1081 ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 7ተኛ ወደ የ መትጹ (Metz) አቡነ ሄርማን ሲጽፉ፣ “ይህ በዓለማውያን በተለይ ደግሞ አምላክን በማያውቁት ሰዎችና ወገኖች የተያዘው ሥልጣን፣ ሁሉን ቻይ አምላክ በምሕረቱና ለክብሩ ሲል ባጸናው ሥልጣን (የቤተክርስትያን ሥልጣን) ስር መሆኑ ... የሚገባ አይደለምን? ነገሥታትና መሣፍንት፣ አምላክን የማያውቁ ትውልዶች መሆናቸው፣ በድንቍርናና በስርቆት በቅጥፈትና በግድያ እንዲያው ባጭሩ በወንጀል ውስጥ የሚኖሩ፣ ዕውር ድንብስ በሆነ ስስት ... ዲያብሎስ ሰዎችን እንዲገዙ የሚያደርግበት አካሄድ ነው ... ”።

“ከእንዲህ ዓይነቶቹ መንግሥታት የፍትሕ አካሄድ ራቅ፣ ያኔ ምን እንደምታገኝ ታያለህ፣ አንድ መንገድ ዳር ሃምሳ የሚሆኑ ኃይለኛ ዘራፊዎችን ካልሆነ በስተቀር ምንን ታገኝ መስሎሃል? ታድያ በጽሞና ካሰብከው እኮ እነዚህ የዓመጽና የሽፍታ ጥርቅሞች በሌላ አገላለጽ ትንንሽ መንግሥታት ማለት አይደሉምን? እነዚህ አንድ መሪ ያላቸው ቡድን አይደሉምን? ታድያ እነዚህም እኮ በአመጽ ዘርፈው ያከማቹትን የሚከፋፈሉበት ስምምነትና ሕግ አላቸው እኮ፣ ... “ (De Civ. Dei IV, 4 the City of God)

በቀጣዩ ክፍል “የጳጳስና ንጉሥ ፉክክር ወይ እልህ” በሚል ንኡስ ርእስ የተካተተውን ታሪክ እንመለከታለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 03 Oct 2019, 09:52

የጳጳስና ንጉሥ ፉክክር ወይ እልህ

ታላቁ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ጎርጎርዮስ፣ የንጉሥ ሄንሪ አገልጋዮችን፣ ለንጉሥ ከገቡለት የአመኔታ ቃለማህላ ነጻ በማድረግ፣ ቤተክህነት ከነገሥታት አንጻር ልትጠቀምበት የምትችል መሳርያ እንዳላት ግልጽ አደርገው በተግባር አሳዩ። ምክንያቱም የፊውዳላዊው ሥርዓት መሠረቱ እርስ በርሳቸው ያደርጉት በነበረው ውልና ማሓላ የተመረኮዘ ስለነበረ ነው። የቅዱስ ጎርጎርዮስ ትልቁ ድል፣ ነገሥታትና የዓለም መሪዎች በቤተክህነት ላይ ሥልጣን የመስጠትና የመንጠቅ የቆየ ልማዳቸውን ማስወገዱ ነው። ይህ የነገሥታትና የመሣፍንት መጥፎ ልማድ፣ የቤተክህነት ሥልጣንና ኃላፊነት ምንጩ መለኮታዊ መሆኑን የሚክድ ልማድ ነው የነበረ። እርግጥ ነው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ይህን መመሪያቸውን ተግባር ላይ በማዋላቸው፣ ትልቅ ዋጋ ከፍለውበታል። ከሮማ ከተማ እንዲባረሩና እንዲሰደዱም ምክንያት ሆኗቸዋል። ይህንን መመሪያቸውን ግን የኋላ ኋላ የሥልጣን ተኪዎቻቸው ወይ ምትኮቻቸውም በቆራጥነትና በድፍረት በመተግበር ተከላክለውታል። በመጨረሻም በብዙ ሃገራት፣ ይህን በተመለከተ እጅግ ላቅ ባለ ሁኔታና በክብር ስምምነት ላይ ተደርሷል። እንግሊዝ ሃገር ውስጥ፣ በ 1107 የወስትሚንስተሩ- ውል፣ ጀርመን ሃገርም በ 1122 የዋርምሱ-ውል፣ በመንግሥትና በቤተክርስትያን መካከል ስምምነት ላይ በመድረስ ውል ተፈራረሙ፣ መንግሥት የሲቪላዊ ሥልጣን፣ ቤተክርስትያንን ደግሞ የመንፈሳዊ ጕዳዮች ሥልጣን እንዲኖራቸው፣ አንዱ በአንዱ ውስጥ እጁን እንዳያስገባ ስምምነት ላይ ተደረሰ። ይህ ደግሞ የቅዱስ ጎርጎርዮስና የምትኮቹ ትግልና ጥረት ፍሬ ነው።

ጀርመናዊው ንጉሥ ሄንሪ 4ተኛ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 7ተኛ ከሥልጣኑ እንደተሻረና እንደተሸነፈ፣ ሄንሪ እንደ የተቃውሞ ማስረጃው አድርጎ ያቀረበው፣ “የነገሥታት መለኮታዊ መብት” (Divine Right of Kings) የሚል ጕዳይን ነው። ይህም ማለት አንድ ንጉሥ የመንግሥት ስልጣን የሚይዝ፣ በአምላክ ፍላጎትና ፍቃድ እንጂ፣ በጳጳስ ፍላጎት አይደለም፤ በተመሳሳይ መልኩ ንጉሥ ከሥልጣኑ የሚሻረው በአምላክ እንጂ በጳጳስ አይደለም። ይህን የመሰለውን አመለካከት የሚደግፉ ጥቂቶች አልነበሩም። እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ የንጉሥ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች አስቀድመው ከገቡት የታማኝነትና ታዛዥነት ማህላ ወይም ቃልኪዳን፣ ጳጳስም ቢሆን ሊፈታቸው ወይም ነጻ ሊያደርጋቸው አይችልም ተባለ።

እንግሊዝ ሃገር ውስጥ የተስፋፋው አመለካከት ደግሞ፣ ጳጳስነትና ንጉሥነት ሁለቱም በየራሱ የግል መስመር በቀጥታ ከአምላክ ነው የመጣው የሚል ነው። ጀርመን ውስጥ የነገሡት የሄንሪ 4ተኛ ተከታዮች እንደ ፍረድሪክ ባርባሮሳ (1152-1190) የመሰሉት ደግሞ፣ የቢዛንታየምን የቄሣረ-ጵጵስናን መንፈስ በመከተል የንጉሥ ዡስቲንያንን ሕግም በማስታወስ- “ንጉሥ (መስፍን) የሚያስደስተውን ማንኛውም ነገር፣ ማለትም ያሰኘውን ነገር ሁሉ፣ የሕግ ኃይል ሊያለብሰው ወይም ሕጋዊነት ሊያጎናጽፈው ይችላል” አለ።

በ 1158 እ.ኤ.አ. ፍረድሪክ ልክ እንደ አንድ አዲስ “የዓለም ገዢ” ታሰበ። በዚህም ምክንያት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተቃውሞ ተሰማ። ቀጥሎ የታየ ከነገሥታት አንጻር ቀላል የማይባል የጳጳሳት ሥልጣን ነበር። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኢኖቼንሲዩስ 3ተኛ የእንግሊዝ ሃገርን ንጉሥ ጆን ላክላንድን አንበረከኩት፤ የፈንሣዩን ንጉሥ ፊሊጵስ አውጉስቱስም በፍች ያሰናበታትን ሚስቱን እንዲቀበላት አስገደዱት፤ የአራጎኑ ንጉሥ ጴጥሮስም፣ ጳጳስ ባስገደዱት መሠረት ግዛቱ በጳጳስ ስር እንድትሆን አደረገ፣ በሃንጋሪና በፖላንድም ለተከሰተው የሥልጣን መወራረስ ጭቅጭቅም እልባት ለማስገኘትና ብያኔ ለመስጠት ተጠሩ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 9ኛ ደግሞ (1227-1241) ከንጉሥ ፍረድሪክ ዳግማይ (1214-1250) ጋር ቀጣይ በሆነ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። በፍረድሪክ ዳግማይ ላይ ድልን የተጎናጸፉት ኢኖቼንሲዩስ 4ኛ ናቸው (1243-1254)። እኝህ ጳጳስ፣ “በዚህ ዓለም ውስጥ እኛ ንጉሠ ነገሥት የሆነው የአምላክ ውክልና አለን” ባይ ነበሩ።

በቀጣዩ ክፍል “የጀላስዩስ ትምህርት” በሚል ንኡስ ርእስ የተካተተውን ታሪክ እንገረምማለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 01 Nov 2019, 03:19

የጀላስዩስ ትምህርት

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጳጳስ ጀላስዩስ ትምህርትም አልተረሳም፤ በ1953 እ.አ.አ. ፕዮስ 12ተኛ የልዮን 13ኛ ሃሳብን ሲተነትኑ እንዲህ ብለዋል- “የጀላስዮስን ትምህርት የሚያንጸባርቀው የልዮን 13ኛ ሓሳብ፣ የቤተክርስትያንን ትምህርትና ሓሳብ ነው የሚያንጸባርቀው፣ ሊባል ይቻላል። ...አንዳንድ ሁኔታዎችን ወደ ጎን ትተህ፣ በመጀመሪያው (ሚለንየም)ሽሕ ዓመታት ይህ ሓሳብ ነግሦ ነበር ...አብዛኞችም ይህን ሓሳብ ይደግፉ ነበር” (መስከ. 24/1995)።

ቅዱስ ጴጥሮስ ዳምያኑስ ይህን የጀላስዩስ ትምህርት ይከተሉ ነበረ። ሆኖም ሁለቱም የመንግሥትና የቤተክህነት ሥልጣን እኩል ጎንለጎን በፍቅር ይሄድ ነበር። የቤተ ክህነት ወገን ፖለቲካዊ ጕዳይ ውስጥ እንዲገቡ፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ጕዳዮችን ለመፈጸምና ለማፋጠን የመንግሥት ሥልጣንና መሳርያን መጠቀም እንደማይገባ ያመለክታል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓስካል ዳግማይ (1099-1116) በተለይ እ.አ.አ. በ1111 ይህን የጀላስዩስ ትምህርት በመከተል፣ እኒያ ነገሥታት በአንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች ላይ የነበራቸውን ሥልጣን (investiture) የሚተው ከሆነ፣ እሳቸውም በበኩላቸው በምላሹ ምድራዊ ግዛታቸውን ለመተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለጡበት ነው። የክሌርቮው ቅዱስ በርናርዶስም የጀላስዩስን ትምህርት በደንብ አድርጎ አስፋፋው፣ በተለይም በቅድስት መንበር ውስጥ በሮማ ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ የነበሩትን ባለሥልጣኖች በተመለከተ፣ ወደ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኤውጀንዩስ 3ኛ የጻፈው De Consideratione የሚል መሠረታዊ መጸሓፉ፣ በርናርዶስ ይህን ጕዳይ በተመለከተ የጀላስዩስ ተከታይ መሆኑን ይገልጻል።

ቅዱስ ቶማስ አኵናስ (1225-75) ደግሞ ግሪካዊው አሪስቶትል ያቀረበውን “ባህርያዊ ሰብአዊ ማኅበር’ የሚል ሃሳብን ሲያስፋፋ እናየዋለን። “የሰው ልጅ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ህልውና እንዳለው የሚካድ አይደልም።” …አንድ ሰው ብቻውን ብቁ የሆነ ኑሮን ሊኖር አይችልም። ስለሆነም የሰው ልጆች በብዛት ወይም በማኅበር መኖር የግድ ካለባቸው፣ ይህን የመሰለውን ማኅበር የሚመራ ሕግና ሥርዓት የግድ ያስፈልጋቸዋል። …ይህ ደግሞ ለጋራ ጥቅም ሲባል ነው”(on the rule of princes I.2)።

ኅብረተሰብና ኅብረተሰቡን የሚያስተዳድረው ሥልጣን፣ በባሕርያዊ ሕግ መሠረት የሚጓዝ ከሆነ፡ ምንጩና መሠረቱ ከአምላክ ነው ማለት ነው፤ ስለሆነም ይህ ተግባር ምንጩ የሰይጣን ስራ ወይም ከአዳም ኃጢአት አይደለም፣ የመካከለኛው ዘመን ታዋቂና ድንቅ መምህር የሆነው ቅዱስ አጎስጢኖስ ሲሆን ከዘመነ “ሬነሳንስ” ተሓድሶ (Renaissance) ጀምሮ እስከ እዚህ ዘመናዊ ሥልጣኔ ግዜ ድረስ ግን፣ ቅዱስ ቶማስ የሱን ማለት የአጎስጢኖስን ትምህርት ይዞ ይገኛል።

ሃገራዊ የንግሥነት(የአፄነት) ሥርዓት፣
(National Monarchs)

ያ አስቀድሞ በአንዳንድ አካላት ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረው በመንፈሳዊ መሪዎች አማካኝነት ይካሄድ የነበረው ሥልጣን (theocracy)፣ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቦኖፋቺዩስ 8ኛ፣ ንጉሥ ፊልጵስ (Philip the Fair) ብርቱ ተቃውሞ እንዳጋጠመው፣ ያ የመካከለኛው ክፍለዘመን ክርስትያናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ወደ አዲስ የሃገሮች ልዑላዊነትና ደንበርተኛነት ተሸጋገረ። በተለይም በፈረንሣይ፣ እንግሊዝ ሃገርና፣ ስፐይን ይፋፋም የነበረው የሃገራዊ ልዑላዊነት (sovereignty) ስሜትና ግንዛቤ ይህንን ሊገታው የሚችል አልነበረም። ስለሆነም በተለያዩ ስፍራዎች በነበሩት መንግሥታት ሰፍኖ የነበረው የንጉሠ ነገሥታዊ (empire) ሥርዓት እየተሸራረፈ ተዳከመ/ከሰመ።

በየስፍራው የነበሩት የሃገሮች ነገሥታትም፣ ይለይለት ብለው ለቤተክርስትያን ተሰጥቶ የነበረን አንዳንድ ምድራዊ ንብረትን የማስተዳደር መብት ቀስ በቀስ ሊቀሟትና ሊያስቀሩት አቀዱ። ከንጉሣዊ ሥልጣን ጎን ለጎን፣ ራሱን የቻለ ሌላ የቤተክህነት ሥልጣን መኖሩ፣ አንድ መንግሥት ውስጥ ሌላ ራሱን የቻለ መንግሥት እንዳለ (እንደመፍጠር) ሆኖ ተቆጠረ፤ ይህ ደግሞ ችግር ፈጠራ ነው በማለት ሞገቱ (ሃሳባቸውን አቀረቡ)።

የፓሪሱ ተወላጅ ዮሓንስ ለንጉሥ ፊልጶስ ሲጽፍ ፣ የቤተክህነት ሥልጣንና የንብረቷ አስተዳደር በንጉሥ ሥልጣን ስር መሆን አለበት የሚል ሓሳብን አራመደ። እንግሊዝ ሃገር ውስጥም ዮሓንስ ዊክሊፍ፡ የቤተክርስቲያን ንብረት ሁሉ በንጉሥ ስር ሊሆን ይገባል ባይ ነበር።

ምንም እንኳን ይህ ሁሉ ተቀባይነትን ባያገኝም፣ ቀስ በቀስ ግን ሲብላላ ቆይቶ፤ በተለይም በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት “የምድራዊ የማስተዳደር ሥልጣን” ያልተደሰቱ ወገኖች ይበልጡኑ ይህንን ሓሳብ አጋጋሉት፣ አናኚ (ኢጣልያ) ውስጥ በተደረገው ህልክ ደግሞ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቦኒፋቺዩስ 8ኛ አላሸነፉም ብቻ ሳይሆን፣ በፈረንሣዊው ንጉሥ ወደ አቪኞን እንደሚጋዙ (እንዲወሰዱ) ተደረገ፣ ሆኖም ከ 1305 እስከ 1377 የነበሩት ጳጳሳት ቤተክርስትያንን አቪኞን ውስጥ ሆነው መሯት፣ ምንም እንኳን የመላው ቤተክርስትያንን መምራት ልክ እንደ ቀድሞው ሁሉ ቢቀጥልም ጳጳሳቶች ሁሉ ግን ፈረንሣዊያን ስለነበሩ በተለይ ለእንግሊዞች ይህ ሁኔታ አልተዋጠላቸውም።

ፀረ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ተቃውሞ፦ ፈረንሣዊው ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ዮሓንስ 22ኛ (1316-34) ለንጉሠ ነገሥትነት እጩዎች ሆነው የቀረቡትን ሁለት ጀርመናውያንን ውድቅ አድርገው፡ አንድ ፈረንሣዊን ልክ እንደ ግዜያዊ አስተዳዳሪነት ሲመድቡ፣ ብርቱና ኃያል ተቓውሞ አጋጠማቸው። ከዚህም በኋላ ጀርመኖች ማንኛውም ምድራዊ አስተዳደርን የሚመለከት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ሥልጣን ሁሉ ውድቅ አደረጉት። በዚህም የረንዘ አዋጅ (1338) በአዲሱ የ(1356) ወርቃዊ አዋጅ ተተካ።

ይህም በበኩሉ ሌላ ብርቱ ተቃውሞን አጋጋለ። በእርግጥም ይህ ተቃውሞ በፓድዋው ማርሲልዮ (Defensor Pacis) በይፋ ታየ። ይህ ደግሞ ጭራሹኑ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን የምድራዊ አስተዳደር ሥልጣን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን፣ የመንፈሳዊ ሥልጣናቸውንም የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ተቃውሞ ነበር። እንደ የፓድዋው ማርሲልዮ አመለካከት ቤተክርስትያን ልክ እንደ የአሪስቶትል የመንግሥተ-ሃገር (State) አመራር መጓዝ አለባት፣ ይህም ማለት ማንኛውም ሥልጣን ሁሉ ከአዋቂዎችና በአስተሳሰብ ከበሰሉ ዜጎች (Aristocracy) የሚመነጭ ነው። ስለሆነም በማርሲልዮን ትምህርትና በተከታዮቹ፣ ዓለም ዓቀፋዊና አህጉራዊ ሥልጣንን ሊጨብጥ የሚገባው “ትልቁ የቤተክርስትያን ጉባኤ” (General Council) ብቻ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአቪኞን ወጥተው፣ ወደ ሮማ እንደተመለሱ ብዙ የፖለቲካ ሰዎች ይህንን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣን በመቃወም ወደ ጉባኤው ስነሓሳብ አዘነበሉ። እንደ እነዚህኞች አመለካከት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የአስፈጻሚነት ሥልጣንና ሚና ብቻ ነው የነበራቸው፣ ስለሆነም በጠቅላላው ጉባኤ ሓጋጊ አካል ፍቃድና ስምምነት አማካኝነት መምራት ይገባቸዋል። ይህ ጉባኤ ለራሱ፡ በአቡናት ካህናትና መእመናን የቆመ እንዲሆን አድርገውም አሰቡ። በመጨረሻም ይህ ነው የሚባል ትልቅ ውሳኔ ሳይወሰን ከዚህ የጉባኤ ሥነሓሳብ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ነጻ ሆኑ፤ ምድራዊውን ነገሮች በተመለከተ ግን ኃይላቸው ተዳከመ ሥልጣናቸውንም ተቀሙ።

ዘመናዊ ዓለምና፡ ብዙኅነት
(Modern Pluralism)

ይህ ዘመናዊ ዓለምና ወቅት በማለት እየጠቀስነው ያለነው የታሪኽ ወቅት፣ በርካታ ሃሳቦች የፈለቁበትና የተስፋፉበት ዘመን ነው። (modern age pluralism ይባላል)። የፕሮተስታንት ለውጥ የተቃወመው ፣ በምድራዊና መንፈሳዊ ጕዳዮች ላይ የነበረን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣንና ቀዳሚነትን ብቻ አይደለም፣ እንዲያውኑም ገደብ-አልቦ ሥልጣን ለጨበጡት ለነገሥታቱ (absolute monarchs) ልዩ ምቹ ስፍራ አመቻቸላቸው። ካቶሊካውያን ነገሥታት ሳይቀሩ ይህን አስተሳሰብና አመለካከት አልተረዱትም ማለት አይቻልም። ሉተርም ቢሆን ቤተክርስትያንን በንጉሥ ሥልጣን ወይ በመንግሥት ስር ትሁን የሚል ዓላማ አልነበረውም። ቆይቶ ከግዜ በኋላ የገባበት ወይ የተቀበለው ግዴታ ነው። ይህም የሆነው (የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት የተቀበለው) ልዑላን መሳፍንቶች ሲጠጉትና ሲያጨበጭቡለት ጊዜ ነው። ቀጥሎም ጭራሹኑ የእነዚህ መሳፍንቶች ጉዳይ አስፈጻሚም ሆነ። በመሆኑም ሉተር በወቅቱ የነበረውን መስፍን በማወደስና በማሞካሸት ልክ እንደ እጣን በውዳሴ ሲያጥነው ታየ። “እርሱ ሁሉንም ሥልጣን የጨበጠ አባት ነው”፣ “ባለፈው ግዜ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሁሉም ላይ ሥልጣን ነበረው፣ አሁን ግን በሁሉም ላይና በሁሉም ስፍራ የበላይ መስፍኑ ነው”። ማለት ጀመረ።

በቀጣዩ ክፍል በዚህ ርእስ ስር የተካተተውን ታሪክ እንቀጥላለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 15 Nov 2019, 09:06

ዘመናዊ ዓለምና፡ ብዙኅነት
(Modern Pluralism
)

ይህ ዘመናዊ ዓለምና ወቅት በማለት እየጠቀስነው ያለነው የታሪኽ ወቅት፣ በርካታ ሃሳቦች የፈለቁበትና የተስፋፉበት ዘመን ነው። (modern age pluralism ይባላል)። የፕሮተስታንት ለውጥ የተቃወመው ፣ በምድራዊና መንፈሳዊ ጕዳዮች ላይ የነበረን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣንና ቀዳሚነትን ብቻ አይደለም፣ እንዲያውኑም ገደብ-አልቦ ሥልጣን ለጨበጡት ለነገሥታቱ (absolute monarchs) ልዩ ምቹ ስፍራ አመቻቸላቸው። ካቶሊካውያን ነገሥታት ሳይቀሩ ይህን አስተሳሰብና አመለካከት አልተረዱትም ማለት አይቻልም። ሉተርም ቢሆን ቤተክርስትያንን በንጉሥ ሥልጣን ወይ በመንግሥት ስር ትሁን የሚል ዓላማ አልነበረውም። ቆይቶ ከግዜ በኋላ የገባበት ወይ የተቀበለው ግዴታ ነው። ይህም የሆነው (የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት የተቀበለው) ልዑላን መሳፍንቶች ሲጠጉትና ሲያጨበጭቡለት ጊዜ ነው። ቀጥሎም ጭራሹኑ የእነዚህ መሳፍንቶች ጉዳይ አስፈጻሚም ሆነ። በመሆኑም ሉተር በወቅቱ የነበረውን መስፍን በማወደስና በማሞካሸት ልክ እንደ እጣን በውዳሴ ሲያጥነው ታየ። “እርሱ ሁሉንም ሥልጣን የጨበጠ አባት ነው”፣ “ባለፈው ግዜ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሁሉም ላይ ሥልጣን ነበረው፣ አሁን ግን በሁሉም ላይና በሁሉም ስፍራ የበላይ መስፍኑ ነው”። ማለት ጀመረ። ከዚህም ጋር ጎን ለጎን ሉተር ያመጣው ሌላ አደገኛ ሓሳብም አለ። ይህም አስተሳሰብ የማኪያቬሊን ትምህርት የሚከተል፡ በግልና በሥልጣን መካከል ስላለው ሞራላዊ ልዩነት የሚመለከት ነው። ይህን አመለካከት ሉተር በቀጥታ ያመጣው ሳይሆን በተዘዋዋሪ መልኩ ያራመደው መርሁ ነው። ስለ ቤተክርስትያን ሲያስተምርም፡ “የማትታየው ቤተክርስትያን የሚያስገድዳትና ልክ የሚያገባት ኃይል የለም፣ ስለሆነም መስፍኑ በግሉ እንደ ግለሰብ መጠን አማኝ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሲያስተዳድርና ሲመራ ግን እንደ ክርስትያን ሆኖ ማስተዳደር የለበትም” አለ። ስለሆነም የሉተር መነሻ ሓሳቡ ምንም ይሁን ምን፣ ቆይቶ “በምልአት መንፈሳዊ” የሆነችውን ቤተክርስትያንን ሲፈልግና ሲሻ፣ ምንም ያልተቀላቀለበትን ሙሉ በሙሉ የዓለማዊ ኅብረተሰብ ዕድገትን፣ ማለትም ከክርስትያናዊ ሆነ ሃይማኖታዊ ተጽዕኖ ነጻ የሆነን ዓለማዊ ኅብረተሰብን የሚደግፍ ሆነ። ሳይታወቀውም አምባገነን ለሆነ ሥርዓት (Totalitarian State) መገዛት የሚፈቅድ ሓሳብን ደገፈ።

በሌላ በኩልም በሃይማኖታዊና እምነታዊ ጕዳይ ካልቪን ከሉተር በከፋ ሁኔታ ከካቶሊኽ የራቀ ቢሆንም ቅሉ፡ ጄነቭ ውስጥ የነበረውን መንፈሳዊ ሁኔታ ላይ የተጠቃለለን የመካከለኛው ዘመን “ተዮክራሲ”ን ማቀብ ወይ ማስፋፋት መረጠ። እንደ ካልቪን አስተሳሰብ መንግሥትና ቤተ ክርስትያን ሃይማኖትና ፖለቲካ እርስ በራሳቸው የተደበላለቁና የተቀየጡ ወይ የተዳቀሉ ናቸው። በዚህ አስተሳሰብ የሚመሩ እንደ ምሳሌነት የሚጠቀሱ ሥርዓቶች፦ በካልቪን ስር የነበረው የጄኔቩ “ዲክታተርያዊ” ሥርዓት፣ በስኮትላንድ የነበረው “ኪርክ” የተሰኘው የ ጆን ኖክስ፣ እንዲሁም በአሜሪካ “ኒዩ ኢንግላንድ” የታየው የመጀመሪያ አካሄድ ይጠቀሳሉ።

በተግባር ሲታይም ከካልቪኑ አስተሳሰብ እጅጉንም የራቀ ቢሆንም፣ በእንግሊዝ ሃገርና በሌሎች ግን፣ አንዳንድ ለውጦች ተደርጎበታል፣ ያም ሆነ ይህ ደግሞ ካፒታሊዝምን ይበልጡኑ አስፋፋው አሳደገውም፣ በመጨረሻም ብዙ መደበላለቅ የታየበት፣ የምዕራቡ ዓለም ሊበራሊዝም ተወለደ።

ይህ አጠቃላይ አመለካከትና ግንዛቤ እንደ ትክክለኛነት ተወስዶ፣ ከነ ሙሉ ድንበሩና ስፋቱ፣ በ 1ኛ እና 2ኛ የዓለም ጦርነቶች ወቅት እርስ በራሱ የተዋጋው ይህ ሁለት ዓይነት መልክና አደረጃጀት የያዘው የክርስትና ወገን ወይ አካል ነው። ያ በፖለቲካ ነጻ መሥመርን የተከተለው ወገን (Political Liberalism)፣ ወሰን-አልቦ ንጉሥነትን የሚያምኑ (Absolute Monarch) ወገኖችን በመቃወም፣ ካፒታሊዝምን በመቃወም፣ አምባገነነትን በመቃወም፣ ምዕራብን በመቃወም፣ ምሥራቅን በመቃወም …ወዘተ።

በቀጣዩ ክፍል "ወደ ዴሞክራሲ አቅጣጫ" በሚል ንኡስ ርእስ ስር የተካተተውን ታሪክ እንቀጥላለን።

Meleket
Member
Posts: 491
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: መንግሥትና ሃይማኖት - ሳይንሳዊ ጥናት

Post by Meleket » 04 Dec 2019, 04:56

ወደ ዴሞክራሲ አቅጣጫ፦ ካቶሊካዊ የኅብረተሰብ ትምህርት ግን ቀስ በቀስ እየተሻሻለ ወደ ሓቀኛ ዴሞክራሲ አቅጣጫ የሚያድግበት ሁኔታዎች ይታይ ጀመር። ሱዋረዝ እንዲሁም ሮበርት በላርሚን ዳግመኛ ያነሳሱት ሓሳብ፣ “ስኮላስቲክ” በመባል በሚታወቀው የነ ቶማስ ኣኵናስ ትምህርት ነው። በዚህ ትምህርትም አማካኝነት ዓለማዊ ፖለቲካዊ ሥልጣን ምንጩ ከፈጣሪ ነው፡ በሕዝብ አማካኝነትም ይመጣል፣ በተግባርም ይውላል። ይህም በመሆኑ ሕዝብ ራሱ በሚያደርገው ምርጫና ውሳኔ በንጉሥ የሚመራ አስተዳደር (monarchy) ወይም ደግሞ የተሻሉ ናቸው በሚባሉ አካላት (aristocracy) የሚመራ አሊያም በሕዝባዊ ሪፖብሊክ መመራትን ራሱ ሕዝቡ ... ይወስን ተባለ። ይህን የመሰለውን ፖለቲካዊ “መናፍቅነትም” የእንግሊዝ ሃገሩ ንጉሥ ጀይምስ (ቀዳማዊ)፣ ከነተከታዮቹ በመሆን አበርትቶ ተቃወመው። ነገር ግን እንደነ ሮበርት በላርሚንን በመሰሉ ምሁራን የተመለመለው እንግሊዛዊው ጆን ሎክ፣ ይህን የንጉሥ ጀይምስ ቀዳማዊን አስተሳሰብ ተቃወመው አወገዘውም፣ በዚህም አማካኝነት አሜሪካን በመሠረቷት አካላት ዘንድ ይህ የ “ስኮላስቲሲዝም” (Scholasticism) ሓሳብና ትምህርት ተስፋፋ።

ቢቶሪያና ሱዋረዝ የተባሉ ምሁሮችም ሂዩጎ ግሮሲዩስን ቀድመው፣ የሕዝቦችን ወይ የሃገሮችን ሮማዊ ሕግ (Jus Gentium) ወይም “ኢንተርናሽናል/ዓለም ዓቀፋዊ ሕግ” በመባል የሚታወቀውን ሕግና ሃሳብ አዳበሩ። ይህን ሃይማኖታዊ ልዩነቶችና ችግሮች በብዛት በሚታዩበት ወቅት የኢንተርናሽናል ሕግ መዳኛ ሆኖ ተገኘ። ያ አስቀድሞ እንደ “የአህጉራዊነት” ካባ ሆኖ ይታይ የነበረው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አመራር አሁን ዳግማኛ የሚነሣበትን ዕድል አላገኘም። አውሮጳ ልትተባበር (ኅብረትን ልትፈጽም) እንኳ ባትችልም ግርግርና ሁከት ውስጥ ከመግባት ግን ይህ የኢንተርናሽናል ሕግ ዋስትና ሆኖ ሲጠብቃት ታየ። በ1530-96 ደግሞ ዣን-ቦዲን የተባለ ምሁር፣ የማንኛቸውንም ሃገራት የግል ልዑላዊነት ሃሳብ በማመንጨቱ፣ ይፈለግ ለነበረው የአህጉራዊነትና የአውሮጳዊነት ኅብረትና ውሕደት እንቅፋት ሆኖ ተገኘ።

በዚህ አዲስ አስተሳሰብ አማካኝነትም በፈረንሣይና በአውስትርያ የቤተክርስትያንን ህልውናና ነጻነት የሚጻረር ሁኔታ ተከሰተ። ካቶሊካዊያን በበዙባቸው ሃገሮችም “የዘውድና የቤተክርስትያን ኅብረት” የሚባል ሓሳብ ገነነ። በዚህ መልኩም በቤተክርስትያንና በመንግሥተ-ሃገር መካከል የሚፈጠር ኅብረት ወይ ሥምረት፣ በእኒያ የቤተክርስትያን ተቃዋሚ በሆኑ አካላት (Liberals) ብርቱ ተቃውሞ አጋጥሞታል።
በዚ ዓይነት አገባብ ከቤተክርስትያን ጋር ተስማምተው የሚሰሩ ነገሥታት ብዙ መልካም ተግባራትን ፈጽመዋል፣ በምዕራቡ ሆነ በምሥራቁ ዓለም የተካሄደ የስብከተ-ወንጌል ስራ በነዚህ ነገሥታት አማካኝነት በተገኘ ዕድልና ድጋፍ መሠረት ነው። ይህ ከነገሥታት በኩል ለቤተክርስትያን የተሰጠው ልዩ ዕድል ግን በአጸፌታው ቤተክርስትያንን ብዙ ክቡር ዋጋ አስከፍሏታል፣ ከነገሥታቱ በኩል የተገኘው ልዩ ዕድል ቢቀርባት ሳይሻል አይቀርም ነበር የሚያስብልም ነው። በ18ኛው ክፍለዘመን አውሮጳ ውስጥ ቤተክርስትያን ሃብታሞችንና መካከለኛ ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች በሙሉ፣ እንዲሁም በ 19ኛው ክፍለዘመን ደግሞ መላውን ሰራተኛ ከሥራቸው ነበር።

የ ፕራሺያ(ጀርመን) ንጉሥ ፍረድሪክ ትልቁ (1740-86) ኢየሱሳውያን ካህናትን “የስራ አጋሮቼ” ሲላቸው፣ ያቺ “ካቶሊኽ” በመሆኗ እጅጉኑ የምትታወቀው ስጳኛ፣ “እጅጉኑ ታማኝ” በመሆኗ የምትታወቀው ፓርቱጋል፣ “እጅጉኑ ክርስትያን” በመሆኗ የምትታወቀው ፈረንሣይ፣ እነዚህ ኢየሱሳውያን ካህናቶችን ሲቃወሟቸውና ከግዛቶቻቸው ሲያባርሯቸው፣ ያ ካቶሊካዊ ያልሆነው የሚባለው ፍረድረክ ግን በነጻ ግዛቱ ውስጥ ይሰሩ ዘንድ እንደፈቀደላቸው ነው ታሪክ የሚመሰክረው፣ እጅግ በጣም የሚገርም የታሪክ እንቆቅልሽ!!!

በቀጣዩ ክፍል "ሊበራሊዝም ያስነሳቸው ለውጦች" በሚል ንኡስ ርእስ ስር የተካተተውን ታሪክ እንቀጥላለን።

Post Reply