Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
fana-solo
Member
Posts: 528
Joined: 11 Jun 2019, 01:43

ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን, በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አያገኝም!

Post by fana-solo » 11 Jul 2019, 16:44

በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አያገኝም!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በውኑ ትሞህተኝነት የለምን?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን "ትምህተኝነት የሚባለው ንግግር የአማራ ጠል ፕሮፓጋንዳ ነው" ሲሉ ከአጽንኦት ጋር ተናግረዋል። በእርግጥ አማራ እንደ ሕዝብ ችግር አለው ብዬ ባላምንም አማራን እንመራዋለን የምትሉ ቡድኖችና ግለሰቦች ግን ሁላችሁም የዚህ ትምህተኝነት የተባለው ተላላፊ የአእምሮ ካንሰር በሽታ ተጠቂዎች ናችሁ ብዬ አምናለሁ። ለዚህ መገለጫዎቹ:
~~~
1ኛ። "አማራ የሰውነት ልክ ነው። ሌላው ሕዝብ ሰው ለመሆን በአማራ ልክ መለካትና መመዘን አለበት!" የምትሉትን ምን እንበለው? ይሄ ትምክተኝነት ካልተብለ ምን ይባል? እርስዎም ቢሆኑ ይህን የትምክህተኝነት ፖለቲካ ነቅፈውት አያውቁም። እንደ መሪ ይህን እያዩና እየሰሙ ዝም ካሉ የእርስዎም ሃሳብ ነው ማለት ነው።
~~~
2ኛ። "የኢትዮጵያ ፈጣሪዋ አማራ ስለሆነ ሌላው ሕዝብ ለኢትዮጵያ ፈጣሪ ለአማራው መስገድና መገዛት አለበት!" ማለት ትምክህተኝነት ካልሆነ ምን እንበለው?
~~~
3ኛ። "ቅማንትን ከነጋዴ ባህር በታች አናስወርደውም!" ብሎ ከመላው የአማራ ክልል ጦር እየመለምሉ በየጊዜው ወደ ቅማንት ምድር ማዝመትና ንጹሃንን መጨፍጨፍ ትምክህተኝነት ካልተባለ ምን እንበለው?
~~~
4ኛ። "ክልሉ ውስጥ ከአማራ ውጭ ሌላ ሕዝብ መኖር የለበትም!" ብሎ እየፎከሩ ዘር ማጽዳት ዴሞክራሲያዊነት ነው ወይስ ትምክህተኝነት?
~~~
5ኛ። በጀብደኝነት ፉከራ ወደ ጃዌ ወረዳ ጦር አዝምቶ ከ250 በላን ንጹሃን ጉሙዞችን መጨፍጨፍ ትምክህተኝነት የተባለው በሽታ የፈጠረው ችግር ካልሆነ ቅድስና ነው እንበለው?
~~~
6ኛ። ከሚሴ ላይ ዘምታችሁ ተፋቅረው የሚኖሩትን ኦሮሞዎችና አማራዎችን ስታጋድሉ በቅድስና ተመርታችሁ ነው ወይስ በትምክህተኝነት ተገፋፍታችሁ?
~~~
7ኛ። የቅማንትን የመብት ጥያቄ ላለፉት 12 ዓመታት ያፈናችሁት ዴሞክራሲያዊነታችሁ ፈቅዶላችሁ ነው ወይስ ትምክህተኝነታችሁ አስገድዷችሁ?
~~~
8ኛ። በ1999 ዓ ም የቅማንትን ሕዝብ ከብሄራዊ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ የሰረዛችሁት በዴሞክራሲ ነው ወይስ በትምክህተኝነት?
~~~
9ኛ። "አማራ ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው፡ ኢትዮጵያ ማለት አማራ ማለት ነው። ሌላው ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለም!" እያላችሁ ባደባባይ ስትናገረ በዴሞክራሲ መንፈስ ነው ወይስ በትምክህተኝነት ሰክራችሁ?
~~~
10ኛ። "ጴንጤና ሙስሊም አይመራንም!" እያሉ በአደባባይ ሰልፍ መውጣት ትምክህተኝነት ካልሆነ ምን እንበለው?
~~~
11ኛ። "አማርኛችንና ታቦታችን መልሱልን!" እያሉ መፎከር ትምክህተኝነት ካልተባለ ምን ይባል?
~~~
12ኛ። "የቅማንትን እጅ እንቆርጣለን!" ማለትስ ዴሞክራሲያዎነት ነው ወይስ የትምክህተኝነት በሽታ የወለደው እብደት?
~~~
13ኛ። "የአማራን አማራነት የምናስጠብቀው በጠብመንጃ ነው ሽምግልናና ውይይት አያስፈልገንም!" እያሉ በየመድረኩ መፎከርና ያልተገባ ጦር ማሰልጠን ለጽድቅ ነው ለትምክህተኝነት?
~~~
14ኛ። ቅማንት ጎንደር ዩኒቨርሲቲን መምራት የለበትም ብላችሁ ዶርተር ደሳለኝን አባራችሁ አማራ መሾም ትምክህተኝነት ካልሆነ ምን እንበለው?
~~~
ልቀጥል? ? ?
~~~
ለጊዜው በዚህ ላቁም። ታዲያ የተከበሩ ሚኒስትር እነዚህን እውነታዎች በተመለከተ ምን ይላሉ? አሁንስ ትምክህተኝነት የለም ይሉ ይሆን? እነዚህን በአማራው ስም እየፈጸማችሁ ሌላው ሕዝብ እንዴት አድርጎ አማራን ይውደድ? የምትሰሩት እኮ አማራን ለማስጠላት እንጂ እንዲወደድ አያደርግም። ሌላውን ህዝብ እንደ ሕዝብ እያንቆሸሹ መወደድ አለ እንዴ? በዚህ አካሄዳችሁ አማራ ካልተጠላ ማን ይጠላ? እስኪ አማራ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በሰላምና እኩልነት አብሮ ለመኖር የሚያችለው ሥራ ሠርታችሁ ከሆነ ንገሩን። በአጉል የገዢነት ቅዠት ውስጥ ገብታችሁ በአማራ ስም ትምክህተኝነትን ታስፋፋላችሁ እንጂ መቼ ነው የህዝቦችን እኩልነት ተቀብላችሁ የምታውቁት?
~~~
በዚህ አካሄዳችሁ ከቀጠላችሁ እንደ ጀመራችሁት የአማራውን ሕዝብ ታዋርዱታላችሁ። ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ታዋጉታላችሁ። ያኔ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አያቅትም። ሁሉም ሕዝብ አማራ ላይ መዝመቱ አይቀርም። ምክንያቱም ማንም ሕዝብ ሊረገጥና በግድ ሊገዛ ስለማይፈልግ።
~~~
ክቡር ሚኒስትር፡ በየዩኒቨርሲቲውና በየመንግሥት ተቋማት ተሰግስገው የአማራነት ሂትለራዊ ዘረኝነት የሚሰብኩ ምሁራን ተንዬ መሃይሞችን ይምከሯቸው! በድሮ በሬ የሚያርስ እንደሌለ ሁሉ በደሮው አማራነት በዚህ ዘመን መግዛት አይቻልም። ዘመን ሰልጥኗል። አንዱ ሕዝብ ሌላውን በሃይል የሚረግጥበት ዘመን አብቅቷል። ዛሬ በዴሞክራሲ እየተወያየን በጋራ የምንገዛዛበት ዘመን እንጂ ሥልጣን በዘር የምንሠጥበት ወቅት አይደለም። አሁን ሥልጣን የሚይዘው የሰለሞን ዘር ሳይሆን የዴሞክራሲ ዘር ነው። ያን ተረት ተረት ተውት። በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ ተቀባይነት የሌለው የድንቁርና እሳቤ ነው። አይጠቅምም። አንዳንዴም እኮ ከዘመኑ ጋር ይዘመናል። ዛሬ ላይ ሆናችሁ በምንሊካዊ አገዛዝ ልትገዙን አታልሙ። ዘመን ሲቀየርማ አርፉ እንጂ!
~~~
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር! እብክዎን እራዎ የሚመሩት ፓርቲ አዴፓም ሆነ ክልሉ ቆም ብለው እንዲያስቡና ከምትሄዱበት የገደል ላይ ጉዞ ተመለሱ። በዚህ ከቀጠላችሁ መከራው ለራሳችሁ ነው። የራሳችሁ ሕዝብ ያጠፋችኋል። ይሄ አይቀርም።
~~~
አዴፓ ከኩኩሉ ጨዋታው መውጣት አለበት። ከትምክህተኝነት በሽታ ካልታከማችሁ ራሳችሁን ታጠፋላችሁ። ከዚህ በሽታ ለመታከም ደግሞ መጀመሪያ ይህ በሽታ እያጠቃችሁ መሆኑን አምናችሁ መቀበልና ራሳችሁን ለማከም የተግባር እርምጃ መውሰድ ነው። አለበለዚያ አለባብሳችሁ እያረሳችሁ አረም ያጠፋችኋል። በቃ ትምክህተኝነት በሽታችሁ መሆኑን ካላመናችሁ እስከመጨረሻው አትድኑም።
~~~
እውነታውን ስለተናገርኩ ሰደበን እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ!
ቸር ይግጠመን!

simbe11
Member
Posts: 1066
Joined: 23 Feb 2013, 13:02

Re: ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን, በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አያገኝም!

Post by simbe11 » 11 Jul 2019, 16:52

If you are TPLF thug, let me tell you this. There will be no better servant that ADP to TPLF in the whole world that can lead the region. Unless you made one from nowhere as you did 26 years ago!!
Therefore better to hide or run away while you can. Otherwise, time is coming. Even Mekele will not provide shelter for criminals for long!!!!

Just saying
Just warning

Post Reply