Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 20846
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Revelations » 09 Jun 2019, 14:34

ለአባ ገዳም ይሁን እንደ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ለኦሮሞም ህዝብ ክብር ፍቅርን አንድነትና አክብሮት አለኝ። ነገር ግን ሠው ነኝና በጉራጌ ዞን ስህተት ከሰራሁ ጥፋትም ካጠፋሁ እኔ በጉራጌ ህዝብ ዘንድ በጆካ ሽምግልና ነው የምዳኘውም። አባትና አያቶቼም በዚሁ በጆካ ጉርዳ ነውና የተዳኙት!

ስህተቴና ጥፋቴ ደግሞ በኦሮሚ ክልል ከሆነ ደግሞ በገዳ ስር ዓት በአባ ገዳ እዳኛለሁ። ገዳንም ስለማከብር .! ይህ ማለት ደግሞ እኔ ገዳን ሳከብር እናንተ ደግሞ የጆካ ጉርዳ ማክበር ይኖርባችኋል። በተረፈ ገዳም በጆካ፣ ጆካም በገዳ ሊጠቃለሉ በፍፁ አይችሉም። ኧራራራ የማይቻል ነገር ነው እንጂ .!

የእናንተን ታሪክ አከብራለሁ የእኔም ደግሞ ታከብሩልኝ ዘንድ ሠብዓዊም ዲሞክራሲያዊም መብቴ በተጨማሪም ባህልና ታሪኬም ነውና መሆን በማይችልና መለወጥና መለዋወጥም! በማይችል ነገር አንድከም ጊዜያችንም አናባክን! እንዴ ..!
Revelations
Senior Member+
Posts: 20846
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Revelations » 09 Jun 2019, 14:38

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 20846
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Revelations » 09 Jun 2019, 14:47

Please wait, video is loading...

tolcha
Member
Posts: 2105
Joined: 27 Feb 2013, 16:51

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by tolcha » 09 Jun 2019, 14:55

You posted 99x, you [deleted]. Those days of your ancestors dreams have gone to come back. I know you know what I am saying. Even if it is bitter, it is a good remedy to heal your rotten brain, so take it down without preconditions!

Revelations
Senior Member+
Posts: 20846
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Revelations » 09 Jun 2019, 15:09

The deal that was made with Berhanu Nega on the sale of Gurage is null and void! እቺን ሃቅ ዋጣት:: :lol: :lol: :lol:
tolcha wrote:
09 Jun 2019, 14:55
You posted 99x, you [deleted]. Those days of your ancestors dreams have gone to come back. I know you know what I am saying. Even if it is bitter, it is a good remedy to heal your rotten brain, so take it down without preconditions!

Maxi
Member
Posts: 4843
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Maxi » 09 Jun 2019, 15:15

#etv በጉራጌ ለ158 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኦሮሞ ገዳ ስርዓት በድጋሚ ተቋቋመ።


https://www.facebook.com/EBCzena/videos ... 514007238/Revelations
Senior Member+
Posts: 20846
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Revelations » 09 Jun 2019, 17:57

ዘይትገረም! ሆርሶ ስለ መላኩ ቢረዳ እዚህ ፎረም ላይ ብዙ እንዳልዘባረቀ ዛሬ ስሙንም አያነሳ:: ለምን? ባንዳ መክዳት ልማዱ ነውና:: ግን ጉራጌ አይሸጥም አይለወጥም!

Revelations
Senior Member+
Posts: 20846
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Revelations » 09 Jun 2019, 18:33

ዛሬ በEBC " ለ158 አመታት ተቋርጦ የነበረው የገዳ ስርአት በጉራጌ ዞን ተቋቋመ " የሚል አደገኛ ዜና ተመለከትኩኝ።
የዜናሁ ለጋላ" መፅሀፍ ደራሲ አባ ባህሬይ አንድ መፈክር ነበራቸው "ጠፍአት ሀገርነ " (አገሬ ጠፋች) የሚል ። ያንን ዘመን ካላነበባችሁ ዛሬ ተደግሞላችኋል። አባ ባህሬይ የ16ኛው ክዘ መባቻ የኦሮሞ አሰቃቂ ወረራ በአይናቸው በብረቱ ተመልክተው የአለም የታሪክ ምሁራንን ባስደነቀ መልኩ መዝግበው ያስቀመጡ ምሁር ነበሩ ። ፕሮፌሰር ጌታቸው ከግእዝ ወደ አማርኛ አሳምረው ተርጉመውታል። የአለም ምሁራን ደሞ ከግእዝ ወደ እንግሊዚኛ፣ጀርመንኛ ፣ፈረንሳይኛና ጣሊያንኛ ተርጉመውታል። የሚያመቸውን መርጦ ማንበብ ነው።
..
በአፄ ልብነ ድንግልናና በልጁ በአፄ ገላውድዎስ የተመራው የክርስቲያን ኪንግዴምና በኢማም አህመድና አሚር ኑር ይመራ የነበረው ሙስሊም ሱልጣኔት የ15 አመታት ጦርነት የወደመንና መከላከል የማይችል ሀገር እንደ አውሎ ነፋስ እየተግተለተሉና እየሰለቡ ህዝብ ሲጠፋ ተቋቁመው ከመጥፋት ከተረፉት ህዝቦች መካከል ጉራጌዎች ነበሩ።
.
አሁን ታሪክ ራሱን በሆረር መልኩ እየደገመ ስለሆነ የዚህ ዘመን ትውልድ የሆነ ሁሉ በግድ ማንበብ ያለበት መፅሀፍ ሊኖር ነው። ፕሮፌሰሮቻችን ማንዳቶሪ ሪድንግ ይሉን ነበር። እነዚህም መፅሀፍት 1ኛ የጋሞው የብርብር ማሪያም መነኩሴ አባ ባህሬይ የፃፉትን "ዜናሁ ለጋላ። 2ኛ " የዶ/ር ስርግው ሀብለስላሴ " Medival Ethiopia " ። 3ኛ የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት "Church and state " ።4ኛ የፕሮፌሰር ሞርዶካይ አቢርን "Ethiopia and the red sea " የሚሉትን ።
..
ህብረተሰብ በግጭት ማሳ ላይ የበቀለ እንደሆነ ይታወቃል ። አሸናፊው ያጠፋል ተሸናፊው ይጠፋል። ከ2ሺህ አመታት በፊት በደቡብ የኖረው ኔቲቭ ጉራጌ የዛሬ 500 አመታት ከቤናድር የመጡትን የኦሮሞ ወረራ ተቋቁሟል ። ብዙ ኔቲቭ ህዝቦች ጠፍተዋል ። ለዚህም ነበር የአይን ምስክሩ አባ ባህሬይ "ጠፍአት ሀገርነ" ያሉት ። በተረፈ ዛሬም እንደበፊቱ ለህልውና የሚደረግ ትግል አለ ።አለበለዚያ ፎርሙላው ሳቅ አለም አብራህ ታለቅሳለች ። አልቅስ ብቻህን ታለቅሳለህ ነው።
@Veronica Melaku

Maxi
Member
Posts: 4843
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by Maxi » 09 Jun 2019, 19:22
በEBC "በጉራጌ የኦሮሞ ገዳ ስርዓት በድጋሚ ተቋቋመ" ተብሎ የተላለፈው ዘገባ በመቃወም ከጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ -ጉህን Gurage people's Movement-GPM


ጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ -ጉህንGurage people's Movement-GPM

ከ158 ዓመት በኃላ ተቋርጦ የነበረው የገዳ ስርዓት ስለማቋቋም በሚል በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬት(ኢቢሲ) በተላለፈው ዜና ላይ ከጉህን የተሰጠ መግለጫ

እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ የየራሱ የታሪክ የባህል እና የእሴት ቅርስ ባለቤት መሆኑ አያከራክርም፡፡በመሠረቱ የአንድ ማሕበረሰብ ታሪክ፣ ባህል እና እሴት እንዲሁም የአንድ ሀገር ታሪክ በአደባባይ ለመናገር ደፍሮ ከመነሳት አስቀድሞ በእጅጉ መዘጋጀትና መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የጉራጌን የባህል፣ የታሪክ፣ እና የእሴት ቅርሶችን ማናናቅ፣ ማጣጣል፣ ማራከስ እና በሌላ ማንነት ለመተካት መሯሯጥ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለውና ባለፉት ስርዓት ያበቃለት ጉዳይ ነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የባለብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ሀገር እንደመሆኗ መጠን በተለያዩ ቋንቋዎችና ባህሎች የበለጸገች መሆኗ ይመሰከርላታል፡፡ እነዚህ ብሔረሰቦች የማንነታቸው መለያ የሆነ ከየትኛውም ጋር ያልተደባለቀ የየራሳቸው ባህል፣ ታሪክ፣ እና እሴት እንዳላቸው ሁሉ ባህላዊ መተዳደሪያ ደንቦች እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ የጉራጌ ህዝብም እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ህዝቦች፣ እንደ ነባር ኢትዮጵያዊነቱ የራሱ የሆነ ባህል ያለው ህዝብ እንደመሆኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ እሳካለንበት ዘመንም ድረስ የዘለቀ አሁንም እየተገለገለበት ያለ የራሱ የሆነ ባህላዊ የመተዳደሪያ ደንቦች ያሉት ህዝብ ነው፡፡

የጉራጌ ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት የህዝቡን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ህይወቱን የሚመራበት የደንብ ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ የዳኝነት ስርዓት በማካሔድ የጉራጌ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጭምር ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ያለው የጉራጌ ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት መገለጫው በመብቶች መከበር፣ በስልጣን ሽግግር፣እና በሁሉም ማህበራዊ ጉዳዮች ውስጥ የሚገባ በእውነተኛ የፍትህ ስርዓት ላይ የተገነባ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ የነበረ እና ያለ የቤተ ጉራጌ ህገ-ደንብ ነው፡፡ በዚህ የጉራጌ ባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ውስጥ የተደነገጉ ህጎችና ደንቦች የሚያስፈጽሙ አባቶች የየራሳቸው የሆነ ባህላዊ ስያሜም ጭምር አላቸው፡፡

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በቀን 30/09/2011 የተካሄደው ዝግጅት የኦሮሞ እና የጉራጌ ሽማግሌዎች በጋራ በመሆን ሀገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት፣ የሁሉቱም ብሔሮች ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት ለማስተዋወቅ እና የልምድ ልውውጥ ከማድረግ አንፃር ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አይካድም፡፡ የኦሮሞ እና የጉራጌ ህዝብ ሀገርን ከጠላት ወረራ ከማዳን አንስቶ በጋብቻ እና በባህል የተሳሰረ ህዝብ እንደመሆኑ መጠን እንዲህ አይነት የጋራ መድረክ መዘጋጀቱ ከመደገፉም በተጨማሪ በሁለቱም ህዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ትስስር ለማጠናከርም ከፍተኛ ጥቅም ስላለው መበረታታት እንዳለበትም እንረዳለን፡፡

በቀጣይም ይህ ሂደት ቀጥሎ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት በማሳተፍ እና በማስፋፋት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ በማድረግ በማንነት ውስጥ ብቻ ከመታጠር ለሀገራዊ መግባባት፣ እኩልነትና አንድነት በጋራ ልንታገል እንደሚገባ እናምናለን፡፡

በዚህም መሠረት የጉራጌን ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት በኦሮሚያ አና በሌሎች ከተሞች በመመስረት የጉራጌን ታሪካዊ ባህላዊ መተዳደሪያ ደንብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በማድረስ ላይ የጉራጌ ሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በጋራ መስራት እንደሚገባን እያሳሰብን ዞኑ በዚህ ጉዳይ ለሚንቀሳቀሱ የጉራጌ ተወላጆች ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ግዴታ እንዳለበት ጭምር ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ሆኖም ግን ጉዳዩን ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር የባህል ወረራ በሚመስል መልኩ ታሪክን ቆርጦ ይዞ መጽሐፍም ይሁን መረጃውን ከታማኝ እና ከገለልተኛ ምንጭ ሳያጣሩ መረጃ መስጠት እና ለክርክር ማቅረብ በህዝቦች መካከል ያለውን መተሳሰብ እና መተቃቀፍ የሚሽር እንደመሆኑ በየትኛውም መልኩ ተቀባይነት ስለማይኖረው በመንግስት ደረጃ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ክትትል ሊደረግበት ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬት ከ158 ዓመት በፊት ተቋርጦ የነበረውን የገዳ ስርዓት በወልቂጤ ከተማ በድጋሚ ተቋቋመ በሚል ያሰራጨው ዜና ፈፅሞ ታሪካዊ እውነታም ማስረጃም የሌለው ተራ አሉባልታ ከመሆኑም በላይ የጉራጌን ባህላዊ አስተዳደር እንደሌለ ለማድረግና የህዝቦችን ትስስር ለመሻር የተደረገ የተወሰኑ ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች አካሄድ በመሆኑ የመንግስት ሚዲያ እንደመሆኑ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ያስተላለፈው ዜና በማስተካከል በድጋሚ መዘገብ እንደሚገባው በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

የጉራጌ ዞን አስተዳደር እና የዞኑ የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ የጉራጌን ታሪክ፣ ባህልና እሴት ከመጠበቅ እና ለትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግ ኃላፊነት አንፃር ህዝባዊ አካታችነቱ እስከምን ድረስ እንደነበረ፣ እና በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ምሁራን፣ አባቶች፣ እና ወጣቶች ጋር አስቀድሞ በጉዳዩ ላይ ምን ያህል ምክክር እንደተደረገበት በአፋጣኝ በይፋ ለህዝብ ማብራሪያ እንድትሰጡበት እንጠይቃለን፡፡
ዝግጅቱን በተመለከተ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ እና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት በሚል በገጻችሁ ያስተላለፋችሁት መልዕክትና እና በተዘገበው ዜና መካከል ያለው ልዩነት በቂ ማብራሪያ በመስጠት ለህዝብ እንድታሳውቁ እንጠይቃለን፡፡

ለመላው ኢትዮጵያውያን ባለፉት ታሪኮቻችን የጠላናቸው እና የእኔነት ስሜት ብቻ የተንጸባረቀባቸው ያሳዘኑን ክስተቶች እና ጠባሳዎች ልናክማቸው ሲገባ ዛሬ በተራችን እኛ ልንደግማቸው እና በሌሎች ላይ ተጨማሪ ጠባሳ ፈጥረን ለልጅ ልጆቻችን ልናቆይ አይገባም፡፡አንድ በሚያደርጉን፣በሚያከባብሩን እና ሊያግባቡን በሚችሉ የታሪክ መዝገቦች ላይ ተንተርሰን ሀገር ከመገንባት ይልቅ በሚያለያዩን እና በሚከፋፍሉን ሴራዎች ተጠምደን ይችን ሀገር የብጥብጥ ቀጠና ለማድረግ የምንቀሳቀስ ኃይሎች ከድርጊታችን ልንቆጠብ እንደሚገባ አበክረን እንገልጻለን፡፡

ታሪካዊ ትስስር እና መስተጋብር ባላቸው በኦሮሞ እና በጉራጌ ህዝብ መካከል የተፈጸመው አይነት አሳፋሪ ድርጊት ለመፈጸም እጃቸውን ከተው የሚንቀሳቀሱ እና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አመራሮች፣ ሚዲያዎች እና አክትቪስቶች መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ በመሆን ሊጋፈጣቸው እንደሚገባ እና አንድነቱን ይበልጥ ማጠንከር እንደሚገባው ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ (ጉህን)


Please wait, video is loading...

info
Member
Posts: 3422
Joined: 05 Dec 2014, 11:33

Re: አባ ገዳ፣ ታሪክህን አከብራለሁ ታሪኬንም አክብር:: [አርቲስት መላኩ ቢረዳ]

Post by info » 11 Jun 2019, 12:18

Many Gurages are unhappy with the EBC Gedda misleading news.


Post Reply