Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 20567
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት?

Post by Revelations » 12 May 2019, 12:40

ጥምረት ነው እንጂ ውህደት አይደለም ::

ሁለት ዋና ነጥቦችን እንመልከት :-

የከሰሙት ሁለት ፓርቲዎች ብቻ ናቸው ሰማያዊና ግንቦት ሰባት :: ሌላው መሪ ምክትል መሪና ሊቀ መንበር ምክትል ሊቀ መንበር የሚለው ጥሩ ምልከታ ይሰጣል::

በነግርራችን ላይ ኢትዮጵያን ሪቪው የተሳሳተ መረጃ በዋና ገፁ ላይ አስቀምጧል:: አውቆ ነው ተሳስቶ ::ፍርዱን ለናንተ ትተናል!|

Please wait, video is loading...


Horus
Senior Member
Posts: 13097
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት?

Post by Horus » 12 May 2019, 14:16

አንጎሉ የከሰመ ረቨሌሽን !!! አሁን ማን ዪሙት ማን ነው የከሰመው???


Revelations
Senior Member+
Posts: 20567
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት?

Post by Revelations » 12 May 2019, 15:40

Horus wrote:
12 May 2019, 14:16
አሁን ማን ዪሙት ማን ነው የከሰመው???
Your boss, that's who!


Abe Abraham
Member+
Posts: 6545
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት?

Post by Abe Abraham » 12 May 2019, 16:31

ከሰመ

ቅርፊት ያዘ ሻረ ዳነ ፤ ጠፋ ጠቈረ ፤ የኩፍኝ የፈንጣጣ የጕድፍ የቂጥኝ የዕካል (ተገብሮ)።

የሞተ ሰው ወዘናው ደም ግባቱ ጠፋ መልኩ ከሰመ መጠጠ።

የደነገጠ በበረኻ በፀሓይ ላይ የሚ ሔድ ሰው ፊቱ ከሰመ ወይንም በማዲያት ከሰለ ጠቈረ።

withered, faded, dried, became sun burnt

shrunken (injury),dried up, lost color (plant),became suntanned

Revelations
Senior Member+
Posts: 20567
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት?

Post by Revelations » 12 May 2019, 17:33

Abe Abraham wrote:
12 May 2019, 16:31
ከሰመ

ቅርፊት ያዘ ሻረ ዳነ ፤ ጠፋ ጠቈረ ፤ የኩፍኝ የፈንጣጣ የጕድፍ የቂጥኝ የዕካል (ተገብሮ)።

የሞተ ሰው ወዘናው ደም ግባቱ ጠፋ መልኩ ከሰመ መጠጠ።

የደነገጠ በበረኻ በፀሓይ ላይ የሚ ሔድ ሰው ፊቱ ከሰመ ወይንም በማዲያት ከሰለ ጠቈረ።

withered, faded, dried, became sun burnt

shrunken (injury),dried up, lost color (plant),became suntanned

Revelations
Senior Member+
Posts: 20567
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት?

Post by Revelations » 13 May 2019, 09:07
ኢዜማ ውህደት ወይንስ ጥምረት? | በማዕረግ ጌታቸው

አንጋፋው የኢህአፓ ሰው ክፍሉ ታደሰ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በየአስራ አራት ዓመቱ የሚነሳ ልክፍት ተጠናውቷታል ይላሉ፡፡ በዚች ሀገር በየ14 ዓመቱ ቀልብን የሚስብ የፖለቲካ ጉዳይ አይጠፋም፡፡ 1953 የመፍንቀለ መንግስት ሙከራ ተካሄደ ፡፡ ከ14 ዓመት በኋላ ንጉሱ ወረዱ ፡፡ 1967 ዓ.ም ስልጣነ መንበሩን የተረከበው ደርግም ከዚህ መጥፎ ዕድል አላመለጠም፡፡ አስራ አራት ዓመት ቆይቶ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገበት፡፡ የኢህአዴግም ዕጣ ፋንታ ተመሳሳይ ነው ፡፡በ1983 ዓ.ም አራት ኪሎ የገባው ህወሓት መራሹ ኃይል በ1997 በዘመን ሱናሚ ተመታ፡፡ የአስራ አራት ዓመት አዙሪታችን ዘጠና ሰባትን ተሰናብቶ 2011 ደጃፍ ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘመኑን ጠብቆ አዳዲስ ዕውነታዎችን እየተጋፈጠ ነው፡፡ ሀገራዊ ቀውሱን ወደ ጎን ትተን ሰሞነኛውን የኢዜማ ምስረታ እንደ አንድ የታሪክ አጋጣሚ እንመለክተው፡፡ የዛሬውን አዲስ ፓርቲ (ኢዜማ )የመሰረቱት አብዛኞቹ ግለሰቦች ከአስራ አራት አመት በፊት ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን የመሰረቱ ናቸው ፡፡ ግን ጉዟቸው እንደ ጅምራቸው አልሰመረም ፡፡ ተቃቅፈው በተሳፈሩበት የፖለቲካ ባቡር ጉዞቸው እየረዘመ ሲሄድ ተቃቃሩ ፡፡ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፤ ልደቱ አያሌውን አታሳዩኝ ማለት ወደዱ ፡፡ ልደቱ አያሌው ኢ/ር ኃይሉን በየመድረክ ይዘልፍ ያዘ ፡፡ቅንጅትን ቅንጅት ያደረጉት ሁለቱ አዕማድ መኢአድና ኢዴፓ በመሪዎቻቸው ጸብ ጎራ ለይተው ተተራመሱ ፡፡

ገና በምስረታው ማግስት የረባ ደጋፊን ሳይዝ ቅንጅትን የተቀላቀለው የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ቀስተ ደመና ፓርቲ እንዲህ ያለው ፀብ የሚጎዳው አልነበረም ፡፡የኢዴፓ ደጋፊዎች በቅንጅቱ ውስጥ ያለ ስልጣን ለመኢአድ ከሚሰጥ ለቀስተ ደመና ቢሰጥ ይሻላል እያሉ እጅ ማውጣ አዘወተሩ ፡፡ መኢአድም ተመሳሳይ ተግባርን በኢዴፓ ላይ መፈፀም ወደደ ፡፡ በዚህ መቀናቀንም ቅንጅትን ከተቀላቀለች ወር እንኳን ያልሞላት የቀስተደመናዋ ብርቱካን ሚደቅስ የቅንጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች ፡፡ ብርሃኑ ነጋም (ፕ/ር) ቅንጅት በምርጫ አሸነፈበት የተባለውን ትልቅ ስልጣን የአዲስ አበባ ከንቲባነት እንዲይዝ ተወሰነ ፡፡

የመኢአድና ኢዴፓ ትርምስ በእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል መርህ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ቀስተደመናን ቢጠቅመውም ቅንጅቱን ግን ለማጥፋት እየተንደረደረ ነበር ፡፡ የተፈራው ሆነ ፡፡ ኢዴፓ ቅንጅቱ የሚወስናቸውን ውሳኔዎች አልቀበልም ማለት ጀመረ ፡፡ በቅንጅት ውስጥ በርካታ ደጋፊ ያለው ድርጅት ኢዴፓ ቢሆንም ስልጣኑን የያዙት ግን ትናንት የመጡ ወገኖች ናቸው የሚለው ሀሳብ ውስጥ ለውስጥ ተቀጣጠለ ፡፡

የመኢአድ ሰዎችም ከዚህ ቁዘማ አላመለጡም ፡፡ለአመታት የታገልነው እኛ ስልጣን የያዘው ትናንት የተመሰረተ ፓርቲ አሉ ፡፡ በጊዜ ሂደት ኢዴፓ የራሱን ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ ከቅንጅቱ ጋር በዚህ መንገድ መቀጠል አይቻልም አለ ፡፡ በመንፈስ ተዋህደናል ያሉት ፖለቲከኞች በየጋዜጣው መሰዳደብ ያዙ ፡፡ ልደቱ ቅንጅቱን አፈረሰው እየተባለ መወራት ጀመረ ፡፡ ህልም የመሰለው ቅንጅት እንደ ቴዎድሮስ መድፍ አንዴ ተኩሶ ዝም አለ ፡፡ በእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ትግል ፈራረሰ ፡፡ አባላቱም ተበታተኑ ፡፡

ዛሬ የዛ ዘመን ፖለቲካ ተወንያን ዳግም ተጣምረዋል ፡፡ቀስተደመና ይዞ ቅንጅቱ ውስጥ የነበረው ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)ኢዜማን ሊመራ ከፊት ሲሰየም የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራር የነበረው አንዷለም አራጌ ምክትል ሆኖ ተሾሟል ፡፡ ኢዜማ የቅንጅት ውርስ ነው ቢባል ስህተት አይመስልም ፡፡ ይሁንና አዲሱ ፓርቲ እንደ ቅንጅት የአራት ድርጅቶች ጥመረት ሳይሆን ውሀደት የፈጠረው ነው ፡፡ ይህ ውሀደት ግን የራሱ መሰረት ያለው ሳይሆን በተሰራ አለት ላይ የኖረ ነው ፡፡ ኢዜማ ውስጥ የተዋህዱ ፓርቲዎች ይብዛም ይነስም የራሳቸው ተከታይ የነበራቸው ናቸው ፡፡ ይህ ደግሞ የትናንት ብቻ ሳይሆን የነገም ታሪካቸው አካል መሆኑ አያከራክርም ፡፡

ሰመያዊ ፓርቲም ሆነ ግንቦት ሰባት ከሰመው ህበረ ብሄራዊ ፓርቲን ቢመሰርቱም ተከታዮቻቸው ግን ኢዜማን የሚደግፉት የእኔን ድምፅ የሚያስማ ግለሰብ አለበት ብለው ሲለሚያምኑ ብቻ ነው ፡፡ እንዲህ ያለው የደጋፊዎች ፍላጎት ታዲያ በኢዜማ አመራሮችም ላይ መስተዋሉ የሚቀር አይመስልም ፡፡ትናንት የተካሄደው የአዲሱ ፓርቲ አመራር ምረጫም ለዚህ ማሰረጃ የሚሆን ነው ፡፡ ኢዜማ ጥምረት አልያም ግንባር ይመስል የአመራር ቦታዎቹን ያደለው ግለሰቦች የመጡበትን ፓርቲ መሰረት አድርጎ ነው ፡፡

ብርሃኑ ነጋ ከግንቦት ሰባት ፣አንዷለም አራጌ ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ ፣ አቶ የሽዋስ ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲሁም ዶ/ር ጫኔ ከኢዴፓ የአዲሱ ፓርቲ አመራር ሆነዋል ፡፡ይህ ደግሞ ከስመዋል የተባሉት ፓርቲዎች መፍረሳቸው የይስሙላ ነው እንዴ? ያስብለናል ፡፡ ኢዜማም በዲፋክቶ ደረጃ ወህድ ፓርቲ አይደለም እንድንል ያስገድደናል ፡፡ ትናንት የተመሰረተው ፓርቲ በውስጠ ታዋቂነት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን መያዙ ብቻውን ችግር አይደለም ፡፡ችግሩ የቅንጅት መንፈስ ወራሾች ከትናንት ውደቀታቸው ያልተማሩ አንደሆነ ነው ፡፡

እነዚህ አመራሮች በኢዜማ ውስጥ ስልጣን ያገኙት የሰማያዊ፣ የግንቦት ሰባት፣አልያም የኢዴፓ መሪ ሆነው በመኖራቸው መሆኑ ባያከራክርም ከዚህ በኋላ እሱን እያሰቡ ከሄዱ ግን መዳረሻቸው ከቅንጅት አይለይም ፡፡ ስለዚህም ውህድ ፓርቲ ነኝ የሚለው ኢዜማ ውሀደቱን የሃሳብና የተግባር ሊያደርገው ይገባል ፡፡ የሀሳብ ውህደት የዜጋ ፖለቲካን ስላራመድክ ብቻ የሚመጣ አይደለም ፡፡ የቅንጅቱ አባላት ሁሉም የዜጋ ፖቲከኛ ነበሩ ፡፡ የሀሳብና ተግባር ውህደት ፖለቲካዊም አሰተዳደራዊም መሆን አለበት ፡፡ ቅንጅት ውስጥ ያሉ አመራሮች በምርጫው ዕጩ መሆን ያለበት ሰው እገሌ ነው፣ እገሌ የሚል ተራ ጉዳይ እንኳን የማያግባባቸው ሆነው ነበር ፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) “የነፃነት ጎህ ሲቀድ” በተሰኘ መፅሀፋቸው ልደቱ አያሌው የራሱ ሰዎች በምርጫው በብዛት ዕጩ እንዲሆኑለት በማሰብ አስረኛ ክፍል ያልጨረሱትን ሁሉ ማስተርስ አላቸው እያለ ያስመዘግብ ነበር ይሉናል ፡፡ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የያዛቸው ግለሰቦች የፖለቲካ ብቃት ባያከራክርም በጥቃቅን ጉዳዮች እንኳ መግባባት የተሳነው ነበር ፡፡ልደቱ አያሌው “መድሎት” ላይ እንደጻፉት ቅንጅት ስሙን ይግነን እንጅ ውስጡ ባዶ፣ ቅርፁ ሰንኮፍ ነው ፡፡የዛሬው የቅንጅት የመንፈስ ልጅ ከዚህ የውደቀት ታሪክ የመማር ተነሳሽነት ሊኖረው ይገባል ፡፡

መሪዎቹም ግለሰባዊ ኢጎቸውን አሰወግደው ህዝባዊ አደራን የሚወጡ መሆን አለባቸው ፡፡ ትናንት ቅንጅት ውስጥ የተፈጠረውን መጓተት ልብ ብለው ተቋማዊ አሰራርን ጊዜ ሳይሰጡ ማስፈን ይኖርባቸዋል ፡፡ ከልማዳዊ የፖለቲካ ሀቲት ተላቀው የድህር እውናዊ የፖለቲካ ፍኖትን ማጤን ግድ ይላቸዋል ፡፡ ያ ካልሆነ ግን ከድርጅት ድርጅት እየተሸጋገሩ ከዚህ ዘመን ደጃፍ የደረሱት ፖለቲከኞቻችን ነገም ሌላ ፓርቲ ሲመሰርቱ አናገኛቸው ይሆናል ፡፡

Post Reply