Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Ivanka Trump: I know why Ethiopia is a poor country

Post by Thomas H » 19 Apr 2019, 09:59

ከሌሎች ማህበረሰቦች አንፃር አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጊዜውን የሚያሳልፈው አልባሌ ቦታ ነው፡፡ ክርስትና የመጣው ከእስራኤል ነው፡፡ ነገር ግን የእስራኤል ህዝብ አንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ጴንጤና ኦርቶዶክስ በሚል ተከፋፍሎ አገር እየበጠበጠ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ኦርቶዶክስና ጴንጤ በክርስትና ስም ተደራጅቶ አገር እያመሰ ነው፡፡ እስልምናን የተቀበልነው ከሳአኡዲ አረቢያ ነው፡፡ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ የመጅሊስ ጥያቄ የለም፡፡ ቢያንስ ሀባሽና ውሀቢያ በሚል ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ሰላም አልተበጠበጠም፡፡ ከእነሱ በላይ በእስልምና ስም አገር እየታመሰ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ አርሶ አደር ህይወቱን የሚገፋው መሬትን በመርፌ ማረሻ እየጫረ ነው፡፡ የአሜሪካና የአውሮፓ ገበሪዎች የማህበረሰባቸውን 15 በመቶ የሚሸፍኑ ቢሆኑም ህይወታቸውን የሚገፉት በትራክተር እያረሱ ነው፡፡ መቀሌን ጨምሮ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ወጣቱ ጊዜውን የሚያሳልፈው የአውሮፓ ፕሪሜር ሊግ በመከታተል ነው፡፡ የአውሮፓና አሜሪካ ወጣት ጊዜውን የሚያሳልፈው በሳይንሳዊ ምርምር ላይ ነው፡፡ በእርግጠኝነት ኦክስፎርድና ሀርቫርድ ተማሪዎቻቸውን አንዴት አንዴት አንደሚያስተምሩ አውቃለሁ፡፡ አንተ ሙሉ ትኩረትህን ከምትሰጠው የቢዮንሴና የሌዲ ጋጋ ኮንሰርት ጀርባ ያለው የምዕራባውያን ወጣት ጊዜውን በሙሉ በሳይንሳዊ ጥናት ያሳለፈ ነው፡፡ አብዛኛው የምዕራባውያን ወጣት የቢዮንሴንና የሪሀናን ኮንሰርት ሲከታተል የምታየው ለመዝናናት ነው፡፡ ለእኛ ግን የቢዮንሴን ኮንሰርት የሙሉ ጊዜ ህይወታችን አካል ነው፡፡ ህዝባችን በፖለቲካ ተሳትፎም አይተነዋል፡፡ የተከበረው ህዝባችን ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣው የሊበራልዝምና የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር ልዩነት ገብቶት አይደለም፡፡ ህዝባችን ሰላማዊ ሰለፍ የሚወጣው በጥምቀትና በአረፋ በአል ስሜት ነው፡፡ በዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ የታዛብኩትን ብነግራችሁ የእኛ ህዝብና ይቺ ፕላኔት አልተገናኙም፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጊዜውን የሚያሳልፈው በአልባሌ ቦታ ነው፡፡ (ህዝብ ሲበላሽ ማየት በጣም አሳዛኝ ነው)

Source: Facebook

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Ivanka Trump: I know why Ethiopia is a poor country

Post by Sam Ebalalehu » 19 Apr 2019, 10:11

Just one correction. I read several years ago, the American farmers who are able to feed America and sell more to many countries in the world were five percent, not fifteen percent of the American population. Although I and you interpret the points you raised on some of the topics differently, I attest this is your best feedback that I read.

Post Reply