Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
derreview
Member
Posts: 94
Joined: 09 Feb 2013, 11:43

የአየር ሃይሉ ጀግና ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ስርዓተ ቀብር በዩጋንዳ በልዩ ክብር ተፈጸመ።

Post by derreview » 15 Apr 2019, 14:09

“የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች
የአፍሪካ ብርቅዬ ልጆች ናቸውና
ለአፍሪካ ያስፈልጓታል።”
የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ

የአየር ሃይሉ ጀግና ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ አጭር የህይወት ታሪክ!

የአየር ሃይሉ ጀግና ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ከአባታቸው ከመምሬ ካሳ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሂሩተ ስላሴ በሲዳሞ ክፍለ ሃገር አለታ ወንዶ ከተማ የካቲት 30 ቀን 1943 ዓ.ም ተወለዱ። በልጅነታቸውም በቤት ውስጥ የቤተክርስቲያን ትምህርት በመማር እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀዳማዊ ሃይለስላሴ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በራስ ደስታ ዳምጠው ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።

ዕድሜያቸው 17 ዓመት እንደደረሰም በሐረር ጦር አካዳሚ የመሰናዶ ትምህርት ቤት በመግባት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ1964 ዓ.ም አጠናቀዋል። በመቀጠልም የ16ኛ ኮርስ የሐረር አካዳሚን በመቀላቀል ለ3 አመታት የሚሰጠውን የመኮንንነት ኮርስ በ1967 ዓ.ም በክብር በማጠናቀቅ በም/መ/አ/ማ ተመርቀዋል። የሶስተኛ አመት የስኒየር ካዴት በነበሩበት ወቅት በታታሪነታቸው እና በጠንካራ የስነ ስርአት አክባሪነታቸው በአጠቃላይ የኮርሱ ኮማንዶ ሆነው ያገለገሉ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው ወጣት እጩ መኮንን ነበሩ።
በ1968 ዓ.ም በምድር ጦር የአየር ክፍል አርሚ አቪየሽን በመመደብ ወደ ኢትዮጵያ አየር ሃይል የበረራ ትምህርት ቤት በመላክ ፒ 17ኛው የበረራ ኮርስን በመቀላቀል ቀደም ሲል በሳልሳ ፋየር ቀጥሎም በሲሴና አውሮፕላኖች ላይ የሚሰጠውን የበረራ ስልጠና በከፍተኛ ችሎታ በማጠናቀቅ እስከ 1969 ዓ.ም ድረስ በምድር ጦር የአየር ክፍል ውስጥ በልዩ ልዩ አውሮፕላኖች ላይ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በመዘዋወር በብቃት አገልግሎታቸውን ፈፅመዋል።
በ1969 ዓ.ም በሶማሊያ የእብሪት ወረራ ወቅት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ኪልጊዚያ ግዛት ፍሮንዚ ቢሽኬክ ከተማ ተልከው በሚግ 8 ላይ በሚሰጠው የበረራ ስልጠና በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ወደ እናት ሃገራቸው ተመልሰው በተለያዩ ግንባሮች ከፍተኛ ግልጋሎትን ሰጥተዋል።
ጎዴን መልሶ ለመያዝ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ከጦሩ ጋር አንድ የቀበሮ ጉድጓድን በመጋራት ላሳዩት ጀግንነት የጦር ሜዳ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ሆነዋል። በመቀጠልም ወደ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድ ሮን በመዘዋወር በሚግ 24 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ላይ የሚሰጠውን የበረራ ትውውቅ ስልጠና በመውሰድ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት በመሄድ ስልጠናቸውን በሚገባ አጠናቀው ወደሃገራቸው ተመልሰዋል።
በሚግ 24 ተዋጊ ስኳድ ሮል ውስጥ በምስራቅም ሆነ በሰሜኑ የሃገራችን ግዛት እና አንድነትን ለማስከበር ከጠላት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ በማበርከት እስከ 1983 ዓ.ም ቆይተዋል። ህወሃት መራሹ ሃይል ሃገሪቷን እስከተቆጣጠረበት ጊዜ ድረስ ከሌሎች ጀግኖች የሰራዊቱ አባላት ጋር በመሆን በምስራቅ በወራሪው የዚያድባሬ ጦርና በሰሜን ከሻብያና ወያኔ ጋር በተደረጉት ፍልሚያዎች የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ልዕልና ለማስከበር በተደረገው ጦርነት ከፍተኛ ጀብዱ ፈፅመዋል።
ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ በግንባር ከፈፀሟቸው አኩሪ ገድሎች መካከል በወታደራዊው ስርዓት የመጨረሻው ቀናቶች ጀግናው አየር ሃይላችን ከፍተኛ ተጋድሎ ላይ በነበሩበት ወቅት አንደኛው የሚግ 23 በራሪ በአየር ላይ ከጠላት በተተኮሰ ፀረ አውሮፕላን ይመታና በጃንጥላ ከሚነደው አውሮፕላኑ ውስጥ ተስፈንጥሮ ይዘላል። የሚግ 23 አብራሪ በአደገኛ የጠላት ቀጠና ውስጥ መውደቁን የተረዳው ጀግናው ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ በከፍተኛ ወኔ እና ድፍረት በተዋጊ ሄሊኮፕተሩ እየተታኮሰ ወደ ምድር በመውረድ በተኩስ እየተናወጠ ካለው ቀጠና ውስጥ ባልደረባውን የሚግ 23 አውሮፕላን አብራሪን ከነህይወቱ ማንሳትና ማዳን የቻለ ወደር ያልተገኘለት ኢትዮጵያዊ ጀግና ነበር።
ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ህወሃት መራሹ ሃይል ደብረዘይትን በተቆጣጠረ እለት እዛው በአየር ሃይሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበረ ሲሆን ቀደም ብሎ የቅኝት በረራ በማከናወን የሁኔታዎችን በፍጥነት መቀያየር በሚገባ የተገነዘበና ራሱንም በመቀየር ለተወሰነ ጊዜ በሃገር ውስጥ በመቆየት የህወሃት አገዛዝ አየር ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ ሲያደርግ የደማላትን እናት ሃገሩን ለቆ በስደት ወደ ኬንያ ከዛም ወደ ኡጋንዳ ለመሰደድ የተገደደ ድንቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነበር።
በወቅቱ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ ለስደት የተዳረጉትን ምርጥ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባሎችን ‘’የአፍሪካ ብርቅዬ ልጆች ናቸውና ለአፍሪካ ያስፈልጓታል።’’ በማለት ከለላና ደህንነት በመስጠት እ.ኤ.አ 1994 የኡጋንዳን አየር ሃይል ሲያጠናክሩ ከተቀጠሩት አንዱ ኢትዮጵያዊው የሄሊኮፕተር ተዋጊ አብራሪ ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ሲሆኑ በተለይም በፕሬዝዳንቱ ዘንድ ተአማኒነት እና የሙያ አድናቆትን በማግኘታቸው በተለያዩ የሙያ ግዳጆች በብቃት በመሳተፍ እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ የተወጡ ሲሆን በኡጋንዳ መከላኪያ የጀግና ስርዓተ ቀብር እንዲፈፀምላቸውና ገድላቸውም በኡጋንዳ የመከላኪያ የጀግኖች ታሪክ መዝገብ ውስጥ ስማቸው በክብር እንዲቀመጥ የኡጋንዳ መንግስት ወስኗል።

በኡጋንዳ በስደት በቆዩበት ዘመንም ያሳድዳቸው የነበረው የህወሃት መራሹ ሃይል በተደጋጋሚ ተላልፈው እንዲሰጡት የ ኡጋንዳን መንግስት ሲወተውት እንደነበርና ጥያቄው ተቀባይነት በማጣቱ በሌሉበት ለፍርድ እንዲቀርቡ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።


ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ በቤተክርስትያን ምስረታ ላይ የነበራቸው አስተዋፅዎ!
ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ከዛሬ ሃያ አመት በፊት በብዙ ኢትዮጵያኖች ጥረት እና ብርቱ ድካም በተመሰረተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በዩጋንዳ ካምፓላ የመካነ ሰላም መድኃኒያለም ቤተክርስትያን የምስረታ ስራ ላይ ጉልህ ሚና ካበረከቱ ሰዎች መሃል አንዱ ነበሩ።
ኢትዮጵያውያን ወገኖች የማምለኪያ ቦታ እና መንፈሳቸውን የሚያድሱበት ቤተክርስትያን ባልነበራቸው በዛ አስጨናቂ ዘመን ላይ ከወ/ሮ ወርቅነሽ በልሁ ጋር በመነጋገር:-
‘’እኛ እዚህ ሃገር ያለን ስደተኞች ሃገራችንን ፣ ሃይማኖታችንን እና ባህላችንን ትተን በችግር ላይ እንገኛለን ... ስለዚህ ቤተክርስትያን መሰራት አለበት።’’ ብለው ቤተክርስቲያን እንዲሰራ ያነሳሱና ከፍተኛ አስተዋፅዎ ያደረጉ በግንባታው ሂደትም ላይም ከፍተኛ ተሳትፎ ያሳዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ ነበሩ። የቤተክርስትያኑ መንፈሳዊ አገልግሎት በተመጀመረበት ወቅትም አገልጋይ ካህናትን በኑሮዋቸው እንዳይቸገሩ ድጋፍ እና አስተዋፅዎ የሚያደርጉ በመሆናቸው ቤተክርስቲያናችን ሁልግዜም መልካም ስራቸውን ስትዘክር ትኖራለች ።
ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ68 አመታቸው ሚያዚያ ሰባት ቀን 2011 ዓ/ም በሃገረ ኡጋንዳ በናካሴሮ ሆስፒታል ህይወታቸው አልፏል። የጸሎተ ፍትሃት ስነስርዓት በካምፓላ መካነ ሠላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያ ዛሬ ጠዋት የተከናወነላቸው ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓታቸውም ላለፉት 26 አመታት ባገለገሏት ሃገረ ኡጋንዳ ሉዌሮ በሚገኘው ካፔካ ብሄራዊ ወታደራዊ የቀብር ስፍራ ሚያዚያ ሰባት ቀን 2011 ዓ/ም {April 15,2018}በከፍተኛ የዩጋንዳ አየር ሃይል እና የመከላከያ ባለስልጣናት በተገኙበት በልዩ ወታደራዊ ስነ ስርዓት የሃዘን ማርሽና ተኩስ ተፈጽሟል።
የእኚህን ጀግና ፣ ሃገር ወዳድና ባለታሪክ የሆኑ ክቡር ሰው ወዳጃችንን ሌተና ኮሎኔል ጌታሁንን በሞት በማጣታችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ነብሳቸውን በቅዳሳኑ በአብርሃም ፣ በይስሃቅ እና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን እያልን ለወዳጅና ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።
Last edited by derreview on 25 Apr 2019, 13:43, edited 3 times in total.

Axumawi
Member+
Posts: 6200
Joined: 28 Apr 2018, 00:31

Re: የአየር ሃይሉ ጀግና ሌተና ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ ስርዓተ ቀብር በዩጋንዳ በልዩ ክብር ተፈጸመ።

Post by Axumawi » 15 Apr 2019, 14:45

RIP
You folks politicize everything
You make even great men smaller. You push people to disrespect even the dead which is against our culture.

You go to extreme and make Hawzien victims speak and not forgive.
You could praise someone for his Technical ability, qualities of leadership..etc. He is dead. May god forgive his soul.

Post Reply