Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 1297
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

የመጨረሻ የኢህአዲግና የአብይ ተስፋ ብአዴንና ወያኔ ብቻ ናቸው:: እነዚህ ድርጅቶች ከኢህአዲግ ቢወጡ አብይ አከተመለት!! ኢህአዲግም ይሞታል;; ወያኔ ምናባቱ ነው የሚጠብቀው?

Post by Abaymado » 14 Apr 2019, 01:48ብአዴን ያለው የፌደራል ስልጣን ጥቅሙ የሚታይ አይደለም; እንደው ባጭሩ የሌላውን ፍላጎት ማሟያ ነው የሆነው:: የደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ጥቅሙ ምን ላይ እንደሆነ አይገባንም:: እና ብአዴን ኢህአዲግን ጥሎ መውጣት አለበት:: ቢቻል ከአብን ጋር ቢዋሃድ ጥሩ ነው:: ግን መዋሐዱ እንዲህ ቀላል አይሆንም:: ይህን ደካማ አቅዋሙን ይዞ ሳያተካክል ማንም የሚፈልገው አይመስለኝም:;
ወያኔም ኢህአዲግ ውስጥ ተዘፍዝፎ ምን እንደሚያገኝ አይታወቅም: በሂደት ወያኔን ለማግለልና አረናን ለማስገባት ሳይታሰብበት አይቀርም:: አካሄዱ ለወያኔ ጥሩ አይደለም:: እና ወያኔ ምን እየጠበቀ ነው?

ብአዴንና ወያኔ ኢህአዲግን ቢሰናበቱ: ደቡብም መፈረካከሱ አይቀርም:: በቃ ኢህአዲግ አከተመለት ማለት ነው:: ደቡብ ባይወጣም ኢህአዲግ በጣም የሞተ ድርጅት ይሆናል:: አብይ ይህንን ካየ ኢህአዲግን አፍርሶ አንድ ወጥ ፓርቲ ያረገዋል ;; ማንም አብይን የሚመርጥ የለም;; ምናልባት ከሶማሊ: ከአፋር ትንሽ ድምፅ ሊያገኝ ይችላል;;ከኦሮምያም ማግኘቱ አይቀርም:: እናም የአብይ ተስፋ የጨለመ ይመስላል;; ኦሮምያ ክልል የሚደረገው ሽኩቻ ራሱ የሚስብ ነው የሚሆነው;; አብይ በኦሮምያ ቢያሸንፍ እንኳን እርስ በርሳቸው መሻኮታቸው አይቀርም:: አብይም ቢሸነፍ ስልጣን መልቀቁን ራሱ እንጠራጠራለን::

ወያኔ ወጥቶ ከሌላ ፓርቲዎች ጋር አንድነት ሊመሰርት ይችላል; ግን ኦነግ እሺ የሚለው አይመስለኝም:: እና ከማን ጋር እንደሚዋሃድ አናቅም;;

ግምቦት ሰባት ደሞ በጉራጌ: በናዝሬት; በአዲስ አበባ : በሌሎች ዋና ከተሞች በሙሉ እና በትንሽም ድምፅ ማግኘቱ አይቀርም::

አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ለማሸነፍ እስክንድር ራሱን ወደ ፓርቲ ቢቀይር ጥሩ ነው:: አዲስ አበባ በአብን ; በግምቦት ሰባትና በኢህአዲግ ትቀፋፈላለች;;

Abaymado
Member
Posts: 1297
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: የመጨረሻ የኢህአዲግና የአብይ ተስፋ ብአዴንና ወያኔ ብቻ ናቸው:: እነዚህ ድርጅቶች ከኢህአዲግ ቢወጡ አብይ አከተመለት!! ኢህአዲግም ይሞታል;; ወያኔ ምናባቱ ነው የሚጠብቀው?

Post by Abaymado » 14 Apr 2019, 07:53

ወያኔ የኢህአዲግ አስቸክዋይ ስብሰባ ጠርቷል:: ምናልባትም ስለአብይ የከሸፈ አስተዳደር ሳይሆን አይቀርም:: ይህ ወያኔ ከኢህአዲግ ጋር የምትቆይበት ዕድል ሳይሆን አይቀርም::

Post Reply