Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 1399
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Surprise: veronika melaku በሕይወት አለች ተብሏል! አካውንቷ ተዘግቷል:: veronica ማለት ደምስ በለጠ ሳትሆን Hailu Bitania ናት!

Post by Abaymado » 08 Feb 2019, 12:10

(በቅድሚያ ግን ለሁሉም የአማራ አክቲቪስቶች ራሳችሁን ጠብቁ: ተጠንቀቁ)
የ veronika መጥፋት ብዞችን አሳዝኗል: እረፍት ነስቷል::
እኔ ከዚህ በፊት በምንም ይሁን በምን አካውቷ ይከፈታል ብያለሁ:: still ብዙዎች veronika ደምስ ናት ብለው ያምናሉ: እናም ሆን ተብሎ የተሰራ ታክቲክ እንደሆነ ያስባሉ:: ግን ብዙ ነገሮች hailu bitania እና veronikan የሚያመሳስላቸው ነገር አለ::


https://www.facebook.com/hailu.bitanya

1) hailu ለሶስት ዓመት ከጠፋ በኃላ በዚህ ፈረንጆች ዓመት ነው ብቅ ያለው::

እንዲህ ብሏል:
እንደምን ከረማችሁ ? አቤት ጊዜዉ ሲነጉድ ? ! የፌስቡክ የቀን መቁጠሪያ የመጨረሻዉን ጽሁፌን በ2016 እንደጻፍኩ ይነግረኛል ፡፡ ዛሬ 2019 ነዉ ፡፡ ሶስት ድፍን አመት ማለት ነዉ ፡፡ይሄን አመታት ሁሉ የት ነበርኩ ? እዚሁ ነበርኩ ፡፡
ወያኔ በአፍጢሟ ስትደፋ እዚሁ አጠገቧ ነበርኩኝ፡፡ ጌታቸዉ አሰፋ ሲፈረጥጥ ፣ክንፈ ዳኘዉ በሰንሰለት ሲጠፈነግ፣ በረከት ስምኦን አራት በአራት በሆነች ክፍል ሲከረቸምበት ነበርኩኝ፡፡

2) ሁለተኛ የ veronika አካውንት ሊዘጋም እንደሚችል መጠርጠር ይቻላል::
እንዲህ ብሏል: -


ዛሬ ቤቴ ቁጭ ባልኩበት ሰአት አካውንቴ እንደተዘጋ የሚናገር ዜና በ You Tube ዜና ማሰራጫ ሰማሁኝ። ዜናው
ሀሰት ነው ። የጠፋሁት ተዘግቶብኝ ሳይሆን ከአሁን በኋላ አካውንቴን ስትራቴጅክሊ ከነጣቂወች ለመጠበቅ የወሰድኩት እርምጃ ነዉ ።
እኔ ሀይሉ ቢታኒያ አስደናቂዋን ቬሮኒካ መላኩን ፈጥሬ 1 አመት እንኳን ሳልፅፍባት 14 ጊዜ አዘግተው በ15ኛው ቬሮዬን ወያኔ ከተባለ ተንከባሎ ከወደቀ ግዙፍ ዓለት ጋር ተጋጭታ እንደ ታይታኒክ ተሰባበረች፡፡ ምቀኛ ትውልድ !!
3) ብዙዎች hailu veronika ነው ብለው ጥንትም መገመታቸው ነው::
4) በአሁኑ ሰዓት ማንነትን ደብቆ ፌስ ቡክ ላይ መቀጠሉ ከባድ ነው:: ፈስቡክ “ስለራሳችሁ መረጃ ካልሰጣችሁኝ አካውንታችሁን እዘጋለሁ” ማለት ጀምሯል::
5) ራሱ hailu እኔ veronika ነኝ ብሏል::

አሁን ጊዜዉ ደረሰ መሰለኝ። የህዝቡም ጥያቄ እየጨመረ ስለመጣ ይሄን አወዛጋቢ ጉዳይ ልቋጨው።
ባለፉት ሁለት አመታት ቬሮኒካ መላኩ የሚለው የብእር ስም የሳይበሩን አለም ተቆጣጥሮ ነበር ። ቬሮ በአካውንቷ ከ150,000 በላይ ተከታይ ለማፍራት 1 አመት ብቻ ነበር የፈጀባት ። የቬሮኒካ ብእር ምትሀታዊ እንደሆነ የታወቀ ነበር ። ጠ/ሚ አይኑን የሚገልጸው በቬሮ ፅሁፍ ነበር ። ቬሮ በሳይበሩ አለም ተአምር ፈጥራ በተቀናጀ ሴራ እንድትከስም ተደርጋለች። በቬሮኒካ መላኩ ስም ካፍቴሪያ : ፋርማሲና ሱቅና ሆቴል ተሰይሞ ነበር ። የቬሮ አካውን በተቀናጀ የወያኔ ኦፕሬሽን ባይዘጋ ኖሮ ወዳጆቿ ሀውልት ያቆሙላት ነበር ።
በመሰረቱ የብእር ስሞች በአለም አቀፍ ህግ የተከበሩና በሚስጥርም የሚጠበቁ መሆናቸው የታወቀ ነው ።
ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን : ጆሴፍ ስታሊን : ጆርጅ ኦርዌል የብእር ስሞች ናቸው ። በሂደት ግን ዋነኛ ስም ሆነው ቀርተዋል ።
በመሰረቱ ዛሬ 1 ሰው ( ወንድሜ አያሌው መንበር ) ብቻ የሚያዉቀውን ጥብቅ ሚስጥር ለማውጣት የተገደድኩት እስከ ዛሬም ድረስ" ቬሮኒካ መላኩ ሞታለች" የሚለውን ዜና አምነው በሀዘን እየቆሰሉ ያሉ ወዳጆቼ እጅጉን ልቤን ስለነካው ብቻ ነው ። አያሌው መንበር ቬሮን ከፈጠርኩበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የሚያውቅ ብቸኛ ሚስጥረኛዬ ነበር።
በመጨረሻ ቬሮኒካ መላኩ ሀይሉ ቢታኒያ ነበረች።
.
ምስክሮች
1ኛ-አዩ (አያሌው መንበር)
2ኛ-ዳዊት ሰለሞን (Code ውቅያኖስ)
3ኛ- መሳፍንት ታምራት (ቤተ አማራ)


6) በሚገርም ሁኔታ veronika ጋር የሚመሳሰል ፅሁፍ ለቅዋል:: ጃዋርንና እስክንድርን የምያነፃፅር (ከስር ለጥፈዋለሁ )

መነበብ ያለበት !
Hailu Bitanya
6 February at 17:45 •
አንድ
.
ጋሼ አሰፋ ጫቦ መሬቱን ገለባ ያድርግለትና በአንድ ወቅት “እናቴን አንዴ እንዲህ ብዬ ጠየኳት፡፡ የሆነ ነገር ስናገር ሰው ሁሉ ይቀየመኛል፡፡ ለምን ይመስልሻል? ብዬ ብጠይቃት፤”
“ክፍት አፍ ስለሆንክ ነዋ” - አለችኝ ›› ብሎ ተናግሮ ሲያስገርመን ነበር ፡፡
.
ጋሼ አሴ አንደበቱ የታረመ ምሁር መሆኑን አዉቃለሁ ፡፡ ይች አባባሉ ግን ዛሬ ትዝ አለችኝ፡፡ ጃዋር ተናገረ ነዉ ጻፈ የሚል ዜና አይቼ ነዉ፡፡ የጃዋርን ክፍት አፍነትና ያለአቅሙ መንፈራገጥ ስሰማ የጋሼ አሴ ንግግር ትዝ አለኝ ፡፡ የጃዋር ችግር ‹‹ የአትርሱኝ ›› ልመና ችግር ነዉ ፡፡ ፈረንጆቹ ይሄን ጉዳይ ሳይንሳዊ ስም አዉጥተዉለት fear of being forgotten ወይም ‹‹ Athazagoraphobia >> በማለት ይጠሩታል፡፡
..
ሁለት
.
ይሄ ፈረንጆቹ ‹‹ ሰዎች ሊረሱኝ ነዉ የሚል ፍራቻ›› fear of being forgotten ወይም ‹‹ Athazagoraphobia >> የሚባለዉን ነገር ከጃዋር ጋር በማገናኘት አጠር አድርጌ ላስረዳ፡፡ ጃ WAR ወደ አገር ቤት እንደ ገባ እንደ ተጎዘጎዘ ትኩስ ቄጠማ ነበር፡፡ እየቆየ እየተረሳ የጃዋር ቄጠማ ደረቀች። እርጥብ ቄጠማ የነበረው፤ ጃዋር እየተረሳ በእግረ ህሊና ብዙ ተረጋግጦ፣ የትዝታ ትርፍራፊ ተበታትኖበት፣ የትውስታ ቅራሬ ተደፍቶበት፤ እንደ ተረጋገጠ ሣር ሆኖ አረፈዉ፡፡ ጃዋርን ዛሬ የተጋጠ አጥንት ማለት ነዉ፡፡ የተጋጠን አጥንት እንኳን ሰዉ ዉሻ አይፈልገዉም ፡፡ ጃዋር ከዚህ የመረሳት በሽታ ለመዉጣት የግድ አጀንዳ ማቅረብ ነበረበት ፡፡
..
ሶስት
.
እስክንድር ነጋንና ጃዋርን ማነጻጸር ሀጢያት መስሎ ይሰማኛል ፡፡ ገና እዚህ ፌስቡክ ላይ የእስክንድርንና የጃዋርን ስም ጎን ለጎን መጻፌ ትልቅ ጥፋት መስሎ ስለሚሰማኝ ኪይ ቦርድ የጠቀጠቁበትን እጄን እንደ ጲላጦስ ሙልጭ አድርጌ እታጠባለሁኝ፡፡ እስክንድር ከመሀተመ ጋንዲና ከኔልሰን ማንዴላ የሚወዳደር ጀግና ነዉ፡፡ እስክንድር መአከላዊ በአሰቃቂ Solitary Confinement ስንት አመት ቆይቶ እስር ቤቱን እንደ እረፍት ስፍራ ይቆጥረው የነበረ ጀግና ነዉ ፡፡ ለእስክንድር ለህዝብ ነጻነት እስር ቤት መግባት ለርሱ ተደደጋጋሚ የህይወት ጎዳና ነበር፡፡ ጃዋርን በእስክንድር ቦታ አንድ ቀን ብታቆዩት ሱሪዉ ተበላሽቶ ዲሀይድሬት አድርጎ ይሞታል፡፡
..
በመጨረሻ
.
ለሜንጫዉ መንጋ የማስተላልፈዉ ጉዳይ አለኝ፡፡የበረራ ጉዳይ የህልዉና ጉዳይ ነዉ፡፡በሕልውና ላይ የተቃጣን ጥቃት በሞራል ሆነ በሕግ መዳኘት አይቻልም። ምክንያቱም፣ ሕልውናን ማጣት በየትኛውም ደንብ ሊጣል ከሚችለው ቅጣት ይበልጣል። Necessity has no law’. And yet there cannot be a necessity that could make what is wrong lawful.” The Science of Right, tran. W. Hastie CH1, Page 6 ፡፡
ህልዉናን ለመጠበቅ በመጣችሁበት መንገድ እንመጣለን ፡፡በረራን የብቻየ አደርጋለሁ ማለት ከእሳት ደመና፣ ውሃን መመኘት ነው፡፡
..
የሰማነዉን በልቡናችን ያሳድርብን
አሜን ፡፡

Abaymado
Member
Posts: 1399
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: Surprise: veronika melaku በሕይወት አለች ተብሏል! አካውንቷ ተዘግቷል:: veronica ማለት ደምስ በለጠ ሳትሆን Hailu Bitania ናት!

Post by Abaymado » 09 Feb 2019, 13:18


ቬሮኒካ hailu bitania አይደለም ይላል ሳተናው ላይ የሰፈረው:: ማስረጃ ያቀረበውም ተስፋዬ ገብረአብን ነው:: ቬሮንካ ተስፋዬን የምትወደው አይመስለኝም:: እናም የአይጥ ምስክሩ ድንብጥ እንደሚባለው መሆኑ ነው:: ከዚህ በታች የደምስን ፁሁፍ አያይዣለሁ :: እናም ቨሮንካና ደምስ የሚገናኙም አይመስልም::: ቨሮንቃ አንዴም ኤርትርውያን ስትዘልፍ ሰምቼ አላቅም: ግን ደምስ ዝርጥጥ ነው ያረጋቸው::
የሆኖ ሆኖ ቬሮንካ ባትኖርም አማራ ብዙ የተማሩ አክቲቪስቶች አሉት እናም ...
ግን ምነው አቃጠላቸው እነሱ?

ሳተናው እንዲህ ዘግቦ ነበር:


ቬሮኒካ መላኩን ሆኖ ለረጅም ጊዜያት ሲተውን የነበረው ሟቹ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ነበር
February 5, 2019
በሞቀ ምጣድ ለመጋገር የቋመጠው ሃይሉ ቢታንያ ቬሮኒካ አይደለም ።
ቬሮኒካ በሚል የፌስቡክ ስም ስለ አማራ ብሄርተኝነት ምክንያታዊና ሳቢ በሆነ መልኩ ስታስነብበን የኖረችው ቬሮኒካ መላኩን ሆኖ ለረጅም ጊዜያት ሲተውን የነበረው እውቁ ጋዜጠኛና ምሁር ደምስ በለጠ ነበር ። ይህን ሁኔታ የሚያውቁት ተስፋዬ ገ/አብን የመሳሰሉ ወዳጆቹም አቶ ደምስ ከማለፉ በፊት ሲናገሩት የቆየ ነገር ነው ።
እናም ቬሮኒካ መላኩ በሚል ስም ስናነበው የቆየነው ደምስ በለጠ ከረጅም አመት ስደት በኋላ ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ መጥቶ ብዙም ሳይቆይ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። ቬሮኒካ መላኩ ዳግም ላትመጣ ይህችን አለም ተሰናበተች ። ከዚያን እለት ጀምሮ እንደ ሃይሉ ቢታንያ አይነት የደምስ በለጠን ቬሮኒካ መሆን የሚያውቁ ሚስጥር አዋቂዎች ይህን የተለመደ ስም ለመውሰድ ሽሚያ ጀመሩ በመጨረሻም ዛሬ ሃይሉ ቬሮኒካ ማለት እኔ ነኝ ብሎ አይኑን በጨው ታጥቦ መጥቷል ። ነገርየው በሞቀ ምጣድ ላይ ለመጋገር መሆኑ ነው ። አትልፋ ፈፅሞ ቬሮኒካን ልትመስል አትችልም ።
በመጨረሻም በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ላለፈው ደምስ በለጠ ወይም በፌስቡክ ስሙ ቬሮኒካ መላኩ አምላክ ነብሱን እንዲያስባት እንመኛለን ። ሞቷል ብሎ የሰው ታሪክ መስረቅ ያስነውራል ።
ሳተናው
ዋሲሁን ተስፋየይህ በደምስ በለጠ 2008/2015 የተፃፈ ነው::

ሬ የሚያስወልደው የተከፈለው ነው !
ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ
ይህ አዲሱ 2008 የኢትዮጵያ
አመት ከዋዜማው ጀምሮ፤ በየሳምንቱ አዳዲስ ክስተቶችን እያሳየን ነው። የሐረር ሰው “ አጃኢብ” ይላል፤
ነገር አልጥም ሲለው። ለዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆኑኝ ፤ከጁላይ 18 ቀን ጀምሮ እያስተዋልኩ ያለሁት ጉዳይ
ነው። ጁላይ 18 ቀን 2015 በኢሳት ሰበር ዜና፤ እንዲህ ሰምተን ነበር። “ወደ ትግል ለመግባት የመሪዎችንም መስዋእትነት ይሻልና የግንቦት 7 መሪዎቹ ወደ ትግል ገቡ ” ነበር የተባለው። “ የግንቦት ሰባት አመራር ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ትግል ሜዳ ገባ ” ሲባል፤ በሁሉም አቅጣጫ ጭብጨባው ሰማይ እንዲደርስ ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም።የጉዳዩን ታላቅነትለመግለፅ፤ የግንቦት ሰባቱ መሪ ደመወዛቸው ሁለት መቶ ሺህ ፤ ማእረጋቸው ፕሮፌሰር፤ ችሎታቸውከሰው የበለጠ፤ እየተባለ ተጋኖ ተወጋ። ወደዚህ ትግል የገቡትና በፎቶም ያየናቸው የግንቦት ሰባቱ ሊቀ-መንበር ብቻ ሳይሆኑ፤ የኢሳቱም ዳይሬክቲንግ ማናጀር ነበሩ።
(ሙሉውን ፁሁፍ እዚህ ይገኛል )


http://moreshinfo.com/wp-content/upload ... %8B%8D.pdf

Post Reply