Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
yaballo
Member
Posts: 2606
Joined: 16 Feb 2013, 02:30

“የዜግነት ፖለቲካ” = የነቴዲ አፍሮ "ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”? “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው በርግጥም የዜጎች ፖለቲካ ነውን? የፈረስ ጫማን ለሰው እግር ..? (ጉለሌ ፖስት መጽሄት).

Post by yaballo » 17 Jan 2019, 18:24

“የዜግነት ፖለቲካ” = የነቴዲ አፍሮ "ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”? “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው በርግጥም የዜጎች ፖለቲካ ነውን? የፈረስ ጫማን ለሰው እግር ..? (ጉለሌ ፖስት መጽሄት - Jan, 2019).

“የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው በርግጥም የዜጎች ፖለቲካ ነውን? — የፈረስ ጫማን ለሰው እግር ...?
By Girma Gutema.<<ከዚህ የጃፓን ታሪክም ሆነ ከላይ ካቀረብኩት ነጥቦች መረዳት እንደሚቻለው “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው ነገር ጽንሰ ሃሳባዊ መሰረቱ በአንድ ሎዓላዊት ሃገር ውስጥ የሚኖሩ ብሄሮችን አንዱን የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ደግሞ ከዛ በታች ያለ አድርጎ የሚበይንና በባለ መጀመሪያ ደረጃ ዜጎች መልክና ልክ ቀደም ብሎ ተበጅቶ ያለውን ሃገራዊ ማንነት (national identity) ተሰደው የሚመጡ ሌሎች ባለዝቅተኛ ደረጃ ዜጎች እንዳያበላሹት ለመከላከል ተብሎ ስራ ላይ የሚውል ነው “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው። ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄን ፖለቲካዊ ጃርገን የሚያቀንቅኑት ወገኖች የትኛውን ብሄር አባላት የባለ መጀመሪያ ደረጃ ዜጎች፣ የትኞቹንስ የባለ ዝቅተኛ ደረጃ ዜጎች አድርጎ ለመበየን ነው ያሰቡት? የዜግነት ፖለቲካቸው ከጥቃት ሊከላከለው ያሰበው ሃገራዊ ማንነትስ የትኛው ይሆን? የዜግነት ፖለቲካን እንደመፈክር እያስተጋቡ ያሉት እነዚህ ወገኖች ሃበሻዊ ማንነትን ልክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ሃገረ-መንግስት ብሄራዊ ማንነት (national identity of modern Ethiopian state) አድርገው የሚያስቡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ የዜግነት ፖለቲካቸው በነቴዲ አፍሮ ቋንቋ የ”ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”ን ብሄራዊ ማንነት ለማስጠበቅ ይሆን በስራ ላይ እንዲውል የሚፈልጉት? ወይስ ሌላ ምክኒያት አለ? “የዜግነት ፖለቲካ” እናራምዳለን እያሉ ያሉት ፖለቲከኞች የነዚህን ጥያቄዎች ምላሾች ከፖለቲካዊው ጽንሰ ሃሳብ አንጻር ተንትነው ሊያስረዱን ይገባል።>>

photo: Artist Afework Tekle's 'Mother Ethiopia'.እንደመግቢያ:

በኢትዮጵያ የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ራሱን “የአንድነት ሃይል” ብሎ የሰየመው (በነገራችን ላይ “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” በሚለው ብሂል መሰረት ይመስላል ይህን ስም ለራሳቸው የሰጡት) እና የማንነት ፖለቲካን (identity politics) ብሎም የኢትዮጵያ ብሄሮች ባለፉት ስድስት አስርታት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄራዊ ጭቆናን ለማስወገድ እንዲሁም የራስን እድል በራስ ለመወሰን ያደረጉትን ቅቡል የእምቢተኝነት ትግል (legitimate resistance) በማጣጣልና በማንቋሸሽ የሚታወቀው የፖለቲካ ስብስብ ፖለቲካዊ ብያኔአቸው ልክ ያልሆኑ አገላለጾችን በግዴለሽነት መጠቀም የቆየ ልማዳቸው ስለመሆኑ ከሚጽፏቸውም ሆነ ከሚናገሯቸው ነገሮች መረዳት አይከብድም። ይሄን ነጥብ በምሳሌዎች ማስረዳት ይቻላል። ይህ የፖለቲካ ቡድን በተደጋጋሚ ቢነገረውም ማስተካከል ካልቻለው ወይም ማስተካከል ካልፈለገው ጉዳዮች አንዱ ይሄንኑ የኢትዮጵያ ብሄሮች የጸረ-ጭቆና ትግልን የሚያይበት መነጽርና የሚገልጽበት መንገድ ነው። በዚህ የፖለቲካ ቡድን አገላለጽ የኦሮሞ ህዝብ ወይም የሌሎቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለነጻነትና የራስን እድል በራስ ለመወሰን የሚያደርጉት ትግል እንደ “የዘረኝነት እንቅስቃሴ” የሚታይ ነው። እውነታው ግን እንኳም የኢትዮጵያ ህዝቦች ቀርቶ የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች ሁላ ዘራቸው አንድ ነውና አንድ ህዝብ ብሄራዊ ጥቅሙን ለማስከበር የሚያደርገው ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ትግል ከሌሎች የኢትዮጵያ ወይ የአፍሪካ ህዝቦች አንጻት ሲታይ የዘረኝነት እንቅስቃሴ ተደርጎ ሊወሰድ በፍጹም አይችልም። የዘር ልዩነት በሌለበት ሁኔታ ህዝቦች መብታቸውንና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር የሚያደርጉትን ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ትግል እንደዘረኝነት እንቅስቃሴ አድርጎ መግለጽ ተራ ፕሮፓጋንዳ እንጂ ሌላ ትርጉም ሊኖረው አይችልም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሊጠቀስ የሚችለው ምሳሌና ይሄው የፖለቲካ ስብስብ ተቸንክሮ የቀረበት (fixation) ስሁት ፖለቲካዊ አገላለጽ “የጎሳ ፖለቲካ” በሚል የኦሮሞን ፖለቲካ ወይም የሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ፖለቲካን ለመግለጽ የሚጠቀምበት አገላለጽ ነው። በመሰረቱ ጎሳ የሚባለው የታችኛው ማህበረሰባዊ አደረጃጀት (social structure) ባብዛኛው የኩሽ ህዝቦች ማህበረሰባዊ አደረጃጀት ውስጥ ያለ ቢሆንም ዛሬ ላይ ምናልባትም ከሶማሊ ህዝብ በቀር ፖለቲካን በጎሳ ደረጃ አዋቅሮ የጋርዮሽ ፖለቲካዊ ተግባር (collective political action) የሚያካሂድ ብሄር ኢትዮጵያ ውስጥ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ይህም የሆነበት ደግሞ የራሱ ታሪካዊና ነባራዊ ምክኒያት አለው። የጎረቤት ሶማሊያ ፖለቲካ የተዋቀረው በጎሳ መዋቅር ላይ ተመስርቶ ሲሆን የሃገሪቱ ፌዴራሊዝምም የጎሳዎችን አሰፋፈር መስመር (clan settlement pattern) ተከትሎ የተካለለ ስለመሆኑ የሚታወቅ ሆኖ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የሚታየው የጎሳ ፖለቲካም ከጎረቤት ሶማሊያ ፖለቲካ ተጽዕኖ የሚቀዳ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። እዚህ ላይ የሶማሌ ክልል ፖለቲካን በጎሳ ያዋቀረው የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ በወያኔዎች ታግዞ እንደሆነ ተደርጎ የሚቀርበው ትንታኔ ትክክል አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የሶማሊዎች የጎሳ አደረጃጀት ወትሮም ጠንካራ መሆኑ፣ ይሄው ማህበረሰባዊ አደረጃጀት በተለይ በጎረቤት ሶማሊያ ሃማኖትም ሆነ ዘመናዊነት ወይም ከተሜነት ሳያለዝበው ፖለቲካዊ ጉልበት መጎናጸፍ መቻልና (politicized መሆኑ) ከህዝቡ ቋንቋ፣ ባህልና የአኗኗር ዘዬ መመሳሰል ጋር ተያይዞ ይሄው የጎረቤት ሃገር ሶማሊያ ፖለቲካዊ እውነታ (political reality) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ማሳደር መቻሉ ነው ትክክለኛው ምክኒያት።

”የአንድነት ሃይሎች” የኦሮሞን ፖለቲካ ”የጎሳ ፖለቲካ” ይሉታል። ነገር ግን ሁሉም የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጎሳ ፖለቲካን አጥብቀው ይቃወሙታል፤ አምርረው ይታገሉታልም። በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ጎሰኝነትን ማራመድ ወይም የጎሳ ፖለቲካን ለማካሄድ መሞከር የሚያስወግዝ ጉዳይ ብቻም ሳይሆን ለከባድ ፖለቲካዊ ኪሳራና ውድቀትም ጭምር የሚዳርግ ስለመሆኑ የኦሮሞ ፖለቲካን የሚከታተልና በትክክል የሚረዳ ሁላ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። በኦሮሞ ውስጥ የጎሳ አደረጃጀት በስራ ላይ የሚውለው በፖለቲካው ውስጥ ሳይሆን በማህበራዊ መረዳጃና መደጋገፊያ (support and solidarity) በመሳሰሉት ቤተሰባዊና የቅርብ ቤተዘመዳዊ ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ ነው። ስለሆነም የኦሮሞን ፖለቲካ ”የጎሳ ፖለቲካ” ብሎ የሚገልጽ የፖለቲካ ቡድን ወይ የጎሳ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት መሆኑን የማያውቅ ነው ወይም ደግሞ ቢያውቅም ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ብሎ ልክ ባልሆነ መንገድ የኦሮሞ ፖለቲካን ለማጠልሸት የሚያደርገው ሸፍጥ ነው።

እነዚህን ነጥቦች ያነሳሁት እንደመንደርደሪያ እንጂ በዚች ጽሁፌ እንኳን ሰፋ አድርጌ ልመለከተው የፈለኩት ይኻው ከላይ የገለጽኩት የፖለቲካ ስብስብ በቅርቡ ይዞት የመጣውና “የዜግነት ፖለቲካ” (politics of citizenship) በሚል ተድበስብሶ እየቀረበ ስላለው የፖለቲካ ስንክሳር (political jargon) ነው። ስለሆነም በዚች አጭር ጽሁፌ በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን አካዳሚያዊ ተዋስኦዎች (academic discourses) እንዲሁም ሳይንሳዊ ጥናቶችን በመፈተሽ “የዜግነት ፖለቲካ” የሚለው አገላለጽ ትክክለኛ ፖለቲካዊ ብያኔና ብያኔው ጥቅም ላይ ሊውል የሚችልበት ሃገራዊና አካባቢያዊ አንድምታ (National/transnational context) ምን እንደሆነ፣ ብሎም በሃገራችንስ “የዜግነት ፖለቲካን” እንደ ማንፌስቶ ወይም እንደ መፈክር ይዞ መንቀሳቀስ ምን ዓይነት ትርጉም ሊኖረው ይችላል? የሚሉትን ነጥቦች አንስቼ በማጣየቅ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪና ጥልቀት ያለው ውይይት እንዲያደርጉ አንባቢያንን በመጋበዝ ጽሁፌን አጠቃልላለው።

የዜግነት ፖለቲካ ምን ዓይነት ፖለቲካ ነው?

የዜግነት ፖለቲካ (Politics of citizenship) በአካዳሚያው ምርምር መስክ ብዙም የተጻፈበት ፖለቲካዊ ጉዳይ አይመስልም። በጉዳዩ ላይ የታተሙትና ጽንሰ-ሃሳቡን አፍታተው ለማቅረብ የሞከሩት ጥቂት ጥናታዊ ጽሁፎችም ቢሆኑ ጉዳዪን የሚተነትኑት ከአለም አቀፍ-ድንበር ዘለል ጾታ -ተኮት የብሄሮች ስደት (transnational gendered migration) አንጻር ሆኖ፣ ትኩረታቸውንም ብሄሮች በአለም አቀፋዊው ድንበሮች ተከፋፍለው በተለያዩ ሃገሮች ውስጥ በሚኖሩባቸው የምስራቃዊና የደቡባዊ ምስራቅ ኤዢያ ሃገሮች ላይ ያደረጉ ናቸው። ጥናቶቹ “የዜግነት ፖለቲካ” የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ የሚያቀርቡት በአንድ ሎአላዊት ሃገር ውስጥ ስለሚደረግ የመደበኛ የሃገሬው ተወላጅ ዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ ጉዳይ አድርገው ሳይሆን በትራንስፖርትና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች እድገትና የንግድ ወይም ዓለም አቀፋዊ የስራ እድሎች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሚመጣ የሰዎች ስደት ወይም ዝውውር ምክኒያት (ስደቱ በተለይም አለም አቀፍ ድንበሮች ወደ ሁለት ወይም ከዛ በላይ ሃገሮች ውስጥ የሚከፍሏቸው ብሄሮች አባላት የሚመለከት ነው) በአንድ ሃገር ብሄራዊ ማንነት (national identity) ብሎም በብሄራዊ ደህንነት (national security) ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችል ፖለቲካዊ ማእቀፍ (political framework) ከማስተንተን አንጻር የቀረበ ነው። ይህ ብያኔ የኢትዮጵያ አንድነት ከምንም ነገር በፊት መቅደም እምዳለበት ደጋግመው በሚናገሩት የፖለቲካ ሃይሎች “የዜግነት ፖለቲካ” ለሚለው ጽንሰ-ሃሳብ ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉ ግራ አጋቢ (confusing) ያደርገዋል። የግራ አጋቢነቱ ዋና ምክኒያት የሚመዘዘው ደግሞ የተጠቀሱት የፖለቲካ ቡድኖች ተርሙን እየተጠቀሙ ያሉት ለመደበኞቹ የኢትዮጵያ ዜጎች ፖለቲካዊ ተሳትፎ መሆኑ ሲሆን፣ የጽንሰ -ሃሳቡ ትክክለኛ ትርጓሜ ግን ከዚህ በተቃራኒ በስደት ከሌላ ሃገር የሚመጡና ሃገሪቱ ውስጥ ካሉ ብሄሮች መካከል የአንዱ ብሄር አባላት ከሆኑ የሌላ ሃገር ዜጎች ፖለቲካዊና ባህላዊ ተሳትፎ ጋር በተያያዘ የሚነሳ የፖለቲካ ጽንሰ ሃሳብ መሆኑ ነው።

ጉዳዪን ይበልጥ ለማብራራት ከጥናቶቹ እናጣቅስ እስቲ። አፒቼ ሺፐር በተባለ የUniversity of Southern California ተመራማሪ የተሰራውና “politics of citizenship and transnational gendered migration in east and Southeast Asia” በሚል ርእስ በ2010 የታተመው ጥናታዊ ጽሁፍ በተጠቀሰው ጉዳይ ላይ ለአንባቢያን ግልጽ በሆነ ቋንቋና አቀራረብ ስፋትና ጥልቀት ያላቸው ትንታኔዎችን ያቀረበ ነው። ጥናቱ እንደ ጃፓን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ሰሜን ኮርያ፣ ታይዋን፣ ቻይና፣ ኢንዶኔዥያና ማሌዥያ የመሳሰሉትን የምስራቃዊና የደቡብ ምስራቃዊ ኤዢያ ሃገሮች ላይ ተመስርቶ የተሰራ የተናጥል ጥናቶችን (case studies) ያካተተ ሲሆን በየሃገሮቹ የሚገኙ የብሄሮች አባላት ከአንዱ ሃገር ወደ ሌላው የሚያደርጉት ስደት በስደተኛ ተቀባዩ ሃገር የውስጥ ፖለቲካ ላይ የሚኖረው ትጽእኖ (impact on domestic politics) ፣ ብሎም ሃገሮቹ በስደተኛ ብሄሮቹ ምክኒያት የሚመጣውን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጽእኖ ለመቋቋም የተከተሉትን ማእቀፍ (framework) ተንትኖ ያቀረበ መሆኑ ጥናቱ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው እንዲሆን አድርጎታል።

በተጠቀሰው የምርምር ስራ ውስጥ እንደቀረበው ከሆነ ይህን በብሄሮች ከአንድ ሃገር ወደ ሌላው ስደት ምክኒያት በስደተኛ ተቀባይ ሃገር የውስጥ ፖሊቲካ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ተጽእኖ ለመቆጣጣር እንደሚያስችል ተገልጾ የቀረበው የትንተና ማእቀፍ (analytical framework) በአንድ ሃገር ውስጥ ሰዎች ሶስት ዓይነት የዜግነት ደረጃዎች ሊኖራቸው እንደሚችል ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፥

1. መብት አልባ ዜግነት (formal citizenship)፥ የዚህ ዓይነቱ ዜግነት የሌላ ሃገር ዜጋም ሆኖ ቢሆን በሃገረ-መንግስቱ ውስጥ ከሚኖሩት ብሄሮች የአንደኛው ብሄር አባል በመሆን ብቻ ሊገኝ የሚችል ነው። ይህ ዓይነቱ ዜግነት በብሄር አባልነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለሃገሩ ተወላጅ ዜጎች የሚሰጠውን የዜግነት መብቶች (citizenship rights) የማያጠቃልል ሊሆን ይችላል። በመሆኑም የዚህ ዓይነቱ ዜግነት መብት አልባ ዜግነት ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ነው። ለምሳሌ ታይዋን ከሃገሯ ውጭ ለሚኖሩ የሃን ቻይኒዝ ብሄር ተወላጆች የዚህ ዓይነቱን መብት አልባ ዜግነት የምትሰጥ ሲሆን ታይዋን ይሄን የምታደርገው እነዚህ ቻይናዊያን በታሪክ በ1911 የኩሚንተንግ አገዛዝ የኵዊንግ ሰርወመንግስትን ለማሰወገድ በተደረገው ትግል ላይ ለሰጡት ድጋፍ ምስጋናና እውቅና ለመስጠት እንደሆነ ተጽፏል።

2. የባለ መብት ዜግነት (substantive citizenship)፥ የዚህ ዓይነቱ ዜግነት የሲቪል፣ የፖለቲካና የማህበራዊ መብቶችን (civil, political and social rights) የሚያጎናጽፍና የዜግነት ግዴታዎችንም ይዞ የሚመጣ ነው።

3. የባለ ልዩ መብት ዜግነት (differentiated citizenship)፥ በአንዳንድ ህብረ-ብሄራዊ ሃገሮች (ለምሳሌ ኢንዶኔዢያና ቻይና) በታሪክ፣ በፖለቲካዊ ወይም በሌሎች ምክኒያቶች የተነሳ ሃገረ መንግስቱ አንዱን ብሄር ከሌሎቹ አንጻር የባለ ልዩ መብት ተጠቃሚ (privileged) ሊያደርገው ይችላል። የባለ ልዩ መብት ዜግነት በአንድ ሃገር ውስጥ እኩልነትን ለማረጋገጥ በልዪ ሁኔታ ሊስተናገዱና የልዩ መብቶች ባለቤትነት እውቅና ሊሰጣቸው የሚገባ ቡድኖች ሊኖሩ ይችላሉ (equal respect justifies differential treatment and recognition of special rights) የሚለውን እሳቤ መሰረት ያደረገ ነው።

ጃፓንና የዜግነት ፖለቲካ ውዝግብ ታሪኳ:

ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በፊት የነበረችው ጃፓንና አሁን ያለችውን ጃፓን የሚያያይዘው የታሪክ ገመድ ”የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለውን ጽንሰ-ሃሳብ ለማብራራት የቀረበውን የትንተና ማእቀፍ ለማስረዳት እንደጥሩ ምሳሌ የሚቀርብ እንደሆነ አጥኚዎቹ ይገልጻሉ።

የታሪኩ ጭብጥ እንዲህ ነው፥
ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ህብረብሄራዊ ሃገረ-መንግስት (multi-ethnic state) ነበረች። ይሄ ሊሆን የቻለው ደግሞ ጃፓን ታይዋንን በ1895 እንዲሁም ኮሪያን በ1910 በመውረር በራሷ ግዛት ስር አስገብታ ስለነበር ሲሆን፣ ይህ ቅኝ ግዛታዊ ድርጊት ከነዚ በቅኝ ግዛት ከተያዙ አካባቢዎች ብሄሮች ወደ ዋናው የጃፓኖች ሃገር ጭምር ለተለያዩ ስራዎች በገፍ ስለገቡ ጃፓን ከአንድ ብሄር ሃገርነት (Uni-ethnic nation state) ወደ ህብረ ብሄራዊ ሃገርነት (multi-ethnic state) መሸጋገር ችላ ነበር። ነገር ግን ጃፓን በጦርነቱ ተሸንፋ በቅኝ ግዛት የያዘቻቸውን የታይዋንና የኮሪያ ግዛቶቿን በማጣቷ ምክኒያት በብሄር ጃፓናዊያን ያልሆኑ ዜጎቿ በሙሉ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡና “ሰላማዊት የአንድ ብሄር ሃገረመንግስት” (peace loving [deleted] state) ከጦርነቱ በፊት የነበረችውን ህብረ -ብሄራዊ ጦረኛ የጃፓን ግዛተ-አጼ (pre-war-multi-ethnic military empire of Japan) እንድትተካ ሊህቃኑና ፖለቲከኞች ስምምነት ላይ ደረሱ። በዚሁ መሰረትም በብሄር ጃፓናዊያን ያልሆኑት ከሃገሪቱ እንዲወጡ ስላደረጉ ጃፓን የአንድ ብሄር ሃገር እንድትሆን ማድረግ ችለው ነበር። ሆኖም ግን ሃገሪቱ በኋላ ላይ ባሳየችው ፈጣን የቴክኖሎጂና የዘመናዊነት እምርታ ምክኒያት በርካታ የውጭ ሃገራት ዜጎች ወደ ጃፓን እየጎረፉ በመሆኑ ሃገሪቱ ከአንድ ብሄር ሃገርነት እንደገና ወደ ህብረ-ብሄራዊት ሃገርነት ራሷን ለመቀየር ተገዳለች።

ከዚህ የጃፓን ታሪክም ሆነ ከላይ ካቀረብኩት ነጥቦች መረዳት እንደሚቻለው “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው ነገር ጽንሰ ሃሳባዊ መሰረቱ በአንድ ሎዓላዊት ሃገር ውስጥ የሚኖሩ ብሄሮችን አንዱን የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ደግሞ ከዛ በታች ያለ አድርጎ የሚበይንና በባለ መጀመሪያ ደረጃ ዜጎች መልክና ልክ ቀደም ብሎ ተበጅቶ ያለውን ሃገራዊ ማንነት (national identity) ተሰደው የሚመጡ ሌሎች ባለዝቅተኛ ደረጃ ዜጎች እንዳያበላሹት ለመከላከል ተብሎ ስራ ላይ የሚውል ነው “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው። ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄን ፖለቲካዊ ጃርገን የሚያቀንቅኑት ወገኖች የትኛውን ብሄር አባላት የባለ መጀመሪያ ደረጃ ዜጎች፣ የትኞቹንስ የባለ ዝቅተኛ ደረጃ ዜጎች አድርጎ ለመበየን ነው ያሰቡት? የዜግነት ፖለቲካቸው ከጥቃት ሊከላከለው ያሰበው ሃገራዊ ማንነትስ የትኛው ይሆን? የዜግነት ፖለቲካን እንደመፈክር እያስተጋቡ ያሉት እነዚህ ወገኖች ሃበሻዊ ማንነትን ልክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ሃገረ-መንግስት ብሄራዊ ማንነት (national identity of modern Ethiopian state) አድርገው የሚያስቡ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ የዜግነት ፖለቲካቸው በነቴዲ አፍሮ ቋንቋ የ”ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”ን ብሄራዊ ማንነት ለማስጠበቅ ይሆን በስራ ላይ እንዲውል የሚፈልጉት? ወይስ ሌላ ምክኒያት አለ? “የዜግነት ፖለቲካ” እናራምዳለን እያሉ ያሉት ፖለቲከኞች የነዚህን ጥያቄዎች ምላሾች ከፖለቲካዊው ጽንሰ ሃሳብ አንጻር ተንትነው ሊያስረዱን ይገባል።

ማጠቃለያ:

የዜግነት ፖለቲካ (politics of citizenship) የተባለው ፖለቲካዊ ጽንሰ-ሃሳብ አንድ ሎዓላዊት ሃገር የብሄሮች ስብጥርን ከምትጋራው ሌላ ሃገር በስደት የሚመጡ የየብሄሩ አባላት በስደተኞች ተቀባይ ሃገር የውስጥ ፖለቲካ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ (impact on domestic politics) መቋቋም በሚቻልበት ፖለቲካዊ ማእቀፍ (political framework) ላይ የሚያጠነጥን ጉዳይ ነው። ጉዳዪ ህብረ-ብሄራዊ በሆኑ የምስራቃዊና የደቡብ ምስራቃዊ ኤዢያ ሃገሮች የሃገሩ ዜግነት በሌላቸው መጤ ግን ደግሞ በሃገሩ ዳርድንበር (territory) ውስጥ ከሚጠቃለሉት የአንዱ ወይም የሌለኛው ብሄር አባላት ምክኒያት ሊመጣ የሚችለው የህዝብ ቁጥር ለውጥ (demographic shift) በሃገሩ የውስጥ ፖለቲካ ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድር ፖለቲከኞች በሃገረ መንግስቱ የሚደገፈውን ብሄርተኝነት (state sponsored nationalism) ይበልጥ እንዲያድግና በመጤ ብሄሮች የሚሸረሸረው ነባሩ ሃገራዊ ማንነት (national identity) እንዲሁም ሃገራዊ አንድነት (National unity) መልሶ ማገገም እንዲችል ድጋፍ የሚሰጡበት ጽንሰ-ሃሳባዊ የፖለቲካ ማእቀፍ ነው።

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ”የአንድነት ሃይሎች” ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ የፖለቲካ ቡድኖች “የዜግነት ፖለቲካ” የሚለውን አገላለጽ በፖለቲካዊ ንግግሮቻቸው ውስጥ እንደመሪ ቃል ለመጠቀም ሲወስኑ ምን ማለታቸው ይሆን? ከላይ በጉዳዩ ላይ የተሰሩ ጥናቶችን በማጣቀስ ለመግለጽ እንደተሞከረው “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው ፖለቲካዊ ጽንሰ-ሃሳብ መጤውንና ነባሩን የአንድ ሃገር ዜጎች በመለየት የመጤውን ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ ...ተጽእኖዎች ለመቆጣጠር/ለመቀነስ ጥቅም ላይ የሚውል ፖለቲካዊ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን ”የአንድነት ሃይሎች” ብለው የሾሙ የፖለቲካ ሃይሎች ይህንን “የዜግነት ፖለቲካ” የሚለውን አገላለጽ እንደመፈክር ሲያስተጋቡ፣እነማንን መጤ፣ እነማን ደግሞ የሃገሩ ነባር ዜጎች አድርገው ቆጥረው ነው? ነው ወይስ ሌላ አዲስ የራሳቸው የሆነ በፖለቲካ ጽንሰ-ሃሳቦች ስብስብ ውስጥ ገና ያልተካተተ ብያኔ (operational definition) አቅርበዋል? በነዚህ ነጥቦች ላይ ውይይት ጋብዤ ጽሁፌን እዚሁ ላይ ላብቃ።

ግርማ ጉተማ (አባጨብሳ) [Article appeared in 'Gulele Post', Jan, 2019].https://www.facebook.com/tsegaye.ararss ... 8643600808

———————-
ማስታወሻ፥ ይህ ጽሁፍ በጉለሌ ፖስት መጽሄት ቅጽ 1 ቁጥር 4 ላይ ታትሞ የወጣ ሲሆን፣ በተነሳው ርእሰ ጉዳይ ላይ ውይይቱ እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይም ይቀጥል ዘንድ እዚሁ ገጼ ላይም ለጥፌዋለው።

Ethoash
Senior Member+
Posts: 21350
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: “የዜግነት ፖለቲካ” = የነቴዲ አፍሮ "ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”? “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው በርግጥም የዜጎች ፖለቲካ ነውን? የፈረስ ጫማን ለሰው እግር ..? (ጉለሌ ፖስት መጽሄት).

Post by Ethoash » 17 Jan 2019, 19:46

i support “የዜግነት ፖለቲካ” as long as this “የዜግነት ፖለቲካ” doesnt use tribe(Amhara )language as Lingua franca

የዘር ፖለቲካ አንፈልግም እያሉ ። የዘር ቋንቋ በዜግነት ላይ መጫን የለበትም

i am sorry Ethiopia doesnt have her own language i hope u will not suggest we use tribe language

without solving this language issue we cant use “የዜግነት ፖለቲካ”... “የዜግነት ፖለቲካ” cant be backdoor for the Amhara to come back on the saddle

Horus
Senior Member
Posts: 13104
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: “የዜግነት ፖለቲካ” = የነቴዲ አፍሮ "ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”? “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው በርግጥም የዜጎች ፖለቲካ ነውን? የፈረስ ጫማን ለሰው እግር ..? (ጉለሌ ፖስት መጽሄት).

Post by Horus » 17 Jan 2019, 21:47

I am Horus. I hate to mince words. Also, I hate lazy minds. Tribalism is chaos. It is also chaotic mind. Here is a tribal chaotic mind attacking the word Habasha and artist poet Tedy Afro yet using the Ethiopian language Amharic. This is not only a chaotic political psychology, it is a crisis of perception.

For you information, the word Gulela' is a Semitic word. There is no Oromo word called gulela'. If there is one, tell us what it means. There has never existed a people called Gulela'. This tribal chaotics, borrow culture and languages like nobody's business and yet try to lecture us about Ethiopia (Medre Habasha). Ethiopia is Habasha. Habasha is Ethiopia. Amharic is An Ethiopic language made up of many Ethiopic languages. Those who hate Amhaic must not use it and talk to themselves with their own tribal language.

Ethiopia will establish a citizen formed free modern democracy. Ethiopiansim is civic nationalism, it is the identity and self-expression of every free Ethiopian citizen. Those who don't want to an Ethiopian citizenship, then that is their right not to vote or participate in Ethiopian democratic politics.

The very word 'identity' has nothing to do with the word tribe or ethnos. Identity is a word that comes from being human being or Sew or Seb. Tribalism a primitive backward method of organization where people who are not related genetically are forced into falsely claimed genetic relativity. This is the chaotic mind's fakery.

To attack the idea of individual liberty and the idea of a free and sovereign individual human being is the ultimate bankruptcy and chaotic vacuum of tribal ideology called by 1001 names.

Again, if you don't like Amharic don't use it. Talk and write your own language. You have no right to tell me what language I must use or or not use.

Tribalism is Chaos. That is all.

Ethoash
Senior Member+
Posts: 21350
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: “የዜግነት ፖለቲካ” = የነቴዲ አፍሮ "ሃበሻዊት ኢትዮጵያ”? “የዜግነት ፖለቲካ” የሚባለው በርግጥም የዜጎች ፖለቲካ ነውን? የፈረስ ጫማን ለሰው እግር ..? (ጉለሌ ፖስት መጽሄት).

Post by Ethoash » 18 Jan 2019, 16:38

Horus wrote:
17 Jan 2019, 21:47
I am Horus
Again, if you don't like Amharic don't use it. Talk and write your own language. You have no right to tell me what language I must use or or not use.

Tribalism is Chaos. That is all.

sorry to burst your bubble Amhara doesnt have a writing system .. they r using ግህዝ ፊደል which Axumiate civilization that make it golden race property .. the Amhara just stole it and claim it as if it is their own.. this is like saying English have a writing system they dont they r using Latin alphabet

have a nice day... had the amhara told the truth and said ፊደል doesnt belong to them then the oromo would have use it..since the Amhara told the oromo they should be Ethiopian national language because they have written letter the oromo reject it.. and move to Latin alphabet..\\\why she is "mother Ethiopian" if Artist Afework Tekle said Ethiopian mother then it would have been acceptable

to me this is more like mother Ethiopia because she is holding a baby
but not according to Artist Afework Tekle for him only Amhara is our mother Ethiopia ....

Post Reply