Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
yaballo
Member
Posts: 2064
Joined: 16 Feb 2013, 02:30

***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by yaballo » 05 Dec 2018, 06:49

***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

የኦሮሞ አርሶአደሮች በደል በደሌ ነው የሚል ማንኛውም አካል በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መገኘት ይችላል፡፡ በፊንፊኔና በፊንፊኔ ዙርያ የምትገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና የኦሮሞ ወዳጆች በሰልፉ ላይ እንድትገኙ ጥሪ ተደርጎላቹኃል።

'እኛ አልተነጋገርንበትም፣' 'እነ እከሌ ሊጠልፉት ነው'፣ 'እነእከሌ ሸኔ ናቸው' ምናምን በሚል ሃሜትና የሴራ ፖለቲካ በመንዛት የሕዝብን ድምፅ ለማፈን መሯሯጥ ለማንም አይጠቅምም፣ አይገባምም። ግድ የሚለው ሁሉ ድምፁን ያሰማ። የማይፈልግ ካለ ተቃውሞውን የማሰማት መብቱ የተጠበቀ ነው።

#Finfinnee_protests!!!<<ታህሳስ ፮ ታላቅ ሰልፍ ይኖራል--በምክንያት!!!
=========================
ሰልፉን የምትቃወምበት በቂና ተጨባጭ ምክንያት ካለህ በምክንያት አስረዳ። አይ "እነ እከሌ፣ እነ ወያኔ፣ እነ ሸኔ፣ ወዘተ ለፖለቲካ ዓላማ እንዳይጠቀሙበት ፈርቼ ነው" ማለትህ ምክንያት አይደለም። እኔም ያንተን ዝምታ መምረጥ፣ "እነ ኦህዴድ፣ እነ አዴፓ፣ እነ ግም. 7፣ ወዘተ የሕዝቡ የተቃውሞ ድምፅ እንዳይሰማ አንተን ለፖለቲካ ዓላማ ይጠቀሙብሃል" ብዬ " ስጋቴን" መግለፅ እችላለሁና።

የዚህ ሰልፍ ዓላማ ግልፅ ነው። ወቅታዊነቱም፣ ጥያቄዎቹም፣ ሰላማዊነቱም እንዲሁ።

የኦሮሞ ሕዝብ በየስፍራው የሞት እራት እየሆነ ነው። ከየአገሩ እየተፈናቀለ ነው። የተፈናቀለው ምንም መንግሥታዊ እርዳታ እያገኘ አይደለም። በሱማሌ የድንበር ወረራም በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ጥቃትም የተፈናቀሉት ሰዎች ተገቢውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንኳን እያገኙ አይደሉም። አሁንም በሞያሌ፣ በአፋር መዳረሻ፣ ወዘተ ኦሮሞዎች በየቀኑ ጥቃት ይደርስባቸዋል። መንግሥትም ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱን ቀጥሏል።

በየዩኒቨርሲቲ ግቢዎች (አሶሳን፣ ጎንደርን፣ አርባ ምንጭን፣ ወላይታ ሶዶን፣ አዲግራትን፣ አክሱምን፣ ወዘተ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል!) ኦሮሞ ተማሪዎች በኦሮሞነታቸው ብቻ እየተደበደቡ፣ እየተሰደቡ፣ ተሸማቅቀው እንዲኖሩ፣ እየተገደዱ ነው። ፊንፊኔ ውስጥ እንኳን ኦሮሞዎች ደህንነት እና ነፃነት እንዳይሰማቸው እየተደረጉ ነው።

የኦሮሞ ሕዝብ የመብት ጥያቄዎች በሙሉ ተድበስብሰው እንዲቀሩ እየተደረገ ነው። አሁን አሁን ደግሞ በመንግሥት በቀጥታ እየተጣሱ ነው።

ለምሳሌ ከመሬት ያለመፈናቀል ጥያቄው ተረስቶአል። ይልቁንም በተጠናከረ መልኩ ከፊንፊኔ ተሻግሮ ወደ ኦሮሚያ እየተስፋፋ ቀጥሎአል። የፊንፊኔ መስተዳድር ከሕጋዊ ሥልጣኑ (ከ jurisdiction) ውጭ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስልጣን ሥር ባለና ከከተማው ድንበር 23 ኪሜ ርቆ በሚገኝ ኮዬ ፈጬ በሚባል መንደር ውስጥ ሕንፃ ገንብቶ ሕዝብን አፈናቅሎ፣ ለመከራ እየዳረገ ነው። ተመሳሳይ ግንባታዎች በሁሉም የከተማው መውጫ በሮች (እስከ ሆሎታ፣ሰበታ፣ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ዱከም፣ ገላን፣ ወዘተ ድረስ) እየተሰሩ እንደነበርና እንዳሉም ይታወቃል።

የመሬት ዘረፋ ያለ ምንም የመንግሥት ሃይ-ባይነት በካሬ ሜትር እስከ አንድ ሺህ ብር እየተቸበቸበ ከለገጣፎ አንስቶ ሰንዳፋን አልፎ ሸኖና ቅንቢት እየደረሰ ነው። መንግሥትና ደላሎቹም እዚሁ አካባቢ ላይ ለደምበኛ ባለሃብቶቻቸው የገበሬውን መሬት ሲቸሩ በገሃድ በቴሌቭዥን እያየን ነው።

ኦሮሞ በአዲስ አበባ ላይ ያለው ሕገ-መንግሥታዊ ጥቅሙ ተረስቶ፣ በተቃራኒው ጥቅሙን የሚሸረሽሩ ተግባራት በየዕለቱ እየተፈፀሙ ይገኛሉ።

የኦሮምኛ ቋንቋን የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ የማድረግ ጥያቄ በመንግሥት ተድበስብሶ ከናካቴው ደብዛው ጠፍቶአል።

የአገር ባለቤትነት ጥያቄው (Gaaffiin abbaa biyyummaa) ሙሉ በሙሉ ተቀብሮ፣ ኦሮሞ ዛሬ አገሩን በጠራራ ፀሐይ እየተነጠቀ ነው። የክልሉ ድንበሮች ከዳር እስከዳር እየተጠቁ የክልሉ እንደክልል የመቀጠል ተስፋ አጠያያቂ እየሆነ ነው።

ጠቅላይ ሚኒሥትሩ፣ ፀንቶ ያለውን ሕገ-መንግሥታዊውን ድንጋጌ፣ ተቋማዊና የአሠራር ማዕቀፍ ወደ ጎን በመተው የማንነትና የድንበር ጉዳይን የሚወስን ኮሚሺን ለማቋቋም የሕግ ረቂቅ ለማስጸደቅ እየተጋ ነው። ይሄም ኮሚሽን የኦሮሚያን ድንበር በመቀየር ክልሉን ይከፋፍላል የሚል ስጋት ሕዝቡ ውስጥ እንዲፈጠር አድርገዋል። የብሔሮችን መብት የሚሸራርፍ የተማከለ (ወይም መብት-የለሽ የፌደራል) ሥርዐት ለመፍጠር እየተጉ ነው የሚል ስጋት እንዲበራከት ሆኗል። ከዚህም የተነሳ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ብሔራዊ ህልውናን ጥያቄ ውስጥ እያስገባው ይገኛል።

እነዚህንና እኒህን የመሳሰሉ ሌሎች ጥያቄዎችን መንግሥት በሂደት ይመልሳል በማለት እስካሁን የኦሮሞ ሕዝብ በትእግስት ሲጠብቅ ቆይቷል። ኦህዴድ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ፣ ትግልና መስዋዕትነት ወደ ሥልጣን የመረማመጃ ድልድይ ከማድረግ ባለፈ ምንም ነገር ለማድረግ አለመፈለጉን በተግባርና በንግግር በተደጋጋሚ አሳይቶአል፣ እያሳየም ነው። በመሆኑም ሰሞኑን፣ ሕዝቡ ትዕግስቱ አልቆ ከጥግ እስከጥግ ገንፍሎ ወጥቶ ድምፁን ለማሰማት ተንቀሳቅሷል።

የፊንፊኔ ከተማ ነዋሪዎችም--በተለይ ኦሮሞዎች--ትዕግስታቸው አልቋል። በመሆኑም ከሕዝባቸው ጎን በመቆም ድጋፋቸውን ለማሰማት፣ እንደ ከተማው ባለቤትና እንደነዋሪነታቸው ድምፃቸው በሰላማዊ መንገድ እንዲሰማ ለመጠየቅ ተነሳስተዋል። ይሄ ደግሞ ከአገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ ጋር የሚሄድ ወቅታዊነቱን የጠበቀ ተግባር ነው።

ይሄን ለማድረግ መነሳት ወያኔነት አይደለም። ጠላትነትም አይደለም። ኦህዴድ ፊንፊኔ ውስጥ የሚደረግ ሰልፍ "በዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ዘንድ ያሳጣኛል፣ መልካም ገፅታዬን ያበላሻል፣ ወዘተ " ብሎ መሸበሩ ትክክል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ለመሪዎች ገፅታ ግንባታ ተብሎ የሕዝብ መብት አይታፈንም። ግዴታውን የማይወጣ መንግሥት፣ ግዴታውን ከመፈፀም ይልቅ በሽንገላና በድለላ ለመኖር የሚፈልግ መንግሥት፣ ገፅታውን ብቻ ሳይሆን ሥልጣኑንም ያጣል፣ ማጣትም አለበት።

ኦህዴድ ይህ እንዳይሆን ሲርበተበት የሥልጣንና የጥቅም ተስፈኞችም አብረው ተደምረው መርበትበት መብታቸው ነው። ሕዝቡን ግን አንዴ "ወያኔ ነው"፣ አንዴ "ሸኔ ነው፣" አንዴ "የጠላት ተላላኪ ነው" እያሉ ድምፁን ማፈን አይቻልም፤ አይፈቀድም።

የሕዝብ ድምፅ ይሰማ። በሰልፍም ጭምር። ድምፄን አላሰማም ካልክ አትውጣ። ማሰማቱንም እቃወማለሁ ካልክ ተቃውመህ ድምፅህን ለማሰማት ሰልፍ ውጣ። ለሕዝብ ግን እኔ አውቅልሃለሁና "እንዳትወጣ" ማለት ምክንያታዊ ያልሆነ አፋኝነት ነው።

#The_people_shall_be_heard!!!>>

Jirta
Member
Posts: 358
Joined: 30 Sep 2018, 07:07

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Jirta » 05 Dec 2018, 11:55

መጀመሪያ ከቀን ጅቦች ተላላኪነት እንጥራ:: ቦንብ ይዞ ቢግኝ ኦሮም:አሸባሪ ተብሎ ቢያዝ እኛ; ተላላኪ ተብሌ ቢያዝ እኛ:: አሁንስ ማን ልኮን ነው:: መጀመሪያ የቀን ጅቦች ይጥሩ:: እነርሱ ከወጡ መሬታችንም አዲስ አበባ ያለው ህንፅም የህዝብ ይሆናል:: እየተላላክ ካገዝካቸው ደግሞ እንኳን መሬትህን እንደለመዱት ነፍስህን ይበሉታል:: ሚስትህንም ይወስዷታል::

የቀንጅቦች ተላላኪ አንሁን::

Ethoash
Senior Member
Posts: 18782
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Ethoash » 05 Dec 2018, 12:06

አንድ ውንድ ጠፍ እነዚህን ስራ ፈቶች አፍሶ ወድ ገጠር ወስዶ የሚያሳርስ ።።። ስልፍና የመንገድ ላይ ዘፈን ሰለቸን። ስራ እንኳን ቢጠፍ መንገድ አስጠሩጋቸው።

Aragaw
Senior Member
Posts: 16217
Joined: 04 May 2007, 12:03

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Aragaw » 05 Dec 2018, 12:16

አቶ አሽትሬ
ወንድማ ሞልቷል አላየሃቸውም እንዴ ይቀን ጅቦችን ሰብሰበው ያለ አንዳች ጥይት ተኩስ ፈስ በፈስ አድርጎ መቀሌ እንደ ከተታቸው።

Ethoash wrote:
05 Dec 2018, 12:06
አንድ ውንድ ጠፍ እነዚህን ስራ ፈቶች አፍሶ ወድ ገጠር ወስዶ የሚያሳርስ ።።። ስልፍና የመንገድ ላይ ዘፈን ሰለቸን። ስራ እንኳን ቢጠፍ መንገድ አስጠሩጋቸው።

Ethoash
Senior Member
Posts: 18782
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Ethoash » 05 Dec 2018, 12:37

Aragaw wrote:
05 Dec 2018, 12:16
አቶ አሽትሬ
ወንድማ ሞልቷል አላየሃቸውም እንዴ ይቀን ጅቦችን ሰብሰበው ያለ አንዳች ጥይት ተኩስ ፈስ በፈስ አድርጎ መቀሌ እንደ ከተታቸው።

Ethoash wrote:
05 Dec 2018, 12:06
አንድ ውንድ ጠፍ እነዚህን ስራ ፈቶች አፍሶ ወድ ገጠር ወስዶ የሚያሳርስ ።።። ስልፍና የመንገድ ላይ ዘፈን ሰለቸን። ስራ እንኳን ቢጠፍ መንገድ አስጠሩጋቸው።

ልብ ሲያውቅ ዶሮ ማታ። ልብ ካለህ እስቲ ከመቸጉበት አስውጣቸው።

እስከዚያ ግን ውሬያቹህ ሰለቸን። ውይ ስሩ ውይ ሌላውን አሰሩ። እሰቲ እስከ ዛሬ ድረስ ዶክተር ፍቅር፣ ለምን ያህል ኢትዬጵያኖች የስራ እድል ከፍቶዋል። አንድ ችግር ባለ ቁጥር ስብሰባ ነው። በስብሰባ ገደላቹህን እኮ። የመሬት መንቀጥቀጥ ደረስ ፣ በሉ እንስብስብ። ይእርስ በርስ ጦርነት ጋይቶዋል፣ በሉ እንስብስብ። ስዎች ተጨራረሱ ፣በሉ እንስብስብ። የሚበላ አጣን ፣በሉ እንስብስብ።

Aragaw
Senior Member
Posts: 16217
Joined: 04 May 2007, 12:03

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Aragaw » 05 Dec 2018, 15:02

ምንም ነገር ወደ ትግራይ እንዳይገባ አድርጎ እዚያው ከቦ የያዙት ምግብ እሲኪያልቅ መጠበቅ ነው። እንደ ተባይ ተንጋግተው ይወጣሉ ወይም የትግራይ ህዝብ ይሚበላው ሲያጣ እጃቸውን ይዞ ያስረክባል። It is that simple.
:lol: :lol: :lol:
Ethoash wrote:
05 Dec 2018, 12:37
Aragaw wrote:
05 Dec 2018, 12:16
አቶ አሽትሬ
ወንድማ ሞልቷል አላየሃቸውም እንዴ ይቀን ጅቦችን ሰብሰበው ያለ አንዳች ጥይት ተኩስ ፈስ በፈስ አድርጎ መቀሌ እንደ ከተታቸው።

Ethoash wrote:
05 Dec 2018, 12:06
አንድ ውንድ ጠፍ እነዚህን ስራ ፈቶች አፍሶ ወድ ገጠር ወስዶ የሚያሳርስ ።።። ስልፍና የመንገድ ላይ ዘፈን ሰለቸን። ስራ እንኳን ቢጠፍ መንገድ አስጠሩጋቸው።

ልብ ሲያውቅ ዶሮ ማታ። ልብ ካለህ እስቲ ከመቸጉበት አስውጣቸው።

እስከዚያ ግን ውሬያቹህ ሰለቸን። ውይ ስሩ ውይ ሌላውን አሰሩ። እሰቲ እስከ ዛሬ ድረስ ዶክተር ፍቅር፣ ለምን ያህል ኢትዬጵያኖች የስራ እድል ከፍቶዋል። አንድ ችግር ባለ ቁጥር ስብሰባ ነው። በስብሰባ ገደላቹህን እኮ። የመሬት መንቀጥቀጥ ደረስ ፣ በሉ እንስብስብ። ይእርስ በርስ ጦርነት ጋይቶዋል፣ በሉ እንስብስብ። ስዎች ተጨራረሱ ፣በሉ እንስብስብ። የሚበላ አጣን ፣በሉ እንስብስብ።

sun
Member
Posts: 3507
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by sun » 05 Dec 2018, 15:29

Hmm... :P

It is sad that human lives are destroyed and large scale displacements takes place. It needs to stop as soon as possible!

But then again it is rather foolish and complete ignorance together with outright irresponsibility to go out constantly shouting, road blocking and demanding too much too soon from a few month old government struggling to put itself in condition and then tackle long standing political, social, economic, security,etc, problems while at the same time already able to do monumental miraculous jobs even during its few months existence calling on them to come out and fix the accumulated problems of some 200 years right away with a blink of an eye.

As a non politician humanist human being I think that the cheap slogan directed against the hard working Obbo Takele Uuma can not be coming from the wisdom of the humanist Gada Oromo slogan but underneath seems to be a hidden tplf dirty slogan to show and publicize that humanist Oromos are not good leaders,according to their standard self serving pattern of thinking, as a result of which the "able tplf leaders" needs to come back and put everything in order, including the bringing back of Maikelawi torture chamber together with all the other prisons and prisoners. :oops:

If there needs to be slogan of this nature, it must first acknowledge positively all the more than good positive changes these leaders achieved with a short time and only after that appeal to them politely to try to fix the current urgent problems. That is only simple wisdom and common tactfulness for achieving positive common goals. By doing and behaving like that you are giving the leaders positive and energizing feedback and help them and yourself to achieve the greater Good slowly but surely. Our new dynamic Prime Minister is a leader of all the Ethiopians that includes all the Oromos.

The new and fresh government of the good PM's job is to fix the problems of all Ethiopians and even beyond ( like he did with Eritrea) including that of all Oromos because problems are contagious in the sense that it jumps from region to region, from country to country, from city to city, from locality to locality.

Our new leaders of Finfinne city Obbo Takele Uumma is a leader of all the Ethiopians residing in Finfinne including the good Oromos of that city where the International organizations such as the Economic Commission for Africa, African Union, etc. including some 109 Embassies. So the idea is, ACT LOCALLY BUT THINK GLOBALLY!

Oromos should not play in to the hands of the desperate tplf cadres and their diverse running dogs who were bought with cash and kind. Demonstrations and self expressions "yes!" but one should refrain from abusing such young freedom of expression by over using and over-consuming it even before it is born and able to see the sunlight.

Change in itself is a process that gets implemented as time marches ahead. It may be smooth and linear fast paced change, slow pace change and or two steps forward and one step back wards depending on the relationships change agents put against the counter agents opposing change while the neutral bystanders look on with wide open eyes, doing nothing.

Actually the tplf oligarchs are working hard to put Oromos against Oromos as well as all the other Ethiopians against other Ethiopians so to come back and place the the same old tplf dictatorship in power again. One should refrain from undermining the difficult tasks of the current leaders even though opinions and emotions are so much abundant in a country of some 100 million people of different nationalities, religions and regions living in a country known for its historical inequality and under developments.

That is why the sane leaders of these Qerros must guide and put rationality and responsibilities in to the heads and actions of some of these rather emotional Qerros, lest the whole positive and transformational forward marching development may be taken back 200 years after which time our dear and near Qerros might go to jails while the rest pushed out to the foreign and domestic refugee camps. Wake up Qerro leadership and do the right leadership daily jobs! Okay? Okay!
:P
Last edited by sun on 05 Dec 2018, 17:08, edited 4 times in total.

present
Member+
Posts: 6599
Joined: 22 Feb 2016, 17:37

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by present » 05 Dec 2018, 16:12

Sun,
I could not say it better!!
sun wrote:
05 Dec 2018, 15:29
Hmm... :P

It is sad that human lives are destroyed and large scale displacements takes place. It needs to stop as soon as possible!

But then again it is rather foolish and complete ignorance together with outright irresponsibility to go out constantly shouting, road blocking and demanding too much too soon from a few month old government struggling to put itself in condition and then tackle long standing political, social, economic, security,etc, problems while at the same time already able to do monumental miraculous jobs even during its few months existence calling on them to come out and fix the accumulated problems of some 200 years right away with a blink of an eye.

Actually the tplf oligarchs are working hard to put Oromos against Oromos as well as all the other Ethiopians against other Ethiopians so to come back and place the the same old tplf dictatorship in power again. One should refrain from undermining the difficult tasks of the current leaders even though opinions and emotions are so much abundant in a country of some 100 million people of different nationalities, religions and regions living in a country known for its historical inequality and underdevelopments.

That is why the sane ledears of these Qerros must guide and put rationalities and responsibilities in to the heads and actions of some of these rather emotional Qerros, lest the whole positive and transformational forward marching development may be taken back 200 years after which time our dear and near Qerros might go to jails while the rest pushed out to the foreign and domestic refugee camps. Wake up Qerro leadership and do the right leadership daily jobs! Okay? Okay!
:P

sun
Member
Posts: 3507
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by sun » 05 Dec 2018, 17:19

“We are products of our past, but we don't have to be prisoners of it.” ~R. Warren, The Purpose Driven Life: What on Earth Am I Here for? :P

Abaymado
Member
Posts: 719
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Abaymado » 05 Dec 2018, 23:48

Tigray ash : wow, you are fluent in Amharic and excelling abebe.b and others. :shock:

Marc
Member
Posts: 128
Joined: 27 Jun 2017, 01:52

Re: ***ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ታህሳስ 6/ 20011ዓ.ም (December 15, 2018) በመስቀል አደባባይ**

Post by Marc » 06 Dec 2018, 02:31

Jirta wrote:
05 Dec 2018, 11:55
መጀመሪያ ከቀን ጅቦች ተላላኪነት እንጥራ:: ቦንብ ይዞ ቢግኝ ኦሮም:አሸባሪ ተብሎ ቢያዝ እኛ; ተላላኪ ተብሌ ቢያዝ እኛ:: አሁንስ ማን ልኮን ነው:: መጀመሪያ የቀን ጅቦች ይጥሩ:: እነርሱ ከወጡ መሬታችንም አዲስ አበባ ያለው ህንፅም የህዝብ ይሆናል:: እየተላላክ ካገዝካቸው ደግሞ እንኳን መሬትህን እንደለመዱት ነፍስህን ይበሉታል:: ሚስትህንም ይወስዷታል::

የቀንጅቦች ተላላኪ አንሁን::
Right !!!!!!! ፋታ የሚሰጥ ጠፋ ፡፡ አንዳንድ ሰዉ እበላለሁ አያለ አራሱንም ሃገርንም ያስበላል ፡፡ ልብ ያለዉ ልብ ይበል !!

Post Reply