Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
babilie
Member
Posts: 4
Joined: 11 Jul 2018, 10:27

የደም ድፍድፍ በኦጋዴን . . . '438 ቀናት' ከተሰኘው መጽሐፍ የተተረጎመ

Post by babilie » 11 Jul 2018, 13:26

መቅድም 11
በእስር ጊዜያችን ወደ መጨረሻው አካብባቢ፥ ጊዜ ማሳለፊያ ያህል፥ ታሪካዊዋን የቫሳ መርከብ በእንጨት ቀርፀን ሰርተን ነበር። እቺን መርከብ እንደ ትሮይ ፈረስ በመጠቀም በውስጥዋ ማስታዎሻዎቻችንን ደብቅብን ለመውጣት ማሰባችንን በታማኞችቻችን በኩል አስወራን። ወሬው ተናፈሰ፥ ተራገበ ብሎም ታመነ። በዚህ ምክንያት መርከቢቷ ተወሰደች።
መርከባችን ተመረመረች፥ ተፈተሸች ግን ቤሳ ቤስቲን ማስታወሻ አልተገኘባትም። ይሁን እንጂ አንድ ያልታወቀ ነገር ይኖራል በሚል፥ ከመመለስ ይልቅ አለመመለሱ አስተማማኝ ስለሆነ መርከባችን የእስርቤቱ ኃላፊ ቢሮ ማሳመሪያ ሆና መደረደሪያ ላይ ተወድባ ቀረች።
መጨረሻ ላይ እስርቤቱን ለቅቀን ስንወጣ ከለበስነው ጨርቅና መጫሚያ በቀር ምንም ጓዝ አልነበርንም። አሳሪዎቻችን ግን ከ13 ደብተሮች ያላነሱ ጽሁፎች እና ሌላ ማስታወሻዎች ቀደም ብለው ሾልከው ስዊድን ውስጥ ይጠብቁን እንደነበር አላወቁም።
በእስር ቤት በነበርንበት ጊዜ ያጋጠመንንና ያደረግነውን ሁሉ በሚስጥር እንጽፈው ነበር። ከአንድ ሺህ ገጻት በላይ ማስታወሻዎች ከትበናል። ማስታወሻዎቹን ሊጠይቁን በሚመጡ ዘመድ እዝማድና በኤምባሲያችን ሠራተኞች አማካይነት ማሳለፍ ችለናል። ማስታወሻወቻችን ባይኖሩ በ438 ዕለታት ውስጥ የተፈጸመውን በቅደም ተከተል ማስታወስና ይህን መጽሐፍ መጻፍ እጅግ ከባድ ይሆንብን ነበር። ለዚህ ሥራችን ግብዓት፥ በጥቅሉ 1000 ገጻት ደዳቤዎች፥ ዕለታዊ ማስታወሻዎች፥ ቃለ መጠይቆች፥ የምርመራ ሰነዶች፥ ካርታዎች በእጃችን ነበሩ። በተጨማሪው አብዱላሂ ሁሴን ይዞት የወጣውን መረጃ አግኝተናል። በምርመራችን ወቅት ለተከሰስንበት ወንጀል እንደ አንድ ማስረጃ በመሆን ቀርቦ የነበረውን ፊልም ያገኘነው ከአብዱላኂ ሁሴን ነው።
አብዱላኂ ቀደም ሲል በሶማሊ ክልል የፕሬዜዳንቱ አማካሪ ነበር። በኋላ በርካታ የሥርዓቱን ግፍ የሚያጋልጡ ማስረጃዎች ይዞ ከአገሩ በመውጣት፥ ለፈጸመው ወኔ የተመላበት ተግባር በዚህ አጋጣሚ ልናመሰግነው እንወዳለን።
በ438 ቀናት ውስጥ የሚያነቡት በዕውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ትረካ አይደለም፥ ዕውነተኛ ታሪክ እንጂ። በወቅቱ የተባለውንና የተደረገውን ሁሉ በሚቻለን ጽፈናል ብለን እናምለን፥ ይሁን እንጂ ንባብን ለማቅለል ሲባል ያስተካከልነው ጽሁፍ፥ እንዲሁም አንዳንድ በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ስንል የቀየርነው ሥም መኖሩን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ማርቲን ሸቢዬና ዩናስ ፔርሾን

babilie
Member
Posts: 4
Joined: 11 Jul 2018, 10:27

Re: የደም ድፍድፍ በኦጋዴን . . . '438 ቀናት' ከተሰኘው መጽሐፍ የተተረጎመ

Post by babilie » 11 Jul 2018, 13:31

ዝግጅት

ስቶክሆልም/ ዳዳኣብ/ ናይሮቢ
ግንቦት ~ ሰኔ

ማርቲን

አርላንዳ አይሮፕላን ማረፊያ ምግብ ቤት ውስጥ ሥጋ ወጥ በድንች እየበላሁ የበረራ ሰዓቴን እጠብቃለሁ። በትልቁ የመስታውት መስኮት አይሮፕላኖች ሲነሱና ሲያርፉ እየታዘብኩ የራሴን ጉዞዎች በምናቤ አስታወስኩ። በ2010 ዓ ም ብቻ 199 ቀናት በጉዞ ላይ ነበርኩ። ላለፉት ሁለት ወራት በካምቦዲያ፥ ሲንጋፖር፥ ታይላንድና ኢንዶኔዢያ ስዘዋወር ቆይቼ ከተመለስኩ ገና ሶስት ቀኔ ነው። አሁንም ልሄድ አርላንዳ አለም ዓቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ እገኛለሁ።
ከአይሮፕላን ማረፊያው ባሻገር ያለው ተፈጥሮ የበጋው ወራት መግባቱን ያበስራል። የበጋው ወራት ሰው ከሥራ አርፎ ከተፈጥሮና ከሰው ጋር በፍቅርና በደስታ የሚያሳልፍበት ወቅት ነው። ለዚህ ነበር ከእንግዲህ ቀዝቀዝ ማለት አለብኝ ብዬ ከራሴ ጋር የተማማልኩትና ከሊንያ ጋር ከተጋባን በኋላ የመጀመሪያውን የበጋ ወራት አብረን እንድናሳልፍ ያቀድኩት።
ሊንያ፥ ትላንት ማታ ስለዚህ ጉዞዬ አንስተን ስናወራ ያለችኝ አሁን ድረስ በአዕምሮዬ ይመላለሳል። “ጭንቅላትህን ብቻ ሳይሆን ልብህንም እንድታዳምጥ ቃል ግባልኝ። ውስጥህን ቅር ካለው አታመንታ፥ ተመለስ።”
በአጉል ጀብደኝነት በጣም ጠንቀኛ ነገር ውስጥ እንደማልገባ ታውቃለች። ኔፓልና ፍሊፒንስ ውስጥ የሽምጥ ተዋጊዎችን እየተከተልኩ ራፖርት ሰርቻለሁ። በአንባገነናዊ የበርማ ግዛት ውስጥም ሥራ ሰርቻልሁ። ሁሌም ራፖርቴን አጠናቅሬ፥ ለሊንያም ስጦታዎች ይዤ በሰላም እገባለሁ።
ሞቢሌን አንስቼ ለሊንያ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ላኩ።
“ስመለስ፥ እስካሁን ያቃጠልነውን የደስታ ጊዜ በሚያክክስ መልኩ እንዝናናለን፥ ሌቭ የኔ ፍቅር። ካንቺ ጋር ውሃ ውስጥ መነከር ተመኘሁ። በጣም እወድሻለሁ። በሚድ ሰመር በዓል ቀን እስከመጨረሻው ተደሰችልኝ።”
ሊንያ ከጉዞዬ እንድም ቀን አስቀርታኝ አታውቅም። ራሴው አምኜበት እንድቀር እንጂ በእስዋ ጥያቄ ከጉዞ እንድቀር አትፈልግም። ስለሆነውም በራሴ ፍላጎት ጉዞዬን በእጅጉ ለመቀነስ ወሰኜ ነበር፥ ግን ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ የዩሃን ጥሪ ዘግይቶ ደረሰኝ። “አንድ ጸሃፊ የሚፈልግ እሳት የላሰ ጉዳይ. . . ከምን ጊዜውም የበለጥ፥ ወደፊትም ለረጅም ጊዜም ሊግጥምህ የማይችል ትልቅ ሥራ፥ አያምልጥህ።” ብሎ ነበር ያቀረበልኝ።
ከዩሃን ጋር ያለን ትውውቅ የተወሰነ ነው። ሙያዊ ነው። አንድ የፍሪላንስ ድርጅት ውስጥ እንሰራ ነበር፥ እሱ አፍሪቃና አሜሪካን ሲዳስስ እኔ በአብዛናው ደቡብ ምስራቃዊ አሲያን ይዤ ነበር። ይህ ነበር የትውውቃችን መሰረት፥ ሌላ የለም።
ባለፉት ሁለት ወራት እሱና እኔ ሐሳባት ስንለዋወጥ፥ ሊገጥሙን ስለሚችሉ ችግሮች ስንወያይ፥ የሚያስፈልጉንን ቁሶች ዝርዝር ስንመዘግብ ነበር ያስለፍነው። ገንዘብ፥ ስንቅና ትጥቃችን በተመለከተ ዝግጅታችን ከሞላ ጎደል ጥሩ ነበር ማለት ይቻላል። ስለ አካባቢው መልክዓ ምድር አቀማመጥና የዓየር ባኅሪ መረጃ ነበረን። ካርታዎችና አጥንተናል፥ ከሶማሊያ ተነስቶ ኦጋዴን ውስጥ እስካለው የነዳጅ ዘይት ጣቢያዎች ያለውን ርቀትም አስልተናል።
ኦጋዴን በምሥራቅ ኢትዮጵያ በኩል ሶማሊያን የሚጎራበት የደኸዬ በረሃማ ቦታ መሆኑን፥ ዱር ገደሉና ሜዳው በእሾሃማ ቁጥቋጦ የተሞላ እንደሆነ፥ ህዝቡ በአብዛኛው በትናንሽ መንደሮች ተሰባስቦ የሚኖርና ቀሪው በበረኃማው ዱር እየተዘዋወረ ፍየልና ግመል በማርባት ኑሮውን የሚገፋ፥ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ መሆኑን ጠንቅቀን አውቀናል።
በኦጋዴን ከርሰ ምድር ውስጥ ውድ ዘይትና ጋዝ አለ። የውጭ አገር ኩባንያዎች ይህን መዓድን ማውጣት ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናትም የነዚህን ኩባንያዎች ፍላጎትና የደሕንነት ሁኔታ በሚገባ ማሙዋላት ስለሚጠበቅባቸው የሚቻላቸውን ያደርጋሉ። በሌላ በኩል፥ ከማዕድኑ የሚገኘው ሃብት የሕዝቡ ነው፥ መንግስትና ኩባኒያዎቹ ብቻ ሃብቱን መቀራመት የለባቸውም ብለው የሚሟገቱ ሰዎችና ቡድኖች አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ድርጅቶችም፥ መንግስት ለኩባንያዎቹ መሬት ለመስጠት ሲል ነዋሪውን ሕዝብ ያፈናቅላል፥ ከመሬቱ መነሳት አሻፈረኝ ያለውን ደግሞ ይገድላል፥ ይላሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ሰዎች በግላቸው ወደ ኦጋዴን እንዲጓዙ አይፈቅድም። በዚህም ምክንያት በኦጋዴን ውስጥ ስላለው ሁኔታ የሚያውቁ ብዙ ሰዎች የሉም። ስለዚህ እዚያ እስክንደረስ ሊገጥሙን በሚችሉ መሰናክሎችና አደጋዎች ዚሪያ የተሟላ መረጃ ማግኘት በጣም ከባድ ነበር።
መደበኛ የመረጃ ምንጮች የሚባሉት እንደ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ፥ ጋዜጠኞችና የበጎ አድራጊ ደረጅቶች አነጋግረናል ይሁን እንጂ ይህን ያህል ሊጠቅሙን አልቻሉም፥ ምክንያቱን እነሱም ቢሆኑ ወደ አካባቢው ዝር እንዲሉ አይፈቀድላቸውም።
ያም ሆነ ይህ ከዩሃን ጋር የተስማማነው አንድ ቁም ነገር ነበር። ይኸውም ለራፖርታዥ ስንል ብቻ ሕይወታችንን አደጋ ላይ የሚጥል አጉል ነገር ማድረግ እንደሌለብን ነበር። ከሁሉም ነገር ደሕንነታችን መቅደም አለበት። ሌላው ሁሉ ሁለተኛ ነው። በዚህ ብንስማማም፥ አንዴ ድንበር ጥሰን ከገባን በኋላ መሬት ላይ የሚኖረው ዕውነታና የያዝነው ዕቅድ ለየቅል ሆነው እንደሚቀሩ ውስጤ ያውቅ ነበር።
ላፕ ቶፔ ላይ በፌስቡክ መልዕክት መጣ። ከዩሃን።
‘ሃሎ አይሮፕላን ማረፊያ ተቀምጠህ ራስህን እየሞላህ ነው?አይደል?’
‘ሃ !ሃ! አይ ቡና ብቻ ነው።’
‘ምን ምን ሸመትክ? ለመጫሚያ ስንት አወጣህ?’
‘አንድ ሶስት ሺ ገደማ፥ ጥሩ ጥሩ የእግር ሹራብ . . . ወፍራምና ስስ’
‘ጥሩ። ከስሶቹ ጥቂት ታውሰኛለህ።’
‘ችግር የለም። ይበቃል።’
‘ወደ ናይሮቢ ተመልሻለሁ። ኦጋዴን ውስጥ አዲስ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል። 37 ሰዎች ተገድለዋል።’
‘መቼ?’
‘ግንቦት 7’
‘ከሌላ ምንጭ በደንብ አጣርተሃል?’
‘ሞክሬ ነበር ግን እንዲህ ትኩስ ሲሆን ከነጻ ምንጮች ፍንጭ ማግኝት ከባድ ነው።’
‘ያልተረጋገጠ ዜና ማሳተምም ያንኑ ያህል ከባድ ነው።’ ብዬ ተሰናበትኩት።
አዲስ ጭፍጨፋ።
ኮምፒዩቴሩን ዘግቼ ወደ አይሮፕላኖቹ የሚወስደው ማለፊያ አቀናሁ።
የእኛ የችግር ገጠሞሽ ስሌት የተመሰረተው ኦጋዴን ውስጥ ሳንታወቅ ገብተን ሳንታወቅ እንወጣለን በሚል እሳቤ ላይ ነው። ከተያዝን ደግሞ ከሁለት ሳምንት በላይ አንታሰርም ብለን ደምድመናል። ከዚህ በፊት ኦጋዴን ውስጥ የተያዙ የውጭ ጋዜጠኞች በዚህ መልክ ነበር ኢትዮጵያ ውስጥ የተስተናገዱትና።
ወደ ኋላዬ ዞር ብዬ በግማሽ ያህል የተጓደለውን አይሮፕላን ማረፊያውን ተመለከትኩት። ወደዚህ ቦታ እንደገና ከተመለስኩ፥ ተሳክቶልናል ማለት ነው።

አይሮፕላን ውስጥ ገብቼ መቀመጫው ላይ አረፍ ብዬ ዘና አልኩ። አየር ላይ ራፖርታዡ አልተጻፈም፥ ዕድሉ ግን መጨረሻ ያለው አይመስልም። የእጅ ስልክ የለ፥ ኤሌክትሮኒክ መልእክት የለ፥ ዳመናና ከሥሩ ያለው ዓለም ብቻ ነው፥ ከርቀት ሲታይ ቀላል ይመስላል። ከተማ እንጅ ሰው ስለማይታይ፥ መርኅ እንጅ መዳረሻ ስለማይታወቅ አዎ ቀላል ይመስላል።
ጉዞ ወደ አፍሪቃ ቀንድ!
ስለቀንዱ የሚባል አንድ ብኂል አለ። “ዲያብሎስ እረፍት ሲሻ የሚሄደው ወደ አፍሪቃ ቀንድ ነው።”
ጋዜጠኛ አንደሽ ኤንማርክ ደግሞ እንዲህ ብሏል “እኛ ምዕራባዊያን፥ አፍሪቃዊያን እንዴት እንደሚሞቱ አንጂ እንዴት እንደሚኖሩ እውቀቱ የለንም።”
ይህ በምዕራባዊያን ሚዲያ ላይ የተሰነዘርው ነቀፋ አሁን ድረስ ትክክል ነው፥ ግን በመጠኑ መለወጥ ጀምሯል። አሁን አሁን ስለ አፍሪቃ ፊልሞች፥ ሙዚቃዎችና የጥበብ ሥራዎች በስዊድን ጋዜጦች ይጻፉ ጀምረዋል፥ አንብበናልም። በሌላ በኩል መከራና እልቂትን በመዘገብ በኩል ብዙ ይቀራል። በተለይ የአፍሪቃ ቀንድ ሽፋን አግኝቶ አያውቅም።
ወደ ቀንዱ የመጓዜን ጉዳይ ያማከርኳቸው የሙያ ጓዶቼ ሳይደብቁ ዕቅዴን ከዕብደት ነበር የቆጠሩት። በአንድ በኩል ትክክል ናቸው። ወደ ኦጋዴን ለመሄድ አንዱና ብቸኛው የጉዞ መንገድ የኢትዮጵያ መንግስት በሚያዘጋጀው መስመር ብቻ ነው። በዚያ መስመር ሄደህ የምትጽፈው ራፖርታዥ ደግሞ መንግስት የሚነግርህ ትረካ ብቻ ነው። እንደ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ መንግስት የሚለውንም ሆነ ተፃራሪዎቹ የሚሉትን መጻፍ ሳይሆን ራሴ በዐይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁት መዘገብ ነው የሚገባኝ።
የስዊድኑ ሉንዲን ግሩፕ የነዳጅ ኩባንያ ኦጋዴን መግባቱ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያስከተለውን መዘዝ በትክክል ለመዘገብ በሶማሊያ በኩል ወደ ኦጋዴን መግባት ብቻ ነው ያለው መንገድ። በመንግስት ወታደሮች ሳንታይ ወደ ነዳጅ ማውጫ ጣቢያው አካባቢ መዝለቅ እንድንችል ደግሞ የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) መንገድ በመምራት ሊተባበረን ተስማምቷል።

የሉንዲን ግሩብ በብዙ የአፍሪቃ ሀገራት መዓድን ሲያወጣ ቆይቷል። በደቡብ አፍሪቃ የተባበሩት መንግስታት የጣለውን ማዕቀብ ጥሶ ወርቅ በማውጣት ሥራው ብዙ ወቀሳ ደርሶበታል። የኮንጎንም ኮፐርና ኮባልት እንዲሁ ይዝቅ እንደነበር ይታወቃል። ከዚያ ወደ ሊቢያ፥ ኤርትሪያና ሶሪያ አቅንቶ ነበር። አሁን ድረስ የሚወቀስበት የደቡብ ሱዳን ነዳጅ ጉዳይም አለ። በደቡብ ሱዳን የሉንዲን ፔትሮሊየም ጋር በተያያዘ 12000 ሰዎች መሞታቸውና 160 000 ሰዎች መፈናቀላቸው በሰፊው ሲዘገብ ቆይቷል።
በኦጋዴንም ተመሳሳይ ሁኔታ እየተከሰተ መሆኑን ዓለም አቀፍ ሰብዓዊያን ድርጅቶች በመናገር ላይ ናቸው። መንደሮች መቃጠላቸውን፥ ሴቶች መደፈራቸውንና የጅምላ ግድያ መካሄዱን ይዘግባሉ። ይሁን እንጅ የሉንዲን ፔትሮሊየም ኦጋዴን ውስጥ የሚሰራውን ሥራ አይጠቅሱም። በአብዛኛው የሚታተሙት ሪፖርቶች ከቀጥተኛ ምንጭ የሚገኙ አልነበሩም። ኦጋዴን አካባቢ ማንም ድርሽ እንዲል ስለማይፈቀድ ከቦታው መረጃ ማግኘት የሚችል አልነበረም።
በበኩላችን ሉንዲን ፔትሮሊየም የነዳጅ ዘይት ኩባንያ ኦጋዴን ውስጥ ዘይት ማግኘቱን አረጋግጠዋል። ድርጅቱ ከ2006 እስከ 2009 ኒው ሬሶሉሽን ጂዮፊዚክስ በሚባል ተቋም አማካይነት ኦጋዴን ውስጥ ጥናት ያካሂድ እንደነበር የሚያስረዱ መረጃዎች በእጄ አሉ። ኒው ሬሶሉሽን ጂኦፊዚክስ ጥናቱም በሚያካሄድበት ወቅት የቀድሞ የእንግሊዝ ልዩ ኃይል ወታደሮችን ባካተተ አንድ የጥበቃ ሰራዊት ይጠበቅ እንደነበር ሁሉ አረጋግጠናል። ይህ ልዩ ሰራዊት ለኢትዮጵያዊያን ወታደራዊ ሥልጠና ይሰጥ እንደነበር የሚጠቁሙ የፎቶግራፍ መረጃዎች በራሱ በጥበቃው ድርጅት ድረገጽ ላይ ይገኛሉ።
ሉንዲን ፔትርሊየም ኦጋዴን ውስጥ ዘይት ማፈላለግም ሆነ ማውጣት የማያዋጣውና ኋላም በህግ ሊያስጠይቀው የሚችል ጣጣ ውስጥ እንዳይገባ ጄኔቫ ውስጥ የሚገኝ ሴፍስቴይናብል (Safestainable) የተሰኘ አንድ ድርጅት መክሮት ነበር። ሉንዲን ፔትሮሊየም በኦጋዴንን ዘይት ጎምጅቶ ስለነበር ምክሩን ወደ ጎን አድርጎ፥ ፕሮጄክቱን አፍሪካ ኦይል (Africa Oil) ለሚባል ድርጅት እንደሸጠ በማስመሰል በአፍሪካ ኦይል ስም ቀጠለበት።
አንድ ጊዜ ቫንኮቨር ለሚገኘው የአፍሪካ ኦይል ዋና ጽ/ ቤት ስልክ ስደውል የተቀበሉኝ ‘ወደ ሉዲን ፔትሮሊየም እንኳን ደህና መጡ! Welcome to the Lundin group!’ በማለት ነበር።

..... to be continued

babilie
Member
Posts: 4
Joined: 11 Jul 2018, 10:27

Re: የደም ድፍድፍ በኦጋዴን . . . '438 ቀናት' ከተሰኘው መጽሐፍ የተተረጎመ

Post by babilie » 12 Jul 2018, 12:56

ዩሃን/ ኬኒያ
ድምፅ መቅጃውን አስጀመርኩት። ቀዩ መብራት በራ።
‘ሶስተኛው ቃለምልልስ፥ ሶስተኛው ዕለት፥ እመቤት ቁጥር አንድ። ሳራ ዕድሜ 38።’
ከፊት ለፊቴ ፕላስቲክ ወንበር ላይ የተቀመጠችው ሴት ዐይኖችዋን ጉልበትዋ ላይ ያቋለፈቻቸው እጆችዋ ላይ ተክላለች።
‘ጁሃን ፔርሾን እባላለሁ። ጋዜጠኛ ነኝ። እዚህ ዳዳዐብ የመጣሁት ኦጋዴን ውስጥ ስላለው ሁኔታ ለማጣራት ነው።
አማኢና የምትባለው አስተርጓሚ ያልኩትን ተረጎምችላት። ሳራ ዐይንዋን ከጉልበትዋ ላይ ሳታነሳ፥ ስሜት አልባ በሆነ አንድ ወጥ ድምፅ መናገር ጀመረች፥
‘ቆራሃይ ከምትባል መንደር ነው የመጣሁ። አርሶ አደር ነኝ። ከባሌና ከልጆቼ ጋር ነበር የምኖረው።
አሚና የኦጋዴን ካርታ ላይ ቦታውን አመለከተችኝና ምልክት ጫረችበት።
ሳራ ከኦጋዴን ከወጣች ሰባት ሳምንትዋ ነው። ትውስታዋ እንዳለ ነው።
‘ወታደሮች ችግር መፍጠር ሲጀምሩ አገር ለቅቄ መሰደድ ተገደድኩ።’
‘ለምን ችግር ፈጠሩባችሁ?’ ጠየቅኳት።
‘አንድ ቀን ቀደም ብሎ ምሽት ላይ ወታደሮቹ ከአማፅያኑ ጋር ተዋግተው ነበር። ማለዳ ላይ መጠለያችንን ከበው እሳት ለቀቁበት። እኛንም መቀጥቀጥ ጀመሩ። ከዚያ አፍሰው ቀብሪደሃር ወስደው እስር ቤት ውስጥ አጎሩን፥ እኔን ባሌንና ሁለት ልጆቼን።’
‘የታሰራችሁት ስንት ትሆናላችሁ። ለምንስ ታሰራችሁ?
በሳራና በአሚና መሃል አጭር የቃላት ልውውጥ ከተካሄድ በኋላ፥ አሚና፥
‘ከአስዋ መንደር አንድ አስር ቤተሰብ ታስሯል። ምክንያቱ ደግሞ አማፅያኑን ትረዳላችሁ በሚል ነው።’ አለች።
ሳራ እንዳብራራችው ወደ ማጎሪያው የተወሰዱት በቡድን በቡድን ነበር። እዚያ ከደረሱ በኋላ ግን ለያይተው ነው ያሰሯቸው። እስዋን ወደ አንድ ትንሽ ክፍል ወስደው ስድስት ወታደሮች በየተራ እየደበደቡ ጥያቄዎች ጠይቀዋታል።
ድርያዋን ከፍታ የደረሰባት ስቃይ የሚያሳዩ ቁስሎችና ጠባሳዎች እያሳየችኝ፥
‘መላ ሰውነቴን በዱላ አላስተረፉኝም። እነማን ኦብነጎች እንደሆኑ ነበር የሚጠይቁኝ። እኔ ተራ አርሶ አደር ነኝ፥ የማውቀው ነገር የለም ስላቸው አላማመኑኝም።’
‘አስገድደው ደፍረውሻል?’
ሳራ ቀሚሷን ሰብሰብ አድርጋ ለትንሽ ጊዜ ዝም አለችና ‘እኔን አልነኩኝም። ወደ ምርመራው ክፍል ነጥለው ከመውሰዳቸው በፊት ከሌሎች ሴቶች ጋር አብሬ ታስሬ ነበር። እዚያ ትንንሾቹን ሴቶች አስገድደው ሲደፍሯቸው አይቻለሁ። አንድ ሌሊት ክፍላችን መጥተው አንድዋን እፊቴ ለአስር ሲፈራረቁባት አይቻለሁ። ሶማሊኛ ነበር የሚናገሩትና እኔን አስቀያሚ አሮጊት ናት ወዲያ በላት ሲሉ ሰማኋቸው’
አስተርጓሚዋ ስሜት የሰጣት አትመስልም። ማርቲን ሴት አስተርጓሚ እንድቀይር የመከረኝ ምክር ጠቅሟል። ምናልባት ወንድ ፊት ይህን ጉዳ አይናገሩ ይሆናል።
‘ቤተሰቦችሽስ?’
‘ከጥቂት ቀናት በኋላ እኔን እነሱ ወደታሰሩበት ግቢ ወሰዱኝ። በሕይወት አገኛቸዋለሁ ብዬ አላመንኩም ነበር። ሳገኛቸው ደስ አለኝ። ሴት ልጄን ግን አስገድደው ደፍረዋት ነበር።’
አሚና ሰዓትዋን አሳየችኝ። አስር ደቂቃ ብቻ ቀርቶናል። ከዚህ ቦታ ቶሎ መሄድ አለብን። የስደተኖች መጠለያ ከመሸ በኋላ አደገኛ ነው።
የሳራ ዘመዶች እነሱን በግቦ ለማስፈታት ሁለት ላሞች ሸጠው ነበር ግን ገንዝቡ አንድ ሰው በላይ ማስፈታት አልቻለም።
‘የተለቀቅኩ ዕለት በጠዋት ሌሎቹን ልጆቼን ይዤ ጠፋሁ። ባሌና ሁለቱ ልጆቼ እዛው ናቸው። አሁን በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም።’
ተጨማሪ ጥያቄዎች ሳሰላስል ሳራ ቀና ብላ በወቃሽ የዐይን ትክታ ተመለከተችኝ።
‘ዓለም እንዲደርስልን ያስፈልጋል። ከኦጋዴን የመጣ ሰው ሁሉ የሚናገረው አንድ ዓይነት ታሪክ ነው። ግን የሚደርስልን አላገኘንም።’
ለቃለምልልሱ አመስግኜያት እቃዬን ስሰበስብ፥ እስዋም ብድግ አለች።
‘በኦጋዴን የሚፈፀመውን ለዓለም አጋልጣለሁ። የነገርሽኝን እነግራለሁ።’ ስላት ትከሻዋን ነቅንቃ ፊትዋን ወደ ጊዚያዊው የስደተኞች መጠለያ አዙራ መንገድ ጀመረች።
ጠርቼ፥ እኔ እንደ ሌላው የተስፋ ቃል ብቻ ሰጥቼ የምሄድ እንዳልሆንኩ፥ እንዲያውም ታሪኩን ወንጀሉ ከተፈፀመበት ቦታ ድረስ ተከታትዬ ለዓለም የማጋልጥ እንደሆነ ለነግራት ዳዳኝ። ግን ምላሴን ሰበሰብኩ። ይህን ዕቅድ አስተርጓሚዋም እንኳን ማዋቅ የለባትም። ኦጋዴን ውስጥ በድብቅ የመግባት ዕቅዳችንን ማንም ማዋቅ የለበትም። ማንም።

ነገሩ ሁሉ የጀመረው ከአንድ አመት ተኩል በፊት ነበር። እኔና የሥራ ባልደረባዬ ኣና ሮክስቫል የአፍሪቃ ቀንድን ችግር ለመዘገብ ኬንያ ውስጥ ዳዳዐብ ከሚባለው ትልቁ የስደተኞች ካምፕ ድረስ መጥተን ነበር። አመጣጣችን በእርስ በርሱ የሶማልያ ጦርነትና በረሃብ ምክንያት ከሶማሊያ የሚፈናቀሉትን ስደተኞች በተመለከተ ራፖርታዥ ለመስራትና ሁኔታ ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ነበር። በወቅቱ ከሶማሊያ የሚጎርፈው ሕዝብ ቁጥር ስፍር አልነበረውም።
የተባበሩት መንግስታት ስደተኛውን የሚመዘግብበት የዶሮ ቤት የመሰለው ቢሮ ድረስ የሚመጣው ተስፋ የቆረጠ ህዝብ ቁጥር በየዕለቱ ሲጨምር ታዝበናል። እኛም ብዙ ሰዎችን ስናነጋግር ሶማሊዎቹ ይነግሩን ከነበረው ለየት ያለ ታሪክ የሚያወጉን ሰዎችም ይመጡ ጀመር።
ከሶማሊያ የሚሰደዱት የሚያወሩት ታሪክ ረሃብ ነክ ሲሆን አዲሶቹ የሚያወሩት በመንግስት የሚደርስባቸውን ግፍ ነበር። እጅግ የሚዘገንን ግፍ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች የመጡት ከኢትዮጵያ፥ ከኦጋዴን ነበር። ሁለቱም ወገኖች ከሰማሊያና ከኢትዮጵያ ይምጡ እንጂ በምንም መለየት የሚቻሉ አይደሉም። ቅኝ ገዢዎች ማን የት አለ ሳይሉ ድንበሩን በማስመሪያ አስምረው ሲቀራመቱ ህዝቡን ከሁለት አገር ለዩት እንጂ አንድ ሕዝብ፥ አንድ ሃይማኖት፥ አንድ ቋንቋና ባህል ነው።
ያ ቅኝ ገዢዎች ያሰመሩት ድንበር ቅርብ ጊዜ ድረስ ሁለቱን መንግስታት ሲያጋጭ ነበር። በ1970 ዎቹ ላይ ሁለቱም መንግስታት ኦጋዴንን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገብተው ነበር። መጨረሻው በኢትዮጵያ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ፥ በሶማሊያ የነበረው ማዕከላዊ መንግስት ፈርሶ ሕዝቡ ወደ ርስበርስ ጦርነት ገባ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር በ1984 ላይ ተቋቋም። ከዚያን ግዜ ጀምሮ በአካባቢው ሰላም አለ ማለት አይቻልም።
ኦጋዴን በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ፥ በዓለምም ከሉ አካባቢዎች ሁሉ እጅግ የደኸየ አካባቢ ነው። ግን በኦጋዴን ምክንያት የሚነሳው ግጭት የግዛት ጥያቄ ብቻ አይደለም። ዘላኑ ህዝብ ሲንቀሳቀስ ከሚያቦነው አመዳም ምድር ሥር ትልቅ ሀብት አለ~ ዘይት። የነዳጅ ዘይት። ይህ ዘይት ሐብት ብቻ አይደለም፥ ኃይልም ነው።
በዚህም ምክንያት በግጭቱ ውስጥ እጃቸው የተነከረ ሶስተኛ ተዋንያንም አሉ~ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች።
ኣፕሪል 24 2007 ፔትሮናስ የሚባል ዘይት አውጪ ኩባኒያ ኦጋዴን ውስጥ ኦቦሊ ከሚባል ስፍራ በኦብነግ ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶበት 74 ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ተዘግቦ ነበር። ኦብነግ ራሱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ 200 የመንግስት ወታደሮች መደምሰሱን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ጥቃቱን በደመ ቀዝቃዛነት የተፈጸመ ጭፍጨፋ ሲል ገልጾታል። ማንም ምን ይበል አንድ ፍንትው ብሎ የወጣ ነገር ቢኖር፥ የግጭቱ ዋና መንስኤ ዘይት መሆኑ ነበር።
ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ኦጋዴንን በብረት አጥር አጠራት ማለት ይቻላል። በኦጋዴን የምግብና የመድሃኒት እርዳታ የሚለግሱ ድርጅቶችን፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትንና ቀይ መስቀልን ሳይቀር ከአካባቢው እንዲወጡ አደረገ። ዘይት አውጪ ኩባኒያዎች ሥራቸውን ለመቀጠል አስተማማኝ ጥበቃና ደሕንነት እንደሚያሻቸው በማሳሳበቸው ምክንያት መንግስት አካባቢውን የማጽዳት ዘመቻ ጀመረ። መንደሮች ተራ በተራ በእሳት ጋዩ። ሰዎች ይታፈሱና በማጎሪያ ቤት ይወረወሩ ጀመር። በእስር ቤት ግድያ፥ ሰቆቃና አስገድዶ መደፈር የኦጋዴኖች እጣ ፈንታ ሆነ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ወደ አጎራባች አገሮች ተሰደዱ።
ማንም ሁኔታው ሊዝብግብ ኣልቻለም። ከኦጋዴን የሚወጣ ወሬ ጠፋ። የውጭ ጋዜጠኛች እንዳይገቡ ቪዛ ይከለከላሉ። የአገር ውስጥ ጋዜጠኛችም አንድ ቃል ቢተነፍሱ ዘብጥያ ይወርዳሉ። በ2007 ሶስት የኒውዮር ታይምስ ጋዜጠኞች በጓሮ ሊገቡ ሞክረው ነበር። ግን ተይዘው ተባረሩ።
እኔና ኣናም የስዊድኑ ሉንዲን ግሩፕ ኦጋዴን ውስጥ መግባቱ ስንሰማ፥ ከነሃሴ በፌት ማለትም ኣፍርካ ኦይል ዘይት ማውጣት ሲጀምር፥ ኦጋዴን ውስጥ ለመግባት ወሰን። ግን አና በወቅቱ ስላረገዘች ማርቲን ሸቢዬ እስዋን ተካ። እሱም ቢሆን ቀድሞ የጀመረው ራፖርታዥ ስለነበረ በታቀደው ሰዓት ሳይሆን ዘግየት ብሏል። ለዚህ ነው አሁን ዳዳዓብ ውስጥ ብቻዬን ያለሁት።

ዳዳዓብ። እንደ ወፍ ቤት በጭራሮ የተሰራች መናኸሪያ፥ የሰው ልጅና እንሰሳት በአንድ ውለው በአንድ ላይ የሚያድሩባት መንደር። የስደት ከተማ!
ዳዳአብ ቡኒ ነች። መሬቱ፥ ሰዉ፥ እንሰሳው ሁሉ አመድ ለብሶ አንድ ከለር ይዟል። ቡኒ ቀለም። USAID የዩኤስ ኤይድ ብራማ ኮንሰርቫና UNHRC የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተካከላቸው ነጭ ድንኳናት በቀር ሁሉም ቡኒ ነው፥ አመዳም።
ባለፈው ዳዳዓብ የነበርኩ ጊዜ የስደተኛው ብዛት 300 000 ነበር። ዛሬ ግማሽ ሚሊዮን ገብቷል። የስደት ከተማዋ መሃል ተመድ የራሱን ሴንተር አጥሮ በታጠቁ ሰዎች ዙርያውን ያስጠብቃል። የሚገባና የሚወጣ ሁሉ በጥበቃዎች በኩል ነው። ብዛትና እርዛት ከፍተኛ መጨናንቅ ፈጥሯል። አዲሱና ነባሩ ስደተኛም የሚኖሩት አብረው ስለሆነ መግባባት የለም፥ በሳቢያው መረጋጋት የለም።
ነባሩ ኑሮ ተክሏል። የጓሮ አትክልት የተካከሉ፥ ሱቅ የከፈቱ፥ ሻይ፥ ቡና፥ ምግብ ቤት የመሳሰለ ቢዝነስ የጀመሩ አሉ። ብዙዎቹ ወጣቶች እዚያው የተወለዱ ናቸው እናም ለነሱ ሕይወት ይኸው ነው። ሌላ አያውቁም። ካምፑን ለቆ መውጣት አይፈቀድም። ወጥቶ የሄደ በኬኒያ ፖሊስ ማንቁርቱን ተይዞ ይመለሳል።
ጀንበር ስትጠልቅ እኔም ወደ ማደሪያዬ ገባሁ። አሁን የማድረው ተመላልሾችና ነጋዴዎች ከሚያድሩበት አንዳንድ ክፍል ኣለው ባራክ የመሰለ ነገር ውስጥ ነው። ኣና የነበረች ጊዜ ከትላልቅ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች የተደረጉልንን ግብዣዎች የሚያሳዩ ወረቀቶች ይዘን ስለነበር የማደሪያ ችግር አልነበረብንም። አሁን ግን ከማርቲን ጋር ያቀድነው ፕሮጀክት ብዙ ብኄራዊ ሕጎችና ደንቦችን የሚጥስ ስለሚሆን እነዚህ ስመ ጥር ድርጅቶችን ማነካካት አልፈለግንም። ስለሆነም የምሰራውና የምንቀሳቀሰው በግሌ ነው።
የካሜራ ቦርሳዬን ከላዬ ላይ አራግፌ፥ ቡትስ መጫማዬን አወልቅኩና የውሃ ኮዳዬ ከአልጋዬ ላይ አንስቼ ውስጡ የነበረውን ውሃ ጨለትኩት። ፊቴን ልታጠብ ባንቧውን ከፈትኩ ግን አጎነፋፍቶ ጸጥ አለ። ያቺኑ ኮዳዬ ላይ የቀረችውን ፊቴ ላይ አፈሰኳት፥ ውሃው ወደ ቡኒ፥ እንዲያውም ወደ ጥላሸት ተቀይሮ ወረደ።
ከዲዝል ጄኔረተር የተዘረጋ ኤሌክትሪክ አለ። አልፎ አልፎ ይቋረጣል፥ አና እሱም ሳይሄድ በዕለቱ የቀረጽኳቸውን የቃለምልልስ ምስሎች ከካሜራው ሜሞሪ ካርድ ወደ ኮምፒዪቴር ጫንኩ። ከዚያ የፋይሉን ይዘትና ጥራት ለማየት አለፍ አለፍ እያልኩ ስመለከት ቆየሁና መሃመድ የተባለ የ40 ዓመቱ ዘላን ጋር ደረስኩ። ዘይት ከሚወጣበት ጄሂዲን ከምትባለው ሰፈር አጥገብ ከምትገኝ፥ ኤል ኦጋዴን ከምትባል መንደር ነው የመጣው። ከመሃመድ ጋር የሁለት ሰዓት ቃለምልልስ ነበር ያደረኩት።
‘የስምንት ልጆች አባት ነኝ። የማለዳ ፀሎት ለማድረስ ስነሳ የመንግስት ወታደሮች ቀያችንን ከበው ሕዝቡን ያዋክባሉ። ሴቶች ባሎቻቸውን ይጣራሉ፥ ይጮሃሉ። ዙሪያ ገባው እሳትና ጭስ ነው። ቤቴ ሲቃጠል ቆሜ አይቻለሁ።’
መሃመድና ሌሎች 17 ወንዶች ወደ ቁጥቋጣማ ቦታ ተወስደው ከቆዩ በኋላ ከመካከላቸው አንድ ወጣት አማፂ ነው ተብሎ ሊረሽኑት አወጡት። አንድ አባት ወጣቱን ለመታደግ ~ የለም ተሳስታችኋል። ልጁ እረኛ ነው በማለት ተቃወሙ። ወታደሮቹ ሽማግሌውንና ወጣቱን፥ ሁለቱን በአንድ ላይ እንደረሸኑ መሃመድ ይናገራል። ከዚህ ትይንት በኋላ መሃመድ ከእገታው አምልጦ ሁለት ሳምንት የሚወስደውን ጉዞ ወደ ዳዳአብ ጀመረ፥
‘ለምን አንዲህ ዓይነት ጥቃት እንደፈጸሙብን አይገባኝም። ወታደሮቹ የሚሉት አማፂያኑን ተረዳላችሁ ነው። ግን ትክክለኛ ምክንያቱ እሱ ሳይሆን፥ ዘይት ከሚያወጡበት ቦታ አጠገብ መኖራችን ይመስለኛል።’
ሌላ ፋይል ከፈትኩ። ፋራህ የ32 ዓመት እድሜ አለው። በቅርብ ከሺላቦ በስተምዕራብ ላዓሶሌ ከምትባል መንደር ነው የመጣው። ባለፈው ዓመት ውስጥ በእሳት ጋይተው የወደሙት ስምንት መንደሮች ካርታዬ ላይ ጠቁሞ ያሳየኝ እሱ ነው። በነዚህ መንደሮች አጠገብ በመንግስት ወታደሮችና በአማፅያኑ መሃል ውጊያ ተካሂዶ እንደነበር ፋራህ ያብራራል። እሱ የመጣባት መንደር ራስዋ በኦብነግ ቁጥጥር ሥር ወድቃ መቆየትዋንና ኋላ ኦብነግ መንደሪቱን ለቅቆ ሲወጣ የአጎራባች መንደሮቹ ዕጣ ፈንታ እንደደረሳት ይናገራል። ፋራህ ራሱ የተያዘው በዚህ ወቅት ነበር። ተይዞ የሰቆቃ ምርመራ ተፈጽሞበታል።
ከመተኛቴ በፊት አንድ ሌላ ፋይል ከፈትኩ። ቡራሌ የ42 ዓመት ዕድሜ ያለው የቀድሞ የዘይት ኩባንያው ሰራተኛ። ከሺላቦ። ወደ ዳዳዓብ የመጣው በ2008 ነው። ቀደም ሲል ጄህዲን ውስጥ ለሁለት የተለያዩ የዘይት አውጭ ኩባንያዎች ሰርቷል። ይሁን እንጂ እነዚህ ኩባንያዎች ሥራ ቢፈጥሩም ይዘውት የመጡት መከራ ስለሚበልጥ አካብባቢው ለቅቀው ቢወጡ ይመርጣል።
‘በእነሱ መምጣት ያገኘነው ምንም ጥሩ ነገር የለም።’
ኮምፒዩተሩ አጥፍቼ ወደ መኝታዬ ስጠቀለልል፥ የቡራሌንና የሌሎቹን አባባል በአንድ አረፍተ ነገር ጠቀለልኩት። “ፈጣሪ ሆይ ይህን ዘይት በመሬታችን ውስጥ እንዳሰፈርክ ሁሉ፥ እባክህ ከመሬታችን ውስጥ አጥፋልን።”

ዐይኔን ጨላማው ላይ አንሳፍፌ በሃሳቤ ቀን ያገኝኋቸው ሰዎች መጡ። ሁዳ፥ በስምንት ወታደሮች ተደፍራ ፅንስዋ የተጨናገፈባት እመቤት፥ መሃመድ፥ የዘር ፍሬው ተጨፍጭፎ መቀመጥና መራመድ የተሳነው ጎረምሳ፥ እንዲሁም አብዱላሂ፥ ወንድሙ እፊቱ ሲረሸን ያየው ከፊቴ አልሄድ አሉ። የመጡበትን መንደር ካርታዬ ላይ ምልክት አድርጌበታለሁ። ከፍተኛ በደልና አሰቃቂ ግፍ በብዛት የሚታየው ዘይት ከሚወጣበት አካባቢ ባሉ መንደሮች ላይ ነው።
ዘይት አውጪ ኩባኒያዎቹ የደሕንነት ጥበቃ ዋስትና ሲጠይቁ በነዋሪው ሕዝብ ላይ የሚያስከትለው መከራ ይረዱት ይሆን? ስዊድን ውስጥ ያለው አክሲዮን ተካፋይ ተራ ሰው ገንዘቡ ምን ያህል እልቂት እንደሚፈጸምበት ይረዳል? ለመሆኑ ስንቱ ነው ግድስ ያለው?
ሁሉም ነገር እንዳቀድነው ከሄደ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዝኤ ውስጥ ኦጋዴን ውስጥ እንገባለን። ካልተሳካ ግን በቃ ምንም አልተራመድንም ማለት ነው። ሌሎች ከተረኩት በላይ የምንለው ነገር አይኖርም።
ወደ ዳዳኣብ ከመጓዜ በፊት ናይሮቢ ውስጥ መጨረሻ ላይ ያገኘሁት፥ የኔንና ማርቲንን ከኦብነግ ጋር የሚያገናኘን ሰውዬ እንዳረጋገጠልኝ ከሆነ፥ ወደ ኦጋዴን ለመግባት ምንም ችግር የለም። ‘ሁሉም ነገር በቁጥጥር ሥር ነው።’ ነበር ያለኝ። እውነቱን ከሆነ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የምናውቀው ይሆናል።

ጉዳይ ፈጻሚ አብዱላሂ ገንዘብ አይበቃውም። ለያንዷንዷ ኢንች ሳንቲም መከፈል አለበት። ጫት ከአፉ አይጠፋም። ታዲያ ቀጠሮ አያከብርም እንጂ ያለውን የሚያደርግ ሰው ነው።
‘እሺ ዛሬ የትኛው ካምፕ ነው የምንሄደው’ አልኩት አብዱላሂን።
‘ሃጋዳራ።’
‘እዛማ በፖሊስ ታጅበን መሆን አለበት።
‘ምን ችግር አለው፥ ፖሊስም አመጣለሁ።’ አለኝ።
ከአምስት ደቂቃና ከአምስት መቶ ሽልንጎች በኋላ አብዱላሂ ሁለት የታጠቁ ፖሊሶች ከተመድ ጽ/ቤት ጥበቃ ሥራቸው አስኮብልሎ አመጣቸውና በጂፕ መኪና ጉዞ ጀመን። እኔ ከኋላ ሁለቱ ፖሊሶች መሃል ቁጭ በዬ አቧራ እያቦነንን የአሸዋ መንገዱን ተያያዝነው።
ሃጋዳራ ያገኘሁት የቀድሞ የሶማሊ ክልል ልዩ ፖሊስ አባል የነበረ ሰው ነው። አብዲ ይባላል። እዚህ ከመጣ አምስት ወራት አሳልፏል። አብዲ ካርታ ላይ አንዳንድ መንደሮች እየጠቆመኝ እያለ ዐይኑ እንባ ያሲቀርር ታዘብኩ። ካርታውን አጣጥፎ አሸዋ ላይ አኖረና በእጁ እንባውን አብሶ ወደኔ ቀና አለ።
‘እነዚህ መንደሮች ውስጥ የተፈጸመውን በየቀኑ አስባለሁ። እኔ አንድ ሰው አልገደልኩም። አንድ ጥይት ኣልተኮስኩ፥ ለዚህ ነው እዚህ ያለሁት። ሰዎችን እንድናሰቃይና እንድንገድል ያስገድዱን ነበር።’
‘በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን በሚል ወጣቶችን በገፍ ሰብስበው ነበር የቀጠሩን። እልፈልግም ማለት አይቻልም። ወይ ኦብነግ ተብለህ ትፈረጅና ፍዳህን ታያለህ፥ አሊያም ልዩ ፖሊስ ሆነህ ሌላው ፍዳ ታሳያለህ። ከዚህ ውጭ ምርጫ የለም።’
ልዩ ፖሊስ የተቋቋመው ኦብነግ በ2007 ላይ የዘይት ማውጫ ጣቢያው ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ነበር። ልዩ ኃይሉ የሶማሊ ተወላጆችን ብቻ የያዘ አሃዱ ነው። አሁን ይህ አሃዱ የፓራሚሊታሪ ደረጃ ላይ ደርሶ የሚታዘዘው በክልሉ የፀጥታ አዛዥ፥ አሁን የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሃመድ ኡማር ነው። ግጭቱ በኢትዮጵያ መደበኛ ሰራዊትና በሶማሌዎች መሃል መሆኑ ቀርቷል። ተወላጁ እርስ በርሱ እንዲተላለቅ የተዘየደ ሥልት ይመስላል።
አብዲ፥ በሐምሌ ወር 2010 ላይ የልዩ ኃይሉን ብጫ መሳይ የደንብ ለብሶ ፋንፋን ከምትባል መንደር ውስጥ ነበር፥ አፍሪካ ኦይል ነዳጅ ከሚያወጣበት አንድ 6 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ። እዚያ ቦታ ላይ ላይ አማፅያኑ አንድ የመንግስት ጦር ቡድን ላይ ጥቃት ሰንዝረው ጉዳት አድርሰው ነበር። በዚህ ምክንያት ፕሬዝዴንቱ ለተሰበሰበው የልዩ ጦር ሰራዊት “እዚህ አካባቢ ሲቪል ሰው የለም።” በማለት የሰጠውን ትዕዛዝ መቼም አይረሳውም።
“ወታደሮቻችንን የገደሉት የመንደሩ ወጣቶች ናቸው። ስለሆነም ሁሉንም እንደመስሳቸዋለን። እረኛውን ሁሉ ቢታጠቅም ባይታጠቅም በሉዋቸው”
‘በእውነት እንዲህ ዓይነት ትዕዛዝ ሰጥቷል?’ በማለት ዐይኑን ትክ ብዬ እያየሁ ጠየቅኩት።
አብዲ ዐይኔን እያየ ራሱን ነቀነቀና፥ ‘መጀመሪያ የሄድነው አንድ አባት፥ እናት፥ ሶስት ሴቶችና አራት የአስራ ቤት ልጆች ያሉበት ቤት ነበር። ሁሉንም ከጎጃቸው ደጃፍ ደረድረን ረሸናቸው። ከርሽናው የተረፈው አንዱ፥ “ሽፍቶች አይደለንም። ኦብነጎች አይደለንም፥ እባካችሁ ተውን” ሲል ለመነን። በዚህ ወታደሮቹም የሆነ ስሜት ተሰምቷቸው ማንገራገር ሲጀምሩ አለቃችን “የፕሬዜዴንቱ ትዕዛዝ ነው፥ እኛ ወታደሮች ነን ቀጥሉ!” በማለት ተቆጣ። ያን የተረፈ ወጣትም ጨርሰነው ቀጠልን።
‘የሚቀጥለው ጎጆ ውስጥ ሶስት የአስራ ቤት ልጆች የነበሩበት ነው። እኛን እንዳዩ ልጆቹ እጆቻቸውን ወደ ላይ አውጥተው ማልቀስና መለመን ጀመሩ።’
አብዲ ዝም አለ።
‘አና?’ አልኩት።
‘ያማል። በጣም የሚያም ነገር ነው። እነሱን ደፍተን ቀጠልን። አጎራባች መንደሮቹንም እንዲሁ። በሰባት ቀን ዘመቻ 170 ሰዎች ጭፍጭፈናል።’
‘ቁጥሩን እንዴት በእርግጨኛነት ልታውቅ ትችላለህ።’
‘በያንዳንዶ ገዳይ ቡድን ውስጥ አንድ ቆጣሪ ተመድቦ ነበር።’
ይህ ሁሉ ሲካሄድ አብዲ አንድ ጥይት አለመተኮሱ ተነቅቶበት በቁጥትር ስር ዋለ፥ ወደ እስር ቤትም ተወረወረ። ከእስር አምልጦ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ ነው ኬንያ የገባው።
‘ከፊቴ የማይጠፋው’ አለ አብዲ፥ ‘ከፊቴ የማይጠፋው አንድ በወራት ብቻ የሚቆጠር ዕድሜ ያለው ሕፃን ነው። እናቱን ገድለን እሱን ሜዳ ላይ ጠለነው ሄድን። ጥለነው ስንሄድ ያሰማ የነበርው ለቅሶ በየሄድኩበት ይከተለኛል። ይሄኔ ጅብ በልቶት ይሆናል። አሁን ሕፃናት ሳይ ራሴን ያመኛል፥ ሳላብድ አልቀርም።’
ከምሳ በኋላ ያነጋገርኩት ኢሊሌ ከምትባል ትንሽ መንደር የመጣውን ኡመርን ነበር። ኢሊሌ ኣፍሪካ ኦይል ዘይት የሚያያፈላልግበትን አካባቢ ከሚዋሰነው ከጎዴ ከተማ አጠገብ ትገኛለች።
ኡመር እንዳወጋኝ ከሆነ የሕዝቡ መከራ የጀመረው ቀስ እያለ ነበር። መጀመሪያ የርዳታ ድርጅቶችን ለቀው እንዲወጡ አደረጓቸው። እነሱ ሲወጡ ህዝቡ ምግብና ሕክምና አጣ። የነዳጅ ዘይት ያለበት አካባቢ ለም ሳር ስላለ ከብቶቻችንን ለግጦሽ የምንወስደው ወደዚያ ነበር። እዚያ ይሚደርስ ከብት እዚያው ይቀረል። የወታደሮች ስንቅ ይሆናል።
‘አንድ ቀን እኔ ከሁለት ሰዎች ጋር ያዙኝ። እጆቼን በኤሌክትሪክ ሽቦ የኋሊት አስረው ወደ ጎዴ አይሮፕላን ማረፊያ ወሰዱኝ። እዚያ እንደደረስን ይደበድቡን ጀመር።’ አለና ሸሚዙን ሰብስቦ ጠባሳውን አሳየኝ።
‘ለአምስት ወራት ያህል እዚያ አቆዩኝ። የጎድን አጥንቴን ሰብረውታል። ደም አሳታውክ ነበር። የኦብነግ አባል መሆኔ እንዳምንላቸው ነበር የሚፈልጉት።’
ሌላ የግፍ ታሪክ። አንድ ሰው ምን ያሕል መስማት ይችል ይሆን?
አህመድ ከሽሂላቦ። መታወቂያው፥ የኢትዮጵያ የጋዝ ኃይል ድረጅት (Calub Gas SC) ሰራተኛ እንደነበር ያሳያል።
አህመድ እንደሚለው ከሆነ፥ ከተወሰኑ ዓመታት ቀደም ብሎ መንግስት አንድ ማሳሰቢያ በየመንደሩ ለጥፎ ነበር። ማስታወቂያው፥ ማንኛውም ሰው የዘይት ኩባንያዎች ካሉበት ሥፍራ 15 ኪሎሜትር ውስጥ እንዳይገኝ የሚያስጠነቅቅ ነበር። አህመድ ራሱ ሕዝቡን ከሥፍራው የሚያባርሩ ወታደሮችን በካምዮን ይጭን ነበር። አንድ ወታደራዊ አዛዥ ሕዝቡ አካባቢውን ለቆ እንዲሄ ሲያስጠነቅቅም በቦታው ሰምቷ። ሕዝቡ ግን ባለለሥልጣናቱ በሰጡት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሥፍራውን አለቀቀም። ከብቱን የሚያበላበት ለም አካባቢ ስለሆነ ህዝቡ መነሳት አይፈልግም። ስለዚህ ወታደራዊ ግብረ ኃይል ሄዶ በአንድ ቀን 60 ቤተሰብ አባረረ።
60 ቤተሰብ ማለት ከ400 እስከ አምስት መቶ ሰው ማለት መሆኑን አሰላሁና፥
‘የነዳጅ ኩባንያዎቹ በወታደር እንደሚጠበቁ ያውቃሉ?’ ስል ጠየቅኩት።
‘እንዴታ! በደንብ ያውቃሉ። ያለወታደር አጀብ በአካባቢው እንዳንቀሳቀስ ሁሉ ተነግሮናል።’
አህመድ ፎቶ እንዳነሳው ፍቃደኛ አይደለም፥ ግን ትረካውን የሚደግፉ ሌሎች ሰነዶች ነበሩት።
‘የነዳጅ ኩባኒያዎቹ ሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን ግፍ የሚያውቁ ይምችስልሃል?’
‘አይመስለኝም። ነዋሪው ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ ለውጭ ሰዎች እንዴት ይነግራሉ?’

ከትንሽ ቀናት በኋላ ናይሮቢ ውስጥ ኢስትሊ ከምትባለው ክፍለ ከተማ ሆቴል በረንዳ ላይ ሆኜ አካባቢው ቃኘሁ። ኢስትሊ በረጅሙ የሶማሊያ እርስ በርስ ጦርነት ዘመን የሶማሊያ ኢኮኖሚ ሞተር ሆና ቆይታለች። ብዙ ሶማሊዎች የሚኖሩት እዚህ ነው። በቅርቡ የታነጹ ሆቴሎችና ንግድ ቤቶች ክፍለ ከተማዋን አሳድገዋታል። የኢኮኖሚው ምንጭ በከፊል ሕጋው ባልሆነ የጫትና የማሳሰሉ ምርቶች ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እንደሆነ ይጠረጠራል።
በተሽከርካሪና በሰው የተጨናነቀውን የኢስትሊን ዋና መንገድ እየታዘብኩ የእጅ ስልኬ ተንቀጠቀጠ። መልዕክት ከማርቲን፥ “አሞራው አርፏል~ከ10 በኋላ እዚያው” ይላል።
ፍርሃት ብጤ ሰውነቴን ሲወረው ተሰማኝ። የዝናቡ ወራት ገብቷል። የኛም ዕቅድ አማፅያኑ የሚጠቀሙባቸው የውሃ ጉድጓዶች ሳይደርቁ መግባት ነው። አልያ ለውሃ ስንል ማሕበረስቡ ወዳለበት መጠጋት ሊኖርብንና በሳቢያው ለመጋለጥ ልንዳረግ እንችላለን።
ወደ ክፍሌ ገብቼ አልጋ ላይ ጋደም አልኩ። ከኦብነግ ጋር የሙያገናኘን፥ መሃመድን አንድ ቀን ሙሉ አልደወለም። ከሱ ጋር መጨራሻ ላይ የተነጋገርነው ወደ ካልጋዩ የምናደርገው ጉዞ በአራት ቀና ወደፊት መራዘሙን ነበር። ወደ ኦጋዴን ለመግባት ያቀድነው በካልጋዩ በኩል ነው። እሱን እያሰብኩ መሃመድ ደወለ።
‘እንዴት ነው?’ አልኩት ቃል ሳይተነፍስ፥ በትንፋሹ ብቻ አውቄው።
‘መልካም ነው ግን ከወዲያኛው በኩል አሁንም መገናኘት አልቻልኩም። ምናልባት ነገ’።
‘እንዴት እንደዚህ ይሆናል?’ አልኩት በስጨት ብዬ።
‘ለወራት ዕቅድ አውጥተናል፥ ግን የደሕንነት ጉዳይን ከእኛ ውጭ ያሉ ሁኔታዎችም ይወስኑታል።’
‘ኦኬ ግን ሁሌ አዎ አዎ ። ሁሌ ችግር የለም፥ ችግር የለም ብቻ ነው፥ የምትለው። ችግር ካለ ንገረኝ፥ ማወቅ አለብኝ።’
‘በውነት ችግር የለም።’ አለና መሃመድ ሳቁን ለቀቀ። እኔም አብሬ ሳቅኩ።
‘ኢሻላ’ አልኩ በመጨረሻ ‘ያሻችሁን ጊዜ ውሰዱ። ዋናው መግባታችን ነው። ዓለም ሰለ ኦጋዴን ማወቅ አለበት። እንጠብቃለን።’
‘ሶማሊያ ውስጥ ያልታጠቀ ሰው የለም። ሁሉም መሳሪያ አለው። የናንተ ጠባቂዎች ጋልካዮ ካሉት ታጣቂዎች በላይ እንዲታጠቁ ያስፈልጋል። ያንንም እናመቻቻለን።’ አለ በመጨራሻ።

ሽሽ ሸሚዝ ለበስኩና አንድ ጉርሻ ትንባሆ ድዴ ሽር ወሽቄ እንደገና ወደ ብርንዳው ወጣሁ። እኩለ ለሊት አልፏል ግን ከተማው አላንቀላፋም። እንቅስቃሴ አለ። አንድ መኪና ሆቴሉ ብራፍ ላይ መጥታ ቆመች። ማርቲን!
በባዶ እግሬ ወደ መግቢያው ሮጥኩ። ተሳሳቅን። ተቃቀፍን። ሻንጣዎቹን ተከፋፍለን ይዘን ገባን።
‘እንኳን መጣህ። ብቸኝነት እንዴት ይደብራል።’
‘በኔም በኩል ያው ነው። አሁን ቦታው ላይ ነን። ሥራ መጀመር ነው።’
የገዛኋቸውን አዲሱን ካሜራ፥ ተጨማሪ ሃርድ ዲስክ፥ ባትሪዎችና ሳትላይት ቴሌፎን አሳየሁት። እሱም ይዞ የመጣውን ቁሳቁስ ከሻንጣው አዋጣ። አንድ ሃምሳ ፈሳሽ ፕሮቲን፥ የሰውነት ፈሳሽ መተኪያ ቅመም፥ ባክቴሪያ ማጠቢያ አልኮል፥ የመጀመሪያ እርዳታ መሽጫ ቁሶች፥ ፕላስተሮች፥ አልቬዶን፥ ቮልታሬን፥ ትንኝ መከላከያ መረብ፥ ውሃ ማጣሪያ ክኒን . . .
‘ከኦብነግ ጋር ግንኙነት እንዴት ነው? ግሪን ነው?’ ማርቲን ጠየቀኝ።
‘ትንሽ ወዲህና ወዲያ ነገር አለ።’ አልኩት። ‘በቅርብ መመሪያ የሚሰጠን ሰው ይመጣል። መሄጃችን ቀን ግን በአራት ቀናት ተላልፏል።’
‘ዳዳኣብስ?’
‘እሱን በአንድ ቃል ሳጠቃልለው፥ ገሃን ነብ እለዋለው።’
ስለኦጋዴን በቃለ ምምልልስ የሰማሁትን እያወራሁለት ተኛን።


... to be continued

babilie
Member
Posts: 4
Joined: 11 Jul 2018, 10:27

Re: የደም ድፍድፍ በኦጋዴን . . . '438 ቀናት' ከተሰኘው መጽሐፍ የተተረጎመ

Post by babilie » 17 Jul 2018, 08:30

ማርቲን
ከናይሮቢ እስክንወጣ አንዳንድ ስደተኛችን ማነጋገር አስበን ከሆቴላችን፥ በመኩና የአንድ ሰዓት መንገድ ራቅ ብለን አንድ ትንሽ ክፍል ተከራየን። መሃመድ እዚያ ድረስ ሰደተኞችን ያመጣል። እኔ እጠይቃለሁ ዩሃን ፎቶና ፊልም ያነሳል።
የመጀመሪያው ሰው አንድ ወጣት ነው። ተማሪ መሆኑንም ነግሮናል።
‘ሰው ነጮቹ የመጡት ነዳጅ ፍለጋ ነው ይላል። እሱ ማስመሰያ ነው። የሚፈልጉት ሌላ ነገር ነው። አንድ ትልቅ ማግኔት መረብ ዘርግተው በአንድ ኪሎሜትር ካሬ ዙሪያ ያለውን ነፍሳት በሙሉ ሲስቡ አይቻለሁ። ቅጠላ ቅጠሉ፥ ንቡ፥ ማሩ አልቀራቸውም ሁሉንም አግበስብሰው በጭነት መኪና ወሰዱ። ከዛፉ ውስጥ መረቁን የሚመጥ ማሽን አላቸው።’
ወጣቱን አመሰገንኩና ልጨብጠው ስል እርሳሴን ተቀብሎ ማሳታወሻ ደብተሬ ላይ አንድ ትልቅ መረብ ሳለ።
‘የሚፈልጉት ነዳጅ አይደለም። አንድ ያልታወቀ ነገር አለ። ዛፉን ሁላ የሚነቃቅሉበት ምክንያት ምንድን ነው። ዛፍ ከሌለ ግመሎች አይኖሩም።’
በተከታታይ ቃል ተቀበልኩ። ከዋርዴር፥ ከሽሂላቦ የመጡበት አነጋገርኩ። የመጡበት ቦታ ቦታ ይለያያ ታሪካቸው ግን አንድ ነው። በግዴታ መፈናቀል፥ ድብደባ፥ እስራት፥ አስገድዶ መድፈር።
አንድ ከኢል ኩራን የመጣ ሰው የነገረን ታሪክ ለየት ይላል። በዚያች መንደር እንደሌሎቹ የወታደሮቹ ግፍ አልደረሰም።
‘እንዴት የናንተ መንደር ሰላም ሊሆን ቻለ?’ ብዬ ጠየቅኩት።
‘እኛጋ ኦብነግ የለም። ኦብነግ ስለሌለ ወታደሮች የሉም።’
‘እናንተጋ ነዳጅ ቁፋሮ ቢጀመርስ?’
‘ያኔ ኦብነግ ይመጣል። ኦብነግ ድሮ ለነፃነት ነበር የሚዋጋው፥ አሁን ግን የኦጋዴን መዓድናት ለመከላከል ነው።
አንድ ሌላ ስደተኛ በመሃል ገብቶ፥ ‘ኦብነግ ልክ ነው። የኛን ሃብት ማንም መጥቶ መውሰድ የለበትም። ነዳጅ ማውጣት ከፈለኩ እኛም ተጠቃሚዎች መሆን አለብን። ከኛ ጋር በመስማማት ነዳጁን ማውጣት ይችላሉ።’
የዕለቱን ሥራ ጨርሰን ወደ ሁቴላችን ሄድን። በበነጋው አንድ ሙሉ ሱፍ ልብስ ከነክራባቱ፥ ቆዳ ጫማ የለበስ ሰው እስጠርቶን እንግዳ መቀበያ ዘንድ ወረድን። የኦብነግ ሰው ነው።
ከኦብነግ ጋር ያለን ግንኙነት ግልዕና ቀላል ነው። ኦጋዴን ውስጥ አስገብተው መንገድ እንዲመሩን ብቻ ነው። እነሱ ከኛ የሚያገኙት ነገር ቢኖር ትግላቸውንና የሕዝባቸውን መከራ ዓለም እንዲያውቅላቸው ዕድል ማግኘታቸው ብቻ ነው። በረሃ ውስጥ 4 ዓመታት መዋጋት አንድ ነገር ነው። ዓለም ሳያውቅልህ ማለቅ ደግሞ ሌላ ነገር ነው።
ክፍላችን ሄደን አንድ ትልቅ የኢትዮጵያ ካርታ አልጋ ላይ ዘረጋን። ሰውየው ጣቱን በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ጠቁሞ የቦታ ሥምና የጉድጓድ ውሃ ያለበትን አካባቢ ያሳየን ጀመር። ኦጋዴን ተወልዶ ኦጋዴን ያደገ ከዘላን ቤተሰብ የተገኘ ልጅ ነው። ግን ከየመን እስከ ናይሮቢ፥ ከጅቡቲ እስከ ጋልካዩ ያላዳረሰውና የማያውቀው ቦታ የለም።
‘የኛን ሰዎች የምታገኙዋቸው እዚህ ነው። እዚህ የሚያደርሱዋቹ ግን የኛ ሰዎች አይደሉም። ኦብነግ ሶማሊያ ውስጥ አይንቀሳቀስም።’ አለን።
ውላችንም እንዲያ ነበር። ከጋልካዮ ወደ ጠረፍ የሚወስዱን የራሳችን ጠባቆዎች ናቸው። የት ድረስ፥ ለምን እንደምንሄድ አያውቁም። የምናናፍሰው ወሬ ሰደተኞችን ኢንተርቪው ለማድረግ የሚል ነው።
‘ታጋዮቻችን አካባቢውን በደንብ ያውቁታል። በሚገባ መርተው ያደርሷችኋል፥ ግን በአካባቢው ወታደሮች ስላሉ ስጋት አለ። ወደ ሰባ የሚጠጉ መንደሮች በድንበር አካባቢ ብቻ ተቃጥለዋል።’
ጣቱን ሺላቦ ላይ ተከለ። ‘የመንግስት ወታደሮችና ልዩ ፖሊስ ይህን ማህበረሰብ መደምሰስ ይፈልጋሉ። ከሁሉም የኦጋዴን መንደሮች የፈናቀለው ሰው አንድ ቦታ እንዲሰባሰብና የርዳታ ራሽን እየሰፈሩለት ሊቆጣጠሩት እንዳቀዱ አውቀናል።’
ከዚያ ቀና ብሎ ‘ቻይናዎቹስ እሺ በአገራቸውም የሰው ልጅ መብት ይረግጣሉ፥ ከነሱ አንጠብቅም፥ የስዊድን ኩባንያ ግን እንዲህ አይነት ፍጅት ከሚፈጽም መንግስት መተባበሩ በጣም ያሳዝናል፥ ያሳፍራል።’ አለ።
‘የኩባኒያው ሰዎች የሚያውቁ ይመስልሃል።’
‘እስር፥ ግድያውን ባያዩ፥ መንደሮች ሲቃጠሉ፥ ህዝብ ሲፈናቀል ያያሉ። ያውቃሉ።’

ዝናቡ የሆቴል ክፍላችንን መስኮት ይገርፋል። እኔም ራሴን አሞኛል ውሃ ስለማልጠጣ ይመስለኛል። ካልተንቀሳቀስኩ ውሃ አይጠጣልኝም። አሁን ግን፥ ከሁለት ሳምንት ጥበቃ በኋላ ማለት ነው፥ እንድንነሳ አማፂያኑ መልዕክት አድርሰውናል። ወደ ጋልካዮ የምንጓዝባቸው ሁለት የአይሮፕላን ቲኬቶች ጠረጴዛ ላይ ናቸው።
ጉዞው ነገ ነው፥ ሆዴ ውስጥ ያበጠ ነገር ይሰማኛል። ግን ጥርጣሪና ፍርሃቴን ለራሴ ይዠዋለሁ።
ዩሃን ከአባቱ ከሼክ ጋር በስካይፕ ያወራል። ጠበቅ ያለ ግንኙነት ያላቸው ነው የሚመስሉት። በየቀኑ ነው የሚደውልለትና ያለበትን ሁናቴ የሚነግረው።
የኔ መንገድ ለየት ይላል። እስካልደወልኩ ድረስ ቤተሰቦቼ ደህና ነው ብለው ነው የሚያምኑት። ከደወልኩ ነገር አለ ማለት ነው። ከሊንያ ጋር ግን ያው በየቀኑ አጭር ጽሁፍ መልዕክት አለ። በቅርቡ ጋብቻ ልናደርግ ወስነናል። ቀኑም ተቆርጧል። ለሰርጉ እንደማልደርስ ይታወቀኛል ግን እንዳልነግራት ደግሞ በሆነ አጋጣሚ ይህን ፕሮጀክት ብንሰርዝ በአንድ ሳምንት ሂያጅ ነኝ።
ይሃን አልጋው ላይ ተጋድሞ ኮምፒዩተሩን ያነባል። እኔ ኤሜልን ከፈትኩ። ዘጋሁና ብሎጌን ከፈትኩ። ጽሁፎቼን ስንቶች እንዳነበቡልኝና እነማን ገብተው እንደነበር አየሁ። ጎብኞቼ ውስጥ አንድ ነብር ሳይ አይኔ ፈጠጠና ዩሃንን ጠራሁት።
LUNDIN OIL SERVICES
ሉንዲን ኦይልሰርቪስ? እጆቼ እየተንቀጠቀጡ ስክሪን ሾት ቶሎ አነሳሁ። ሰኔ 7 ቀን ስዊዘርላን ከሚገኘው ቢሯቸው ነበር የገቡት። ከአራት ቀን በፊት ማለት ነው።
‘ሥራችንን እስክንጨርስ ከነሱ ጋር ኮንታክት እንዳናደርግ ተባብለን አልነበረም እንዴ?’ አለ ዩሃን።
‘ታዲያ መች ኮንታክት አረኳቸው!’
‘ምንድን ነው ታዲያ! ምን እናድርግ አሁን?’
‘ለምን ብሎጌ ውስጥ ገቡ? ምንስ አገኙ? ስለፊሊፒንስ የሰው ንግድ፥ ስለ ኢንዶኔዢያ መዓድናት ነቅፌ ጽፌአለሁ። መጨረሻ ላይ ወደ ናይሮቢ እንደምበርር።’
አንድ ትልቅ መልቲ ናሽናል ኮርፖሬሽን አንድን በራሪ (ፍሪላንስ) ጋዜጠኛ መከታተሉ ገርሞኝ፥ ለምን ያህል ጊዜ ቡሎጌን ከፍተው እንደቆዩ መረመርኩ። ሩብ ሰዓት ገደማ ቆይተዋል።
‘ፕሮጀክታችንን እንሰርዘው እንዴ?’ ጠይቀ ዩሃን በሃሳብ ተወጥሮ።
ጥያቄው ተገቢ ነው፥ ቶሎ መልስ ማግነት አለበት። የምንጓዘው ነገ ማለዳ ነው።
አንድ ነገር ትዝ አለኝ። እኔ ራሴ እዚህ ከመጣሁ በኋላ የሉንዲን ድረገጽ ውስጥ ገብቼ ነበር። ዌብ ፕሮክሲ ስላልተጠቀምኩ፥ IP ቁጥሩን ሊያገኙትና ከናይሮቢ አድ ሆቴል ውስጥ እንደተጎበኙ ሊያውቁ ችለዋል። ተሳሳትኩ። በዚህ ሰዓት እነሱ ደረ ገጽ ውስጥ ምን አስገባኝ! ያውም ስለ ድጂታል መርጃ ጥንቃቄ እያወቅሁ!
ሌሊቱ አንድ አባ እንቅልፍ ሳይወስደን ቶሎ ነጋ። የመጀመሪያው የብርሃን ጨረር ክፍላችንን ሲዳስስ ብድግ አልኩ።
‘እህ ምን አሰብክ?!’
‘ቀጥል!’

to be continued...

Post Reply