Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ሁሉንም አስተባብሮ ህወሀትንና የቆመለትን የትግሬ ገዥ መደብ ድባቅ የመምታት አቅም እያላቸው በህወሀት እየተበሉ ያሉ የኦህዲድ መሪወች ና በህወሀት አሽከርነት ለመቀጠል ለህወሀት ሲሉ አማራዉን ፊዳ የሚያደርጉት የበአዴን መሪወች ያበሳጩኛል።

Post by Tintagu wolloye » 08 Mar 2018, 10:13

የህወሀት ሲጠባ የለመደ ጥጃነት፣ኦህዲድ የእዚህን አይረኬ ጥጃ ጩኸት ጆሮ ዳባ ለማለት አለመቻልና የብአዴን መሪወች ህዝቡ ለእዚህ ሌላው ቀርቶ እየጠባም እንኳ መጮሁን ለማያቆም ጥጇ ህዝብ በአንኮላ ወተት እንዲያቀርብ ከጥጃው የበለጠ የመጮሀቸው ጉዳይ ለማንም የሚገባ ነገር አይደለም።

ብአዴን አማርኛ ተናጋሪ ህወሀት መሆኑ የታወቀ ነውና የ‘ወንድ ወንድ ሽተት‘ ጥሪው አይመለከተውም። ጥሪየ ኢህአዲግ የሚባለውን ቀምበር ሰብሮ ከሌሎች ተቃዋሚወች ጋር ለማበር ድፍረት ላጣውና እንደተፈራው አዋጅ ታውጆ አባላቱ የጥቃት ሰለባ የተደረጉትን ኦህዲድን ነው። እንከፎቹ ብአዴኖች አጋፍጠው ዘወር ይላሉ እንጅ የድርጅት ጓዶቻችን ተጠቁ ብለው ከንፈር አይመጡም።እናም ኢህአዲግን አሽቀንጥሮ በመጣል ራስን መሆን፣ነፃ ወጥቶ ህዝብን ለነፃነት ማብቂያው ጊዜ አሁን ነው።

በልጀ ታክሲ ውስጥ ከፈጣሪ ምስል ግርጌ የተለጠፈው የለማ ፎቶ የገባ የወጣው ሀሳብ ሳይሰጥበት ወይም በለሆሳስ፣ ፈገግታው ጮሆ ድጋፍ ያላሳየበት ጊዜ ጥቂት ነው።የአይጋ ፎረመኞች ያሉት አልቀረምና፣ለሳይበር አጋዚነት የቀጠሯቸው የጠመዱት ሁሉ እየሆነ ያለው አሁን ነው።

ጅብ ከሚበላህ ጅቡን በልተህ፣የበላህበትን ምክንያትህን ተናዘዝና ቅድስናን አግኝ መባሉ እራስን ለመከላከል መደረግ ያለበትን አድርጎ ካስፈለገ ማብራሪያውን መስጠት እንደሚገባ ይጠቁማል።