Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

ገዳይ፣አሳሪና ገራፊው ህወሀት እስከ ሀገር አጥፊና ኢፍትሀዊ ህግጋቱ፣እስከ ስለላ መዋቅሩና አጋዚው አሁንም በቦታው አለ።እስረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከ26 አመት እስር ሳይፈታ የፖለቲካ እስረኞች ልጆቹ ከስር ተፈቱ ብሎ አይቦርቅም።ህወሀት የሞላውን ወህኒ ለጊዜው አጉድሎ ዳግም ማጨቅ ያውቅበታል ( ትንታጉ ነኝ)

Post by Tintagu wolloye » 03 Jan 2018, 14:25

የህወሀት ብልጠት ማለቂያ የለውም።ይግድላል፣ያስራል፣ይቅርታ ጠይቁና ተፈቱ ይላል። የፈታውን ጨምሮ አበራክቶ ያስራል። በሌላ፣በኩል በስብሻለሁ፣ገምቻለሁ ይላል፣ተሳስቻለሁ ኢ ዲሞክራሲያዊነት አጥቅቶኛል፣ሙስና አዝጎኛል፣የዲሞክራሲው ምህዳር ጠቧል፣ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል የለም ወዘተ።ነገሩ ሲጠቃለል የህዝብን ጩኸት መቀማት ነው ህወሀት የያዘው።ነፍሱን በዲያቢሎስ ግራ ያውላትና ያ የእርጉም ሽንት እርጉም፣መለስ ዜናዊ ታህሳስ 26 1985 ያን ሁሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በጥይት አስፈጅቶና፣በጩቤ አስዘልዝሎ፣ "በጥይት የገደልነው፣በጩቤ የዘነጠልነው ሰልፈኛ መበተኛ አስለቃሽ ጭስ በውጭ ምንዛሬ ገዝተን ስላላስገባን ነው" ሲል መመፃደቁን ያልሰማ የለም።ቀጥሎ ያን ሁሉ ፕሮፌሰር ሆን ብሎ እንዳላባረረና አገሪቱን በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ተጋዳላዮች ሞልቶ በሀገሪቱ የትምህርት ሂደት ላይ የማይጠገን ጉዳት እንዳላደረሰ ስንት አመት ቆይቶ አይኑን በጨው በማጠብ " መባረራቸው ስህተት ነበረ"ብሎን አረፈ። ተማሪወቹ በጥይት መፈጀታቸው ሰልፍ መበተኛ አስለቃሽ ጭስ ጠፍቶ ነው ተባለ።የ97ቱ እልቂትስ? ያን ተከትሎ የተፈፀመው እስርና ግርፋትስ?

የግድያና እስሩ፣የግርፋቱና መሳደዱ ነገር ሰፍቶና ተንሰራፍቶ የለየለትና ብሄር ተኮር ሆኖ ፣ማን አሳሪና ገዳይ፣ማን ሟችና በግፍ ተሰቃይ መሆኑ ለይቶለት አረፈ። ብሄር ተኮር የመሆኑ ሁኔታ ገሀድ እንዳይሆን የፈራው ህወሀት የሶማሌ ክልልን ተተግኖ "ብቻየን አይደለሁም" ሊለን ሞክሯል።

ለህወሀት ግድያ አፈናና እስር ያልተበገረው ኢትዮጵያዊ በአንድ በኩል እንደ ህዝብ ህብረቱን በመጠበቅ፣በሌላ በኩል ደግሞ ለአይቀሬው ሀገራዊ ዲሞክራሲ እየታገለ ይገኛል።ይሁንና በህዝቡ ህብረትና አይበገሬነት የተደናገጠው ህወሀት ማዘናጊያ የሚላቸውን እርምጃወች እንደሚወስድ ትንታጉን ጨምሮ ሌሎች ተንታኞችና ውስጥ አዋቂወች እነደጠቆሙት ህወሀት በጥገናዊ ለውጥ ራሱን ማዳን ብቻ ሳይሆን በስልጣን ላይ ማቆየት እየሞከረ ይገኛል። የህወሀት "ጅብ እስኪነክስ ያነክሳል" አይነት ዘዴ ላልገባው የሚያደርገውን መሰሪ ነገር ሁሉ በአመኔታና በበጎነት አይቶ ለጭብጨባ እጆቹን ሊያገናኝ ቢጣደፍ አይገርምም።ግና ስለ ህወሀት የማታለያ እርምጃወች ሳይሆን ስለራሱ ስለህወሀት ፀረ—ኢትዮጵያዊነትና ኢ—ዲሞክራሲያዊነት መናገር በራሱ ትርጉም አልባ፣እየሆነ መጥቷል። ነገሩ የሳጥናኤልን ምንነትና ፍጣሬት essence) እያወቁ ስለሰራው ተንኮል መዘርዘር ከእሱ ሌላ የሚጠበቅ ያስመስላል አይነት ነው። ለጥቅሙ ከመፀሀፍ ቢጠቅስ የተፈጥሮ ባህርዪን አይለውጠውም።

የህወሀትን " ለጥቅም ከመፀሀፍ የመጥቀስ" ተግባር እንዲህ አየዋለሁ።
1) ከህወሀት ጋር የፖለቲካ ድርድርም ሆነ ውድድር ማካሄድ ፍፃሚውን ሁሉም ከህወሀት ጋር የተደራደረ፣ሊወዳደር የሞከረ ከደረሰበት መማር ይችላል። ህወሀት ይበልጥ ከፋ፣ይበልጠደ አከረረ፣ይበልጥ የስብሀት ነጋና ቤተሰቦቹ የግል ንብረት ሆነ እንጅ ከጥንቱ አልተሻለም። ይህን እኩይ ድርጅት ወንጀሉን አንብቦ፣መሪወቹን ለፈፀሙት ህልቆ መሳፍርት ግፍና ዝርፊያ ለፍርድ አቅርቦ ሲያበቁ ፋይላቸውን ዘግቶ ወደማይፈጠሩበት የዲሞክራሲ መንገድ ማምራት እንጅ ሌላ አማራጭ የለም።
2)በህወሀት የደህንነትና ወታደራዊ መዋቅር ላይ ዲሞክራሲ ተተክሎ አይበቅልም!! ህወሀትን በምንም መልኩ ያካተተ ሽግግርም ተባለ ድርድር የኋላኋላ መጨረሻው አንድም ብጥብጥ አለዚያም መፈንቅለ መንግስት ይሆናል።
3) የህወሀት ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ—ዲሞክራሲ ህጎች በአሉበት ናቸው። በብሄር የመቧደን ህግና አከላለል በቦታው ተቀምጦ በብሄር ተቧድናችሁ አትጋጩ፣አትጋደሉ አይሰራም።በፀረ— ሽብር ስም የተደነገገው ህግ በአለበት ተቀምጦ ህጉ ተጠቅሶ የታሰሩት ይፈቱ መባሉ "አለባብሰው ቢያርሱ" ከመሆን አይዘልም።
3) የሚፈቱት መታሰር ያልነበረባቸው ዜጎች መሆናቸው ተዘንግቶ ማሰር ሳይገባው አስሮ ያንገላታው ህወሀት "ከእስር ፈታ" ተብሎ ጭብጨባ ማቅለጥ በተኮላሹት፣በእስር ዘመናቸው ሁለመናቸውን ለአጡት ወንድም እህቶቻችን ክብር መንሳት ነው።
4) ህወሀት ግፍ ሰርቶ ይቅርታ ተጠያቂ፣ጨፍጭፎ ራሱን ከተጠያቂነት ውጪ ማድረግን ስልት አድርጎታል። የህወሀት መሪወች በህግ ፊት ቆመው መጠየቃቸውን ከዘነጋን ታግለን የምንፈጥረው ተጠያቂ መንግስት ስለመኖሩ ከወዲሁ መርሳትና ግፍን ለመሸከም ትካቫችንን መደልደል፣ሌላ ገዢና የግዞት ዘመን መኖሩን አውቀን ለመገደልና ለመጋዝ ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብናል።ህወሀት አንድም ጊዜ፣አንዱንም ገዳይና ጨፍጫፊ ለህግ አቅርቦ ሲቀጣ አልታየም።ምክንያቱም ትእዛዝ ሰጪው እሱ ነውና!!

ለወሬ ጠማኝነት፣ቀድሞ ለማጨብጨብ ከመቸኮል በአንድ በኩል ትግሉን ወደተፈለገው ግብ ለማድረስ እየታገልን በሌላ በኩል የህወሀትን እኩይ አካሄድ እያጠናን ማጋለጥ ያስፈልገናል።

ደርግ " ቅይጥ ኢኮኖሚ" ብሎ በማወጅ ደርጋዊ ሚስቶ ሊያበላን ሞክሮ ከሽፎበታል።እንደ ህወሀት ሁሉ በቃላት ኳኳታ የማይታማው ደርግ "መድበለ ፓርቲ " የሚል ‘ አዲስ‘ ፅንሰሀሳብ አስደምጦናል።የህወሀቱ "ምህዳሩ ጠቧል" አሰልች ጩኸት የደርጉን "መድብለ ፓርቲ" ባዶ ወሬ ያስታውሰናል።የምንፈልገው የካቢኔ ሹም ሽር፣በህወሀት ውስጥም ሆነ በሌላው የሚደረገው ብወዛ አይደለም።በወያኔ ወታደራዊና የፀጥታ መዋቅር ላይ የሚመሰረት አሻንጉሊት መንግስትም አይደለም።የስርአት ለውጥ ነው፣ስር ነቀል።

የነበሩና ያሉ ችግሮች ጊዜ ተወስዶ የሚበጠሩበት፣ዳግመኛ ላይደገሙ፣ዳግመኛ ላናነሳቸው፣ግን በታሪካችን ሁነኛ ቦታ፣ይዘው የሚቀመጡበት፣ በማንም ነምንም የማይነቃነቅ የዲሞክራሲ መሰረትና የህግ የበላይነት የሰፈነበት ስርአት የሚኖርበት የስር ነቀል ለውጥ ዋዜማ ላይ ነንና ለህወሀት ሰለባ ለመሆን አንጣደፍ!!! ህወሀትን በልተን በእዚያ፣ጉልበት ሀገራችንን አንድና ነፃ፣ትድድራችንን ዲሞክራሲያዊና ከህግ በታች የሆነ እናደርጋለን።

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1467
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: ገዳይ፣አሳሪና ገራፊው ህወሀት እስከ ሀገር አጥፊና ኢፍትሀዊ ህግጋቱ፣እስከ ስለላ መዋቅሩና አጋዚው አሁንም በቦታው አለ።እስረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከ26 አመት እስር ሳይፈታ የፖለቲካ እስረኞች ልጆቹ ከስር ተፈቱ ብሎ አይቦርቅም።ህወሀት የሞላውን ወህኒ ለጊዜው አጉድሎ ዳግም ማጨቅ ያውቅበታል ( ትንታጉ ነኝ)

Post by Tintagu wolloye » 03 Jan 2018, 20:21

የወልደያወቹ ወጣቶች፣የጎንደሮቹ ፋኖወች፣የወለጋወቹ ቄሮወች ወዘተ እስር ቤታቸው ማእከላዊ አይደለም።ቁጥራቸወደ ግን ከማእከላዊው እስረኞች በመቶ እጅ ይበልጣል።ነባር እስረኞችን ጌታቸው አሰፋ ወደ አስገነባውና ናዝሬት አካባቢ ወደሚገኘው አዲሱ ግና በስፋቱ ማእከላዊን በብዙ እጅ የሚበልጠው አለም በቃኝ ለማጓጓዝ ጊዜው አልፈቀደም። እና አሮጌን እስረኛ ፈትቶ ፈትቶ አዲሱንና ትኩሱን የለውጥ አርበኛ፣ቄሮና ፋኖ ለአዲሱ ማሰቃያ፣በማሟሻነት መጠቀም ተፈልጓል።ድሮ መብት ይከበር ነበር ።አሁን ወያኔ በህይወት ቆመን ከእንግዲህ አይገዛንም ሆኗል ጥሪው።ለውጥ አለ። ሰልፉም አሰላለፉም ተቀይሯል።የህወሀት ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሞቶ በምትኩ ኢትዮጵያዊ ትብብር በቅሏል። በጠላትነት የተፈረጀው የትግሬው የገዢ መደብ መሪ ህወሀት ሆኗል።ብሄር ተኮር ጥቃት እየሰነዘረ ነው በኦሮሞና በአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ። ያሰረው ህዝብ ሳይፈታ፣በአሳሪው ውድቀት ሳይካስ ረፍት የለም!

Post Reply