Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

የአራዳ ልጆች ወግ። ትገራ (ትንታጉ ዘወሎ)።

Post by Tintagu wolloye » 01 Jan 2018, 15:54

ሁለት ጓደኛሞች ወደ ጭፍራ ቤት ለመሄድ ይዘጋጃሉ።አንደኛው እምቧለሌ እየዞረ ያለሙዚቃ ይደንሳል።
"ምንድነው እሱ?!"
"ትገራ።"
" 'ጥገራ' ማለትህ ነወ? ከጎንደር ትናንትና መጥተህ ጥገራና ጭፈራ ቢምታታብህ አይገርመኝም።"
" ትገራ ነው ይሄ የጭፈራ አይነት። ደረቅ ልምምድ እያደረግሁ ነው ያለ ትግርኛ ዘፈን።"
" እንዴ?!እንዴ?! ትሞክር የለ እንዴ!ከየት ለመድከው?!"
"ሀገሬ ወልቃይት ሄጀ ልበልህ?"
" እዚያ የትግርኛ ጭፈራ ኮሌጅ ተከፈተ እንዴ?"
" ወይ ኮሌጅ!! ወልቃይቴ መሬቱ እንጅ መማሩ አይፈለግም። ግን ትግርኛ ቋንቋና ትግርኛ ጭፈራ ግን ወዶ ሳይሆን በግዱ ይማራታል።"
" እና ተምረሀል?"
" ለነገሩስ አምልጨ ነበር።ጎንደር ገባሁ።"
" እና ልትመለስ ነው እንዴ ወዳገርህ ትግርኛ መለማመድ .... "
" እዚህስ አዲሳባ መች ቀረልን።"
"ሳልሰማ!አዲሳባም ወደትግራየ ተከለለች?"
"ያው በለው! አለትግርኛ ሌላ የማይነገርበት ሰፈር ተበራክቷል፣ሰፍቷልም። ምን እሱ ብቻ። አታይም!ትግርኛ ዘፈን ብቻ ነው በላይ በላዩ ሲለቀቅ የማየው።አማርኛ ፊልም ተብሎ ተዋናዩ ትግሬ ብቻ ነው።አማርኛ በትእዛዝ ተምራ ሀብታም የሆነችውን ሚስ ትግራይ ብትረሳ ከእሷ በሁዋላ ስንትና ስንቱ የፊልም እንደስትሪውን መለማመጃም፣መረማመጃም አደረገው!!እኔ እምለው ሌላው ምን በላው?"
" ትግርኛ ተናጋሪው የሚዘፍንበትና የሚያሾፍበት፣ ሌላው የታቀበበት ምክንያት ይኖራላ!እነ ኤፍሬም ይሄው ኮንሰርት ሰረዙ አይደል? ሰው ሶሞትና ሲፈናቀል እያዩ መጨፈር አንድም ግዳይ ጣይ መሆንን አለዚያ ከገዳይ ወገን መሆንን ያመለክታል።"

" ሹፍ!ስጨፍር ጎበዝ ነኝ! ሹፍ!!"
" እኔ ትግርኛ አልችል? ሂድና ከሚገማገሙት ዘንድ ተገምገም!!"
" መስሎህ ነው እንጅ ሁሉም መተገሩ አይቀርም።"
"ካልተገራችሁ አትኖሩም ተባለ እንዴ? "
" ያው በለው። ካለትግርኛ በቀር አታዘፍኑ፣ካለ ዳሽን ቢራ አትሽጡ የተባለ ይመስል እሱ ሁኗል በየጭፈራ ቤቱ።ሌላው ሲደንስ ተመልካች ልሁን?ይልቅህ አንተም ተለማመድ።"
" በል ቀርቻለሁ።"
" ምነው?"
" አንተ ወልቃይቴ ሆነህ ነው፣ተከልለህ። እኔም በይፋ እስክከለል እጠብቃለሁ እንጅ ከወዲሁ እለማመዳለሁ ብየ እግሬ ተጠላልፎ አልወድቅም።"
Last edited by Tintagu wolloye on 06 Jan 2018, 15:54, edited 3 times in total.

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የአራዳ ልጆች ወግ። ትገራ (ትንታጉ ዘወሎ)።

Post by Tintagu wolloye » 03 Jan 2018, 04:02

ትግርኛ ተናጋሪው የሚዘፍንበትና የሚያሾፍበት፣ ሌላው የታቀበበት ምክንያት ይኖራላ!እነ ኤፍሬም ይሄው ኮንሰርት ሰረዙ አይደል? ሰው ሶሞትና ሲፈናቀል እያዩ መጨፈር አንድም ግዳይ ጣይ መሆንን አለዚያ ከገዳይ ወገን መሆንን ያመለክታል

Tintagu wolloye
Member
Posts: 1433
Joined: 02 Sep 2016, 16:59

Re: የአራዳ ልጆች ወግ። ትገራ (ትንታጉ ዘወሎ)።

Post by Tintagu wolloye » 06 Jan 2018, 16:09

ትግርኛ ተናጋሪው የሚዘፍንበትና የሚያሾፍበት፣ ሌላው የታቀበበት ምክንያት ይኖራላ!እነ ኤፍሬም ይሄው ኮንሰርት ሰረዙ አይደል? ሰው ሶሞትና ሲፈናቀል እያዩ መጨፈር አንድም ግዳይ ጣይ መሆንን አለዚያ ከገዳይ ወገን መሆንን ያመለክታል።

Post Reply